TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.1K photos
1.5K videos
211 files
4.09K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#ዋግኽምራ 📍 የኢትዮጵያ ጠ/ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ በፋሲካ ዋዜማ በአማራ ክልል ፤ ዋግ ኽምራ ዞን የሰቆጣ ከተማ ማእከላዊ እዝ እና ማህበረሰቡን መጎብኘታቸውን ፅ/ቤታቸው አስታውቋል። ዶ/ር ዐቢይ ፤ ከማህበረሰቡ አባላት ጋር ባደረጉት ውይይት የአገው ሕዝብን የኪነ-ህንፃ ልህቀት እና ፍልስፍናዊ መሰረት አድንቀው እነዚህን እሴቶች የመጠቀም እና ፈተናዎችን ለማሸነፍ አንድነትን ማስጠበቅ ያለውን ጠቀሜታ…
#Woldia📍

የኢትዮጵያ ጠ/ሚ ዶክተር ዐቢይ አህመድ የዒድ አል ፈጥርን ዋዜማ ከወልድያ ከተማ ሕዝብና በአካባቢው ካለው ሠራዊት ጋር ማክበራቸውም ገለፀዋል።

በዚህም የተሰማቸድን ደስታ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ላይ አስፍረዋል።

ጠ/ሚኒስትሩ ፥ " ጀግናው ሠራዊታችን የሕዝቡን ደኅንነት እና ልማት በደሙ ለማስከበር ወትሮ ዝግጁ መሆኑን አረጋግጧል። " ያሉ ሲሆን " ይሄንን ሕዝብና ሠራዊት በዓላማ አንድነት ያጸናውን ግንብ፣ እንኳን ሊደፍሩት ሊጠጉት አስፈሪ ነው " ሲሉ ገልፀዋል።

ከጥቂት ቀናት በፊት በትንሳኤ በዓል ዋዜማ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በአማራ ክልል ዋግኽምራ ዞን ሰቆጣ ከተማ ተገኝንተው ከማእከላዊ እዝ እና ከማህበረሰቡ ጋር ተገናኝተው እንደነበር ይታወሳል።

@tikvahethiopia
የአሠልጣኞች ሥልጠና ጥሪ

የተሳትፎ መመዝገቢያ ቅፅ: ለሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት የሥነ ዜጋና ሥነ ምግባር ትምህርት መምህራን መሠረታዊ የሰብዓዊ መብቶች ፅንሰ-ሐሳቦች ላይ ያተኮረ የአሠልጣኞች ሥልጠና

የመብቶች ዴሞክራሲ ዕድገት ማዕከል (CARD) በአዲስ አበባ፣ ቢሾፍቱ ፣ አዳማ፣ ደብረብርሀን፣ ድሬዳዋ፣ ሀዋሳና ሀረሪ ክልሎች ውስጥ ለሚገኙ የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት የስነዜጋና ስነምግባር ትምህርት መምህራን የሰብዓዊ መብቶች ፅንሰ-ሐሳቦች ላይ ያተኮረ የአሠልጣኞች ሥልጠና ለመስጠት አቅዷል።

ሥልጠናው “የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች አዲስ ትውልድ’’ የተባለውና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች ላይ ትኩረቱን አድርጎ የሚሠራው ፕሮጀክት አንዱ አካል ነው መሆኑን ገልጿል።

ከስልጠናው በኋላ ተቋሙ በተጠቀሱት አካባቢዎች በቀጣይነት ለሚኖረው የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች መሰረታዊ የሰብዓዊ መብቶች ስልጠና ሂደቶችን በማስተባበር ተሳታፊዎች እንዲሆኑ ለማድረግ አቅዷል።

ለመመዝገብ https://bit.ly/3vu4rZK
#MayDay

በዓለም ለ133ኛ ጊዜ በኢትዮጵያ ደግሞ ለ47ኛ ጊዜ የሚከበረውን የላብ አደሮች ቀን በአዲስ አበባ ስታዲየም በተለያዩ ሁነቶች ተከብሯል።

የሠራተኞች መብት አለመጠበቅ፣ የኑሮ ውድነትና ሰራተኞች የሚያገኙት ደሞዝ አለመጣጣም፣ ከጊዜ ወደጊዜ ግጭቶች መከሰት ፣ ዲሞክራሲ በፈተና ውስጥ መግባትና ሌሎች ችግሮች እንዲፈቱ ተጠይቋል።

በዕለቱ ከተላለፉት መልዕክቶች ፦

🪧 " ሠራተኛው መልካም አስተዳደርን ይሻል "

🪧 " ግጭት እና ጦርነት ቆሞ የአገራችን ሠላም ይረጋገጥ "

🪧 " ሀገር አቀፍ መነሻ ደመወዝ ወለል እንዲወሰንልን እንጠይቃለን "

🪧 " የቤት ሰራተኞች መብት ይከበር "

🪧 " ለኑሮ መሻሻል መንግስት የንግድ ስርዓቱን ያሻሽል "

