TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
"ስብሰባ ለማድረግ ተቸግሬያለሁ" - ኢዜማ

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) ህዝባዊ ስብሰባዎችን ለማድረግ ስንቀሳቀስ ችግር እየገጠመኝ ነው አለ፡፡

ፓርቲው በየሳምንቱ ህዝባዊ ስብሰባዎች የሚያደርግ መሆኑን የገለጸ ሲሆን፤ ጥቅምት 9 ቀን 2012 ዓ.ም ከደጋፊውና አባላት ጋር ስብሰባ ለማድረግ ሲንቀሳቀስ በወጣቶች ረብሻ መፈጠሩን የፓርቲው ፀኃፊ አቶ አበበ አካሉ ገልፀዋል፡፡

ፓርቲው የደረሰበት የሠላም መታወክ መንግስት ፀጥታ አስከብራለሁ ብሎ ከሚሰረው ስራ ጋር የሚጻረር ነው ብለዋል አቶ አበበ፡፡

አሁን ያለንበት ወቅት የምርጫ ጊዜ እንደመሆኑ ፓርቲው በርካታ ቦታዎች ተንቀሳቅሶ የመስራት ሀሳብ አለው ያሉት ፀሀፊው፤ ሆኖም ግን በአዲስ አበባ ፓርቲው የገጠመው ግርግር መንግስትን የሚያስተች ነው ብለዋል፡፡

ፓርቲው ውጣ ውረዶች እየገጠሙት ቢሆንም በሰላማዊ ትግል ለመፍታት ጥረት እያደረገ መሆኑን ነው አቶ አበበ አክለው የገለጹት፡፡

Via #AhaduTV
@tsegabwolde @tikvahethiopia

#DIREDAWA

የድሬ ዳዋ ነዋሪዎች ጥያቄ!

በድሬ ዳዋ ስር ለሰደደው የሥራ እጥነት ችግር መፍትሔ ከመስጠት ይልቅ ለብሔራቸው ብቻ እየወገኑ ያሉ አመራሮች ተጠያቂ እንዲደረጉላቸው ነዋሪዎች ጠየቁ፡፡

የከተማዋ አስተዳደር ግጭት ለመፍጠር ከሌሎች አካባቢዎች ተደራጅተው የሚንቀሳቀሱና በተደጋጋሚ ወደ ድሬ ዳዋ ከተማ በመግባት ሽብር የሚፈጥሩ አጥፊዎች ላይ እርምጃ እንዲወስድም ነዋሪዎች አመልክተዋል፡፡

አስተዳደሩ ከነዋሪዎች ጋር ባደረገው ውይይት የከተማዋ ምክትል ከንቲባ አህመድ መሐመድ አጥፊዎችን ለሕግ በማቅረብ በኩል በቁርጠኝነት እንደሚሰራ ተናግረዋል፡፡

‹‹ድሬ ዳዋ በአገር አቀፍ ደረጃ አንደኛ የሥራ እጥ ከተማ የመሆኗ መንስኤ የስደተኞች በር መሆኗ ጭምር ነው፤ የሥራ እጥ ቁጥር 24.5 በመቶ ነው፤ ይህን በከፍተኛ ደረጃ መቀነስ ለሰላም ትልቅ ዋጋ አለው›› ሲሉ ምክትል ከንቲባው ተደምጠዋል፡፡ የውይይቱ የተሳተፊዎች መንግሥት ከቃል ባለፈ የሕዝቡን የመኖር መብት፣ ከስጋትና ከፍርሃት ነፃ የማድረግ ኃላፊነቱን በፍጥነት እንዲወጣ ጠይቀዋል፡፡

ምንጭ፦ #AhaduTv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የኃይማኖት መሪዎች የሰላም ጥሪ!

የፌደራልና የክልል መንግሥታት የብዙኃኑ ፍላጎት ሰላም መሆኑን ተረድተው ለዘላቂ ሰላምና ብሔራዊ መግባባት እንዲሰሩ የኃይማኖት መሪዎች ተማፀኑ፡፡

የኢትዮጵያ የኃይማኖት ተቋማት ጉባኤ በሰጠው መግለጫ የተገኙ የእምነት መሪዎች ሰሞነኛውን ግጭትና ጥቃት በምሬት በማውገዝ ወንጀለኞች ለፍርድ እንዲቀርቡ ጠይቀዋል፡፡

እንባ እየተናነቃቸው መግለጫ ሲሰጡ የተስተዋሉት አባቶች በኢትዮጵያ ሰው በአደባባይ ሲገደልና ሲታረድ እንደማየት ቀውስ የለም ብለዋል፡፡

በክልሎች መንግስታት መካከል የሚታየው ውጥረት የፖለቲካ ኃይሎች የሚፈጥሩት አጀንዳ መሆኑን ኣባቶቹ አስምረውበታል፡፡ በመሆኑም በመጀመሪያ ደረጃ የመንግሥት አካላት እርስ በርሳቸው እርቅ እንዲፈፅሙም በአጽንኦት ጠይቀዋል፡፡

የፌደራልና የክልል የጸጥታ አካላት የኢትዮጵያን ሰላም ሁሌም ነቅተው እንዲጠብቁና ተገቢ ያልሆኑ አዝማሚያዎችን ቀድመው በመገንዘብ እንዲከላከሉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ሰሞኑን የተከሰተው ግጭት ኃይማኖታዊ ገፅታ እንዲላበስ እየተደረገ ያለው በሌሎች ኃይሎች እንጅ ፍፁም ሃይማኖታዊ መሠረት እንደሌለው እንገልፃለን ሲሉም አሳስበዋል፡፡

Via #AHADUTV
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በዋሽንግቶን ዲሲ ሰላማዊ ሰልፍ ተደርገ!

በኢትዮጵያ ሰሞኑን የነበረውን ግጭትና ጥቃት በማውገዝ ወንጀለኞች ለሕግ እንዲቀርቡ የሚጠይቅ ሰላማዊ ሰልፍ በዩናይትድ ስቴትስ መዲና ዋሽንግተን ዲሲ ተካሔደ፡፡ በኢትዮጵያ የሰኣት ስሌት ማክሰኞ አመሻሹን በተካሔደው ሰልፍ በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን በአገሪቱ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ፊት ለፊት ተገኝተው ጥያቄያቸውን አሰምተዋል፡፡

ሰልፈኞቹ የሰሞኑን የፀጥታ ችግር የቀሰቀሱም ይሁን በቀጥታ ተሳትፈው ሰው የገደሉ፣ ያቆሰሉ፣ ንብረት ያወደሙና ያፈናቀሉ አካላት ለሕግ እንዲቀርቡ ጥሪ ሲያቀርቡ ተደምጠዋል፡፡ ይህ እስኪሆንም ጥያቄያቸውን እንደሚቀጥሉ ጠቁመዋል፡፡ በበርካቶች መስዋዕትነት በተገነባች አገር የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ለመጠፋፋት ሳይሆን ለበጎ ነገር እንዲተባበሩ፤ ተደማጭነት ያላቸው ሰዎችም ተከታዮቻቸውን ለበጎ ነገር እንዲያነሳሱ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ምንጭ፦ #AhaduTv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#US

ዩናይትድ ስቴትስ ኢትዮጵያ፣ግብፅና ሱዳን በኅዳሴው ግድበ ላይ የሚያደርጉትን ውይይት እንደምትደግፍ ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕ ለግብፁ አቻቸው ተናገሩ፡፡ ሁለቱ መሪዎች ሰኞ በስልክ ተነጋግረዋል ያለው ነጩ ቤተ መንግሥት ግብፅም ወደ ውይይት እንድትመለስ ትራምፕ ለፕሬዘዳንት አብደል ፋታህ አል ሲሲ መምከራቸውን አክሏል፡፡

አል ሲሲ ትራምፕን ባመሰገኑት የማኅበራዊ ትስስር ገጽ መልዕክታቸው ትራምፕ ሦስቱ አገራት እንዲወያዩና መፍትሔ ላይ እንዲደርሱ ለሳዩት የተለየ አቋም ሊደነቁ ይገባል ሲሉ የዋሽንግተን አቻቸውን አሞካሽተዋል፡፡

የሦስትኛ ወገን አደራዳሪን ስትማፀን የከረመችው ካይሮ ከአዲስ አበባና ካርቱም በኩል ይሁንታን ማግኘቷን ተከትሎ ላደራድራችሁ ወዳለችው ዋሽንግተን ሰኞ የውጭ ጉዳይ ሚንስትሯን መላኳ ይታወሳል፡፡ ለድርድር ሳይሆን ለውይይት ብቻ ነው የምገኘው ያለችው ኢትዮጵያም ለጥቅምት 26ቱ ውይይት የውጭ ጉዳይ ሚንስትሯን ሰኞ አመሻሹን ልካለች፡፡

ምንጭ፦ #AhaduTV
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የፕሬዘዳንት ማሃሙድ አባስ ምስጋና...

የሀገረ ፍልስጤም ፕሬዚደንት ማህሙድ አባስ የአፍሪካ መንግስታት ለፍልስጤም ትግል ለሚያደርጉት ድጋፍ ምሥጋናቸውን ልከዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ለቀጣናው ሰላምና መረጋጋት የተጫወቱትን ሚናም አድንቀዋል።

#AHADUTV
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot