#BULE_HORA_UNIVERSITY
የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ በገዳ ስርዓት ላይ ትምህርት መስጠት ጀመረ፡፡ ትምህርቱ የገዳ ስርዓትን መልካም እሴቶች በማስተማር በተቋሙ ሰላማዊ የመማር ማስተማር ሂደትን በዘላቂነት ለማረጋገጥ ተስፋ እንደተጣለበትም ተመልክቷል፡፡
የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዶክተር ጫላ ዋታ ለኢዜአ እንደገለጹት ባለፉት ጊዜያት በተቋሙ ሰላማዊ የመማር ማስተማር ሂደትን ለማረጋገጥ ዘርፈ ብዙ ጥረቶች ቢደረጉም የተፈለገውን ያህል ውጤት አልተገኘም፡፡
ዩኒቨርሲቲው በአዲሱ ፍኖተ ካርታ የገዳ ስርአትን ጨምሮ የተለያዩ ትምህርቶችን መስጠት መጀመሩን አስታውቀዋል፡፡ የገዳ ስርአት በትምህርት መልክ መሰጠቱ ስርዓቱን ከማበልጸግና ከማስተዋወቅ ጎን ለጎን በስርዓቱ ውስጥ ያሉትን መልካም እሴቶች በማስተማር በዩኒቨርሲቲው ሰላማዊ የመማር ማስተማር ሂደት በዘላቂነት ለማስቻል ተስፋ መጣሉን ተናግረዋል፡፡
የትምህርቱ መጀመር መንግስት በተያዘው ዓመት ከፍተኛ የትምህርት ተቋማትን ከጸጥታ ስጋት ነጻ ለማድረግ ለጀመራቸው ሥራዎች አጋዥ መሆኑንም ዶክተር ጫላ አስረድተዋል፡፡
ምንጭ፦ ኢ.ዜ.አ
@tsegabwolde @tikvahethiopia

This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የቤተሰብ ጭንቀት...
በምዕራብ ኦሮሚያ ካለፈው ቅዳሜ ጀምሮ ኢንተርኔት ጠፍቷል ፤ ስልክም አይሰራም። በዛ አካባቢ ቤተሰብ ያላቸው ዜጎች ሃሳብ ገብቷቸዋል። ቢቢሲ ካነጋገራቸው አስተያየት ሰጭዎች መካከል አንደኛው ይህን ብሏል፦
"ስልክ ስለተቋረጠ ቤተሰቦቻችንን ማግኘት አልቻልንም። ከፍተኛ የደህንነት ስጋት ውስጥ እንዳሉ ቀድመው ነግረውን ነበር። ይባስ ብሎ ባለፉት አምስት ቀናት ያሉበትን ሁኔታ መጠየቅ አለመቻችላችን አሳስቦናል። ይኑሩ ይሙቱ አለማወቃችን ከፍተኛ ስጋት ውስጥ ከቶናል። እኔ በበኩሌ ባለፉት 6 ቀናት በተለያየ መንገድ ቤተሰቦቼን ለማግኘት ሞክሬ አልቻልኩም።"
#BULE_HORA_UNIVERSITY
ከተማሪዎች መካከል ለቢቢሲ የተናገሩት፦
"ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ ወጥተን ነበር ግቢ ፖሊስ ቀጠቀጠን፤ 8 ሰው ነው በጥይት የተመታው አንድ ልጅ ሞቷል። ወለጋ ዞን ደምቢ ዶሎ ከተማ 07 ቀበሌ ልጅ ነው። ሰልፍ የወጣነው ወለጋ ላይ ያለው ሁኔታ ትክክል አይደለም፤ የቤተሰቦቻችን ድምፅ ከሰማን ወር ሊሞላን ነው፣ኢንተርኔት የለም፤ የባንክ ሲስተም የለም፤ሁሉም ነገር የለም እነሱ ላይ ያለውን ነገር እንዲቆምልን ብለን ነው ሰልፍ የወጣነው።"
የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ የኮሚኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ዳንኤል ሰይፉ ለቢቢሲ የተናገሩት፦
"ተማሪው እራሱ ሰላማዊ አካሄድ አልነበረውም ፤ ድንጋይ መወርወር መስታወቶችን ፣ የዶርሞችን የመማሪያ ላብራቶሪ ክፍል መስታወቶችን የማውደም ስራ ነበር። ተማሪው ላይ አልተተኮሰም። ከፍ ተደርጎ ሲተኮስ ነበር። እንደውም እኛ ይሄን ሁሉ ጥይት አልተኮስንም። ከውጭ በጀርባ የገባ ፣ ከተማሪው ጀርባ የገባና ተማሪው ውስጥ ሆኖ የሚተኩስ አካል እንዳለ ነው የፀጥታ ኃይሉ እየገለፀ ያለው"
#BBC
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia