TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.91K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
❤️የውቕሮ ኣፀደ ህፃናት ተማሪዎች ዛሬ በኣከባቢያቸው የኣንበጣ መንጋ ሲያባሩሩ የሚያሳይ ፎቶ ነው ካላይ የምትመለከቱት፤ ሁላችንም ከተተጋገዝን ኣከባቢያችን ነፃ ማድረግ አንችላለን!!

Via ተስፋይ (መቐለ የቲክቫህ ቤተሰብ)
PHOTO: GECHO

@tsegabwolde @tikvahethiopia
❤️በፎቶው ላይ የምትመለከቱት የፖሊስ ኦርኬስትራ አባል ነው፤ ባለው ችሎታ በሙዚቃ መሳሪያ የአምበጣ መንጋ ማባረር ዘመቻ ላይ ተሳትፎ ሲያደርግ ይታያል!! ከተባበርን ከተጋገዝን አካባቢያችን ነፃ ማድረግ እንችላለን!!

PHOTO: Abel ZeKiros
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Audio
በአቶ ገመቺስ ታደሰ ግድያ ጋር ተያይዞ የተጠረጠሩ በቁጥጥር ሥር ዋሉ!
#ነቀምት

ዛሬ ምሽት የአሜሪካ ድምፅ ራድዮ ጣቢያ በሰራው ዘገባ በምራዕብ ቀጠና የኢትዮ ቴሌኮም ኃላፊ አቶ ገመቺስ ታደሰ ግድያ ጋር ተያይዞ የተጠረጠሩ ሁለት ግለሰቦች ቁጥጥር ሥር መዋላቸውን የነቀምቴ ከተማ ፖሊስን ጠቅሶ ዘግቧል፡፡ ኃላፊው ከትናንት በስቲያ ዕሁድ አመሻሽ 1 ሠዓት ገደማ ማንነታቸው ባልታወቁ ግለሰቦች መገደላቸውን ፖሊስ አስታወቋል፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
"ቲክቫህ ስፖርት" ስፖርታዊ ጉዳዮችን እጅግ ባማረና ለየት ባለ አቀራረብ መከታተል ትችላላችሁ። እንዲሁም በየጊዜው የተለያዩ ስጦታዎችን ከቲክቫህ ስፖርት አጋሮች የማግኘት እድልም ይኖራችኃል!!

Join @tikvahethsport 👇

https://t.iss.one/joinchat/AAAAAFb8M0pNEZTiGM68rg

(ከ30,000 በላይ ቤተሰቦች ያሉበት ትክክለኛው)
.
.
"ቲክቫህ መፅሄት" በዋናው ቻናል ላይ በስፋት የማይዳሰሱ ገዳዮች የውጭ ሀገር መረጃዎች፣ የስልጠና ዕድሎች፣ የቴሌቪዥን፣ የሬድዮ ፕሮግራሞች ጥቆማ፣ ቱሪዝም፣ ባህል፣ ኪነ ጥበብ፣ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መረጃዎችን ማግኘት ትችላላችሁ።

(87,000 በላይ ቤተሰቦች ያሉበት ትክክለኛው)

Join @tikvahethmagazine👇

https://t.iss.one/joinchat/AAAAAEcez-UrldBjOpa-qQ

ውድ ቤተሰቦቻችን ማንኛውም አስተያየት ሀሳባችሁን በ @tikvahethiopiaBot መላክ ትችላላችሁ!!
🔖እናስተዋዉቅዎ!

1. የሚሸጥ መኪና እና ቤት አሎት???
የትም ሳይዞሩ ጸሐይ ሳይመታዎት የትም ሳይደቅሙ መሸጥ ይፈልጋሉ? አሁኑኑ ይደውሉ ያሉበት አንመጣለን።
2. የሚከራይ መኪና እና ቤት አሎት? ይንገሩን?
3. የሚሸጥ መኪና እና የመኪና ኪራይ አገልግሎት ይፈልጋሉ?
CALL US, WE WILL SEND PROFESSIONALS TO YOU TO TAKE PICTURES AND CHECK YOUR CAR CONDITION!
Email: [email protected]
Tel. 0919320032 Address:-Addis Ababa
Join👉 @obanicar @obanicar @obanicar

☀️መልካም ቀን ይሁንላችሁ! #ETHIOPIA☀️
#Fake አህመድ ተሾመን በሚመለከት በማህበራዊ ትስስር ገፆች እየተሰራጨ የሚገኘው መልዕክት #ሀሰተኛ ነው። ድምፃዊው በፌስቡክ ገፁ እንዳሳወቀው መልዕክቱ እሱ ያለው እንዳልሆነ ገልጿል።

"ውድ አድናቂዎቼ እንዲ አይነት መልዕክት በፍፁም አላስተላለፍኩም ይህ የኔ ፖስት አይደለም እኔ ፖስት ያደረኩኝ አስመስለው ፖስት አርገው ነው።" አህመድ ተሾመ

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#FakeNews "የምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስ ብጹዕ አቡነ ጎርጎርዮስ የግድያ ሙከራ ተደረገባቸው" ተብሎ በፌስቡክ የተሠራጨው ወሬ ሀሰት ነው።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሦስቱ የዓባይ ተፋሰስ አገራት በዋሽንግተን ሊገናኙ ነው!

የላይኛው የዓባይ ተፋሰስ አገራት የሚባሉት ኢትዮጵያ፣ሱዳን እና ግብጽ ድርድር አዘል ውይይቶችን ለማድረግ በኅዳር 26/2012 በአሜሪካ ዋሽንግተን እንደሚገናኙ የግብጽ የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር አስታውቋል።

ኢትዮጵያ በዓባይ ወንዝ ላይ የምትገነባው የኃይል ማመንጫ ግድብ በግብጽ በኩል ከፍተኛ የሆነ የውሃ መቀነስ ያጋጥማል የሚል ቅሬታ ሲቀርብበት ነበር። ከዚህም ጋር ተያይዞ ግብጽ ከዓባይ እስከ ዘጠና በመቶ የውሃ ፍጆታ እንደምትጠቀም አስታውቃለች። በመጪው ኅዳር ወር በአሜሪካ የሚካሔደው ድርድር በቅርቡ ግብጽ ሦስተኛ የአደራዳሪ አካል መግባት እንዳለበት ያቀረበችውን ሃሳብ ኢትዮጵያ መቀበሏን ተከትሎ እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል።

በተባበሩት መንግሥታት ጠቅላላ ጉባኤ ላይ የግብጹ ፕሬዘዳንት አብዱል ፈታህ አልሲሲ የአሜሪካ አቻቸውን በዓባይ ጉዳይ ላይ ጣልቃ እንዲገቡ የጠየቁ ሲሆን ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕም የቀረበውን ጥሪ በመቀበል በጉዳዩ ላይ እንዲያደራድሩ ሲናተር ስቴቨን ሙነቺንን መድበዋል።

ምንጭ፦ አዲስ ማለዳ ጋዜጣ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
"መንግሥት ለሥራ አጥ ወጣቶች ያቀረበው ተዘዋዋሪ ፈንድ ብድር አቅርቦት ዘግይቶብናል"፦ ወጣቶች

በአዲስ አበባ ከተማ ያለውን የሥራ አጥ ቁጥር ለመቀነስ እና የወጣቶችን ሕይወት ለመቀየር በተለያዩ ሥራዎች መሰማራት ለሚፈልጉ ወጣቶች መንግሥት 2 ቢሊዮን ብር ተዘዋዋሪ ፈንድ መድቦ እንቅስቃሴ እያደረገ ይገኛል።

በፕሮግራሙ ሴቶች እና አካል ጉዳተኞች ያለምንም የዕድሜ ገደብ መሳተፍ ሲችሉ፤ ዕድሜያቸው ከ18 እስከ 34 የሚገኙ ወንድ ወጣቶችም በዕድሉ ተጠቃሚ እንዲሆኑ መንግሥት አቅጣጫ አስቀምጧል።

በአዲስ ብድር እና ቁጠባ ተቋም የገበያ እና ቢዝነስ ልማት ክፍል ኃላፊ የሆኑት አቶ መስፍን ፊጡማ በተለይ ለኢቢሲ እንደገለጹት በአሁኑ ሰዓትም 21 ሺህ አባላት ያሏቸው 7 ሺህ ኢንተርፕራይዞች ተጠቃሚ ሆነዋል።

ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/ETH-10-30

ምንጭ፦ etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#NewsAlert

አሜሪካ የአል ባግዳዲን ተተኪ መግደሏን አስታወቀች!

የአይ ኤስ አይ ኤስ ቡድን መሪ የነበረውን አቡበከር አል ባግዳዲን ይተካል ተብሎ በቁጥር አንድ የተያዘውን ሰው የአሜሪካ ወታደሮች እንደገደሉ ፕሬዚዳንት ትራምፕ አስታወቁ፡፡ ፕሬዚዳንቱ በትዊተር ገጻቸው እንዳስታወቁት ግለሰቡን ወታደሮቹ መግደላቸው ተረጋግጧል፤ ይህን እንጂ የግለሰቡን ማንነት፣ የት እና መቼ እንደተገደለ የገለፁት ነገር የለም፡፡ የአይ ኤስ አይ ኤስ የሽብር ቡድን ዋና መሪ አቡ በከር አል ባግዳዲ ከቀናት በፊት በአሜሪካ ወታሮች መገደሉ የሚታወስ ነው፡፡

ምንጭ፦ EPA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከፍተኛ የስራ ሀላፊ ከሀገር መኮብልለዋል!

ለ11 ዓመታት ያህል በኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣን የመገናኛ ብዙሃን ፈቃድና ምዝገባ ዳይሮክተሬት  ዳይሬክተር የነበሩት  አቶ ሙሉጌታ ሲሳይ መንገሻ  ካናዳ ቶሮንቶ ጥገኝነት መጠየቃቸው ተሰምቷል።

በባለስልጣ መስሪያ ቤቱ የመገናኛ ብዙሃን ፈቃድና ምዝገባ ስራ ላይ ለመሰማራት ለሚፈልጉ ወገኖች ፈቃድ የሚሰጠው እሳቸው የሚመሩት ዳይሮክተሬት እንደሆነ የሚናገሩት ዳይሬክተሩ በተለይ የመንግስት ባለስልጣት ተፅእኖ ይደረግ እንደነበር ገልጠው በተለይም ለፖለቲካው ቅርበት ላላቸው ወገኖች ከህጉ ውጭ ፈቃድ እንዲሰጣቸው ግፊት ይደረግ እንደነበር ባለፈው ሳምንት በካናዳ ቶሮንቶ እየተዘጋጀ በ143 ሀገራት በኢንተርኔት በሚደመጠው ከራዲዮ መገናኛ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልስ ገልፀዋል፡፡

እንደ ዋልታ ያሉ ለመንግስትና ለገዢው ፖርቲ ቅርበት ያላቸው ሚዲያዎች ህጉ ከሚያዘው ውጭ በፍጥነት ፍቃድ እንዲሰጣቸው ግፊት ከመደረጉም በላይ ዋልታ ፈቃድ ሳይሰጠው የቴሌቪዥን ስርጭት መጀመሩን ተናግረዋል፡፡

ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በህግ ከተሰጠው ሃላፊነት አልፎ በህትመት ስራዎች የይዘት ቁጥጥር ውስጥ ይገባ እንደነበር የጠቀሱት አቶ ሙሉጌታ መንግስትን ይተቻሉ ተብለው በተፈረጁ የህትመት ውጠቶች ላይ የህትመት ትንተና እየሰራ ለመንግስት ያቀርብ እንደነበር ተናግረዋል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/ETH-10-30-2

ምንጭ፦ ቁምነገር መፅሄት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#BADALE

በቡኖ በደሌ ዞን በደሌ ወረዳ አንድ ተማሪ ወንዝ ውስጥ ገብቶ ለመዋኘት ሲሞክር በውሃው ተወስዶ ህይወቱ ማለፉን ፖሊስ አስታወቀ። የወረዳው ፖሊስ አዛዥ ሳጅን አሳቤ እያሱ እንዳሉት  ተማሪው ህይወቱ ያለፈውም ጥቅምት 15 ቀን 2012ዓ.ም ከመቱ ዩኒቨርሲቲ የበደሌ ግብርናና ደን ሳይንስ ኮሌጅ በቅርብ ርቀት በሚገኘው ዳበና ወንዝ ውስጥ ገብቶ ነው።

የኮሌጁ ተማሪ የነበረው ግለሰቡ  የልደት ቀኑን ለማክበር በሚል በዕለቱ ከጓደኞቹ ጋር የማስታወሻ ፎቶግራፍ ለመነሳት እና ለመዋኘት ወደ ወንዙ ሄዶ እንደነበር አዛዡ የዓይን እማኞችን ጠቅሰው ገልጸዋል።

“ተማሪው በዋና ላይ እንዳለ በወንዙ በመወሰዱ የአካባቢው ህብረተሰብ እና ፖሊስ ባካሄዱት ፍለጋ አስክሬኑ ከአራት ቀናት በኋላ ዛሬ ተገኝቶ ወደ በደሌ ሆስፒታል ተወስዷል” ብለዋል። አስክሬኑ  ለተጨማሪ ምርመራ ወደ ጳውሎስ ሆስፒታል እንደሚላክና ከተጣራም በኋላ  ወደ ቤተሰቦቹ እንደሚሸኝ ሳጅን አሳቤ አስታውቀዋል። አካባቢው ክረምት ከበጋ የሚፈሱ ትላልቅ ወንዞች የሚገኙበት በመሆኑ ተማሪዎች ለመዝናናት በሚል ወንዞች ውስጥ ደፍረው ባለመግባት ጥንቃቄ እንዲያደርጉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

Via ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በዋሽንግቶን ዲሲ ሰላማዊ ሰልፍ ተደርገ!

በኢትዮጵያ ሰሞኑን የነበረውን ግጭትና ጥቃት በማውገዝ ወንጀለኞች ለሕግ እንዲቀርቡ የሚጠይቅ ሰላማዊ ሰልፍ በዩናይትድ ስቴትስ መዲና ዋሽንግተን ዲሲ ተካሔደ፡፡ በኢትዮጵያ የሰኣት ስሌት ማክሰኞ አመሻሹን በተካሔደው ሰልፍ በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን በአገሪቱ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ፊት ለፊት ተገኝተው ጥያቄያቸውን አሰምተዋል፡፡

ሰልፈኞቹ የሰሞኑን የፀጥታ ችግር የቀሰቀሱም ይሁን በቀጥታ ተሳትፈው ሰው የገደሉ፣ ያቆሰሉ፣ ንብረት ያወደሙና ያፈናቀሉ አካላት ለሕግ እንዲቀርቡ ጥሪ ሲያቀርቡ ተደምጠዋል፡፡ ይህ እስኪሆንም ጥያቄያቸውን እንደሚቀጥሉ ጠቁመዋል፡፡ በበርካቶች መስዋዕትነት በተገነባች አገር የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ለመጠፋፋት ሳይሆን ለበጎ ነገር እንዲተባበሩ፤ ተደማጭነት ያላቸው ሰዎችም ተከታዮቻቸውን ለበጎ ነገር እንዲያነሳሱ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ምንጭ፦ #AhaduTv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#BULE_HORA_UNIVERSITY

የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ በገዳ ስርዓት ላይ ትምህርት መስጠት ጀመረ፡፡ ትምህርቱ የገዳ ስርዓትን መልካም እሴቶች በማስተማር በተቋሙ ሰላማዊ የመማር ማስተማር ሂደትን በዘላቂነት ለማረጋገጥ ተስፋ እንደተጣለበትም ተመልክቷል፡፡

የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዶክተር ጫላ ዋታ ለኢዜአ እንደገለጹት ባለፉት ጊዜያት በተቋሙ ሰላማዊ የመማር ማስተማር ሂደትን ለማረጋገጥ ዘርፈ ብዙ ጥረቶች ቢደረጉም የተፈለገውን ያህል ውጤት አልተገኘም፡፡

ዩኒቨርሲቲው በአዲሱ ፍኖተ ካርታ የገዳ ስርአትን ጨምሮ የተለያዩ ትምህርቶችን መስጠት መጀመሩን አስታውቀዋል፡፡ የገዳ ስርአት በትምህርት መልክ መሰጠቱ ስርዓቱን ከማበልጸግና ከማስተዋወቅ ጎን ለጎን በስርዓቱ ውስጥ ያሉትን መልካም እሴቶች በማስተማር በዩኒቨርሲቲው ሰላማዊ የመማር ማስተማር ሂደት በዘላቂነት ለማስቻል ተስፋ መጣሉን ተናግረዋል፡፡

የትምህርቱ መጀመር መንግስት በተያዘው ዓመት ከፍተኛ የትምህርት ተቋማትን ከጸጥታ ስጋት ነጻ ለማድረግ ለጀመራቸው ሥራዎች አጋዥ መሆኑንም ዶክተር ጫላ አስረድተዋል፡፡

ምንጭ፦ ኢ.ዜ.አ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሮቤና ዲንሾ ከተሞች መረጋጋት ጀምረዋል!

በባሌ ሮቤና ዲንሾ ከተሞች ከሰሞኑ ተከስቶ የነበረውን ሁከት መቆጣጠርና ከተሞቹም መረጋጋት መጀመራቸውን የባሌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ገለጹ።

ዋና አስተዳዳሪው አቶ አደም ኢድሪስ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ ባሳለፍነው ሳምንት በዞኑ ባሉ 20 ወረዳዎች የተቃውሞ ሰልፎች መካሄዳቸውን ዋና አስተዳዳሪው አስታውሰው፤ በሰልፉ የተሳተፉ የአካባቢው ነዋሪዎች ሃሳባቸውን በሰላማዊ መንገድ አስተላልፈው ሁሉም በሰላም ወደየቤታቸው የተመለሱ ሲሆን፤ በሮቤና ዲንሾ በተባሉ ወረዳዎች ላይ ችግር መከሰቱን ተናግረዋል።

በዲንሾ ተከስቶ የነበረውን ግጭት የሐይማኖት አባቶችና የሀገር ሽማግሌዎች በባህላዊ መንገድ ለማብረድ መቻሉን፤ በሮቤ የነበረው ሁኔታ ጠንከር ያለ ስለነበር በዜጎች ህይወትና ንብረት ላይ ጉዳት መድረሱን ዋና አስተዳዳሪው ገልጸዋል።

ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/ETH-10-30-4

ምንጭ፦ ኢፕድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
"አንዳንድ ሚዲያዎች ግጭቱ በአጠቃላይ በባሌ እንደሆነ አስመስለው የሚያቀርቡት ዘገባ ስህተት ነው። በዞኑ ሃያ ወረዳዎች ያሉ ሲሆን ግጭት የተከስቶ የነበረው በሁለቱ ወረዳዎች ከዚያም አልፎ ደግሞ ሁኔታው ጠንከር ያለው በአንድ ከተማ ብቻ ነበር"- የባሌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አደም ኢድሪስ

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ETHIOPIA

በኢትዮጵያ በቀጣይ 10 ዓመታት ዉስጥ ከ10 ሚሊዮን በላይ ለሚሆኑ ወጣቶች የስራ እድል ያገኛሉ ተብሏል፡፡ የስራ እድል ፈጠራ ኮሚሽን ከማስተር ካርድ ፋዉንዴሽን ጋር በመተባበር ለ3 ሚሊዮን ወጣቶች የስራ እድል መፍጠር የሚያስችል ፕሮጀክት ይፋ አድርጓል፡፡

የስራ እድሎቹ የሚፈጠሩትም፣ በቱሪዝም፣ በግብርና፣ በአምራች ኢንዱስትሪና በአይ ሲቲ ዘርፎች መሆኑ ተገልጧል፡፡ የስራ እድል ፈጠራ ኮሚሽን ኮሚሽነር ዶር ኤፍሬም ተክሌ ኢትዮጵያ ልትበለጽግ የምትችለዉ፣ሁላችንም በየግላችን የአቅማችንን ስንሰራ ነዉ ብለዋል፡፡

ከተቋቋመ አንድ አመት የሆነዉ የስራ እድል ፈጠራ ኮሚሽን በተለይም ባለፋት 6 ወራት ጀምሮ የተሻለ እንቅስቃሴ እያደረገ እንደሚገኝና በዚህ ዓመትም ለ 3 ሚሊዮን ወጣቶች የስራ እድል ለመፍጠር እየሰራ እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡

Via Ethio FM 107.8
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከተማ አጀንዳ አጋሮች ትብብር መድረክ ምስረታ እየተካሄደ ነው!

በከተሞች ሁለንተናዊ ዕድገት ላይ የሚሰሩ የልማት አጋሮችን የሚያስተሳስረውና የከተሞችን ልማት ለማፋጠን በሚደረገው ጥረት ተባብሮ ለመስራት ከፍተኛ ሚና ሚና እንደሚኖረው የታመነበት የከተማ አጀንዳ አጋሮች መድረክ ምስረታ በኢንተር ኮንቲኔንታል ሆቴል እየተካሄደ ነው።

በከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴርና በUN HABITAT ትብብር የተመሰረተው የትብብር መድረኩ በከተሞች አጀንዳ ላይ የሚሰሩ መንግስታዊ ተቋማትን፣ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችን፣ ዓለም አቀፍ የልማት አጋሮችንና ሌሎች ባለድርሻ አካላትን የሚያስተሳስር እንደሆነ በምስረታው ላይ ይፋ ተደርጓል።

የምስረታውን መድረክ በንግግር የከፈቱት የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስትር ክብርት ኢንጂነር አይሻ መሀመድ የትብብር መድረኩ በከተሞች ለጋሽ እና የልማት አጋሮች ድጋፋቸውን በተቀናጀና በተናበበ መልኩ ለማከናወን ትልቅ ሚና እንዳለው ተናግረዋል።

በምስረታው ላይ ዓለም አቀፍ ፣መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ሀላፊዎችና ተወካዮች ፣ አምባሳደሮች ምሁራንና የማህበራት ተወካዮች እንዲሁም ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል።

Via Ministry of Urban Development and Construction
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከሩዋንዳ ካለፈ ታሪኳ ብቻ ሳይሆን ከቴክኖሎጂ አብዮቷም ብዙ የምንማረው አለን!

ሩዋንዳ የመጀመሪያውን የኤሌክትሪክ መኪና በኪጋሊ ማሽከርከር ጀምራለች፡፡ ይህ በአፍሪካ የመጀመሪያ የሆነው የቮልስዋገን ምርት ኢ-ጎልፍ የተሰኘች በኤሌክትሪክ የሚሰትራ መኪና የማስጀመሪያ መርሃ ግብሩ የቮልስዋገን እና የሳይመንስ ሙከራ ፕሮጀክት አንድ አካል መሆኑንም ሲ ጂ ቲ ኤን በዘገባው አስነብቧል።

በሩዋንዳ ለሚንቀሳቀሱት አራት ኢ-ጎልፍ ኤሌክትሪክ መኪኖች የሙከራ ኘሮጀክትም የመጀመሪያ ምዕራፍ የሆነ አንድ የኃይል መሙያ ጣቢያ መኖሩም ተጠቅሷል።

ወደፊት 16 የሚሆኑ ተጨማሪ መኪኖች ገበያውን የሚቀላቀሉ መሆናቸውን የሀገሪቱ ባለስልጣናት ጠቁመው፤ ለዚሁ ፕሮጀክት የሚሆኑ 15 የሃይል መሙያ ጣቢያ መሰረት ልማቶች በኪጋሊ እንደሚኖርም ተናግረዋል፡፡

መኪኖቹ የሚሸፍኑት ርቀት እንደ መሬቱ አቀማመጥና የጭነት መጠን የሚወሰን ቢሆንም ሃይል ሙሉ በሙሉ ከተሞላላቸው እስከ 230 ኪሎ ሜትር ርቀት የሚጓዙ መሆናቸውን ሲ ጂ ቲ ኤን በዘገባው አስፍሯል፡፡

https://telegra.ph/ETH-10-30-4

Via EBC
@tikvahethiopia @tikvahethmagazine