#BADALE
በቡኖ በደሌ ዞን በደሌ ወረዳ አንድ ተማሪ ወንዝ ውስጥ ገብቶ ለመዋኘት ሲሞክር በውሃው ተወስዶ ህይወቱ ማለፉን ፖሊስ አስታወቀ። የወረዳው ፖሊስ አዛዥ ሳጅን አሳቤ እያሱ እንዳሉት ተማሪው ህይወቱ ያለፈውም ጥቅምት 15 ቀን 2012ዓ.ም ከመቱ ዩኒቨርሲቲ የበደሌ ግብርናና ደን ሳይንስ ኮሌጅ በቅርብ ርቀት በሚገኘው ዳበና ወንዝ ውስጥ ገብቶ ነው።
የኮሌጁ ተማሪ የነበረው ግለሰቡ የልደት ቀኑን ለማክበር በሚል በዕለቱ ከጓደኞቹ ጋር የማስታወሻ ፎቶግራፍ ለመነሳት እና ለመዋኘት ወደ ወንዙ ሄዶ እንደነበር አዛዡ የዓይን እማኞችን ጠቅሰው ገልጸዋል።
“ተማሪው በዋና ላይ እንዳለ በወንዙ በመወሰዱ የአካባቢው ህብረተሰብ እና ፖሊስ ባካሄዱት ፍለጋ አስክሬኑ ከአራት ቀናት በኋላ ዛሬ ተገኝቶ ወደ በደሌ ሆስፒታል ተወስዷል” ብለዋል። አስክሬኑ ለተጨማሪ ምርመራ ወደ ጳውሎስ ሆስፒታል እንደሚላክና ከተጣራም በኋላ ወደ ቤተሰቦቹ እንደሚሸኝ ሳጅን አሳቤ አስታውቀዋል። አካባቢው ክረምት ከበጋ የሚፈሱ ትላልቅ ወንዞች የሚገኙበት በመሆኑ ተማሪዎች ለመዝናናት በሚል ወንዞች ውስጥ ደፍረው ባለመግባት ጥንቃቄ እንዲያደርጉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
Via ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia