TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.4K photos
1.43K videos
206 files
3.95K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#JoeBiden

በውዝግብ በተሞላው 2020 አሜሪካ ፕሬዜዳንታዊ ምርጫ ጆ ባይደን ያሸንፋሉ ተብሎ እየተጠበቀ ነው።

የጆ ባይንደን ምርጫ ቅስቀሳ ማናጀር ባይደን ወደ ዋይት ሃውስ የሚያስገባቸውን ድምፅ ያገኛሉ (ምርጫውን ያሸንፋሉ) ብለዋል።

አጠቃላይ ቆጠራው እስካሁን ተጠቃሎ አልተጠናቀቀም።

ጆ ባይደን በይፋዊ የትዊተር ገፃቸው ከላይ የምትመለከቱትን መረጃ አጋርተዋል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#JoeBiden

ጆ ባይደን የ2020 አሜሪካ ፕሬዜዴንታዊ ምርጫ ለማሸነፍ ተቃርበዋል።

እስካሁን ሙሉ ለሙሉ ውጤት ተጠቃሎ ባይገለፅም ባይደን 264 ለ 214 ትራምፕን እየመሩ ይገኛሉ።

ፕሬዜዳንት ሆኖ ለመመረጥ 270 ድምፅ ያስፈልጋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#JoeBiden

ጆ ባይደን ከ270 በላይ ድምፅ አግኝተው 46ኛው የአሜሪካ ፕሬዚደንት ለመሆን እየተቃረቡ ነው።

ባይደን ቁልፍ በተባሉ ግዛቶች እየመሩ ይገኛሉ። (SBS)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#JoeBiden

የቀድሞው የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ ፥ ጆ ባይደን 46ኛው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ሆነው በመመረጣቸው "የእንኳን ደስ አሎት" መልዕክት በትዊተር ገፃቸው አስተላልፈዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#JoeBiden

ጆ ባይደን የፕሬዜደንታዊ ምርጫው ውጤት በኤሌክቶራል ኮሌጅ #ተረጋግጦላቸው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ሆነው በይፋ መሰየማቸውን BBC ዘግቧል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#DrAbiyAhmed #JoeBiden

የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ከአሜሪካ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ጋር የስልክ ውይይት አደረጉ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ከአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ጋር በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ግልፅ የስልክ ውይይት ማድረጋቸውን አስታውቀዋል።

ከፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ጋር በተለይም በሁለትዮሽ ግንኙነት እና በቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ የስልክ ውይይት ማድረጋቸውን ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ የትስስር ገጻቸው ላይ ጠቁመዋል።

ውይይቱ ሁለቱ አገራት በጋራ መከባበር ላይ የተመሰረተ ገንቢ ተሳትፎ በማድረግ ትብብራቸውን ለማጠናከር ትልቅ ጥቅም እንዳለው ሁለታችንም ተስማምተናል ብለዋል።

#DrAbiyAhmed #ENA

@tikvahethiopia