TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የፌዴሬሽን ምክር ቤቱ ውሳኔ👆

ጊዜያዊ አስተዳደር ለክልሉ ከፍተኛ የሕግ አስፈፃሚ አካል የተሰጡትን ተግባሮች እንደሚኖሩት ተገልጿል።

በተለይም ጊዜያዊ አስተዳደሩ ፦

ሀ) አስፈፃሚ አካሉን ይመራል፣ ያስተባብራል፤
ለ) የጊዜያዊ አስተዳደሩን ኃላፊዎች ይመድባል፤
ሐ) ሕግና ሥርዓት መከበሩን ያረጋግጣል፤
መ) አግባብ ባለው ህግ መሰረት በክልሉ ምርጫ የሚከናወንበትን ሁኔታ ያመቻቻል፤
ሠ) የክልሉን እቅድና በጀት ያፀድቃል፤
ረ) በፌዴራል መንግስቱ ሚሰጡ ሌሎች ተግባሮችን ያከናውናል ተብሏል።

የኢፌዴሪ ፌዴሬሽን ምክር ቤት
ጥቅምት 28/2013 ዓ/ም

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
ሰላም የሚወርደው መቼ ነው ?

የጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥ እና ጠ/ሚ አብይ አህመድ ምላሽ ፦

"...ይህ ግጭት የሚቆመው ህግን ስናስከብር ብቻ ነው።

የትግራይ ህዝብ ፣ የትግራይ ልዩ ኃይል እና የትግራይ ሚሊሻ መገንዘብ ያለበት ጥፍር የነቀሉ፣ ሰው የገደሉ፣ ሀብት የዘረፉ ወንጀለኞች ተለቅመው ወደ ህግ ሲቀርቡ በዛው ሰዓት ሁሉም ነገር ያበቃል፤ ይቆማል።

ይህ ፀብ ከጥቂት ስግብግብ ጁንታዎች ጋር እንጂ ከማንም ጋር ባለመሆኑ ሙሉ ግጭቱ እና ሁኔታው የሚቆመው እነዚህ ኃይሎች ለህግ ሲቀርቡ እና ህግ በሁላችንም ላይ የሚሰራ መሆኑን ስናረጋግጥ ነው።"

* ከዚህ በተጨማሪ እርቅ፣ ሰላም፣ ውይይት የሚለውን ሀሳብ ስለሚያነሱ አካላትን በተመለከተም ሀሳቡን እንደማይቀበሉት አረጋግጠዋል።

ላለፉት ሁለት ዓመት ተኩል ስለሰላም ፣ ለፍቅር ፣ ስለአንድነት ፣ ስለአብሮነት ያደረግናቸው ሙከራዎች ሁሉ እንደድካም እና እንዳለመቻል ነው የተቆጠሩት ብለዋል። "ደከም ሲል እርቅ ፤ ጠንከር ሲል ገዳይ ከሆነ ኃይል ጋር በሁለት መለዮ መጫወት አይቻልም" ሲሉ ተደምጠዋል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#EthiopianAirlines

በዛሬው ዕለት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሁለት እጅግ ዘመናዊ የኤርባስ ኤ 350 አውሮፕላኖችን መረከቡን አሳውቋል።

ይህንን በተመለከተ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ተወልደ ገብረማርያም ያስተላለፉት መልዕክት ከላይ ተያይዟል።

በነገራች ላይ አየር መንገዱ ከኤር ባስ ፋውንዴሽን ጋር በመተባበር አዳዲሶቹ አውሮፕላኖች ጭኖ ያመጣውን የእርዳታ እቃዎች ለጤና ጥበቃ ሚኒስቴር በዛሬው እለት መለገሱንም አሳውቋል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#BREAKING

CNN ጆ ባይደን የአሜሪካ ፕሬዜዳንት ሆነው መመረጣቸውን ይፋ አድርጓል።

ባይደን በፔንሲልቬኒያ ግዛት ማሸነፋቸው ተገልጿል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#ሰበር_ዜና

ዶናልድ ትራምፕ በምርጫው ተሸነፉ።

ጆ ባይደን 46ኛው የአሜሪካ ፕሬዜዳንት ሆነ ተመርጠዋል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#JoeBiden

የቀድሞው የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ ፥ ጆ ባይደን 46ኛው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ሆነው በመመረጣቸው "የእንኳን ደስ አሎት" መልዕክት በትዊተር ገፃቸው አስተላልፈዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#KamalaHarris

ካማላ ሃሪስ የመጀመሪያዋ ሴት ምክትል ፕሬዝዳንት ሆነዋል።

እንዲሁም ጥቁር እና እሲያ አሜሪካዊ ምክትል ፕሬዝዳንት በመሆን ታሪክ ሰርተዋል።

ካማላ ሃሪስ ከሕንድ ከሆኑት እናታቸው እና ከጀማይካ ከሆኑት አባታቸው በካሊፎርኒያ ነበር የተወለዱት።

የ55 ዓመቷ ካማላ ሃሪስ ከጆ ባይደን ጋር በመሆን አሜሪካንን ለመጪዎቹ 4 ዓመታት ይመራሉ። [BBC]

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#COVID19Ethiopia

የ24 ሰዓት የኮቪድ-19 ሪፖርት ፦

• የተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ - 6,028
• በበሽታው የተያዙ - 455
• ህይወታቸው ያለፈ - 6
• ከበሽታው ያገገሙ - 845

በአጠቃላይ በሀገራችን 99,201 ሰዎች በበሽታው መያዛቸው ሲረጋገጥ ፤ የ1,518 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ 58,948 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል።

306 ሰዎች በፅኑ ታመው የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ሰበር_ዜና ዶናልድ ትራምፕ በምርጫው ተሸነፉ። ጆ ባይደን 46ኛው የአሜሪካ ፕሬዜዳንት ሆነ ተመርጠዋል። @tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
ጆ ባይደን ማናቸው?

ጆ ባይደን የቀድሞ የፕሬዝደንት ባራክ ኦባማ ምክትል ፕሬዝደንት ሆነው አገልግለዋል።

የባይደን ደጋፊዎቻቸው የውጪ ጉዳይ ፖሊስ አዋቂ ናቸው ይሏቸዋል።

ጆ ባይደን የፖለቲካ ሕይወታቸው የጀመረው ከ47 ዓመታት በፊት ነበር።

ባይደን የአሜሪካ ፕሬዝደንት ለመሆን ጥረት ማድረግ የጀመሩት ደግሞ ከ33 ዓመታት በፊት እ.አ.አ. 1987 ጀምሮ ነው።

በጥቁር አሜሪካውያን ዘንድ ትልቅ ተቀባይነት አላቸው።

* የጆ ባይደን ውጭ ፖሊሲ ጉዳይ

ባይደን ዶናልድ ትራምፕ ያበላሹትን የውጭ ግንኙነት አስተካክላለሁ ፤ አሜሪካ ያስቀየመቻቸውን ወዳጆቿን ልብ እጠግናለሁ ብለዋል።

ከኢራን እና ከቻይና ጋር የሚከተሉት ፖሊሲም ትራምፕ ጋር የሚቃረን ነው።

ይህ መረጃ ከBBC የተወሰደ ነው።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#BidenHarris2020

ጠ/ሚር ዶክተር አብይ አሕመድ ለጆ ባይደን እና ካማላ ሃሪስ 'የእንኳን ደስ አላችሁ' መልዕክት በይፋዊ ትዊተር ገፃቸው ላይ አስተላልፈዋል።

"ኢትዮጵያ በቅርበት አብራችሁ ለመስራት በመጠባበቅ ላይ ናት" ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#FDREDefenseForce

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ መከላከያ ሠራዊት ምክትል ኤታማዦር ሹም እና የኦፕሬሽን ዘርፍ ኃላፊ የሆኑት ጄኔራል ብርሃኑ ጁላ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ መከላከያ ሰራዊቱ ፦
- ዳንሻን
- ባከርን
- ከሽራሮ አስከ ሽሬ ያሉ አካባቢዎች ሙሉ በሙሉ ተቆጣጥሮ ወደ ፊት እየገሠገሠ ነው ብለዋል።

መከላከያ "በከሀዲ ቡድኑ" እጅ ያሉ ከባድ መሳሪያዎች ሙሉ በሙሉ አውድሟልም ብለዋል።

ጄኔራል ብርሃኑ ጁላ፥ "የመከላከያ ሰራዊት ሕዝብ እንዳይጎዳ ለማድረግ እና ጽንፈኛውን ኃይል ከህዝብ ለይቶ ለመምታት በጥንቃቄ እየተንቀሳቀሰ ነው" ብለዋል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#FDREDefenseForce

የመከላከያ ሰራዊት ኢንዶክትሪኔሽን ዋና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ሜ/ጀ መሀመድ ተሰማ፥ ሰራዊቱ ሀገርን ከጥፋት የማዳን ተልዕኮውን በአጭር ጊዜ ያጠናቅቃል አሉ።

የኢትዮጵያን ዕድገት ማይፈልጉ ታሪካዊ የሆኑ ጠላቶች የታላቁ ህዳሴ ግድብ እንዳያደናቅፉ የሀገሪቱ የፀጥታ ሀይሎች በተጠንቀቅ በቆሙበት ባሁኑ ሰዓት ላይ የናት ጡት ነካሾች ሀገሪቱን በመድፈር ውጊያ ከፍተውብናል ብለዋል።

ሜ/ጄ መሀመድ ተሰማ፥ "ይህ ጦርነት ሀገርን ለውጭ አሳልፎ የሚሰጥና ፅንፈኛው ሀይል የስልጣን ጥማቱን ለማርካት የገባበት ነው" ሲሉ ተናገራዋል።

በአሁን ሰዓት ይህን ውጊያ ለመመከት መላው የፀጥታ ኃይሎች እየተዋጉ ወንጀለኞችን ወደ ህግ ለማቅረብ ፍልሚያ ላይ ይገኛሉ ሲሉ አስረድተዋል።

ዳይሬክተሩ ሜ/ጄ መሀመድ ፥ "ሠራዊቱ ፅንፈኛውን ሀይል በአጭር ጊዜ በቁጥጥር ስር በማዋልና ለህግ በማቅረብ የአካባቢው ሕዝብ ከነበረበት ጭቆና ነፃ እንደሚወጣ እናረጋግጣለን" ብለዋል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#BREAKING

የአማራ ክልል ፕሬዜዳንት አቶ ተመስገን ጥሩነህ የስልጣን መልቀቂያ ጥያቄ አቀረቡ።

አቶ ተመስገን ጥያቄውን ያቀረቡት ምክር ቤትቱ 5ኛ ዙር 6ኛ ዓመት የስራ ዘመን 16ኛ መደበኛ ጉባኤውን በሚያካሂድበት ወቅት ነው።

ሀገሪቱ ካለችበት ወቅታዊ ሁኔታ አንፃር በተሠጣቸው ተልእኮ ምክንያት ነው ጥያቄውን ያቀረቡት ተብሏል።

የምክር ቤት አባላቱ በጉዳዩ ላይ ሰፊ ምክክር ካካሄዱ በኋላ ጥያቄያቸውን ተቀብሏል።

ለቀጣይ የክልሉ በርእሰ መስተዳድርነት "አቶ አገኘሁ ተሻገር" በእጩነት መቀረባቸውን ኢቲቪ ዘግቧል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#BREAKING

አቶ አገኘው ተሻገር የአማራ ክልል ርእሰ መስተዳድር ሆነው ተሾሙ።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#BREAKING

ከጥቅምት 25 ቀን 2013 ዓ.መ ጀምሮ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የተሰጡ ሹመቶች ፦

- አቶ ደመቀ መኮንን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር

- ጄኔራል ብርሃኑ ጁላ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም

- ሌ/ጄኔራል አበባው ታደሰ የጦር ኃይሎች ምክትል ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም

- አቶ ተመስገን ጥሩነህ የብሔራዊ መርጃ እና ድህንነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር

- ኮሚሽነር ደመላሽ ገ/ሚካኤል የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽነር

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#BREAKING

ጠ/ሚር ዶክተር አብይ አህመድ ከጥቅምት 25 ቀን 2013 ዓ/ም ጀምሮ አቶ ገዱ አንዳርጋቸውን የጠቅላይ ሚንስትሩ የብሔራዊ የደህንነት አማካሪ ሚንስትር አድርገው ሾመዋል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia