TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
300 ሚሊዮን ብር ተሰረቀ!

ከንግድ ባንክ፣ከዳሽን፣ከኦሮሚያ ኢንተርናሽናል የደንበኞች የባንክ አካውንት 300 ሚልየን ብር በላይ በተጭበረበረ ቼክ ተሰረቀ። 23 ተጠርጣሪዎችን ፓሊስ አስሯል። አቀነባባሪው ከሀገር ወጥቷል።

Via Tesfaye Getenet/ካፒታል ጋዜጣ/
@tsegabwolde @tikvahethiopia
‹‹የእነ አቶ ልደቱን እንቅስቃሴ በሕግ እናስቆማለን›› - ዶ/ር ጫኔ ከበደ

ኢዴፓ ይገባናል የሚለው የእነ አቶ ልደቱ አያሌው የአመራር ቡድኑ፤ በቀጣይ የፓርቲውን ንብረቶች ለማስመለስ ኢዜማን በሕግ እንደሚከስ ያስታወቀ ሲሆን የቀድሞ አመራሮች በበኩላቸው፤ ‹‹የግለሰቦቹን›› እንቅስቃሴ በሕግ እናስቆማለን ብለዋል፡፡

በኢዴፓ ብሄራዊ ም/ቤት ላይ የተጣለው እገዳ በምርጫ ቦርድ ተነስቶልናል ያለው የአቶ ልደቱ አያሌው ቡድን፣ የእገዳውን መነሳት ተከትሎ፣ አስቸኳይ ስብሰባ አድርጎ ውሳኔ ማሳለፉን አስታውቋል፡፡ 

በቀድሞ የፓርቲው አመራሮች (ማለትም ኢዜማን በተቀላቀሉት) ዶ/ር ጫኔና ሌሎች አመራሮች ምትክ አቶ አዳነ ታደሰን ፕሬዚዳንት፣ ወ/ት ጽጌ ጥበቡን ምክትል ፕሬዚዳንት አድርጎ ብሄራዊ ም/ቤቱ መርጧል ያለው የእነ አቶ ልደቱ ቡድን፣ በጥቂት ወራት ውስጥም የፓርቲውን ጠቅላላ ጉባኤ ለመጥራት መወሰናቸውን አስታውቀዋል፡፡ 

ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/ETH-08-25-2
እሁድ እንዴት እያለፈ ነው? @tsegabwolde ላይ በየአካባቢያችሁ እየተሰሩ ያሉ መልካም ተግባራትን ማጋራት ትችላላችሁ።
የEBS ስፖርት አዘጋጁ ትንሳኤ መልካም ስራዎች👆

ወጣት ትንሳኤ ይባላል የስፓርት አሰልጣኝ ነው። ኢ.ቢ.ኤስ ቲቪ ማለዳ 12:30--1:30 በድጋሚ 02:00---03:00 ከሰኞ እስከ ሰኞ የሚታይ የቲቪ ፕሮግራም አለው።

ወጣት ትንሳኤ ከስፖርቱ በተጨማሪ የሚወዳትን ሀገርና ህዝቦቿን በመልካም ስራ ያገለግላል ይህን በጥቂቱ ልበላችሁ፦

•በየወሩ መንገድ ለሰው የሚባል "ከመኪና ነፃ ቀን" አለ በበጎ ፍቃድ #በነፃ ስፓርት ያሰራል።

•በተለያዩ መስቀል አደባባይ በሚዘጋጁ ፌስቲባሎች ላይ በነፃ ያገለግላል።

•ሜቆዶንያም በሳምንት አንድ ቀን እየሄደ አረጋዊያንን በነፃ በስፓርት ያዝናናቸዌ

ከሰሞኑን ደግሞ በራሱ ተነሳሽነት የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር አዘጋጅቶ ነበር፦

• ወጣቱ ስፖርተኛ ትንሳኤ ለTIKVAH-ETH ሲናገር፦ "ይህንን ችግኝ ለመትከል የተነሳውበት አላማ የጠቅላይ ሚኒስተራችንን ሐሳብ በመደገፍ ነው" ይላል! የተሰሩትንም ስራዎች እንዲህ ዘርዝሮ ነግሮናል።

1.የአከባቢውን ነዋሪዎችን የእምነት አባቶችን፤ የቀበሌ ሊቀመንበሮችን፣ የወንጂ ከንቲባን በማነጋገር ደብዳቤም በመላክ ጥሪ አደረገላቸው እነሱም ተስማምተው አብረውት ተከሉ።

2. ለእምነት ተቁአማት በሙሉ ችግኞችን በግቢያቸው በመትከል እንደሚንከባከቡት ቃል ገብተውለታል።

3. በወንጂ ሸዋ ስካር ፍብሪካ ድርጅቱን በፈለገው ቦታ አስቆፍሮ ወጣት ትንሳኤ ችግኞችን ገዝቶ በመረጡት ቦታ ተክለዋል።

4. ለግሪን ኤሪያ በታጠረ ቦታም ተተክሏል
ወንጂ ገፈርሳ ከንቲባው በተገኙበት ይህ የተከናወነው።

5. ከሀይስኩል ት/ቤትናኢሊመንተሪ ት/ቤት ተማሪዎች ጋር ችግኝ ተከላው ተከናውኗል።

ወጣት ትንሳኤ ይዞት የተነሳውት መሪ ቃል "አንድ ችግኝ መትከል ለመንደራችን፤ ለሐገራችን፤ ለአለምልችን" የሚል ነው።

ከችግኝ ተከላው በተጨማሪ...

ወላጆቻቸው ለሞቱባቸው ልጆች የድብተር እስክርቢቶ፣ እርሳስ በመግዛት አበርክቷል፤ ለወጣቶችም ካሶችን ሸልሟል።

በስራዎቹ ማን እንዳገዘውም ነግሮናል፦

•የበቆጂ ውሃ ባለቤት 500 ችግኞችን ገዝተው አብረው በመትከልም ተባብረውታል።

• አልባር አስመጪና ላኪ ድርጅት 500 ችግኞችን ገዝቶለታል

የሚገርመው ግን ...

ወጣት ትንሳኤ ሰለሞን 5000 ሺህ ችግኞችን ገዝቷል። የአንዱ ችግኝ ዋጋ ከ 50--80 ብር ደርሳል።

በመጨረሻም እንዲህ ብሏል፦

"በጎ ስራ በአንድ ቀን ተሰርቶ የሚያልቅ ነገር አይደለም። የሚቀጥል ስራ ገና ይጠብቀኛል።...ሌላው ብዙ ወጣቶች ውልግዜ ከመንግስት መጠበቅ የለብንም እኛም ባለን ነገር ማገዝ መነሳሳትን ለመፍጠር ነው። ተቀባይ ብቻ ሳንሆን ሰጪም መሆን እንዳለብን ለማመልከት ነው።"

እኛም በርታልን ብለናል!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ባህርዳር

የሻደይ፣ አሸንድዬና ሶለል በዓል በክልል ደረጃ ለ2ኛ ጊዜ በባህርዳር ከተማ እየተከበረ ነው። በበዓሉ ላይ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድ አቶ ተመስገን ጥሩነህ እና የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትርና ዶክተር ሂሩት ካሳውን ጨምሮ የተለያዩ የፌደራልና የክልል ባለስልጣናት ታድመዋል።

Via #FBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በቀጣይ ዓመት በዩኒቨርሲቲዎች የትምህርት አሰጣጥ ሰላማዊ በሚሆንበት መንገድ ላይ የሚመክር ጉባዔ በመቐለ እየተካሄደ ነው። ጉባዔውን የኢትዮጵያ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ኅብረት “የ2012 የትምህርት ዘመን ሰላማዊና ብሩህ እናደርጋለን!” በሚል መርህ ያዘጋጀው ነው።

Via #ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
እሁድ እንዴት እያለፈ ነው?

"እኛ የፖይለት ወጣቶች በጎ አድራጎት ማህበር ከቢሾፍቱ ወጣቶች ጋር በመተባበር በየአመቱ የምናዘጋጀው የደም ልገሳ ፕሮግራም ዘንድሮም ቀጥሎ ዛሬ እሁዳችንን #ደም_በመለገስ እና ሌሎችም እንዲለግሱ እያስተባበርን እንገኛለን።"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ልጆችን በጉዲፈቻ ለማሳደግ ፈልገው ወደ አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሴቶች እና ህፃናት ቢሮ የሚያቀኑ አሳዳጊዎች በሚያጋጥማቸው የመልካም አስተዳደር ችግር መጉላላት እየደረሰባቸው መሆኑን ገለፁ፡፡ ቢሮው በበኩሉ መጉላላቱ እንዳለ አምኖ የአሰራር ሥርዓቱን ለማዘመን እየሰራ መሆኑን አስታውቋል፡፡

Via #EPA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የቴፒ ነገር...

TIKVAH-ETHIOPIA ከቴፒ ከተማ ነዋሪ ቤተሰቦቹ መልዕክቶችን እያስተናገደ ነው። ከተማይቱ አይሁንም ቢሆን አስተማማኝ ደህንነት የላትም፤ መንግስት ኃይሉን አጠናክሮ ሰላምና ደህንነትን ማስጠበቅ አለበት ብለዋል። በተለይም የከተማው መግቢያና መውጫዎች ላይ ከፍተኛ ወንጀሎች እንድሚፈፁ ገልፀዋል።


"ከቴፒ ነው የምጽፍላቹ! N ነኝ ቴፒ ነዋሪ ነኚ ቴፒ ላይ ከአቅም በላይ የሆነ ነገር አለ። ህገወጥነት በዛ፣ የሠው ነብሥ እየጠፍ ነው። በቀላሉ ሠው እየተዘረፈ ነው። መናኸሪያ ከተዘጋ ዛሬ 6 ቀኑ ነው። እኔ የከባድ መኪና ሹፌር ነኝ ትላንትና ከቦንጋ ቴፒ እየተጓዝኩኝ ቴፒ መግቢያ ላይ እኔን ጨምሮ 2 ባጃጅ ሹፌር ጋር ተደብድበን ገንዘባችንን ሥልካችንን ተዘረፍን። የመኪና የባጃጅ መሥታዋት ሣይቀር ተሠባበረብን። የመንግሥት ያለ በሉልን! እባካቹ! መንግሥት ሀይሉን ጨምሮ ጫካ ውሥጥ የመሸጉትን ህገወጦች ይያዝልን።"

በስራ ጉዳይ ቴፒ ከተማ የማገኙ የTIKVAH-ETHIOPIA ቤተሰብ አባላት እንደነገሩን ላለፉት ቀናት በደህንነት ስጋት ከከተማው መውጣት እንዳልቻሉ ነግረውናል።

▫️የሚመለከታቸውን የመንግስት አካላት አነጋግረን የምናገኘው ምላሽ ካላ እናሳውቃችኃለን። #ETHIOPIA

@tsegabwolde @tikvahethiopia
"በዛሬው እለት 4ኛው ዙር የኢትዮጵያ ቡና ቤተሰብ ሩጫ ተካሂዷል። ከሩጫውም ጎን ለጎን ደብተርም ተለግሷል።"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የትብብር የትምህርት ፕሮግራም እንዳይሰጡ የታገዱት ዩኒቨርሲቲዎች ኦዲት እንዲደረጉ ተጠየቀ!

ከግል ተቋማት ጋር #በትብብር የሚሰጧቸውን የትምህርት ፕሮግራሞች እንዲያቋርጡ ማሳሰቢያ የተሰጣቸው የመንግሥት ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት፣ ኦዲት መደረግ እንዳለባቸው የከፍተኛ ትምህርት አግባብነትና ጥራት ኤጀንሲ አስታውቋል፡፡

ከግል ተቋማት ጋር በመተባበር ከዋና ካምፓሳቸው ውጪ በአዲስ አበባና በሌሎች አካባቢዎች ተማሪዎችን ተቀብለው ሲያስተምሩ የነበሩት ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ፣ ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ፣ ሐሮማያ ዩኒቨርሲቲና ጅማ ዩኒቨርሲቲ የአገርን ሀብት የሚያባክን አሠራር የሚከተሉ በመሆናቸው የግድ ኦዲት መደረግ እንዳለባቸው የገለጹት፣ የኤጀንሲው ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ታምራት ሞታ ናቸው፡፡

ኤቢኤች ከተባለ አማካሪ ተቋም ጋር በትብብር በአዲስ አበባ ተማሪዎችን ተቀብሎ የሚያስተምረውን የጅማ ዩኒቨርሲቲ አሠራር በምሳሌነት ያቀረቡት ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ፣ በኤቢኤች ካምፓስ የሚማሩ ተማሪዎች በተርም 75 ሺሕ ብር እንደሚከፍሉና ከዚህም ውስጥ 52 በመቶ የሚሆነው ለኤቢኤች፣ ቀሪው ደግሞ ለጅማ ዩኒቨርሲቲ ገቢ የሚደረግበት አሠራር መኖሩን ገልጸዋል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/ET-08-25-2
በአሜሪካ የሚደርስበትን ዘር ጥቃት በመሸሽ ኑሮውን አፍሪካ ያደረገው ግለሰብ!

በአሜሪካ የሚደርስበትን የዘር ጥቃት በመሸሽ ኑሮውን በአገረ ጋና መስርቶ እየኖረ መሆኑን ቢቢሲ አስነብቧል፡፡ ኦባዴል ካምቦን የተባለው ትውልደ አሜሪካዊው አሜሪካ እያለ መልኩ ጥቁር በመሆኑ በፖሊሶች ዘር ተኮር ጥቃት ሲደርስበት እንደቆየ ይናገራል፡፡

በተለይ በአሜሪካ ቆይታው የህይወቱን ወሳኝ ምዕራፍ የቀየረው በአውሮፓዊያኑ 2007 ተገቢ ያልሆነ ክስ ተመስርቶበት ፍርድ ቤት ከቀረበ በኋላ መሆኑን ኦባዴል ካምቦን አስታውሷል፡፡

ክሱም በግለሰቡ መኪና መቀመጫ ስር የተቀባበለ የጦር መሳሪያ መገኘቱና ይህም በተሸከርካሪው ላይ ሆኖ በሌሎች አካላት ላይ ተኩስ ለመክፈት የታሰበ እንደሆነ የሚል ነበር፡፡

ይሁን እንጂ ግለሰቡ ያልተቀባበለ ህጋዊ መሳሪያ የያዘ በመሆኑና በኋላ ላይ ጉዳዮ ሲጣራ ከቀረበበት ክስ ነፃ ሊወጣ መቻሉን ነው የተነገረው፡፡ በወቅቱ በቀረበበት ክስ ክፉኛ የተደናገጠው ግለሰቡ በአሜሪካ በስራ ያጠራቀመውን 30 ሺህ ዶላር ይዞ እትብቱ የተቀበረበት አገር ዳግም ላይመለስ ከቤተሰቡ ጋር አክራ ጋና ለመኖር ወሰነ፡፡

በአሁኑ ወቅትም በአገረ ጋና በአፍሪካ ጥናት ተቋም መምህር ሆኖ እያገለገለ ሲሆን ከባለቤቱና ከሶስት ልጆቹ ጋር በመሆን በአሜሪካ የተነፈገውን ነፃነት እያጣጣመ ስኬታማ ኑሮ እየኖረ መሆኑን ዘገባው ያትታል፡፡

Via #BBC/etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ፎቶ📸የኢትዮጵያ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ኅብረት “የ2012 የትምህርት ዘመን ሰላማዊና ብሩህ እናደርጋለን!” በሚል መርህ በመቐለ ያዘጋጀው መድረክ።

ፎቶ:#Leul
@tikvahethiopia @tikvahethiopia
ለሚመለከተው አካል...

"ወደ ጅማ መንገድ #ሳጃ መግቢያው ጋር ነዳጅ የያዘ ቦቴ #ተገልብጦ መንገድ ተዘግቶብናል የሚመለከተው አካል ቶሎ ችግሩን እንዲፈታልን መልዕክታችን ይድረስ፤ ወደ አዲስ አበባም ሆነ ወደ ጅማ የሚሄዱት መኪኖች ቆመዋል አከባቢው ደግሞ ለማምሸት እና ለማደር የማይመች ቦታ ነው።" ሄኖክ/TIKVAH-ETH/

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ደቡብ_ኮሪያ

ጠ/ሚር ዐቢይ አሕመድ በደቡብ ኮርያ የኢትዮጵያ ኤምባሲ በተዘጋጀ የእራት ግብዣ ከኢትዮጵያ ኮሚኒቲ አባላት ጋር ተገናኙ። ጠ/ሚር ዐቢይ አሕመድ የኮሚኒቲ አባላቱ በመደመር እሴቶች ላይ በማተኮር ባሉበት ሆነው ሀገራቸውን እንዲረዱ አበረታትተዋል።

ምንጭ፦ የጠቅላይ ሚ/ር ፅ/ቤት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ሄልዝ_ብሬክ|የኢፌዲሪ ጤና ሚኒስቴር ሰራተኞች የሻይ እረፍታቸውን “የጤና እረፍት” በማለት ወደ አካል ብቃት እንቅስቃሴ ቀይረዋል፡፡ የሚኒስቴሩ ሰራተኞች ከሰዓት በኋላ ያላቸውን የሻይ እረፍት “የጤና እረፍት” በማለት የአካል ብቃት እንቅስቃሴ በማድረግ ማሳለፍ ጀምረዋል።

የዓለም አቀፉ ጤና ድርጅት ባለፈው መስከረም ይፋ እንዳደረገው ዓለም ህዝብ 1 ነጥብ 4 ቢሊዮን ወይም ከአራት ስዎች አንዱ የጤናና አካል ብቃት እንቅስቀሴ አያደርግም።

ይህም በመሆኑ በርካቶች አላአስፈላጊ ውፍትርና የጤና ችግር እያጋለጣቸው መሆኑን አመልክቷል። በተለይም  እንደ ስኳር፣ ደም ግፊትና ሌሎች በተላላፊ ላልሆኑ ሽታዎች በብዛት የተጋለጡ መሆኑን   መረጃው ጠቁሟል።

Via #ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia