TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.5K videos
211 files
4.1K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
" ... ሱዳን እየሄደችበት ያለው መንገድ የተሳሳተ እና የማይጠቅማት በመሆኑ ከድርጊቷ ብትቆጠብ መልካም ነው" - አምባሳደር ዲና ሙፍቲ

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ የሆኑት አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ፤ ሱዳን ከተሳሳተው መንገዷ እንድትመለስ አሁንም ኢትዮጵያ ትጠይቃለች አሉ።

ሱዳን በተጠናቀቀው አመት የኢትዮጵያን ድንበር አልፋ የተለያዩ ትንኮሳዎችን ማድረጓን ያስታወሱት አምባሳደር ዲና " አሁንም ሱዳን ከተሳሳተው መንገዷ እንድትመለስ ኢትዮጵያ ትጠይቃለች " ብለዋል።

አምባሳደር ዲና ፥ የኢትዮጵያ መንግስት ከሱዳን ጋር ያለውን የድንበር ውዝግብ በትዕግስት መከታተሉን ያነሱ ሲሆን በተጠናቀቀው 2013 ዓ / ም ኢትዮጵያ ከገጠሟት ችግሮች የሱዳን ድንበር ውጥረት አንዱ መሆኑን አስታውቀዋል።

ቃል አቀባዩ ፥ " ችግሩ ባይፈታም ኢትዮጵያ 🇪🇹 ግን ጉዳዩን በበሳል ዲፕሎማሲ እይታ ተከታተለዋለች " ብለዋል። ሱዳን እየሄደችበት ያለው መንገድ የተሳሳተና የማይጠቅማት በመሆኑ ከድርጊቷ ብትቆጠብ መልካም እንደሆነ ተናግዋል፡፡

ከእንደዚህ አይነት ድርጊት በዘለለ ደግሞ #የአፍካውያን_ኩራት በሆነው አየር መንገዳችን ስም ለማጠልሸት የሚደረገውንም ድርጊት ኮንነዋል፡፡

Credit : Ethio FM 107.8

@tikvahethiopia