🪧 " የኑሮ ውድነትን ማረጋጋት የመንግስት ኃላፊነት ነው "

🪧 " መንግስት ለኑሮ ውድነት መፍትሄ ይስጥ "

በየዓመቱ እ.ኤ.አ ግንቦት 1 ቀን የሚከበረው የላብ አደሮች ቀን (ሜይ ዴይ) የሰራተኞችን መብት ማስከበር ዋነኛ አላማው ነው።

ፎቶ፦ ኢብኮ

@tikvahethiopia
#ቴሌግራም

ቴሌግራም ዘንድሮም ልክ እንደ 2021 በመላው ዓለም ላይ በብዛት ዳውንሎድ ከተደረጉ ምርጥ አምስት (5) መተግበሪያዎች አንዱ መሆን ችሏል።

ቲክ ቶክ የ1ኛ ደረጃን ሲይዝ ፤ ኢንስታግራም ሁለተኛ ፣ ፌስቡክ ሶስተኛ ፣ ዋትስአፕ ደግሞ አራተኛ ደረጃን ይዘዋል።

ምንጭ፦ https://www.searchenginejournal.com/tiktok-most-downloaded-app-in-q1-2022/447790/

@tikvahethiopia
የዒድ አልፈጥር በዓል ሰኞ ይከበራል።

ዛሬ ጨረቃ ባለመታየቷ ነገ ረመዷን 30 ሆኖ ዒድ አልፈጥር በዓል ሰኞ ሚያዝያ 24 ይሆናል።

ምንጭ ፦ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠ/ም/ቤት

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የዒድ አልፈጥር በዓል ሰኞ ይከበራል። ዛሬ ጨረቃ ባለመታየቷ ነገ ረመዷን 30 ሆኖ ዒድ አልፈጥር በዓል ሰኞ ሚያዝያ 24 ይሆናል። ምንጭ ፦ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠ/ም/ቤት @tikvahethiopia
ፎቶ ፦ የሸዋል ወር ጨረቃ 🔭 ዛሬ ቅዳሜ ሚያዚያ 22 አልታየችም።

በዚህም ነገ እሑድ ሚያዚያ 23 የቅዱሱ የረመዳን ወር 30 ይሆናል ፤ የዒድ አልፈጥር በዓል ደግሞ ሰኞ ሚያዚያ 24/2014 ይከበራል።

ከወዲሁ የእስልምና🕌እምነት ተከታይ የሆናችሁ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት በሙሉ እንኳን ለ1443ኛው የዒድ አልፈጥር በዓል አደረሳችሁ።

@tikvahethiopia
የጎንደር ከተማ አስተዳደር እስልምና ጉዳዮች ም/ቤት በጎንደር የተፈፀመውን ኢሰብዓዊ ድርጊቶች አሻራቸው እንዳይገኝ በመንግስት ጭምር እገዛ ተደርጎ እንዲጠፋ ከፍተኛ የሆነ ጥረት ተካሂዷል አለ።

ም/ቤቱ ይህን ያለው ትላንት ባወጣው ወቅታዊ መግለጫ ነው።

ከሚያዚያ 18 - 21 በነበረው ሁኔታ በምእመናን ላይ እጅግ ዘግናኝ ግፍ ተፈፅሟል ፤ ለቀብር የሄዱ ሰዎች ላይ በቦንብ እና በመትረየስ የተቀላቀለ ከፍተኛ ጥቃት ደርሶባቸዋል፤ በርካቶች በተደራጀ እና ቀድሞ በተዘጋጀ ኃይል ተጨፍጭፈው ህይወታቸው አልፏል፤ እንስቶች ክብረ ንፅህናቸው ተደፍሯል፤ መስጅዶች ክብራቸው ተጥሶ ተቃጥለዋል፣ ፈርሰዋል፣ ተደብድበዋል ሲል ም/ቤቱ አስታውሷል።

የንግድ ድርጅቶች በተጠና እና በሰለጠነ መልኩ ተዘርፈዋል ፤ በቃጠሎ ወድመዋል፤ መኖሪያ ቤቶች ተጠቅተዋል፤ በሌላ በኩል የተፈፀሙ ኢሰብዓዊ ድርጊቶች አሻራቸው እንዳይገኝ በመንግስት ጭምር እገዛ ተደርጎ እንዲጠፋ ከፍተኛ ጥረት ተካሂዷል ሲል አሳውቋል።

ም/ቤቱ አሁን ላይ ጎንደር በኮማንድ ፖስት ውስጥ መግባቷን ገልጾ በዚህም ሙስሊሙ ምእመን አንፃራዊ መረጋጋት እያገኘ ነው ብሏል፤ ነገር ግን አሁንም በተናጠል የማጥቃትና የማሳደድ ሁኔታ መቀጠሉንና ምእመናን በየመስጅዶች ለመጠለል የተገደዱበት ሁኔታ በስፋት መከሰቱን በማስረዳት የዜጎች ህይወትና ሀብት ዋስትና የሚያገኝበት ሁኔታ እንዲሰፍን አሳስቧል።

በተጨማሪ በከተማይቱ ከተፈጠረው ክስተት ጋር በተያያዘ በገፍ ለእስር የተዳረጉ ንፁሃን ምእመናን ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲፈቱ ጠይቋል።

ህይወታቸው ለተነጠቁት ንፁሃን ምእመናን ፍትህ እንዲሰፍንላቸው፤ የጠፋና የወደመ ሀብት ንብረት በአስቸኳይ ተጠንቶ በዚያ ልክና መጠን የመልሶ ግንባታና የካሳ ሂደት በፍጥነት እንዲከናወን ጠይቋል።

(ዝርዝሩን ከላይ ያንብቡ)

@tikvahethiopia
#GONDAR

የጎንደር ከተማ ተቀዳሚ ም/ ከንቲባ አቶ ዘውዱ ማለደ በወቅታዊ የጎንደር ሁኔታ ዙሪያ ትላንት መግለጫ ሰጥተው ነበር።

በመግለጫቸው ፤ " በጎንደር ከተማ በተፈጠረው ግጭት ተሳታፊዎችን ለመያዝ ሁሉም የከተማዋ ነዋሪዎች ትብብር እያደረጉ ነው " ብለዋል።

አቶ ዘውዱ እስካሁን ከ370 በላይ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተደረገ መሆኑን ገልፀው ተጨማሪ ተጠርጣሪዎችንም ለመያዝ እየተሰራ ነው ብለዋል።

" የተፈጠረው ግጭት የሁለቱንም ሀይማኖቶች የማይወክል የጥቂት ጸረ ሰላም ሀይሎች እኩይ ድርጊት ነው " ያሉት አቶ ዘውዱ " በግጭቱ የ15 ሰው ህይወት ጠፍቷል፤ ንብረት ላይም ጉዳት ደርሷል " ብለዋል።

በከተማው ተዘግተው የነበሩ አንዳንድ የከተማዋ ሱቆች ተከፍተው አሁን ላይ ሰላማዊ እንቅስቃሴ መጀመሩን እና የከተማዋን ሰላምና ጸጥታ አስተማማኝ ለማድረግ እስከቀበሌ ድረስ ግልጽ ውይይቶች እየተደረጉ መሆኑን አሳውቀዋል።

🔻

በሌላ በኩል ፦ የከተማዋን ጸጥታ ለማስጠበቅ የሚያግዙ መመሪያዎች ተግባራዊ ይደረጋሉ ተብሏል።

በዚህም ፦

➡️ ከምሽቱ አንድ ሰዓት በኋላ የእንቅስቃሴ ገደብ ተጥሏል።

➡️ ከተፈቀደላቸው የጸጥታ ሀይሎች ውጭ ማንኛውም ግለሰብ የጦር መሳሪያ ይዞ መንቀሳቀስ አይችልም።

➡️ ወደ ከተማ የሚገባ ማንኛውም ሰው የይለፍ መታወቂያ ሳይኖረው የጦር መሳሪያ ይዞ መግባት ተከልክሏል።

@tikvahethiopia
#ስልጤ_ዞን

ከትላንትና ቅዳሜ ጀምሮ በስልጤ ዞን የመንግስት እና የግል ባለ ሁለት እግር ተሽከርካሪ ሞተሮች እና በተለምዶ ባጃጅ የሚባሉት የባለ ሶስት እግር ተሽከርካሪዎች እንቅስቃሴ እንዲቋረጥ ተደርጓል።

ይህን ውሳኔ ያሳለፉት በስልጤ ዞን የተቋቋመው ጊዜያዊ ግብረ ሀይልና የዞኑ ትራንስፖርትና መንገድ ልማት መምሪያ ናቸው።

ባለፉት ቀናት በተወሰኑ አከባቢዎች ላይ የተፈጠሩ ችግሮችን መሰረት አድርጎ ሊከሰት የሚችለውን የሰርጎ ገቦችን እንቅስቃሴ ለመቆጣጠርና የዞኑን ህዝብ ሰላም ለማረጋገጥ ሲባል ውሳኔ መተላለፉን አሳውቀዋል።

የሞተሮች እና የባጃጆች እንቅስቃሴ በዞኑ በሁሉም አከባቢዎች እስከ ዒድ ድረስ ሙሉ በሙሉ ተቋርጦ የሚቆይ ሲሆን አሽከርካሪዎች ይህን አክብረው እንዲንቀሳቀሱና ከፀጥታና ህግ አስከባሪዎች ጋር በትብብር እንዲሰሩ ተጠይቋል።

የተላለፈውን መመሪያ በሚጥሱ አሽከርካሪዎች ላይ አስፈላጊው እርምጃ በየደረጃው እንደሚወሰድ ግብረሀይሉ ያስጠነቀቀ ሲሆን መመሪያው በሁሉም ወረዳዎችና ከተማ አስተዳደሮች ነው ተግባራዊ እየተደረገ የሚገኘው።

@tikvahethiopia