TIKVAH-ETHIOPIA
* AFAR የአፋር ክልል መንግስት በዛሬው ዕለት ባወጣው መግለጫ ሽብርተኛ ተብሎ የተፈረጀውን የህወሓት ቡድን ከአፋር ክልል ፈንቲ ረሱ ሙሉ በሙሉ ማስወጣት መቻሉን አሳውቋል። ቡድኑ ፈንቲ ረሱ ሙሉ በሙሉ እንዲወጣ ፥ የአፋር ህዝብ፣ የአፋር ልዩ ሀይል፣ ሚሊሺያ እና ህዝባዊ ሰራዊት፣ የሀገር መከላከያ ሰራዊት፣ እንዲሁም አጠቃላይ የኢትዮጵያ ህዝብ ባደረጉት ትግል መሆኑን አመልክቷል። የአፋር ወስንን ጥሶ…
* Afar
የአፋር ሰብዓዊ መብት ድርጅት ሊቀመንበር የሆኑት ገአስ አህመድ የህወሓት ታጣቂዎች ተቆጣጥረው ከነበረው ያሎ፣ ጎሊና፣ አውራ እና እዋ ወረዳዎች ተጠራርገው መውጣታቸውን አረጋገጡ።
አቶ ገአስ ዛሬ ምሽት ለጀርመን ድምፅ ሬድዮ በሰጡት ቃል የአፋር ልዩ ኃይል ፣ የአፋር ሚሊሻ፣ የአፋር ታጋዮች ከትላንት በስቲያ እዋን ፤ ትላንት ደግሞ አውራ ጎሊና እና ያሎን አስለቅቀው ሙሉ በሙሉ መቆጣጠራቸውን ገልፀዋል።
ህወሓት ተቆጣጥሯቸው በነበሩት ቦታዎች ውድመት ደርሷል ያሉት አቶ ጋአስ በጎሊና በሚገኘው የጤና ተቋም፦
- ሙሉ በሙሉ ዝርፊያ ተፈፅሟል።
- ቢሮዎች ፣ የሰራተኞች ዶክመንቶች ተዘርፈዋል፣ ተመዝብረዋል፤ ግማሹን አቃጥለዋል ሲሉ አስረድተዋል።
በሌላ በኩል አቶ ገአስ አህመድ ተጎጂዎችን ለማቋቋም ስለሚሰራው ስራም ያስረዱ ሲሆን የክልሉ መንግስት በተወሰነ ደረጃ በነፍስ ወከፍ እርዳታ ሲያደርግ ነበር ፤ ያ ግን አጥጋቢ ስላልነበር ብዙ ሮሮዎች ይሰሙ ነበር ብለዋል።
አቶ ገአስ በእነሱ በኩል በቅርቡ ጎፈንድሚ አካውንት በመክፈት ለተፈናቃዮች እርዳታ ለማሰባሰብ ጥረት እያደረጉ መሆኑን በማንሳት የተፈናቀሉትን ወገኖችን ፣ ተጎጂዎችን መልሶ የማቋቋሙ ስራ የሁሉም ኢትዮጵያዊ ዜጎች ስራ ነው ፤ ይህንን ኃላፊነትም ሁሉም ይወጣዋል ብዬ አምናለሁ ሲሉ ገልፀዋል።
ከዚህ ቀደም በግለሰብ እንዲሁም በክልሎችም ደረጃ ተፈናቃዮችን ለመርዳት በተወሰነ ደረጃ እንቅስቃሴ እንደነበር ያስታወሱት አቶ ጋአስ አሁን ትልቁ ስራ የተፈናቀሉ ሰዎችን ወደቦታቸው መልሶ ማቋቋሙ ነው ፤ ይህንንም የኢትዮጵያ ህዝብ በጋራ ሆኖ ያደርገዋል ብዬ አምናለሁ ብለዋል።
@tikvahethiopia

#Tigray #Afar
የዓለም አቀፍ ቀይ መስቀል ኮሚቴ (ICRC) እና የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር ከተለያዩ የትግራይ ክልል አካባቢዎች ተፈናቅለው በሽራሮ እና አስገደ ወረዳዎች ለሚገኙ ከ42 ሺ በላይ ሰዎች አስቸኳይ ፍላጎታቸውን ለማሟላት የሚረዱ ፦
- መሰረታዊ የቤት ውስጥ መገልገያ እቃዎችን፣
- መጠለያ ቁሳቁሶች
- የንጽህና መጠበቂያ ቁሳቁሶችን አከፋፍለዋል፡፡
በሌላ በኩል ICRC በአፋር ክልል ለሚገኘው ዱፕቲ ሆስፒታል የድንገተኛ ህክምና ግብአቶችን አድርሷል።
የዱብቲ ሆስፒታል አስተዳደር ዶ/ር መሐመድ የሱፍ ፥ ‹‹የቆሰሉ በርካታ ህሙማንን በማስተናገድ ላይ ስለምንገኝ የህክምና ቁሳቁስ እጥረት እያጋጠመን ነው ፤ ዓለም አቀፍ ቀይ መስቀል ኮሚቴ የድንገተኛ ህክምና ግብአቶችን እና መኝታዎችን አቅርቦልናል፡፡ አሁን ህሙማንን ማከም እና ህይወት አድን ቀዶጥገናዎችን ማከናወን እንችላለን" ሲሉ ገልጸዋል፡፡

በዙሪክ ዳይመንድ ሊግ በሪሁ አረጋዊ አሸነፈ።
ዛሬ ምሽት በስዊዘርላንድ፣ ዙሪክ በተካሄደ የዳይመንድ ሊግ ውድድር በ5000 ሜትር ወንዶች ውድድር አትሌት በሪሁ አረጋዊ በ12:58.65 በሆነ ሰዓት 1ኛ በመውጣት ሲያሸንፍ አትሌት ዮሚፍ ቀጄልቻ በ13:04.29 በሆነ ሰዓት 5ኛ በመውጣት አጠናቋል።
በሴቶች 5000 ሜትር አትሌት እጅጋየሁ ታዬ በ14:30.30 በሆነ ሰዓት 3ኛ ስትወጣ አትሌት ፋንቱ ወርቁ በ14:43.60 ስድስተኛ ደረጃ በመያዝ ውድድሯን ፈፅማለች።
Credit : EAF

#Update የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ እና ከጋናው ፕሬዚዳንት ናና አኩፎ-አዶ ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ መከሩ። ዶ/ር ዐቢይ በይፋዊ የማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ላይ ፥ "ከልዑካን ቡድኔ ጋር በአክራ በሚገኘው ቤተ መንግሥታቸው ተቀብለው በበርካታ ጉዳዮች ላይ ስላደረግነው ውይይት ለፕሬዚዳንት ናና አኩፎ-አዶ አድናቆቴ ይድረሳቸው" ብለዋል። አክለው ኢትዮጵያና ጋና በሁለትዮሽ እና…
#Update
የኢትዮጵያ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ወደሀገራቸው ተመልሰዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ እና የልዑካን ቡድናቸው #በሴኔጋል እና #በጋና ያደረጉትን የስራ ጉብኝት አጠናቀው ዛሬ ወደኢትዮጵያ መመለሳቸው የጠ/ሚ ፅ/ቤት አሳውቋል።
የሥራ ጉብኝቱ የተሳካ እንደነበር ፅ/ቤቱ ጨምሮ ገልጿል።
ፎቶ ፦ ፋይል

#MIND_ETHIOPIA
'ሀገራዊ የምክክር ሂደት በኢትዮጵያ'
ነገ ጳጉሜ 4 ቀን 2013 ዓ/ም ጥዋት ማይንድ ኢትዮጵያ "ሀገራዊ የምክክር ሂደት በኢትዮጵያ" በሚል ርዕስ ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር በስካይ ላይት ሆቴል ምክክር እንደሚያካሂድ ለማወቅ ችለናል።
በዚህም መድረክ ላይ አለም አቀፍ እና ሀገራዊ ልምዶች እንዲሁም የማይንድ ኢትዮጵያ አመሰራረት ፣ እንቅስቃሴና ቀጣይ ስራዎች ላይ ጥልቅ ውይይት ይካሄዳል ተብሎ ይጠበቃል።
በውይይት መድረኩ በጉዳዮቹ ላይ የጋራ መግባባት ለመፍጠር መታሰቡንም ለማወቅ ችለናል።
እነማን ይሳተፉበታል ?
- የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች
- የሲቪክ ማህበራት አመራሮች
- የግሉ ዘርፍ አመራሮች
- የሚዲያ ተቋማት አመራሮች
- የመንግስት አካላት
- የማይንድ ምክር ቤት አባላት
- የሀይማኖት መሪዎች
- የሀገር ሽማግሌዎችና የሰላም እናቶች ተወካዮች ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል።

#እንቁጣጣሽ #መስቀል #ኢሬቻ
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የእሳት እና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የአዲስ አመት በአልን ጨምሮ የመስቀል እና የኢሬቻ በአልን ተከትሎ ሊከሰቱ ከሚችሉ ማናቸውም ድንገተኛ አደጋዎች ማህበረሰቡን መታደግ የሚያስችለውን የቅድመ አደጋ ዝግጁነት ስራ መሰራቱን አሳውቋል።
ይህ የተገለፀው በኮሚሽኑ የአደጋ ምላሽ ዘርፍ ሰራተኞች ከማዕከል እና ቅርንጫፍ መስሪያ ቤቶቹ ጋር ባደረገው ውይይት ላይ ነው።
ኮሚሽኑ ቅድመ ዝግጅቱን ያጠናቀቀ ቢሆንም አደጋ ሳይከሰት ቀድሞ ለመከላከል የህበረተሰቡ ተሳትፎ ጉልህ ሚና አለው ተብሏል።
በመድረኩም ላይ ለ2014 ዓመት መስከረም ወር ላይ ለሚከበሩት ሶስቱ በዓላት፦
- አዲስ ዓመት
- መስቀል
- ኢሬቻ በዓላት ለአደጋ ምላሽ አገልግሎት የሚውሉ በቂ ግብአቶች እና ተሽከርካሪዎች መመደባቸውን የተገለፀ ሲሆን በዚህም መሰረት በ10 ክፍለ ከተማ 918 የአደጋ ሠራተኞች ፣ 39 ከባድ የአደጋ ተሽከርካሪዎች እና 22 የቅድመ ሆስፒታል አገልግሎት የሚሰጡ አምቡላንሶች ዝግጁ መሆናቸው ተገልጿል።
#ጥቆማ
ህበረተሰቡ ሳይዘናጋ እራሱን ከድንገተኛ አደጋ መከላከል እንዳለበት ተገልጿል፤ ጥንቃቄ እያደረገ ለሚገጥመው ማንኛውም አደጋ ግን ወደ ተቋሙ ስልክ ቁጥሮች ፦
• ነፃ ስልክ መስመር 👉 939
ወይም በቀጥታ የውስጥ መስመሮች ፦
• 0111555300
• 0111568601
• 0111264848 ላይ በመደወል አገልግሎቱን 24 ሰዓት ማግኘት ይችላል ተብሏል።

#Burji
የቡርጂ ልዩ ወረዳ ንግድና ገበያ ልማት ጽ/ቤት ያለምንም መሰረታዊ ምክንያት የተጋነነ የዋጋ ጭማሪ በተደረገባቸው ምርቶች ላይ እርምጃ እየወሰደ እንደሚገኝ አሳውቋል።
በዚህም መሰረት ፅ/ቤቱ እንዳሳወቀው ፦
- በ8 ብር ስሸጥ በነበረው እንቁላል ካለፈው የቅዳሜ ገበያ ጀምሮ በ5 ብር እየተሸጠ ነው።
- ዶሮ ከ700 እስከ 800 ብር ሲሸጥ የነበረው የሸማቹን አቅም ባገናዘበ መልኩ ከ300 እስከ 500 ብር እንዲሸጥ እየተደረገ ነው።
- በቆሎ በኪሎ 30 ብር ስሸጥ የነበረው ከ20-23 ብር ዝቅ እንዲል ተደርጓል።
- በአካባቢው በስፋት የሚመረተው የጤፍ ምርት በኪሎ 50 ብር ድረስ ሲሸጥ የነበረ ሲሆን ከ37 እስከ 40 ብር እንዲሸጥ እየተደረገ ነው።
በፍራፍሬ እና በሌሎች ምርቶች ላይ ተመሳሳይ እርምጃ እየተወሰደ መሆኑን ፅ/ቤቱ አሳውቋል።
Credit : SRTA

" ... ሱዳን እየሄደችበት ያለው መንገድ የተሳሳተ እና የማይጠቅማት በመሆኑ ከድርጊቷ ብትቆጠብ መልካም ነው" - አምባሳደር ዲና ሙፍቲ
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ የሆኑት አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ፤ ሱዳን ከተሳሳተው መንገዷ እንድትመለስ አሁንም ኢትዮጵያ ትጠይቃለች አሉ።
ሱዳን በተጠናቀቀው አመት የኢትዮጵያን ድንበር አልፋ የተለያዩ ትንኮሳዎችን ማድረጓን ያስታወሱት አምባሳደር ዲና " አሁንም ሱዳን ከተሳሳተው መንገዷ እንድትመለስ ኢትዮጵያ ትጠይቃለች " ብለዋል።
አምባሳደር ዲና ፥ የኢትዮጵያ መንግስት ከሱዳን ጋር ያለውን የድንበር ውዝግብ በትዕግስት መከታተሉን ያነሱ ሲሆን በተጠናቀቀው 2013 ዓ / ም ኢትዮጵያ ከገጠሟት ችግሮች የሱዳን ድንበር ውጥረት አንዱ መሆኑን አስታውቀዋል።
ቃል አቀባዩ ፥ " ችግሩ ባይፈታም ኢትዮጵያ 🇪🇹 ግን ጉዳዩን በበሳል ዲፕሎማሲ እይታ ተከታተለዋለች " ብለዋል። ሱዳን እየሄደችበት ያለው መንገድ የተሳሳተና የማይጠቅማት በመሆኑ ከድርጊቷ ብትቆጠብ መልካም እንደሆነ ተናግዋል፡፡
ከእንደዚህ አይነት ድርጊት በዘለለ ደግሞ #የአፍካውያን_ኩራት በሆነው አየር መንገዳችን ስም ለማጠልሸት የሚደረገውንም ድርጊት ኮንነዋል፡፡
Credit : Ethio FM 107.8

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግስት ዛሬ ባወጣው መግለጫ መተከልና ካማሺ ዞኖች ሚንቀሳቀሰው በሽብርተኛ ድርጅትነት የተፈረጀው የህወሃት ቡድን ተላላኪ ነው ያለው " ጸረ-ሠላም ኃይል" ሽፍትነትን የኑሮ አካል በማድረጉ በክልሉ በምንም ሁኔታ ሠላም እንዲኖር አለመፈለጉን በተግባር እያሳየ ይገኛል ብሏል።
ክልሉ ከፌዴራል መንግስት ጋር በመሆን ባለፉት ጊዜያት በዞኖቹ የተፈጠረውን የፀጥታ ችግር ለመፍታት የተለያዩ እርምጃዎችን ከመውሰድ ባሻገር የተለያዩ አማራጫጮችን አስቀምጦ ሲሰራ እንደነበር አስታውሷል።
ችግሩን በሠላማዊ መንገድና በውይይት ለመፍታት ከፍተኛ የሆነ የበጀት፣ጊዜ፣ሰው ኃይል በመመደብ ለወራት የዘለቀ ከፍተኛ ጥረት ማድረጉን ገልጿል።
በሁለቱ ዞኖች ከሚንቀሳቀሰው የጥፋት ቡድኑ አባላት መካከል የተወሰኑት የቀረበውን 'ሠላማዊ ድርድር' በመቀበላቸው የተሃድሶ ስልጠና እንዲወስዱ መደረጉን አስታውሷል።
ነገር ግን መንግስት ያስቀመጠውን የሠላማዊ ድርድር ዕድል እንደ ፍርሃትና ሽንፈት በመቁጠር የህወሓትን ተልውኮ ለማስፈጸም የተሃድሶ ስልጠና የወሰዱት የጥፋት ቡድኑ አባላት ሳይቀር ወደ ጫካ በመግባት አሁንም በንጹኃን ዜጎች ላይ ጥቃት እያደረሱ ዜጎች ደክመው ያፈሩትን ሃብትና ንብረት መዝረፍ ቀጥለውበታል ብሏል።
የክልሉ መንግስት እና የመተከል ዞን የተቀናጀ ኮማንድ ፖስት የችግሩን አሳሳቢነት በመረዳት፦
-ከሃገር መከላከያ ሠራዊት
-ከፌዴራል ፖሊስ
-ከየክልሎች የልዩ ኃይል አባላት
-ከሚሊሺያ አባላትና ከግል ታጣቂዎች ጋር በመሆን በጥፋት ቡድኑ ላይ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ የሚወሰደውን እርምጃ በአጭር ጊዜ ውስጥ ለማጠናቀቅ ዝግጅት ማድረጉን ክልሉ አሳውቋል።
በዚህም በመተከልና ካማሺ ዞኖች የሚኖሩ የህብረተሰብ ክፍሎች እራሳቸውን ከጥፋት ቡድኑ እንዲለዩ ጥብቅ ማሳሰቢያ ተላልፏል።

#Ethiopia
ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ፣ ጳጉሜ 3/2013 ዓ. ም. ያቀረቡትን ሳምንታዊ የጠቅላላ ትምሕርተ ክርስቶስ አስተምህሮአቸውን ሲያጠቃልሉ፣ #ኢትዮጵያዊያን በሙሉ መስከረም 1/2014 ዓ. ም. የሚያከብሩት አዲሱ ዓመት የመረዳዳት ዓመት እንዲሆን በመመኘት የመልካም ምኞት መግለጫ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
በአገሪቱ ውስጥ እየተካሄደ ባለው ጦርነት ምክንያት ከፍተኛ ሰብዓዊ ቀውስ መከሰቱን አስታውሰው፣ አዲሱ ዓመት፣ የተመኙትን ሰላም አግኝተው የወንድማማችነት እና የአንድነት ሕይወት የሚኖሩበት እንዲሆን ተመኝተዋል።
በሌላ በኩል የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን በምታስተዳድራቸው ተቋማት የሚሠሩ ሠራተኞች በሙሉ ከጳጉሜ 1 ቀን 2013 ዓ.ም. ጀምሮ በልዩ ሁኔታ ሰለኢትዮጵያ ሰላም በመጸለይ ላይ እንደሚገኙ ቤተክርስቲያኗ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አሳውቃለች።
በተለይ የጳጳሳት ጉባኤ ጠቅላይ ጽ/ቤት ሠራተኞች ሰኞ ጳጉሜ 1 ቀን 2013 ዓ.ም. ጠዋት በእንድ ላይ በመሰብሰብ ልዩ ጸሎት እና ምህልላ አድርገዋል።
የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን በሀገራችን የተለያዩ እካባቢዎች በተፈጥሮ እና ሰው ሰራሽ ችግሮች ምክንያት የተፈናቀሉ ወገኖችን ያሉበት ስፍራ ድረስ ሄዶ በመጎብኘት እና ፈጥኖ ደራሽ እርዳታ በማድረግ ግንባር ቀደም ተዋናይ መሆኗን ገልፃለች።
በጳጳሳት ሳይቀር የተመሩ የተለያዩ የልዑካን ቡድኖችን በመላክ ጉብኝት ካደረገችባቸው አካባቢዎች መካከል ፦
- የደቡብ፣
- የኦሮሚያ፣
- የትግራይ
- የአፋር እና የአማራ ክልሎች ይገኙባቸዋል።
ከዚህም በተጨማሪ በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች የእርቅ እና የሰላም ግንባታ ተግባራትን በማከናወን የተሳካ ውጤት ማስመዝገቧን ቤተክርስቲያኗ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በላከችው መልዕክት ገልፃለች።

እናት ፓርቲ ለአፋር እና ሱማሌ ክልል ርዕስ መስተዳደሮች ደብዳቤ ላከ።
ፓርቲው በላከው ደብዳቤው በአዳይቱ እና ገዳማይቱ አካባቢ ባለው ችግር ምክንያት የሚጠፋው የንፁሃን ህይወት እንደሚያሳስበው ገልጾ ክልሎቹ ያለውን ችግር በውይይቱ ይፈቱት ዘንድ ጠይቋል።
እናት ፓርቲ ፥ "ኢትዮጵያ በክፉ ሀሳብ በተጠነሰሰ ጦርነት እየተለበለበች ባለችበት በዚህ ወቅት በአዳይቱና ገዳማይቱ አካባቢ፣ በሁለቱ ክልሎች መካከል እሰጥ አገባው ተባብሶ ጦርነት ወደሚመስል ኩነት መቀየሩ እና በዚሁ ሳቢያ ከዕለት ወደዕለት ንጹሓን መሞታቸው እጅጉን ያሳስበናል" ብሏል።
በሌላ በኩል እናት ፓርቲ በሰሜን ጎንደር ዞን፣ ዳባት ወረዳ፣ ጭና ቀበሌ በንጸሓን ላይ የደረሰውን ጭፍጨፋ በጽኑ አወግዛለሁ ብሏል።
እንዲህ ያሉ ተመሳሳይ ተግባሮች " ሕወሓት " በተቆጣጠራቸው የሰሜን ወሎ አካባቢዎች ዳግም ላለመፈጸማቸው ዋስትና የለምና መንግስት አስፈላጊውን ርብርብ ሁሉ አድርጎ እንዲታደጋቸው ሲልም ፓርቲው ዛሬ ባወጣው መግለጫ አሳስቧል።