#Burji
የቡርጂ ልዩ ወረዳ ንግድና ገበያ ልማት ጽ/ቤት ያለምንም መሰረታዊ ምክንያት የተጋነነ የዋጋ ጭማሪ በተደረገባቸው ምርቶች ላይ እርምጃ እየወሰደ እንደሚገኝ አሳውቋል።
በዚህም መሰረት ፅ/ቤቱ እንዳሳወቀው ፦
- በ8 ብር ስሸጥ በነበረው እንቁላል ካለፈው የቅዳሜ ገበያ ጀምሮ በ5 ብር እየተሸጠ ነው።
- ዶሮ ከ700 እስከ 800 ብር ሲሸጥ የነበረው የሸማቹን አቅም ባገናዘበ መልኩ ከ300 እስከ 500 ብር እንዲሸጥ እየተደረገ ነው።
- በቆሎ በኪሎ 30 ብር ስሸጥ የነበረው ከ20-23 ብር ዝቅ እንዲል ተደርጓል።
- በአካባቢው በስፋት የሚመረተው የጤፍ ምርት በኪሎ 50 ብር ድረስ ሲሸጥ የነበረ ሲሆን ከ37 እስከ 40 ብር እንዲሸጥ እየተደረገ ነው።
በፍራፍሬ እና በሌሎች ምርቶች ላይ ተመሳሳይ እርምጃ እየተወሰደ መሆኑን ፅ/ቤቱ አሳውቋል።
Credit : SRTA
@tikvahethiopia

በንፁሀን ገበያተኞች ላይ በተፈፀመ ጥቃት በርካቶች ተገደሉ።
በቡርጂ ልዩ ወረዳ በ " ሶያማ ቡርጂ " ገቢያ ለመሸጥ በወጡ ንጹሐን ዜጎች ላይ በተፈጸመ አሰቃቂ ጥቃት የ9 ሰዎች ህይወት ማለፉን በኦሮሚያ ክልል የምዕራብ ጉጂ ሱሮ ቡርጉዳ ወረዳ አስታውቋል።
ጥቃቱ የተፈጸመባቸው ሰዎች ገበያተኞች እንደሆኑና ወደ ቡርጂ ከተማ በመጓዝ ላይ እያሉ '' የዚህን ሀገር ሰላም መረጋጋት በማይወዱ የ2ቱን ህዝቦች አንድነት በማይፈልጉ '' ባላቸው ሰዎች መፈጸሙን ወረዳው አስታውቋል።
በጥቃቱ እስካሁን ህይወታቸው እንዳለፈ ከተገለጸው 9 ሰዎች በተጨማሪ በ21 ሰዎች ላይ ከፍተኛ ጉዳት ደርሶ በቡሌ ሆራ ሆስፒታል እና በሶሮቲ ጤና ጣቢያ ህክምና እየተደረገላቸው ይገኛል ብሏል።
ወረዳው '' በዚህ ጭካኔ በተሞላበት መልኩ ህዝባችን ላይ በተፈጸመው ድርጊት ላይ የተሳተፉ ግለሰቦች በፍጥነት ተጣርቶ በህግ ሊጠይቁ ይገባል '' ያለ ሲሆን ሲሆን ህዝቡም ጉዳዩን በማስተዋልና በመረጋጋት እንዲከተተልና የህግ የበላይነት እንዲከበር የበኩሉን እንዲወጣ ጠይቋል።
የቡርጂ ልዩ ወረዳም ባወጣው ሀዘን መግለጫ ጥቃቱ መፈጸሙን ገልጿል።
'' የሸኔ ኦነግ እና የአጀንዳቸው ተሸካሚዎች አገራችንን የመበታተን አጀንዳ አንግበው በሕዝቦች መካከል ጥርጣሬ እንዲፈጠር በአዋሳኝ አከባቢዎች በቡርጂ አርሶ አደሮች እንድሁም ሰላማዊ የጉጂ አርብቶ አደሮች ላይ በተደጋጋሚ ጥቃት ቢያደርሱም ሰላም ወዳዱ ሕዝባችን እስካሁን ሰላሙን ጠብቆ ቆይቷል፡፡ '' ሲል መግለጫው ይጠቅሳል።
የትላንት ( 27/09/2014 ዓ.ም) ጥቃት '' የፀረ ሰላም ኃይሉ በማሳቸው በነበሩ አርሶ አደሮች ላይ ጥቃትና ግዲያ በመፈፀሙ ምክንያት የቡርጂን ባሕል እና ዕሴት በፍጹም በማይወክል አግባብ የሰላም መኖር የሚያንገሸግሻቸው ጥቅት ቡድኖች በገበያተኞች ላይ ላይ አሰቃቂ ግዲያ እና ጉዳት አድርሰዋል፡፡'' ብሏል።
ጥቃቱ ታስቦ በነበረበት ልክ እና መጠን ቢሆን ኖሮ አሁን ከደረሰው በላይ ጉዳት ልደርስ ይችል ነበር ያለው መግለጫው '' አብዛኛው ሕዝባችን ሰላም ወዳድነቱን በተግባር በማሳየት ወንድም ሕዝብ የሆነውን የጉጂ ሕዝብ ሸሽጎ በጉያው አቆይቶ ሸኝቷል '' ሲል ጠቅሷል።
እስካሁን ድረስ ንፁሃንን በአሰቃቂ ሁኔታ የገደሉ አካላት ስለመያዛቸው የተገለፀ ነገር የለም።