TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.4K photos
1.43K videos
206 files
3.95K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ስለ ትግራይ ህዝብ ከዶ/ር አብይ....

"ለኢትዮጵያ ህዝብ ከፍተኛ ጥሪ ማቅረብ ምፈልገው ስለ ትግራይ ህዝብ ነው። የትግራይ ህዝብ ዴሞክራሲ ይመጣል፤ ሰላም ይመጣል ብሎ ከማንም በላይ ልጆቹን ገብሯል። አሁን ዛሬ መልካም አስተዳደር ችግር ያለው ትግራይ ክልል ውስጥ ነው።

የትግራይ ክልል የተለየ ነገር ያገኘ የሚመስለን ዴሞክራሲ ያለው የሚመስለን፤ የተጠቀመ የሚመስለን በተለይ #ደቡብ#ኦሮሚያ#አማራ አካባቢ ያለን ሰዎች #እባካችሁን የትግራይ ህዝብ አሁንም ውሀ ለመጠጣት ይቸገራል። አሁንም ያገኘው አንዳች ትርፍ የለም።

በተሳሳተ መንግድ ጥቂት ሰዎች ተሳስተው ሲያሳስቱን ወለጋ ጫፍ ያለ የጋዝ ነጋዴ ጭምር በስመ ትግራይ መ ቅጣት ተገቢ አይደለም። ምንም የሚያውቀው ነገር የለም። ያገኘው ነገር የለም። ይሄን የምለውን ነገር የማያምን ሰው በፈለገው መንገድ ትግራይ ገጠር ሄዶ ማየት ይችላል። ምናገረው እውነት ነው። #ጥቂቶች በስሙ ነግደው ይሆናል እንጂ የትግራይ ህዝብ የተለየ ጥቅም ያገኘው ነገር የለም።

ጥቅም አላገኘው እምብዛም ጥቅም አይፈልግም። የተለየ እንዲደረግለት አይፈልግም።

የአብዬን ወደ እምዬ የሚባል ነገር አይሰራም። Mr X አጠፋ ብለን የማያውቁ ሰዎችን ጭምር በዛ ወንጀል ሀሳብ በቂም፣ በጥላቻ ማየት ለኢትዮጵያ አይበጅም። መለየት ያስፈልጋል።

ይሄ ጥቃት እየባዛ ከመጣ ዘር መጨረስ ያመጣል። ይሄ ደግሞ ወርደት ለልጆቻችን ያሸጋግራል።"

ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ አህመድ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀርበው ከተናገሩት የወሰድኩት።

ፍቅር ያሸንፋል!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ስለ ትግራይ ህዝብ ከዶ/ር አብይ....

"ለኢትዮጵያ ህዝብ ከፍተኛ ጥሪ ማቅረብ ምፈልገው ስለ ትግራይ ህዝብ ነው። የትግራይ ህዝብ ዴሞክራሲ ይመጣል፤ ሰላም ይመጣል ብሎ ከማንም በላይ ልጆቹን ገብሯል። አሁን ዛሬ መልካም አስተዳደር ችግር ያለው ትግራይ ክልል ውስጥ ነው።

የትግራይ ክልል የተለየ ነገር ያገኘ የሚመስለን ዴሞክራሲ ያለው የሚመስለን፤ የተጠቀመ የሚመስለን በተለይ #ደቡብ#ኦሮሚያ#አማራ አካባቢ ያለን ሰዎች #እባካችሁን የትግራይ ህዝብ አሁንም ውሀ ለመጠጣት ይቸገራል። አሁንም ያገኘው አንዳች ትርፍ የለም።

በተሳሳተ መንግድ ጥቂት ሰዎች ተሳስተው ሲያሳስቱን ወለጋ ጫፍ ያለ የጋዝ ነጋዴ ጭምር በስመ ትግራይ መ ቅጣት ተገቢ አይደለም። ምንም የሚያውቀው ነገር የለም። ያገኘው ነገር የለም። ይሄን የምለውን ነገር የማያምን ሰው በፈለገው መንገድ ትግራይ ገጠር ሄዶ ማየት ይችላል። ምናገረው እውነት ነው። #ጥቂቶች በስሙ ነግደው ይሆናል እንጂ የትግራይ ህዝብ የተለየ ጥቅም ያገኘው ነገር የለም።

ጥቅም አላገኘው እምብዛም ጥቅም አይፈልግም። የተለየ እንዲደረግለት አይፈልግም።

የአብዬን ወደ እምዬ የሚባል ነገር አይሰራም። Mr X አጠፋ ብለን የማያውቁ ሰዎችን ጭምር በዛ ወንጀል ሀሳብ በቂም፣ በጥላቻ ማየት ለኢትዮጵያ አይበጅም። መለየት ያስፈልጋል።

ይሄ ጥቃት እየባዛ ከመጣ ዘር መጨረስ ያመጣል። ይሄ ደግሞ ወርደት ለልጆቻችን ያሸጋግራል።"

ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ አህመድ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀርበው ከተናገሩት የወሰድኩት።

ፍቅር ያሸንፋል!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
86,660 ብር ደርሰናል!

ምዕራፍ አንድ በ24 ሰዓት ውስጥ ሊጠናቀቅ ነው! 13,340 ብር ብቻ ይቅረናል(100,000 ብር)። የብሩን ማጠን ሳይሆን #አብሮነታችንን ማስመስከራችን ለቀጣይ ጉዟችን ትልቅ አቅም ይሆነናል። የዛሬው ህብረታችን ነገም ሌሎች ወገኖቻችን ለማገዝ ትልቅ አቅም ይፈጥርልናል።

#ኦሮሚያ #ሀረሪ #ደቡብ #ትግራይ #ሱማሌ #አፋር #ቤንሻንጉል #ጋምቤላ #አማራ #አዲስ_አበባ_ከተማ_አስተዳደር #ድሬዳዋ_ከተማ_አስተዳደር የምትገኙ የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት ትልቅ ክብር አለን!

Account number(CBE): 1000277462439

@tsegabwolde @tikvaethiopia
#ኮኮሳ የኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ ሰራተኞች አረንጓዴ አሻራቸውን አሳርፈዋል። #ኦሮሚያ #ኢትዮጵያ
5ኛው አመት የTIKVAH-ETH የመፅሃፍት ማሰባሰብ ዘመቻ ከነገ ነሃሴ 20 እስከ መስከረም 30 በመላው ሀገሪቱ ይካሄዳል!!

ላለፉት አመታት በአብዛኛውን በከተሞች አካባቢ የሰራነውን ስራ #በማጠናከር ዘንድሮ ደግሞ ከከተማ ውጭ ወደሚገኙ የመጀመሪያና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ትኩረታችንን እናደርጋለን።

ምን አይነት መፅሃፍት ነው ከቤተሰባችን አባላት የምናሰባስበው?

•ከ1ኛ ክፍል ጀምሮ እስከ 12ኛ ክፍል ድረስ መደበኛ የመማሪያ መፅሃፍትን/Text Book/ እንዲሁም አጋዥ መፅሃፍት ብቻ

•በተለያዩ ቋንቋዎች የተዘጋጁ ትውልዱን ይጠቅማል፤ እውቀት ያስጨብጣል የምንላቸው መፅሃፍት።

•ትንሹ መስጠት የሚቻለው መፅሃፍ 1

•መፅሃፍቱ የሚገቡት ገጠራማ አካባቢ ለሚገኙ እና በአካል ሄደን ለምንለያቸው ቤተ መፅሃፍት

#እርሶ ምን ማድረግ ይችላሉ??

√ቢያንስ አንድ የመማሪያ መፅሃፍ ለሚወዷት ለኢትዮጵያ መለገስ ይችላሉ። እንዲሁም ከፍተኛ የመፅሃፍት ችግር ያሉባቸው ቦታዎችን በመለየት የማስተባበር ስራ ሊሰሩ ይችላሉ።

•TIKVAH-ETH በሀገሪቱ በየትኛውም አካባቢ ለምትገኙ የበጎ አድራጎት ማህበራት ይህን ሀገራዊ ስራ እንድታግዙ ጥሪውን ያቀርብላችኃል።

•የዘንድሮ ተፈታኝ ተማሪዎች ደግሞ ትልቁን ድርሻ በመውሰድ ከተማራቹባቸው እና ስትጠቀሟቸው ከነበሩት መፅሃፍ መካከል ቢያንስ አንዱን ለመጪው ትውልድ በስጦታ አበርክቱ።

•በStopHateSpeech ጉዞ ተሳታፊ የነበራችሁ የቤተሰባችን አባላት ይህን ለሀገርና ለትውልድ የሚሰራን ስራ በሙሉ አቅማችሁ እንድታግዙ ጥሪ እናቀርባለን።

•በውጭ ሀገር የምትገኙ የቤተሰባችን አባላት ጠቃሚ ናቸው የምትሏቸው መፅሃፍት በመላክ አልያም እዚህ ሀገር ባላችሁ ወዳጅና ዘመድ መፅሃፍት እንዲገዛ በማድረግ ይህን

#ኦሮሚያ
#አማራ
#ትግራይ
#ደቡብ
#ሱማሌ
#አፋር
#ሀረሪ
#ጋምቤላ
#ቤኒሻንጉል
#አ/አ ከተማ አስተዳደር
#ድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር

🏷በማኛውም አይነት ቋንቋ የተዘጋጀ የመማሪያ መፅሃፍ መለገስ ይቻላል!!
-------------------------------------------------------
በአሁን ሰዓት ልየታ ከተደረገባቸው አካባቢዎች መካከል፦

#ራያ_ቆቦ በራያ ቆቦና ዙሪያዋ የምትገኙ የቤተሰባችን አባላት መፅሃፍት ለመለገስ እና ይህን ስራ ለማስተባበር ከቤተሰባችን አባል #ሉላይ ጋር ይገናኙ፦ +251949256094

#ድሬዳዋ በድሬዳዋ ከተማ እና አካባቢው የምትገኙ ደግሞ ከቤተሰባችን አባል መሃሪ 0915034762/መሃሪ/ ጋር መገናኘት መፅሃፍ መለገስ ትችላላችሁ።

ሌሎች አካባቢዎች ላይ እኛም ለሀገራችን መስራት እንፈልጋለን የምትሉ እውቅና ያላችሁ ማህበራት ካላችሁ መልዕክት አስቀምጡልን @tsegabwolde 0919743630

5ኛው አመት የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት የመፅሃፍ ማሰባሰብ ዘመቻ!

@tsegabwolde @tikvahethiopia
«15 ሚሊዮን ብር #በማጭበርበር ከባንክ የወሰደ ሰው ታስሯል። በፌስቡክ ላይ ያለው ታሪክ ይኸ ሰው የታሰረው መንግሥትን ስለተቃወመ ነው የሚል ነው» የሶማሌ ክልል ምክትል ፕሬዝዳንት ሙስጠፋ ዑመር ተቃዋሚዎች ለምን ይታሰራሉ? ተብለው በOMN ሲጠየቁ።

«ለአካል ጉዳተኞች የሚገዙ #ዊልቸሮችን አጭበርብሮ የተሰባበሩ ያመጣና በኦዲት ከተረጋገጠ በኋላ የታሰረ ሰው አለ። እሱም በሶሻል ሚዲያ ላይ ፎቶው እየዞረ ይኸ ሰው የታሰረው በመንግሥት ላይ ቅሬታ ስላቀረበ ነው የሚባል ነገር አለ»

#ኦሮሚያ_ሚዲያ_ኔትዎርክ

Via #EsheteBekele
@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ኦሮሚያ #ትኩረት

በኦሮሚያ ክልል በተለያዩ የወለጋ አካባቢዎች አሁንም በቀጠለው የፀጥታ ችግር በርካቶች ህይወታቸው እያለፈ ፣ አካላቸው እየጎደለ፣ ንብረታቸው እየወደመ እንደሚገኝ ቤተሰቦቻችን ጠቁመዋል።

ባለፉት ዓመት ህዝቡ በሰላም እጦት ብዙ ቢሰቃይም መፍትሄ ሳይገኝ አሁንም እየተባባሰ በመቀጠሉ ንፁሃን ክፉኛ እየተጎዱ እና ስቃያቸውም እየተባባሰ እንደሚገኝ ነው ቤተሰቦቻችን የገለፁት።

ከጥቂት ቀን በፊት የፀጥታ ችግር ባለባቸው በወለጋ የተለያዩ አካባቢች ላይ #ንፁሃን እንዲጠበቁ ፣ የህዝቡ ስቃይ ትኩረት ባለማግኘቱ የሰሜን ክፍሉን ያህል ትንሽ እንኳን ትኩረት እንዲሰጠው እና ዘላቂ መፍትሄ እንዲፈለግ ቤተሰቦቻችን ተማፅኖ ማሰማታቸው አይዘነጋም።

ከሰሞኑን በተለይም በምዕራብ ኦሮሚያ በሚገኙት ሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን ጃርዳጋ ጃርተ ወረዳ እና በምስራቅ ወለጋ ኪረሙ ወረዳ ውስጥ በርካቶች ህይወታቸው አልፏል፣ ንብረታቸው ወድሟል ፣ #ሰላምን_ፍለጋ ሸሽተው ወደ ሌሎች አካባቢዎችም መግባታቸውን ለመስማት ችለናል።

አንድ የቤተሰባንች አባል ይህንን ጉዳይ በተመለከተ ፤ " ለንፁሃን ጭፍጨፋ ፣ ለንብረት ውድመት ለዚህ ሁሉ ምስቅልቅል ተጠናቂነት መኖር አለበት " ብሏል።

" እውነት መንግስት / አስተዳዳሪ ነኝ ፤ የህዝብንም ደህንነት አስጠብቃለሁ የሚል ካለ የትኛው አካል ለሚፈጠሩት ችግሮች ምክንያትና መንገድ እየሆነ እንዳለ ፣ ማን ግፍ እየፈፀመ እንዳለና ለዚህም ድርጊት ተባባሪ እየሆነ እንዳለ ምርመራ በማድረግ ማሳወቅ አለበት ፤ በየዕለቱ ሰዎች እየረገፉ ፣ እየተፈናቀሉ ፣ እየተራቡ እያዩ ዝም ያሉት ዓለም አቀፍ ማህበረሰብ ከእንቅልፋቸው ነቅተው መፍትሄ እንዲመጣ ንፁሃንን ከሞት እንዲድኑ ድምፃቸውን ማሰማት መቻል አለባቸው ። " ብሏል።

የመንግስት ዋናው ስራ የዜጎችን ደህንነት ማስጠበቅ ፤ ከየትኛውም የታጠቁ አካላት የሚደርስን ጥቃት መከላከል ፣ አጥፊዎችን መቅጣት ነው ይህን ማድረግ ባይቻል እና ንፁሃን ቢጎዱ ተጠያቂነት መኖር አለበት ሲል አክሏል።

በኦሮሚያ ክልል ባለው ፀጥታ ጉዳይ ፤ በመንግስት መዋቅር ውስጥ የሚታዩ ችግሮች መኖራቸውን ይህም በተደጋጋሚ መገለፁን ነገር ግን እስካሁን መፍትሄ እንዳልተገኘለት ገልጿል።

" ህዝብ መንግስት አለኝ ሚለው ደህንነቱ እንዲጠበቅ እንጂ በየዕለቱ ያለበት ችግር እየተባባሰ ህይወቱን እያጣ፣ እጅግ ደክሞ ያፈራው ንብረቱ እየወደመበት እንዲቀጥል አይደለም " ያለው ይኸው የቤተሰባችን አባል ባለፉት ጊዜያት እሱን ጨምሮ ቤተሰቦቻቸው በግጭት ቀጠና ውስጥ ያሉ ወገኖች ያሳለፉት ስቃይ በቃላት የሚገለፅ እንዳልሆነ አስረድቷል።

በኦሮሚያ ውስጥ የፀጥታ ችግሮች ባለባቸው ቦታዎች ስለሚደርሰው ስቃይ ብዙ ቢነገርም መፍትሄ ሳያገኝ ዛሬም የሰዎች ህይወት እየተቀጠፈ እንደቅጠል እየረገፈ ይገኛል።

የአንድ ሀገር ዜጎች ህይወታቸው በግፍ እየረገፈ እየታየ ለችግሩ መፈጠር በተለያዩ አቅጣጫዎች የተለያዩ ምክንያቶች እየተደረደሩ ፣ ጥላቻዎችም እየተሰበኩ፣ ሁኔታዎችም #ከመሻሻል ይልቅ ክፉኛ እየተባባሱ ቀጥለዋል።

ህዝቡ ሰላም ርቆት፣ ኢኮኖሚው ደቆ፣ አርሶ እንዳይበላ ሆኖ፣ እየታፈነ ሚሊዮኖች እየተጠየቀበት ፣ መውጫ እና መግቢያ አጥቶ ፣ የሚወዳቸውን እየተነጠቀ፣ ዓመታትን በገፋበት የግጭት ቀጠናዎች መፍትሄ እንዲያገኝ ግፊት ማድረግ እንደሚገባ ቤተሰቦቻችን ገልፀዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#USA #ETHIOPIA የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን ዛሬ ከጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ጋር በስልክ መምከራቸውን የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አሳውቋል። ውይይቱ የነበረው በሰሜን ኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላም ለማምጣት በሚደረገው ጥረት ዙሪያ እንደነበር ተገልጿል። አንቶኒ ብሊንከን ፤ የኢትዮጵያ መንግስት በትግራይ ክልል እና በጎራባቹ አፋር እና አማራ ክልሎች ያለውን ያልተገደበ የሰብአዊ ድጋፍ…
#Update

የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ትላንት ምሽት ያወጣውን መግለጫ ቀይሮታል።

መስሪያ ቤቱ ትላንት ምሽት የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን እና የኢፌዴሪ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ በስልክ መነጋገራቸውን አሳውቆ ነበር።

በተደረገው ንግግር ላይ ያወጣውን መግለጫ ቀይሮት በድረገፁ ላይ የአውጥቷል።

ንግግሩ የነበረው በኢትዮጵያ ሰላም፣ ብፅግናና መረጋጋት ላይ ያተኮረ ነበር ብሏል መ/ቤቱ።

ብሊንከን ፥ በሰሜን ኢትዮጵያ የጦርነት ማቆም ስምምነትን በመተግበር ረገድ መሻሻል መኖሩን ጠቁመው በ #አማራ እና #ኦሮሚያ ክልሎች ያለው ሁኔታ ግን አሳሳቢ መሆኑን ገልጸዋል።

የውጭ ጉዳይ መ/ቤቱ ፤ ብሊንከንና ጠቅላይ ሚኒስትሩ የምግብ ዕርዳታን በፍጥነት ለማስጀመር የጋራ ግብን ለማሳካት የሰብአዊ ርዳታ ስርጭት ስርዓትን በተጠናከረ ሁኔታ ለመዘርጋት ያለመ ውይይት ማድረጋቸውን አመልክቷል።

የአፍሪካ ቀንድን በተመለከተ ብሊንከን በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ላይ ለሚደረገው ዲፕሎማሲያዊ መፍትሄ አሜሪካ ሙሉ ድጋፍ እንደምትሰጥ ገልጸዋል።

በሱዳን ያለውን ቀውስ ለመፍታት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ላደረጉት ቀጠናዊ ጥረቶች አድናቆታቸውን መግለፃቸውን የውጭ ጉዳይ መ/ቤቱ ባወጣው መግለጫ ላይ አመልክቷል።

@tikvahethiopia
#ኦሮሚያ

በመንገደኞች ላይ በተፈፀመ ጥቃት የሰዎች ህይወት ማለፉ ተነገረ።

በኦሮሚያ ክልል፣ ምስራቅ ወለጋ ዞን ጊዳ አያና ወረዳ መንገደኞችን አሳፍሮ በሚሄድ ተሽከርካሪ ላይ በደረሰ ጥቃት ህይወት መጥፋቱን እና ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች ሆስፒታል መግባታቸው ታውቋል።

ግድያው የተፈፀመው ዛሬ አርብ መስከረም 4 ቀን 2016 በ " አንዶዴ ዲቾ " የሚባል ቦታ ላይ መሆኑን ተነግሯል።

ግድያውን በተመለከተ የዞኑ አስተዳደር የፀጥታ ቢሮ ፤ " ድርጊቱ የተፈፀመው ዲቾ ላይ ነው " ያለ ሲሆን ከአንገር ጉተን ወደ ጊዳ በሚጓዝ የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ ላይ ነው ጥቃቱ የተፈፀመው " ሲል ገልጿል።

የፀጥታ ቢሮው የድርጊቱ ፈፃሚዎች " የአማራ ፅንፈኛ ታጣቂዎች " ናቸው ብሏል።

ቢሮው ፤ " በአካባቢው ጸጥታውን የሚያውኩ ታጣቂዎች አሉ። ታጣቂዎቹ በተሽከርካሪ የሚጓዙ ሰዎችን በመንገድ ላይ በማስቆም ነው ድርጊቱ የፈፀሙት " ሲል ገልጿል።

ዲቾ ላይ እስከ 30 የሚደርሱ ሰዎች እንደተገደሉ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ በርካታ ዘገባዎች ተሰራጭቷል።

ሆኖም ግን የዞኑ አስተዳደር የተገደሉት አምስት ሰዎች እንደሆኑ ገልጿል።

ቃሉን ለቢቢሲ አፋን ኦሮሞ የሰጠው ተጎጂዎቹ ለህክምና የተወሰዱበት የጊዳ አያን ሆስፒታል ባለሙያ (ለደህንነቱ ስሙ ያልተጠቀሰ) በጥቃቱ የሞቱት ሰዎች ቁጥር አምስት ነው ብሏል።

ባለሙያው " በመጀመሪያ አምስት ሰዎች ከባድ ጉዳት ደርሶባቸው ወደ እኛ መጡ " ያለ ሲሆን እነዚህ አስቸኳይ ህክምና ካገኙ በኋላ የአራት ሰዎች አስክሬን ደረሰ ፤ ሆስፒታል ውስጥ ከነበሩት ውስጥ አንዱ በህክምና ላይ እያለ ህይወቱ አልፏል ሲል ተናግሯል።

እንደ ባለሙያው ገለጻ በህክምና ላይ የሚገኙት እና አስክሬናቸው እነሱ ጋር የመጣ ሰዎች በሙሉ #ወንዶች ናቸው።

" አሁን አራት ሰዎችን እያከምን ሲሆን ከእነዚህ ውስጥ ሦስቱ ከባድ ጉዳት ደርሶባቸዋል። እነሱን ለማዘዋወር ምንም ምቹ መንገድ የለም፣ ጉዳቱ ከአቅማችን በላይ ነው። የደም እጥረት አለብን  " ብለዋል ባለሙያው።

በነገው እለትም የጸጥታ ሃይሎች ተጎጂዎችን ወደ ተሻለ ህክምና መስጫ መውሰድ ከቻሉ ይህንን ለማድረግ መታቀዱንም ተናግረዋል።

በህክምና ላይ ያሉ ሁሉም የተጎዱ ሰዎች በጥይት ተመትተዋል ብለዋል።

የምስራቅ ወለጋ ዞን አስተዳደርና ጸጥታ ቢሮ በጥቃቱ የተገደሉት ሰዎች ቁጥር ከፍተኛ እንደሆነ በማህበራዊ ሚዲያ የተሰራጨው ዘገባ ሀሰት ነው ብሏል።

አሁን ጥቃቱ በተፈፀመበት አካባቢ እና በሌሎች አካባቢዎች ታጣቂዎች በሰላማዊ ሰዎች ላይ ጉዳትና ማፈናቀል እያደረሱ እንደሆነ የገለፀው የፀጥታ ቢሮው ታጣቂዎቹ ወደ ክልሉ አልፈው የገቡ ሳይሆን በዛው የሚንቀሳቀሱ ፤ ትናንሽ የታጠቁ ቡድኖች ናቸው ብሏል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ መረጃውን ያገኘው የ " ቢቢሲ አፋን ኦሮሞ " ነው።

NB. የሟቾች ቁጥርን በተመለከተ የሆስፒታል እና የዞን ባለስልጣናት የገለፁት ቁጥር አምስት ቢሆንም በጥቃቱ የተገደሉ ሰዎች ከ30 በላይ እንደሆነ የሚገልጹ መረጃዎች በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ ተሰራጭተዋል። አንድ የአካባቢው ነዋሪ ደግሞ ከሆስፒታል እና ከወረዳው ባለስልጣናት መረጃ በተለየ ሁኔታ የሞቱ ሰዎች 7 ናቸው ብሎ ተጨማሪ አስክሬን እየተፈለገ ነው ብሏል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ተጨማሪ መረጃዎችን ሲያገኝ የሚያቀርብ ይሆናል።

@tikvahethiopia
#ኦሮሚያ

" በቤጊ ሁለት ቀበሌዎች ረሃብ ተከስቷል "

በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ወለጋ ዞን ቤጊ ወረዳ በሁለት ቀበሌዎች ረሃብ መከሰቱ ተነገረ።

በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሽብርተኝነት የተፈረጀውና ራሱን " የኦሮሞ ሕዝብ ነጻ አውጪ " ብሎ የሚጠራው ታጣቂ ቡድን ከ2011 ዓ.ም ጀምሮ ሲንቀሳቀስባቸው ከነበሩ አካባቢዎች መካከል በቤጊ ወረዳ በሁለት ቀበሌዎች ረሃብ መከሰቱን የምዕራብ ወለጋ ዞን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገለጸ።

የምዕራብ ወለጋ ዞን አስተዳዳሪ አቶ ሰለሞን ታምሩ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል፣ " ሸኔ የያዛቸውና ለጥቂት ጊዜያት ያስተዳደራቸው ወረዳዎች ነበሩ።  እነዛ ወረዳዎች ብዙ ችግሮች ገጥሟዋቸዋል " ብለዋል።

ለአብነት ታጣቂ ቡድኑ ሲንቀሳቀስባቸው በነበሩ አንዳንድ አካባቢዎች #ረሃብ መከሰቱን ገልጸዋል።

አቶ ሰለሞን ፣ " እስፔሻሊ ጠረፍ ላይ የሚገኙ ቀበሌዎች ተጎድተዋል። በምዕራብ ወለጋ ዞን ቤጊ ወረዳ ተጋባና ሻንታ ቀበሌዎች ረሃብ አለባቸው " ብለዋል።

ረሃብ ተከሰተበት የተባለውን የቤጊ ወረዳ ሁኔታን ሲያስረዱም አቶ ሰለሞን ፣ " መሰረተ ልማት፣ ቀበሌዎች፣ የአስተዳደር ጽሕፈት ቤቶች ጤና ኬላዎች፣ ጤና ጣቢያዎች ከ2011 ዓ.ም ጀምሮ በጣም ጉዳት የደረሰበት ወረዳ ነው " ብለዋል።

" ከጤና ጋር በተያያዘ ቢያንስ 45 የሚሆን ጤና ኬላ ወድሟል ወደ አምስት ጤና ጣቢያዎች ተቃጥለዋል " ሲሉ አስታውሰው፣ ወረዳውን ታጣቂ ቡድኑ ሲቆጣጠረው አርሶ አደሩ እንዳያርስ በማዳበሪያ እንዳይጠቀም፣ ማኅበረሰቡ የሕክምና አገልግሎት እንዳያገኝ ማድረጉን አስረድተዋል።

" ሸኔ አገሪቱን ወደ ድህነት የሚመራ እንጂ ምንም አላማ የሌለው ነው " ያሉት የዞኑ አስተዳዳሪ ታጣቂ ቡድኑ " በቄለም ወለጋና  በቤጊ፣ በቆንዳላ በተለይ ገጠሩን አካባቢ ተቆጣጥሮ ጉዳት አድርሷል። ሰው ገድሏል። ብዙ ንብረቶች በዚህ ታጣቂ ቡድን ወድመዋል " በማለት ተናግረዋል።

ረሃብ የተጋረጠባቸው የሰሊጥ አምራቾች ናቸው ያሉት የዞኑ አስተዳዳሪ፣ " ሸኔ አርሶ አደሩ ማዳበሪያ በሚወስድበት ጊዜ ቀቅሎ እንዲበላ ሲያደርግ ነበር። መብላት ማለት እንደ ምግብ እንዲበላ በማድረግ እንዳያርስበት፣ እንዳይጠቀምበት ማድረግ ነው " ብለዋል።

ነዋሪዎች በበኩላቸው በተከሰተው ረሃብ የሰዎች ሕይወት ማለፉን ገልጸው፣ መንግሥት የምግብ ድጋፍ እንዲያደርግ ጠይቀዋል።

አክለውም፣ በወባ ወረርሽኝም የሰው ሕይወት እያለፈ መሆኑን አስረድተዋል።

በረሃብ የሞተ ሰው እንዳለና እንዴሌለ ማብራሪያ እንዲሰጡ ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ለቀረበላቸው ጥያቄ በሰጡት ምላሽ አቶ ሰለሞን ፣ " ከረሃብ የተነሳ የሞተ ሰው ሪፓርት አልደረሰኝም። ከምግብ ጋር በተያያዘ ግን የኦሮሚያ ቡሳ ጎኖፋ ሰሞኑን 400 ኩንታል ዱቄት አድርሷል። እርዳታ ግን አሁንም ያስፈልጋል " ብለዋል።

ከረሃብ ባሻገርም በዞኑ በሚጉኙ ወረዳዎች የወባ ወረርሽኝ እንደተከሰተ፣ #የሞቱ ሰዎችም እንዳሉ ገልጽው፣ መንግሥትና መንግስታዊ ያልሆኑ የተራድኦ ድርጅቶች እርብርብ እንዲያደርጉ ጠይቀዋል።

መንግሥት " ኦነግ ሸኔ " እያለ የሚጠራውና እራሱን የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት የሚለው ታጣቂ ቡድን ከላይ በምዕራብ ወለጋ ዞን በቀረበበት ክስ ዙሪያ ይፋዊ ምላሽ የሚሰጥ ከሆነ ተከታትለን እናሳውቃለን።

@tikvahethiopia
#ኦሮሚያ

" ከ1 ሺህ በላይ ሃኪሞችን ለመቅጠር  ብፈልግም ተቀጣሪ አጣሁ " - የኦሮሚያ ክልል ጤና ቢሮ 

የኦሮሚያ  ክልል ጤና ቢሮ 1 ሺህ 100 ሀኪሞችን ለመቅጠር  ባለፈዉ ዓመት ሰኔ ወር  2015 ዓ.ም ማስታወቂያ ቢያወጣም ተቀጣሪዎችን ባለማግኘቱ በጀቱን ወደ ሌላ ዘረፍ  ማዛወሩን ማስታወቁን ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 ሬድዮ ጣቢያ ዘግቧል።

የቢሮዉ  ምክትል ሃላፊ ዶ/ር ጉሻ በለኮ ለሬድዮ ጣቢያው በሰጡት ቃል ፤ በሰኔ 2015 ላይ 1 ሺህ 100 ሀኪሞችን ለመቅጠር ማስታወቂያ የወጣ ቢሆንም ተቀጣሪዎችን ባለማግኘቱ  ቢሮዉ በጀቱን ለሌላ ጉዳይ ማዋሉን ተናግረዋል፡፡

" ለ 2 ወራት ያክል ማስታወቂያዉን ክፍት ብናደርግም ገበያ ላይ ተቀጣሪዎችን አላገኘንም "  ሲሉ ኣክለዋል።

ምክትል ኃላፊው ፤ በየአንዳንዱ ጤና ተቋም ሀኪሞች መኖር ስላለባቸዉ ያንን ለማሟላት ማስታወቂያ መውጣቱን አስረድተው " ሀኪሞችን ባለማግኘታችን በምትኩ  የጤና ኤክስቴንሽን ባለሙያዎችን፣ አዋላጆችን እና ነርሶችን ለመቅጠር ተገደናል "  ሲሉ ተናግረዋል።

ከዚህ በፊት ለመላዉ ኦሮሚያ አገልግሎት የሚሰጡ የጤና ባለሙያዎች ቁጥር 72 ሺህ ነበር ያሉት ሃላፊዉ አሁን ላይ ቁጥሩ ወደ 85 ሺህ ከፍ ማለቱን ተናግረዋል።

" በተቻለን አቅም ማስታወቂያ አዉጥተን ገበያ ላይ የነበሩትን ለመዉሰድ ሞክረናል ነገርግን አሁንም የሀኪሞች ዕጥረት አለ " ብለዋል፡፡

" ማስታወቂያ አይተዉ የመጡትን እንቀጥራለን ፤ ካልመጡ ግን ገበያዉ ላይ የሰዉ ሃይል እንደሌለ ነዉ የሚቆጠረዉ " ሲሉም አስረድተዋል።

ምክትል ሃላፊዉ በተጨማሪም ባለፈዉ ዓመት ሃኪሞችን ለመቅጠር ባወጣነዉ ማስታወቂያ ሀኪሞችን ማግኘት ስላልቻልን ወደ 7 መቶ አከባቢ የሚሆኑ የተለያዩ ባለሙያዎችን ቀጥረናል ሲሉም ለሬድዮ ጣቢያው ተናግረዋል።

የዚህ መረጃ ባለቤት ኢትዮ ኤፍ ኤፍም 107.8 ሬድዮ ጣቢያ ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ስልክአምባ " 12 ሰዎች ናቸው የተገደሉት፤ .. ቤቶች ተቃጥለዋል፤ ከብቶችም እየተነዱ ተወስደዋል " - ነዋሪዎች " 11 ሰዎች ስለመገደላቸው መረጃ ደርሶናል መረጃውን የማጣራት ስራ እየሰራን ነው " - ኢሰመኮ ️በኦሮሚያ ክልል ፤ በምዕራብ ሸዋ ዞን ፤ ኖኖ ወረዳ ስልክ አምባ ከተማ ባለፈው ሠኞ ታጣቂዎች በፈጸሙት ጥቃት 12 ሰዎች መገደላቸውን ነዋሪዎች ለቪኦኤ ሬድዮ ጣቢያ በሰጡት ቃል ተናግረዋል።…
#ኦሮሚያ #ኖኖ #ስልክአምባ

በኦሮሚያ ክልል ፤ በምዕራብ ሸዋ ዞን ፤ ኖኖ ወረዳ ሰርገኞችን ዒላማ ባደረገ ጥቃት ከ20 በላይ ሰዎች መገደላቸውን የአካባቢው ኮማንድ ፖስት እና ነዋሪዎች ገለጹ።

የኖኖ ወረዳ ኮማንድ ፖስት ኃላፊ አቶ ተሾመ ሰቦቃ ለቢቢሲ አፋን ኦሮሞ በሰጡት ቃል ፥ ጥቃቱ ቅዳሜ ሰኔ 8 ንጋት ላይ ነው የተፈጸመው።

ጥቃት አድራሾቹ " ጽንፈኛ የአማራ ታጣቂዎች  ናቸው " ብለዋል።

ኃላፊው " ሰርገኞቹ ቤት ውስጥ እያሉ በር ዘግተውባቸው ቦምብ ወረወሩባቸው። ቤት ውስጥ ከነበሩት አንድም በሕይወት የወጣ የለም። እዚያው ተቃጥለው አልቀዋል "  ሲሉ ሁኔታውን አስረድተዋል።

አንድ የአካባቢው ነዋሪ ታጣቂዎቹ ሰርግ ቤቱ ላይ ከአንድ በላይ ቦምብ ወርውረው ሙሽሮቹን እና አብረዋቸው የነበሩ ሰዎችን መግደላቸውን ተናግረዋል።

የኮማንድ ፖስት ኃላፊን ጨምሮ የአካባቢው ነዋሪዎች በሰጡት ቃል ፥ በሰርግ ቤት ላይ የተነሳውን እሳት ለማጥፋት የመጡ የአካባቢው ነዋሪዎች በታጣቂዎቹ የተኩስ እሩምታ ተከፍቶባቸው በርካታ ሰዎች ተገድለዋል።

የአካባቢው ነዋሪ የሟቾች ቁጥር ከ30 እስከ 50 ሊደርስ እንደሚችል ተናግረዋል።

በጥቃቱ ሙሽሪት እና ሙሽራውን ጨምሮ የሰርጉ ታዳሚዎች የሆኑ ሰዎች በሙሉ ሕይወታቸው ማለፉን ነዋሪው ተናግረዋል።

የወረዳው የኮማንድ ፖስት ኃላፊ አቶ ተሾመ ሰቦቃ ፥ " በእሳት ተቃጥለው የሞቱ ሰዎችን ቁጥር መለየት አስቸጋሪ በመሆኑ ትክክለኛውን የሟቾች ቁጥር መለየት አልተቻለም " ሲሉ ለቢቢሲ ቃላቸውን ሰጥተዋል።

ባለፈው ሚያዚያ ወር ላይ በዚህ ወረዳ በ5 ቀበሌዎች በተፈጸመ ጥቃት 12 ሰዎች መገደላቸውን ፤ ቤቶች መቃጠላቸውን ፣ ከብቶችም እየተነዱ መወሰዳቸውን ነዋሪዎች መግለጻቸው ይታወሳል።

ኢሰመኮም መረጃውን የማጣራት ስራ እየሰራ እንደነበር መግለጹ አይዘነጋም።

ከሟቾች አብዛኛዎቹ የአማራ ብሔር ተወላጆች እንደነበሩ ፤ ጥቃት ፈጻሚዎችም የ " ሸኔ (የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት) ታጣቂዎች " እንደሆኑ ነዋሪዎች መናገራቸው ይታወሳል።

@tikvahethiopia
#ኦሮሚያ

በኦሮሚያ ክልል ፣ ሰሜን ሸዋ ዞን ወጫሌ ወረዳ ታጣቂዎች ባደረሱት ጥቃት በርካታ ሰዎች ተገድለዋል።

ዛሬ ጥዋት ወጫሌ ወረዳ በተፈጸመው ጥቃት የወረዳው አስተዳዳሪ አቶ ንጉሴ ኮሩን ጨምሮ በርካቶች ነው የተገደሉት።

የወጫሌ ወረዳ አጎራባች ይሆነው አለልቱ ወረዳ ፥ የቀድሞው የወረዳው አሁን ደግሞ የወጫሌ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ንጉሴ ኮሩ መገደላቸውን አረጋግጧል።

ለዶቼ ቨለ ሬድዮ ቃላቸውን የሰጡ አንዲት ነዋሪው " የወረዳው አስተዳዳሪን ጨምሮ ብዙዎች ህይወታቸው አልፏል። የጉዳቱ መጠን እስካሁን የተጣራ አይመስለኝም " ብለዋል።

ጉዳት የደረሰባቸው ሆስፒታል መግባታቸው ተሰምቷል።

የወረዳው ዋና ከተማ ሙከጡሪ ከአዲስ አበባ 82 ኪሎሜትር ርቀት ላይ ነው የሚገኘው።

@tikvahethiopia
#Ethiopia #USA

የአሜሪካ ከፍተኛ ባለስልጣናት ኢትዮጵያ ይገኛሉ።

በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ማሲንጋን ጨምሮ፣ የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ምክትል ረዳት ሚኒስትር ስፔራ፣ የአሜሪካ መከላከያ ሚኒስቴር ምክትል ረዳት ፀሀፊ ፋሬል እና ሌሎችም የተካተቱበት ልዑክ ከሀገር መከላከያ ሚኒስትር ኢንጂነር አይሻ መሐመድ ጋር መክረዋል።

በወቅቱም ኢንጂነር አይሻ ፤ ኢትዮጵያ ከአሜሪካ ጋር ላላት የረዥም ጊዜ ወታደራዊ ግንኙነት ትልቅ ዋጋ እንደምትሰጥ እንደገለጹና ይህንኑ ትብብር የበለጠ ለማጠናከር ኢትዮጵያ ፍላጎት እንዳለት መናገራቸውን ሀገር መከላከያ ሰራዊት ገልጿል።

የአሜሪካ ኤምባሲ እንዳለው ከሆነ ደግሞ በምክክሩ ላይ #በአማራ እና #ኦሮሚያ ያለው ግጭት ጉዳይ ተነስቷል።

ሌላው የቀድሞ ተዋጊዎችን ዲሞብላይዝ በማድረግ ወደ ማህበረሰቡ መልሶ ለመቀላቀልና ለማቋቋም ስለሚደረገው ስራ (DDR) ውይይት ተደርጓል።

በኢትዮጵያ እና በአሜሪካ መካከል ያለውን ወታደራዊ ትብብር በማጠናከር ላይም ትኩርት ያደረገ ምክክር መደረጉን ከኤምባሲው የተገኘ መረጃ ያሳያል።

#USA #USEmbassy

@tikvahethiopia