TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.2K photos
1.5K videos
211 files
4.1K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#UPDATE

ስቴም ፓወር ከቪዛ እና ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር ባዘጋጁት የሥራ ፈጠራ ክህሎት እና መሰረታዊ የፋይናንስ ትምህርት ላይ በመጀመሪያው ዙር 114 ሰልጣኞች እድሉን ያገኙ ሲሆን በሁለተኛው ዙር ከ190 በላይ ሰልጣኞች ስልጠናውን ወስደዋል።

ስልጠናውን ከወሰዱ ሰልጣኞች መካከል የራሳቸውን የፈጠራ ሀሳብ ይዘው ለመጡ የመነሻ የገንዘብ ተሰጥቷቸው በቡድን እንዲሁም በግል ሆነው ሥራቸውን ጀምረዋል። ሥራቸውን ከጀመሩ በኋላም የቴክኒካል ድጋፍ እየተደረገላቸው ይገኛል።

ስቴም ፓወር ፣ ከቪዛ እና ከቲክቫህ ኢትዮጵያ አጋርነት እየተካሄደ ያለው ይህ ፕሮጀክት ከሰብ ሰሀራ በታች ካሉ ሀገራት ቪዛ ካከናወናቸው ፕሮጀክቶች ምርጡ በመሆን ተመርጧል።

በሥራ ፈጠራ ክህሎት እና በመሰረታዊ የፋይናንስ ትምህርት ላይ ያተኮረው ይኸው ስልጠና ሦስተኛ ዙር ሰልጣኞችን ተቀብሎ ለማሰልጠን በምዝገባ ላይ ይገኛል። በሥልጠናው መሳተፍ የምትፈልጉ በተለይ የፈጠራ ሀሳብ ያላችሁ በነጻ መመዝገብ ትችላላችሁ።

ለመመዝገብ https://forms.office.com/r/ybgjUvNkKE

@tikvahethiopia
"...ከበዓሉ ጋር ተያይዞ ርችት መተኮስ በፍፁም የተከለከለ ነው" - የአዲስ አበባ ፖሊስ

የአዲስ አበባ ፖሊስ ከበዓሉ ጋር ተያይዞ ርችት መተኮስ በፍፁም የተከለከለ መሆኑን በዛሬው ዕለት አሳውቋል።

ክልከላው የተላለፈው የተለያዩ አጋጣሚዎችን በመጠቀም የከተማውን ሰላም ለማደፍረስ የሚንቀሳቀሱ የጥፋት ሃይሎችን ለመቆጣጠር እና ምቹ ሁኔታ ማሳጣት እንዲቻል ነው ሲል ፖሊስ ገልጿል።

ህብረተሰቡ ከበዓሉ ጋር ተያይዞ ርችት መተኮስ በፍፁም የተከለከለ መሆኑን ተገንዝቦ ለጋራ ደህንነት አስፈላጊውን ትብብር ሊያደርግ እንደሚገባ ፖሊስ አሳስቧል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Bahirdar በአማራ ክልል መዲና ባህር ዳር ከተማ ማታ ማታ የሚኒቀሳቀሱ ባጃጆች ቁጥር እንዲወሰን ተደረግ። ይህ ውሳኔ የተላለፈው አሁን ባለው ወቅታዊ ሁኔታ ወንጀል እንዳይከሰት ለመቆጣጠር ያመች ዘንድ እንደሆነ ተነግሯል። እንደሀገር ሆነ እንደ ክልል የተከሰተውን የፀጥታ ሁኔታ በተገቢ መንገድ ለመምራት በባህር ዳር በህጋዊ መንገድ ተደራጅተው የትራንስፖርት አገልግሎት እየሰጡ የሚገኙ የባጃጅ ማህበራት…
* ባህር ዳር

"የሰዓት ገደቡ ተነስቷል" - የባህርዳር ከተማ ፀጥታ ም/ቤት

በአማራ ክልል መዲና ባህርዳር ከተማ እስከ ምሽቱ አራት (4) ሰዓት ተጥሎ የነበረው የሰዓት ገደብ ከዛሬ ጀምሮ መነሳቱን የባህርዳር ከተማ አስተዳደር የፀጥታ ምክር ቤት አስታውቋል።

በሌላ በኩል በየከተማው መግቢያና መውጫ ከፖሊስ፣ ከአድማ ብተና ውጭ ማንም መኪና አስቆሞ መፈተሽ የተከለከለ መሆኑን ጥብቅ ማሳሰቢያ ተላልፏል።

የባህር ዳር ነዋሪዎች ለፖሊስና ለፀጥታ አካላት መረጃ እና ጥቆማ ለመስጠት በ 0582264666 መደወል ይችላሉ ተብሏል።

Credit : ባህር ዳር ኮሚኒኬሽን

@tikvahethiopia
#ETHIOPIA😷

በኮቪድ-19 ሳቢያ በአንድ ቀን የ27 ዜጎች ህይወት አለፈ። በየዕለቱ በሽታው የሚገድላቸው ሰዎች ቁጥር እይሻቀበ ነው።

ዛሬ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የጤና ሚኒስቴር ይፋ ባደረገው ሪፖርት ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ 27 ሰዎች ሲሞቱ ከተደረገው 7,728 የላብራቶሪ ምርመራ ደግሞ 1,352 ሰዎች ለቫይረሱ ተጋላጭ ሆነው ተገኝተዋል።

የዛሬው ሪፖርት እንደሚያሳየን 756 ሰዎች በፅኑ ታመዋል [ከትላንትናው በ30 ሰዎች ጨምሯል]

የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ከቀን ወደ ቀን እየከፋ በመሆኑ መላው የቲክቫህ አባላት ጥንቃቄያችሁን ከመቼውም ጊዜ በላይ እንድታጠነክሩ አደራ እንላለን።

@tikvahethiopia
መተከል ዞን ግድያው ቀጥሏል።

ትላንት በዚሁ መተከል ዞን ዳንጉር ወረዳ 5 የጸጥታ ኃይሎች እና 1 የቻይና ዜጋ በታጣቂዎች ተገድለዋል።

ይህንንም ግድያ የክልሉ የሰላም ግንባታ እና ጸጥታ ቢሮ ለኢትዮጵያ ኢንሳይደር ድረገፅ በሰጡት ቃል አረጋግጠዋል።

ትላንት አመሻሽ ላይ በታጣቂዎች በተፈጸመው ጥቃት ፤ በመንገድ ስራ ላይ የተሰማሩ አንድ ቻይናዊ እና ኢትዮጵያዊ መገደላቸውን ቢሮው ገልጿል።

በትላንቱ ጥቃቱ የተገደሉት የጸጥታ ኃይሎች፤ አንድ የመከላከያ ሰራዊት አባል እና አራት የፌደራል ፖሊሶች ናቸው። ከእነርሱ በተጨማሪ ሁለት የጸጥታ ኃይሎች ላይ የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል።

በጥቃቱ ህይወታቸውን ያጡት ቻይናዊ እና ኢትዮጵያዊ የመንገድ ሰራተኞች ፤ ከግልገል በለስ ወደ ጉባ በሚወስደው የ70 ኪሎ ሜትር መንገድ ስራ ላይ የተሰማሩ እንደነበር የክልሉ ሰላም ግንባትና ፀጥታ ቢሮ አሳውቋል።

የግልገል በለስ – ጉባ መንገድ ከአዲስ አበባ በደብረ ማርቆስ፣ አንጅባራ እና ቻግኒ አድርጎ ወደ ህዳሴው ግድብ የሚወስድ ዋነኛ መንገድ ነው።

Credit : www.ethiopiainsider.com

@tikvahethiopia
* ደብረ ማርቆስ

" ከዛሬ ጀምሮ በደብረ ማርቆስ የተጣለው የሰዓት ዕላፊ ገደብ እስከ ምሽቱ 4 ሰዓት እንዲሆን ተወስኗል " - የደ/ማርቆስ የፀጥታ ግብር-ሃይል

በደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳር ከዚህ ቀደም የተላለፉት ሌሎች ውሳኔዎች እንደተጠበቁ ሆነው የሰዓት ዕላፊ ገደቡ ማሻሻያ እንደተደረገበት የደ/ማርቆስ የፀጥታ ግብር-ሃይል አስታውቋል።

በዚህ መሰረት ከንጋቱ 12 ሰዓት በፊት መንቀሳቀስ እንደማይቻል የተከለከለው የሰአት እላፊ ገደብ ወደ ንጋቱ 11 ሰዓት ዝቅ እንዲል ተደርጓል።

ከምሽት 3 ሰዓት የነበረው የሰዓት ዕላፊ ገደብ ደግሞ ወደ ምሽቱ 4 ሰዓት ተሻሽሏል።

የከተማዋ ማህበረሰብ ለራሱ ሰላም ሲል የተጣለውን የሰዓት ገደብ አክብሮ መንቀሳቀስ እንደሚገባው ተገልጿል።

@tikvahethiopia
ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ አዲሱ 2014 ዓ.ምትን በማስመልከት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ።

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት አዲሱን ዓመት 2014 ዓ/ም በማስመልከት ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ ባስተላለፉት አባታዊ መልዕክት ዘመኑ አዲስ ሊሆን የሚችለው እኛ በምናበረክተው ሥራ እንጂ ዘመኑ በራሱ አዲስ ሊሆን አይችልምና እግዚአብሔር አምላክ የሚወዳችሁ እና እግዚአብሔርን የምትወዱ ልጆቻችንና ወገኖቻችን በሙሉ አዳዲስ ሥራዎችን በመፍጠር አዲሱን ዓመት በሁለመናው አዲስ አድርገን እናክብረው ብለዋል።

አዲስ ዓመት ሲመጣ የደስታና የተሐድሶ ልቡና ዘመን እንዲሆንልን ከመመኘት ጋር በብሩህ ተስፋ መቀበላችን መልካም ነው። ያሉት ቅዱስ ፓትርያርኩ ይሁንና የሰላምና የእድገት ምኞታችን ወደ ተጨባጭ ፍሬ ሊደርስ የሚችለው በሥራ ብቻ መሆኑን መገንዘብ ይኖርብናል ብለዋል።

ቅዱስነታቸው አዲሱን ዓመት በማስመልከት ለመላው ኢትዮጵያዊያን ያስተላለፉት አባታዊ የመልካም ምኞት መግለጫ መልዕክት ሙሉ ቃል ከላይ ቀርቧል።

ምንጭ፦ የኢኦተቤ ህዝብ ግንኙነት መምሪያ

@tikvahethiopia
24 አገር በቀል የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች የአዲስ ዓመት የሰላም ጥሪ አቀረቡ።

የሰላም ጥሪው ያቀረቡ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶቹ ባሁኑ ወቅት አገራችን ኢትዮጵያ በከባድ ቀውስ ውስጥ ትገኛለች ሲሉ ገልፀዋል።

- በትግራይ
- በአማራ
- በምዕራብና ደቡብ ኦሮሚያ
- በሶማሊ
- በአፋር
- በቤኒሻንጉል ጉሙዝ
- በደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልሎች በሚካሔዱ ግጭቶች ምክንያት በሺሕ የሚቆጠሩ ወገኖቻችን እየሞቱ ነው ብለዋል።

በመቶ ሺሕዎች የሚቆጠሩ ከቀያቸው እየተፈናቀሉ መሆኑንም አንስተዋል። ሚሊዮኖች የአስቸኳይ ጊዜ ዕርዳታ ላይ ጥገኛ እየሆኑ ነው ሲሉ ገልፀዋል።

"ሕፃናት ልጆቻችን፣በዕድሜ የገፉ ወገኖቻችን እና ሴቶቻችን በተለየ ሁኔታ ለመከራ ተጋላጭ እየሆኑ፣ ጾታዊ ጥቃትንና ግድያን ጨምሮ የተለያዩ የሰብዓዊ ጥሰቶች ሰለባ በመሆን ላይ ናቸው" ብለዋል።

ኢኮኖሚው በከፍተኛ ደረጃ እየተጎዳ፣ መሠረተ ልማቶች እየወደሙ መሆኑንም አንስተዋል።

ግጭቶችን በሰላም ለመፍታት የሚጠቅሙ የሽምግልናና የዕርቅ ባሕላዊና ማኅበራዊ አቅሞችን ለመጠቀም እየተደረገ ያለነው ሁለገብ ጥረት እስካሁን ሰላምን ሊያረጋጋጥ እንዳልቻለ ድርጅቶቹ አንስተዋል።

በዚህም ሕዝቡ ለዘመናት ደግፈው ያቆዩ ማኅበራዊ እሴቶች ሳይቀሩ አደጋ ላይ ሊወድቁ ይችላሉ ብለዋል።

"በዚህ ሰብዓዊ፣ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ቀውስ ውስጥ በመቆየት የምናገኘው ነገር ቢኖር ያሁኑ ማኅበራዊ ግንኙነታችንን የበለጠ ማሻከር ብቻ ሳይሆን፥ለመጪው ትውልድም ቂምና ቁርሾ ማውረስን ሊሆን ይችላል" ሲሉ ገልፀዋል።

የአገር በቀል ሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶቹ ላለፉት በርካታ ወራት በኢትዮጵያ እየተስተዋሉ ያሉ ግጭቶች በአስቸኳይ መቆም አለባቸው ያሉ ሲሆን ለሰላም ዕድል ሊሰጠው ይገባል በሚል ጥሪ አቅርበዋል።

* ዝርዝሩን ከላይ ይመልከቱ።

@tikvahethiopia
ከወራት በፊት የጀመረው ምርመራ ተጠናቋል።

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (UN) እና ኢሰመኮ ምርመራ ቡድን በትግራይ ያካሄዱትን የመስክ ስራ አጠናቀዋል።

ሁለቱ ተቋማት የመስክ ምልከታ አድርገው መረጃዎችን ፤ ቃለመጠይቆችን እና ሌሎች አስፈላጊ ማስረጃዎችን የመሰብሰብ ስራዎችን ማጠናቀቃቸውን ተገልጿጻ።

የመስክ ምርመራ ስራው የተካሄደው ፦
- በመቐለ
- ውቅሮ፤
- ሳምረ፤
- አላማጣ፤
- ቦራ፤
- ማይጨው፤
- ዳንሻ፤
- ማይካድራ፤
- ሁመራ፤
- ጎንደር ፤
- ባህርዳር እና አዲስ አበባ ከተሞች ነው።

ተቋማቱ የጋራ ምርመራቸውን ያካሄዱት ከፈረንጆቹ ግንቦት 16 አስከ ነሀሴ 20 ቀን 2021 ድረስ ሲሆን ከ200 በላይ ሰዎችን ቃለመጠይቅ አድርገዋል።

በሁለቱ የጋራ ተቋማት የመስክ መርማሪዎች በአደጋው የተጎዱ ፦
- ሰዎችን፤
- የአይን ምሰክሮች፤
- የሲቪል ማህበረሰብ ተቋማት ሰራተኞችን፤
- የክልል እና የፌደራል ተቃማት ሰራተኞችን እና አመራሮችን፤
- የህክምና ባለሙያዎችን፤
- የፍትህ አካላትን እና ሌሎች ስለ ጉዳዩ ያውቃሉ የተባሉ አካላትን እና ተቋማትን ሁሉ ቃለመጠይቅ አድርገዋል።

ከዚህ በተጨማሪም፦ የምስል እና የዶክመንት ማስረጃዎችን፤ ቪዲዮዎችን እና ሌሎች ለምርመራ ይጠቅማሉ የተባሉ መረጃዎችን ሁሉ አሰባስበዋል።

በአካባቢዎቹ የደህንነት ችግር መኖሩ ለምርመራ ስራው እንቅፋት እንደሆነባቸው ገልፀዋል።

Credit : Al AIN

@tikvahethiopia
ሩሲያ ለኢትዮጵያውያን አዲስ ዓመት " እንኳን አደረሳችሁ " መልዕክት አስተላለፈች።

ሩሲያ አዲስ አበባ በሚገኙት አምባሳደሯ ኤቭጌኒ ቴርኪን የኢትዮጵያውያን አዲስ ዓመትን በማስመልከት እንኳን አደረሳችሁ መልዕክቷን አስተላልፋለች።

አምባሳደር ኤቭጌኒ ቴርኪን ዛሬ በአማርኛ ቋንቋ ባሰላለፉት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት ፥ "በመጪው ዓመት ኢትዮጵያውያን ቤተሰቦች ሁሉ ብልፅግና ፣ ሰላም ፣ ፍቅር እንዲሰፍንላችሁ ከልብ እመኛለሁ" ብለዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የጊኒው መፈንቅለ መንግስት ... በምዕራብ አፍሪካዊቷ አገር ጊኒ ውስጥ ወታደሮች መፈንቅለ መንግሥት አካሂደው ባለፈው ዓመት በምርጫ ያሸነፉትን ፕሬዝዳንት ከመንበራቸው ማስወገዳቸውን ገለጹ። ወታደሮቹ መፈንቅለ መንግሥት አካሂደው ሥልጣን መቆጣጠራቸውን የሚያሳይ ቪዲዮ በቴሌቪዥን ከታየ በኋላ ፕሬዝዳንቱ አልፋ ኮንዴ የት እንዳሉ አልታወቀም። ወታደሮቹ በአገሪቱ ብሔራዊ ቴሌቪዥን ላይ ቀርበው የአገሪቱን መንግሥት…
ጊኒ ከአፍሪካ ህብረት አባልነት ታገደች።

ባለፈው ሳምንት መጨረሻ እሁድ ዕለት መፈንቅለ መንግሥት የተካሄደባት ጊኒ ከአፍሪካ ህብረት አባልነቷ ታግዳለች።

ይህን ያሳወቀው የህብረቱ የፖለቲካ ጉዳዮች የሰላምና ደህንነት መምሪያ ነው።

ጊኒ ከአፍሪካ ህብረት አባልነት ከመታገዷ በተጨማሪ አባል ከሆነችበት 15 አባላት ያሉት የምዕራብ አፍሪካ ሀገራት የኢኮኖሚ ማህበረሰብ (ኢኮዋስ) ከትላንት በስቲያ ታግዳለች።

ጊኒን ሲመሩ የነበሩት ፕሬዚዳንት አልፋ ኮንዴ በኮሎኔል ማማዲ ዱምቦያ በሚመራው የወታደሮች ቡድን ከስልጣናቸው እንዲነሱ መደረጉ አይዘነጋም።

መፈንቅለ መንግሥቱ የተመድ ዋና ፀሃፊ እና የአሜሪካ አመራሮችን ጨምሮ በአፍሪካ ህብረትና በተለያዩ የቀጠናው መሪዎች ተወግዟል።

Credit : BBC

@tikvahethiopia
* MSF

MSF በተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች የሚያከናውናቸውን ሥራዎቹን አቋርጧል።

MSF ስራውን ያቋረጠው በተጣለበት እገዳ መሆኑን ገልጿል።

MSF በላከው መግለጫ ከኢትዮጵያ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ኤጀንሲ የተጣለበትን የስስት ወራት ዕገዳን በማክበር ፦
- በአማራ፣
- በጋምቤላ፣
- በሶማሌና
- በደቡብና ሰሜን ምዕራብ ትግራይ ክልል ውስጥ ያለውን ሥራውን አቁሟል።

በተጠቀሱት አካባቢዎች ያለውን ሥራውን ቢያቋርጥም ፦
- በአዲስ አበባ፣
- በኦሮሚያ ጉጂ፣
- በደቡብ ክልልና
- በደቡብ ምሥራቅ ትግራይ ውስጥ የህክምናና የሰብአዊ እርዳታ አገልግሎቱን ይቀጥላል።

የእገዳ ትዕዛዙ ከተሰጠው በኋላ የሚደረገው ምርመራ እስኪጠናቀቅ ድረስ የሚሰጠውን የህክምናና የሰብአዊ እርዳታ ሥራዎችን ጨምሮ ሁሉንም ተግባራቱን ለ4 ወራት አቋርጧጣ።

በዚህም መሠረት MSF ባሉት ክሊኒኮች ውስጥ የነበሩ ታካሚዎች በአጭር ማስጠንቀቂያ እንዲወጡ መደረጉንና 1 ሺ የሚደርሱ ኢትዮጵያውያን ሠራተኞቹ ከቤታቸው ሆነው እንዲጠባበቁ እንዲሁም ሁሉም በሚባል ደረጃ የውጭ አገር ዜጋ የሆኑ ሠራተኞቹ ከአገሪቱ እንዲወጡ መደረጋቸውን አመልክቷል።

MSF እነዳለው የሚያካሂደው የህክምናና የሰብአዊ እርዳታ ሥራ እንዲያቋርጥ የታዘዘው በአገሪቱ ያለው የተለያየ አይነት የሰብአዊ እርዳታ ፍላጎት ከፍተኛ በሆነበት ጊዜ መሆኑን ገልጿል።

በሌላ በኩል ዮሀንስ፣ ማሪያና ቴድሮስ በጭካኔ ሁኔታ ከተገደሉ ሶስት ወራት እንዳለፋቸው የገለፀው MSF የግድያቸው ሁኔታ ካለመጣራቱም በላይ ለግድያው ዋስትና የወሰደ አካል የለም ብሏል።

@tikvahethiopiA
* እንዳትደናገጡ !

የኢፌዴሪ መከላከያ ሚኒስቴር ነገ መስከረም 1/ 2014 ዓ/ም የሚከበረውን የአዲስ ዓመት ማብሰሪያ ምክንያት በማድረግ በዕለቱ ከንጋቱ 12 ሰዓት ላይ ለ21 ጊዜ መድፍ እንደሚተኮስ አስታውቋል።

ህብረተሰቡ ይህን አውቆ እንዳይደናገጥና የጸጥታ አካላት የሚጠበቅባቸውን ሃላፊነት እንዲወጡ የአዲስ አበባ ፖሊስ አሳስቧል።

@tikvahethiopia
እንቁጣጣሽ ሎተሪ ወጣ !

እንቁጣጣሽ ሎተሪ ዛሬ አርብ ጷጉሜን 5 ቀን 2013 ዓ.ም በብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር ዕድል አዳራሽ ከምሽቱ 12፡00 ሰዓት ላይ በህዝብ ፊት ወጥቷል፡፡

በዚህም መሰረት የወጡት የአሸናፊ ዕጣ ቁጥሮች እንደሚከተሉት ሆነዋል፡፡

1ኛ. 20,000,000 ብር የሚያስገኘው የ1ኛ ዕጣ ቁጥር 0580856

2ኛ. 10,000,000 ብር የሚያስገኘው የ2ኛ ዕጣ ቁጥር 0470508

3ኛ. 5,000,000 ብር የሚያስገኘው የ3ኛ ዕጣ ቁጥር 1973063

4ኛ. 3,000,000 ብር የሚያስገኘው የ4ኛ ዕጣ ቁጥር 0612715

5ኛ. 1,500,000 ብር የሚያስገኘው የ5ኛ ዕጣ ቁጥር 0816001

6ኛ. 750,000 ብር የሚያስገኘው የ6ኛ ዕጣ ቁጥር 1963913

7ኛ. 300,000 ብር የሚያስገኘው የ7ኛ ዕጣ ቁጥር 0716025

8ኛ. 20 ዕጣዎች እያንዳንዳቸው ብር 20,000 የሚያስገኘው ዕጣ ቁጥር 37510

9ኛ. 20 ዕጣዎች እያንዳንዳቸው ብር 10,000 የሚያስገኘው ዕጣ ቁጥር 79593

10ኛ. 20 ዕጣዎች እያንዳንዳቸው ብር 5,000 የሚያስገኘው ዕጣ ቁጥር 27663

11ኛ. 200 ዕጣዎች እያንዳንዳቸው ብር 2,000 የሚያስገኘው ዕጣ ቁጥር 8326

12ኛ. 200 ዕጣዎች እያንዳንዳቸው ብር 1,000 የሚያስገኘው ዕጣ ቁጥር 2843

13ኛ. 2,000 ዕጣዎች እያንዳንዳቸው ብር 500 የሚያስገኘው ዕጣ ቁጥር 022

14ኛ. 20,000 ዕጣዎች እያንዳንዳቸው ብር 300 የሚያስገኘው ዕጣ ቁጥር 42

15ኛ. 200,000 ዕጣዎች እያንዳንዳቸው ብር 100 የሚያስገኘው ዕጣ ቁጥር (የማስተዛዘኛ ዕጣ) ደግሞ 2 ቁጥር በመሆን ወጥቷል፡፡

Credit : National Lottery Administration

@tikvahethiopia