TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ፎቶ📸በአዲስ አበባ ደረጃ የሻደይ አሸንድዬ እና ሶለል በዓል ማጠቃለያ በሚሊኒየም አዳራሽ በድምቀት እየተከበረ ነው፡፡ በበዓሉ ላይ ኢ/ር ታከለ ኡማ እና የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ተመስገን ጥሩነህ እንዲሁም ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሀላፊዎችን ጨምሮ በርካታ የህብረተሰብ ክፍል ተሳታፊ ሆነዋል፡፡ በተመሳሳይ ሁኔታ የአሸንዳ በዓል በከፍተኛ ድምቀት በቀጣዩ ሳምንት በአዲስ አበባ ደረጃ የሚከበር ይሆናል፡፡

Via MayorOfficeAA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
እሁድ እንዴት እያለፈ ነው?

"እኛ የኮተቤ መሰረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ወጣቶች ትላንትና እንዲሁም ዛሬ እሁድን ደም በመለገስ እያሳለፍን እንገኛለን። እሮብ ደግሞ ወላጅ አልባ ህፃናትን ለመጎብኝት እቅድ ይዘናል።"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
እሁድ እንዴት እያለፈ ነው?

"እሁድን በጌርጌሲዮን የአእምሮ ህሙማን መርጃ ማህበር በማሳለፌ ደስታ ተሰምቶኛል። የማህበሩ መስራች አቶ መለስ እና ባልደረቦቻቸው እየሰሩ ስላሉት በጎ እና የተባረከ ስራ በእጅጉ ማመስገን እወዳለሁ። በአስቸጋሪ ሁኔታዎች ሆነው ያላቸውን ፅናት እያደነቅሁ ሁሉም ባለድርሻ አካላት በምትችሉት በሙሉ ከጎናቸው እንድትቆሙ አበረታታለሁ። የበጎ አድራጎት ስራ ላይ የተሳተፉ ወገኖቻችን ጋር መንግስት በጋራ ለመስራት የሚያስችሉ መንገዶች ላይ እየሰራንባቸው እንገኛለን።" ዶ/ር አሚር አማን/በፌስቡክ ገፃቸው ላይ ያሰፈሩት/

@tsegabwolde @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#MoH የጤና ሚኒስቴር የስራ አካባቢን ለሰራተኞች እና ለተገልጋዮች ምቹ ለማድረግ የስራ ክፍሎችን የማደስ እና የማስዋብ ተግባራትን አከናውኗል፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-SPORT መቐለ 70 እንደርታ እያደረገ የሚገኘውን ጨዋታ መረጃዎች ለማግኘት የስፖርት ገፃችንን ይጎብኙ👇
https://t.iss.one/joinchat/AAAAAFb8M0pNEZTiGM68rg
ፎቶ📸በአዲስ አበባ ደረጃ የሻደይ አሸንድዬ እና ሶለል በዓል ማጠቃለያ በሚሊኒየም አዳራሽ!

@tsegabwolde @tikvahethiopia
"ኢትዮጵያውያን በመደመር እሴቶች ላይ በማተኮር ሀገራቸውን ሊረዱ ይገባል"-ዶ/ር ዐቢይ አህመድ
.
.
በደቡብ ኮሪያ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን በመደመር እሴቶች ላይ በማተኮር ሀገራቸውን መርዳት እንደሚገባቸው ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ አሳሰቡ፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከኢትዮጵያዊያኑ ጋር በሀገራዊ ጉዳይ ላይ ውይይት አድርገዋል፡፡ በሀገራዊ ጉዳይ ላይ ከኢትዮጵያዊያኑ ለተነሳላቸው ጥያቄም ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለኢትዮጵያዊያኑ በመደመር እሴቶች ላይ በማተኮር ባሉበት ሆነው ሀገራቸውን እንዲረዱ አበረታትተዋል::
በኢትዮጵያ ኤምባሲም የእራት ግብዣ ተደርጎላቸዋል፡፡

ምንጭ፡-የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#SayNoToRacism

"My ancestors and my parents suffered for my generation to be free today, to work, to take the bus, to play football. #Racist insults are ignorance and can only make me #stronger and #motivate me to fight for the next generation." Paul Pogba/ON RACIST ABUSE/

@tsegabwolde @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#uodate በክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ላይ የተሰማሩ ወጣቶች ለንባብ አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ መጽሐፍትን በማሰባሰብ ለአማኑኤል የአእምሮ እስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ለገሱ፡፡ ወጣቶቹ ከአዲስ አበባ የወጣቶችና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ቢሮ ጋር በመተባበር በሆስፒታሉ ኑ! መደርደሪያዉን እንሙላ በሚል መሪቃል መጽሐፍ የማሰባሰብ ፕሮግራም አከናውነዋል፡፡

Via #AMN
@tsegabwolde @tikvahethiopia
እኛም በስልካችን እሁድን በመልካም ስራ!

"አንድ ብር ለአንድ ልብ" 6710

በትንሹ 3 መልዕክት ይላኩ!

ወደዚህ ግሩብ ግቡና እየሆነ ያለውን ተመልከቱ፤ ሀገር አለን የምንለው ለዚህ ነው። ሁሌም ለበጎ ስራ አብረን ስለቆምን!!

Screenshot ወደዚህ ግሩፕ👇

https://t.iss.one/joinchat/FCD9AhWFZJX_rX95-4rWNQ
#update ወጣቶች አንድነታቸውን እና ጥንካሬያቸውን ለሀገር አንድነት፣ግንባታ እና ለሰው ልጆች መብት መከበር እንዲያውሉት የአዴፓ ምክትል ሊቀመንበር አቶ ዮሐንስ ቧያለው ጥሪ አቀረቡ፡፡ የሻደይ፣ አሸንድዬ እና ሶለል የማጠቃለያ ዝግጅት በአዲስ አበባ ሚሊኒዬም አደራሽ ተከብሯል፡፡

በማጠቃላይ ዝግጅቱ የተገኙት የአማራ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (አዴፓ) ምክትል ሊቀመንበር አቶ ዩሐንስ ቧያለው በእንኳን አደረሳችሁ መልዕክታቸው ‹‹ውበታችሁን፣ አንድነታችሁን እና ጥንካሬያችሁን ለሀገር አንድነት፣ ግንባታ እና ለሰው ልጆች መከበር ተጠቀሙበት›› ሲሉ ጥሪ አስተላልፈዋል፡፡

በበዓሉ ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ዑማ በበኩላቸው የሻደይ፣ አሸንድዬ እና ሶለል በዓል በዓለም የማይዳሰስ የቅርስ መዝገብ ውስጥ እንዲሰፈር የበኩላቸውን ድርሻ እንደሚወጡ ተናግረዋል፡፡ በበዓሉ ለታደሙት የኅበረተሰብ ክፍሎችም የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

Via #AMMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
እሁድ እንዴት እያለፈ ነው?

እኛ የአምቦ ወጣቶች ዛሬ!


Gammachuu haadholii keenya sanbataa

በፎቶው ላይ የምትመለከቷቸው እናቶቻችን ጎረቤታሞችና በአንድ ቀን በተመሳሳይ ሁኔታ ልጆቻቸውን በግፍ የተነጠቁ/የተገደሉባቸው እናቶች ናቸው። ምንም እንኳን ልጆቻቸውን በሞት ቢነጠቁም በልጆቻችው በአምቦ ወጣቶች እገዛ የቤት እድሳት ተደርጎላቸዋል። ወጣቶቹ ለዚህ ስራ ድጋፍ እገዛ ላደረጉላቸው ወንድሞቻቸው በአጠቃላይ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

Galannii haadholii keenyaa isiin haa qaqqabuu

#አሸብር_መገርሳ

@tsegabwolde @tikvahethiopia
285 ባለሀብቶች እንደተሰወሩ ተሰማ!

በጋምቤላ ክልል ለግብርና ኢንቨስትመንት መሬት የወሰዱ ባለሃብቶች ፈጥነው ወደ ሥራ እንዲገቡ የክልሉ መንግሥት ጥሪ አቀረበ። በክልሉ በግብርና ኢንቨስትመንት ለመሰማራት መሬት የተረከቡ 285 ባለሃብቶች ከአካባቢው እንደተሰወሩ ተገልጿል።

የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኡሞድ ኡጁሉ ሰሞኑን በአበቦ ወረዳ የባለሃብቶችን እርሻ በጎበኙበት ወቅት እንዳሳሰቡት ለኢንቨስትመንት የክልሉ መንግሥት ኢንቨስትመንት ለአገር ልማት ያለውን ድርሻ በመገንዘብ መሬት የተሰጣቸው ባለሀብቶች ሥራ ፈጥነው መጀመር ይጠበቅባቸዋል።

በክልሉ በግብርና ኢንቨስትመንት ለመሰማራት ከገቡት ከ700 በላይ ባለሃብቶች መካከል 285ቱ መሬት ተረክበው መሰወራቸውን ተናግረዋል። የኢንቨስትመንቱ ዘርፍ ለአገር ልማትም ሆነ ለዜጎች ሥራ ለመፍጠር ዓይነተኛ መሣሪያ መሆኑን የገለጹት ርዕሰ መስተዳድሩ፣ የክልሉ መንግሥት የባለሃብቶች ችግሮች ለመፍታት ዝግጁ መሆኑን አስታውቀዋል። ለዚህም አልሚ ባለሃብቶች በመደገፍ ረገድ የክልሉ መንግሥትና በየደረጃው ያለው አመራር በትኩረት ይሰራል ብለዋል።

Via #ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ማስታወቂያ

አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ለ2012 ዓ.ም. በማታ መርሃግብር ለመጀመሪያ ዲግሪ ትምህርት አመልካቾችን ይጋብዛል። በዚህም መሰረት አመልካቾች የሚከተሉትን ማሟላት ይጠበቅባቸዋል፦

1. በዲግሪያችሁ ለምታመለክቱ 40 ብር በመክፈል የወጪ መጋራት ያጠናቀቃችሁበትን የሚገልፅ ደብዳቤ ከትምህርት ማስረጃ ማቅረብ፤

2. በዲፕሎማችሁ ለምታመለክቱ150 ብር በመክፈል ከትምህርት ማስረጃ ጋር የCOC ደረጃ 3 ወይም 4 ማቅረብ

3. ዲፕሎማችሁ የአስተማሪነት ሆኖ ለምታመለክቱ 150 ብር በመክፈል ዲፕሎማ በጨረሳችሁበት የትምህርት አይነት ብቻ በመመዝገብ የትምህርት ማስረጃ ማቅረብ

4. ለPreparatory አመልካቾች ከ2004-2011ዓ.ም. ድረስ ብቻ ትምህርት ሚኒስቴር ባወጣው መስፈርት መሰረት ለከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ነጥብን የምታሟሉ 40 ብር በመክፈል ከትምህርት ማስረጃ ጋር በማያያዝ ማቅረብ

5. ከተለያዩ ዩኒቨርስቲዎች በተለያየ ምክንያት አቋርጣችሁ ለምታመለክቱ የወጪ መጋራት ያጠናቀቃችሁበትን የሚገልፅ ደብዳቤ 40 ብር በመክፈል ከትምህርት ማስረጃ ጋር በማያያዝ ማቅረብ

6. ለያሬድ ሙዚቃ ትምህርት ቤት እና ለአለ ፈለግ ስእል ትምህርት ቤት በቀን መርሃ ግብር ማመልከት የሚችሉት በPreparatory ከ2004-2010 ዓ.ም. ተምረው የጨረሱና ትምህርት ሚኒስቴር ባወጣው መስፈርት መሰረት ለከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ነጥብን አምጥተው ለነበሩ የወጪ መጋራት ክፍያ ያጠናቀቁበትን ደብዳቤ ከትምህርት ማስረጃ ጋር ማያያዝ፡፡

የምዝገባ ቀን-ከነሐሴ 20 እስከ ጳጉሜ 1 2011 ዓ.ም
የምዝገባ ቦታ-በሬጅስትራር ህንፃ ቢሮ ቁጥር 203
የክፍያ ቦታ-ከሬጅስትራር ህንፃ ቢሮ ቁጥር 7 ወይም 8

ማሳሰቢያ፡-

1. አመልካቾች በዩኒቨርስቲው ድረ-ገጽ (portal.aau.edu.et ) ላይ ማመልከትና የመመዝገቢያ ቁጥሩን በመያዝ የትምህርት ማስረጃ አንድ ኮፒ ከአንድ ጉርድ ፎቶግራፍ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

2. በዲፕሎማ አመልካቾች የዩኒቨርስቲውን የመግቢያ ፈተና ጊዜን ፤ የትምህርት ክፍሎቹን ዝርዝር እና ተጨማሪ ማብራሪያ ከዩኒቨርስቲው ድረገጽ (www.aau.edu.et) እና (www.portal.aau.edu.et) ማግኘት የምትችሉ መሆኑን ያሳውቃል፡፡

#አአዩ_ሬጅስትራር

@tsegabwolde @tikvahethiopia
5ኛው አመት የTIKVAH-ETH የመፅሃፍት ማሰባሰብ ዘመቻ ከነገ ነሃሴ 20 እስከ መስከረም 30 በመላው ሀገሪቱ ይካሄዳል!!

ላለፉት አመታት በአብዛኛውን በከተሞች አካባቢ የሰራነውን ስራ #በማጠናከር ዘንድሮ ደግሞ ከከተማ ውጭ ወደሚገኙ የመጀመሪያና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ትኩረታችንን እናደርጋለን።

ምን አይነት መፅሃፍት ነው ከቤተሰባችን አባላት የምናሰባስበው?

•ከ1ኛ ክፍል ጀምሮ እስከ 12ኛ ክፍል ድረስ መደበኛ የመማሪያ መፅሃፍትን/Text Book/ እንዲሁም አጋዥ መፅሃፍት ብቻ

•በተለያዩ ቋንቋዎች የተዘጋጁ ትውልዱን ይጠቅማል፤ እውቀት ያስጨብጣል የምንላቸው መፅሃፍት።

•ትንሹ መስጠት የሚቻለው መፅሃፍ 1

•መፅሃፍቱ የሚገቡት ገጠራማ አካባቢ ለሚገኙ እና በአካል ሄደን ለምንለያቸው ቤተ መፅሃፍት

#እርሶ ምን ማድረግ ይችላሉ??

√ቢያንስ አንድ የመማሪያ መፅሃፍ ለሚወዷት ለኢትዮጵያ መለገስ ይችላሉ። እንዲሁም ከፍተኛ የመፅሃፍት ችግር ያሉባቸው ቦታዎችን በመለየት የማስተባበር ስራ ሊሰሩ ይችላሉ።

•TIKVAH-ETH በሀገሪቱ በየትኛውም አካባቢ ለምትገኙ የበጎ አድራጎት ማህበራት ይህን ሀገራዊ ስራ እንድታግዙ ጥሪውን ያቀርብላችኃል።

•የዘንድሮ ተፈታኝ ተማሪዎች ደግሞ ትልቁን ድርሻ በመውሰድ ከተማራቹባቸው እና ስትጠቀሟቸው ከነበሩት መፅሃፍ መካከል ቢያንስ አንዱን ለመጪው ትውልድ በስጦታ አበርክቱ።

•በStopHateSpeech ጉዞ ተሳታፊ የነበራችሁ የቤተሰባችን አባላት ይህን ለሀገርና ለትውልድ የሚሰራን ስራ በሙሉ አቅማችሁ እንድታግዙ ጥሪ እናቀርባለን።

•በውጭ ሀገር የምትገኙ የቤተሰባችን አባላት ጠቃሚ ናቸው የምትሏቸው መፅሃፍት በመላክ አልያም እዚህ ሀገር ባላችሁ ወዳጅና ዘመድ መፅሃፍት እንዲገዛ በማድረግ ይህን

#ኦሮሚያ
#አማራ
#ትግራይ
#ደቡብ
#ሱማሌ
#አፋር
#ሀረሪ
#ጋምቤላ
#ቤኒሻንጉል
#አ/አ ከተማ አስተዳደር
#ድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር

🏷በማኛውም አይነት ቋንቋ የተዘጋጀ የመማሪያ መፅሃፍ መለገስ ይቻላል!!
-------------------------------------------------------
በአሁን ሰዓት ልየታ ከተደረገባቸው አካባቢዎች መካከል፦

#ራያ_ቆቦ በራያ ቆቦና ዙሪያዋ የምትገኙ የቤተሰባችን አባላት መፅሃፍት ለመለገስ እና ይህን ስራ ለማስተባበር ከቤተሰባችን አባል #ሉላይ ጋር ይገናኙ፦ +251949256094

#ድሬዳዋ በድሬዳዋ ከተማ እና አካባቢው የምትገኙ ደግሞ ከቤተሰባችን አባል መሃሪ 0915034762/መሃሪ/ ጋር መገናኘት መፅሃፍ መለገስ ትችላላችሁ።

ሌሎች አካባቢዎች ላይ እኛም ለሀገራችን መስራት እንፈልጋለን የምትሉ እውቅና ያላችሁ ማህበራት ካላችሁ መልዕክት አስቀምጡልን @tsegabwolde 0919743630

5ኛው አመት የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት የመፅሃፍ ማሰባሰብ ዘመቻ!

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ጠ/ሚር ዐቢይ አሕመድና ልዑካቸው የኮርያ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ተቋምን ጎብኝተው የኮርያን ጠንካራ ኢኮኖሚ ለመገንባት ሳይንስና ቴክኖሎጂ በተጫወተው ሚና ዙሪያ ማብራሪያ ተደርጎላቸዋል።

ምንም እንኳን ተቋሙ በአሁን ወቅት ያለው የሥራ ግንኙነት ከሳይንስና ከፍተኛ ትምህርትና ከአዳማ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ ጋር ቢሆንም ጠ/ሚር ዐቢይ አሕመድ ይህንኑ መሳይ ተቋም በኢትዮጵያ ለማቋቋም በትብብር መስራት እንደሚፈልጉ ገልፀዋል።

ምንጭ:- የጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#uodate ጠ/ሚር ዐቢይ አሕመድ ከኮሪያው ኤግዚም ባንክ ፕሬዚዳንት ጋር ተገናኝተው ተወያይተዋል። ሁለቱ ወገኖች ለኢትዮጵያ ሲደረጉ በነበሩና በአዳዲስ ድጋፎች ዙሪያ መክረዋል።

በአሁኑ ወቅት በኤግዚም ባንክ ድጋፍ ከ600 ሚልዮን የአሜሪካ ዶላር በላይ የሚፈጁ ፕሮጀክቶች እየተከናወኑ ሲሆን ከዚህም በተጨማሪ 300 ሚሊዮን ዶላሩ በ2011-2012 በኮርያ ኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ልማት ትብብር ፈንድ ማእቀፍ ስር የተፈረመ ነው።

ምንጭ:- የጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ፎቶ📸ጠ/ሚር ዐቢይ አሕመድና ልዑካቸው በደቡብ ኮርያ ይፋዊ ጉብኝታቸ በኮርያ ጦርነት ወቅት ለወደቁ መታሰቢያ በሆነው በሴውል ብሄራዊ #የመቃብር ቦታ ጉንጉን አበባ አስቀምጠዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የወረዳ አስተዳዳሪው ላውንቸር እና ሌሎች ከባድ የጦር መሣሪዎችን በማዘዋወር ተጠረጠሩ!

•የአፋር ክልል ፖሊስ ተጠርጣሪውን ይዞ እንዲያቀርብ ትዕዛዝ ደርሶታል።


በአፋር ክልል ዳሊሳጊ ወረዳ አስተዳዳሪ የሆኑት መሐመድ የጊሊስ ላውንቸር እና ከባድ መትረየስን ጨምሮ ሌሎች 11 ዓይነት ከባድ እና ቀላል መሣሪያዎችን ሲያዘዋውሩ ተገኝተዋል በሚል ክስ ተመሰረተባቸው።

ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ በፌደራሉ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ችሎት በመሰረተው ክስ የወረዳ አስተዳዳሪው ከኹለተኛ ተከሳሽ ጋር በመሆን በመንግሥት መኪና የጦር መሣሪያዎቹን ሲያዘዋውሩ ተገኝተዋል ሲል አብራርቷል። በአፋር ክልል ባቲ ተብሎ በሚታወቀው ኬላ ላይ በቁጥጥር ሥር የዋሉት እና መኪናውን ሲያሽከረክሩ የነበሩት ጀማል ሁሴን ፍርድ ቤት የቀረቡ ሲሆን ፍርድ ቤቱም የዋስትና መብታቸውን ነፍጓቸዋል።

መሐመድ ጊሊስን ግን የክልሉ ፖሊስ ይዞ እንዲያቀርብ ቢታዘዝም ይዞ ለማቅረብ እንዳልቻለ ፖሊስ ለፍርድ ቤት ገለጿል። የክልሉ መንግሥትም የተያዙት ጦር መሣሪዎች የክልሉ ንብረት ከሆኑ እንዲያሳውቅ እንዲሁም የሚዘዋወሩትም ለሥራ ዓላማ ከሆነ እንዲገለጽ ከፍርድ ቤቱ ጥያቄ ቀርቧል።

እስካሁን በቁጥጥር ሥር ያልዋሉትን አንደኛ ተከሻሽን የፌደራል ፖሊስ ይዞ እንዲያቀርብ ችሎቱ ትዕዛዝ የሰጠ ሲሆን በተመሳሳይም የክልሉ ፖሊስም ተከሻሹን እንዲያቀርብ ፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ ሰጥቷል።

ፍርድ ቤቶች እስከ ጥቅምት መጀመሪያ በእረፍት ምክንያት በሥራ ላይ ያለመሆናቸውን ተከትሎም ለኅዳር አንድ ቀጠሮ የሰጠ ሲሆን በተመሳሳይ በዕለቱ ፍርድ ቤቱ ክስ እንደሚሰማ ይጠበቃል።

ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/ETH-08-26

Via አዲስ ማለዳ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በጎርፍ አደጋ ከ60 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል!

በሱዳን ከባድ ዝናብ ባስከተለው ጎርፍ ከ60 በላይ ሰዎች መሞታቸውን የሃገሪቱ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል፡፡ በሃገሪቱ ከሃምሌ ወር ጀምሮ እየጣለ ባለው ከባድ ዝናብ ምክንያት በ15 አካባቢዎች ከ2መቶ ሺህ በላይ ሰዎች ጉዳት እንደደረሰባቸው ተነግሯል፡፡

እንደ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሪፖርት ከ 37 ሺህ በላይ ቤቶች በጎርፉ ሳብያ ፈርሰዋል ወይም ጉዳት ደርሶባቸዋል፡፡ በሱዳን የዝናባማ ወቅት እስከ የፊታችን ጥቅምት ወር ድረስ የሚቆይ በመሆኑ ጎርፍ ከዚህ በላይ አደጋ እንዳያደርስ ተሰግቷል፡፡

Via #ቢቢሲ
@tsegabwolde @tikvahethiopia