TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#SayNoToRacism በየትኛውም የምድር ክፍል በሰው ልጅ ላይ የሚፈፀምን የዘረኝነት ጥቃት አጥብቀን እናወግዛለን!! የቆዳ ቀለማችን ቢለያይም ውስጣችን አንድ ነው። #PaulLabilePogba #TIKVAH_ETHIOPIA
#SayNoToRacism

"My ancestors and my parents suffered for my generation to be free today, to work, to take the bus, to play football. #Racist insults are ignorance and can only make me #stronger and #motivate me to fight for the next generation." Paul Pogba/ON RACIST ABUSE/

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#SayNoToRacism

ዉድ የቲኪቫህ ኢትዮጵያ ስፖርት ቤተሰቦች በዛሬው የቲኪቫህ ስፖርት አምዳችን አሳሳቢ እየሆነ በመጣው የዘረኝነት ጉዳይ ያዘጋጀንላችሁ ፅሁፍ አለ። በአንድ ወቅት ላይ የዚህ ድርጊት ሰላባ የነበረው የናፖሊ እና የሴኔጋል ብሐራዊ ቡድን የመሀል ተከላካይ ካሊዱ ኩሊባሊ ካሰፈረው ማስታወሻ ላይ የተናገረውን ባማረ አቀራረብ አመሻሹ ላይ ይዘንላችሁ እንቀርባለን።

ቲኪቫህ ኢትዮጵያ እና ቲኪቫህ ኢትዮጵያ ስፖርት ዘረኝነትን ያወግዛል።

#SayNoToRacism #TikvahEthiopiaAgainstRacism
#TikvahEthiopiaSportAgainstRacism
#WeAreAgainstRacism

Join TIKVAH-ETH SPORT👇
https://t.iss.one/joinchat/AAAAAFb8M0pNEZTiGM68rg

@tikvahethsport
@kidusyoftahe
@yidaaa
#SayNoToRacism

ሮሜሎ ሉካኩ ከትላንት ምሽት የዘረኝነት ጥቃት በኋላ ያስተላለፈው መልዕክት!

"ባሳለፍነው ወር በርካታ ተጫዋቾች የዘረኝነት ጥቃት ደርሶባቸዋል። እኔም በትላንትናው ዕለት የጥቃቱ ገፈጥ ቀማሽ ሆኛለው። እግር ኳስ ሁሉም የሰው ዘር በእኩል የሚዝናናበት ጨዋታ ነው አንዱን ከሌላው ማግለል የምንወደውን ጨዋታ ዝቅ ያደርገዋል።

በሁሉም ሀገራት የሚገኙ የእግርኳስ ፌዴሬሽኖች ለእንደዚህ አይነት ማግለል ጠንከር ያለ እርምጃ ይወስዳሉ ብዬ ተስፋ አደርጋለው። የማህበራዊ ትስስር አውታሮች (ኢንስታግራም ትዊተር ፌስቡክ እና ሌሎችም ) ከእግር ኳስ ክለቦች ጋር እጅ እና ጓንት ሆነው መስራት ይጠበቅባቸዋል ምክንያቱም አብዛኛው የሚለጠፉ መልእክቶች ስር ቀለምን መሰረት ያደረገ ጥቃት ስለማይጠፋ ነው።

ክቡራት እና ክቡራን አሁን 2019 ላይ ነው የምንገኘው በዚህ የሰለጠነ ወቅት ላይ ወደፊት መሄድ ሲገባን የኋልዮሽ ጉዞውን ተያይዘነዋል ስለዚህ እኛ ኳስ ተጫዋቾች ህብረታችንን አጠንክረን የምንወደውን እግር ኳስ ንፁህ ለማድረግ አንድ አቋም ላይ መድረስ አለብን" ሮሜሎ ሉካኩ ክለቡ ኢንተርሚላንን አሸናፊ ያደረግችዋን ግብ ካስቆጠረ በኋላ በ ካግላሪ ደጋፊዋች የዘረኝነት ጥቃት ከደረሰበት በኋላ ያስተላለፈው መልዕክት።

ቲኪቫህ ኢትዮጵያ እና ቲኪቫህ ኢትዮጵያ ስፖርት ዘረኝነትን ያወግዛል።

#SayNoToRacism #TikvahEthiopiaAgainstRacism
#TikvahEthiopiaSportAgainstRacism
#RomeluLukaku

@tikvahethsport @kidusyoftahe @yidaaa