TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
211 files
4.1K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
አቶ ዮናስ ከስልጣናቸው ተነሱ...

(ከጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት @eliasmeseret)

ላለፉት ስምንት አመታት የኢትዮጵያ ቅርስ ጥበቃ ባለስልጣን ዳይሬክተር ጀነራል የነበሩት አቶ ዮናስ ደስታ በጠ/ሚር #አብይ_አህመድ ትእዛዝ ከስልጣናቸው ተነስተዋል። አቶ ዮናስ ዛሬ ማለዳ ለአለም አቀፉ ጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት በላኩት የፅሁፍ መልዕክት "ወደሚቀጥለው የህይወቴ ምእራፍ ስሸጋገር የተደበላለቀ ስሜት ቢኖረኝም የጠ/ሚር አብይን እርምጃ በፀጋ ተቀብያለሁ" ብለዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የዊክሊክሱ ዋና አዘጋጅ አሳንጄ የኢኳዶርን ኢምባሲ ለስለላ እንደተጠቀመበት ፕሬዚዳንቱ ተናገሩ፡፡ጁሊያን አሳንጀ በለንደን የሚገኘውን የኢኳዶር ኢምባሲን እንደ ‹‹ስለላ ማዕከል ›› እንደተጠቀመበት የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ተናግረዋል፡፡ ፕሬዚዳንት ለኒን ሞሪኖ ለዘ ጋርዲያን ጋዜጣ እንደተናገሩት የቀድሞው የኢኳዶር መንግስት በኢምባሲው አማካኝነት ድጋፎችን ለሌሎች ሀገራት ‹‹በጣልቃገብነት››ይሰጥ ነበር ብለዋል፡፡

Via ቢቢሲ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ኢትዮጵያ የኒውክሌር ቴክኖሎጂን ጥቅም ላይ ለማዋል የሚያስችላትን ስምምነት ከሩስያ ጋር ተፈራረመች። በሩስያ በተካሄደው 11ኛው አቶም-ኤክስፖ ላይ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶ/ር ጌታሁን መኩሪያ እና የሩስያ ስቴት አቶሚክ ኢነርጂ ኮርፖሬሽን ዳይሬክተር ጀነራል አሌክሲ ሌካቼቭ የኒውክሌር ቴክኖሎጂን ጥቅም ላይ ለማዋል የሚያስችል የትግበራ ስምምነት ተፈራርመዋል። የትግበራ ፍኖተ ካርታ ስምምነቱ የኒውክሌር ቴክኖሎጂን በግብርና፤ የህክምናውን ዘርፍ ለማዘመን፤ ለማምረቻው ዘርፍ ግብዓት እና ለመሳሰሉት ጥቅም ላይ ለማዋል የሚያስችል ነው፡፡ በተለይ በአለም እያደገ የመጣውን የህክምና ዘርፍ በኢትዮጵያ ለማዘመንና የቀዶ ጥገና ህክምናን የተቀላጠፈ ለማድረግ የኒውክሌር ቴክኖሎጂን ጥቅም ላይ ለማዋል እንደሚሰራ ዶ/ር ጌታሁን መኩሪያ ተናግረዋል፡፡ ትልልቅ ኢንደስትሪዎችን ለመገንባት በዝናብ ላይ ጥገኛ ከሆነ የሃይል ማመንጫ ኢትዮጵያ መላቀቅ አለባት ያሉት ሚኒስትሩ ፊታችንን ወደ ድብልቅ ኢነርጂ እናዞራለን ብለዋል፡፡

ምንጭ፦የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ያቤሎ አካባቢ 790 ኪሎ ግራም የሚመዝን #ካናቢስ ሚያዝያ 5 ቀን 2011 ዓ.ም በኦሮሚያ ፖሊስ አባላት መያዙን የገቢዎች ሚኒስቴር ገልጿል። ሆኖም ዕፁን ሲያዘዋውር የነበረው ግለሰብ ማምለጡ ነው የተነገረው፡፡ ካናቢሱ በቁጥጥር ስር የዋለው ከመሐል ሀገር ወደ ኬንያ በመጓጓዝ ላይ በነበረበት ወቅት መሆኑን ከሞያሌ ጉምሩክ ቅርንጫ ጽህፈት ቤት የተገኘው መረጃ ያመላክታል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
"ኢትዮጵያን #የሚያጠፏት እኔ አውቅላችኃለሁ ባዮች ናቸው" ፕሮፌሰር ደጀኔ አየለ
.
.
የአሁኑ ትውልድ ራሱን ከጥላቻ ንግግሮች በማራቅ በአንድነት፤ በፍቅር ኢትዮጵያን እንዲገነባ የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዘዳንት ጥሪ አቀረቡ። ፕሮፌሰሩ ጥሪውን ያቀረቡት TIKVAH-ETH በወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ባዘጋጀው #StopHateSpeech/የፀረ ጥላቻ ንግግር/ ዘመቻ መድረክ ላይ ነው።

ወጣትነት ማለት ያልተለኮሰ ሻማ ነው ያሉት ፕሮፌሰር ደጀኔ -- ሰይጣን ሲለኩሰው የጥፋት እና የውድመት ኃይል ይሆናል፤ በመልካምነት እና በበጎነት ሲለኮስ ደግሞ ሀገር ይገነባል፤ ሀገር ይታደጋል ብለዋል። አክለውም ሁሉም ወጣት የእርስ በእርስ ግጭት ተፈጥሮባቸው ከነበሩት ሀገራት #በመማር ከጥላቻ ንግግሮች በመቆጠብ፤ በሰላም በፍቅር እና በአንድነት ለኢትዮጵያ እንዲሰራ ሀገራዊ ጥሪ አቅርበዋል።

በመጨረሻም ፕሮፌሰር ደጀኔ የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላትን ያመሰገኑ ሲሆን ለሰላም እና ለፍቅር የሚደረገውን ጉዞ #እንደሚደግፉ ገልፀዋል፤ በ#StopHateSpeech ጉዞ ተሳታፊ የሆኑ ወጣቶችንም ያበረታቱ ሲሆን "ነገ ታሪክ ያስታውሳችኃል ጉዟቹን ቀጥሉ ሁሉም ከእናተ ዘንድ ይሰለፋል" ብለዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ስራ አቁመዋል...የኢንተርንሺፕ ተማሪዎች!!

ለጥያቄዎቻችን ተገቢ #መልስ ይሰጠን ያሉ #የአርሲ_ዩኒቨርሲቲ የህክምና ኢንተርንሺፕ ተማሪዎች ስራ አቁመዋል።

ተጨማሪ መረጃዎች ይኖሩኛል!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የአርሲ ዩኒቨርሲቲ ስራ ያቆሙ የህክምና ኢንተር ንሺፕ ተማሪዎች ዛሬ ወደስራ ካልተመለሱ አስተዳደራዊ እርምጃ እንደሚወስድ ገልጿል። ለTIKVAH-ETH አስተያየታቸውን የሰጡ ተማሪዎች በበኩላቸው እያነሳን ላለነው ጥያቄ አመርቂ መልስ እንዲሰጠን እንጠይቃለን ብለዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update አቶ #በረከት_ስምዖን እና አቶ #ታደሰ_ካሳ የእምነት ክህደት ቃላቸውን እንዲሰጡ ለሚያዝያ 14 ቀን ተቀጠሩ፡፡ በጥረት ኮርፖሬት የሀብት ምዝበራ ተጠርጥረው በፍርድ ቤት ጉዳያቸው እየታዬ የሚገኙት አቶ በረከት ስምዖንና አቶ ታደሰ ካሳ #የተከሰሱበት ዝርዝር ጉዳይ ትናንት በጽሑፍ ደርሷቸዋል፡፡ ዛሬ ፍርድ ቤት የቀረቡት ተጠርጣሪዎቹ ጽሑፉ ብዛት ስላለው በአግባቡ አንብበውና ተረድተው የእምነት ክህደት ቃላቸውን ለመስጠት ተጨማሪ ጊዜ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል፡፡ ፍርድ ቤቱም የተከሳሾቹን አቤቱታ ተመልክቶ ለሚያዝያ 14 ቀን 2011ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡

Via #AMMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
"....ይቅርታ ወንዝ ነው፡፡ ድንበርም የለውም፡፡ ወደ ሁሉ ይፈሳል፤ ሁሉን ያጠጣል፤ ሁሉን ደግሞ ያለመልማል፡፡ ይቅርታ ርቀውም ቀርበውም የነበሩትን በአንድነት የሚሰበሰብ የምስራች ድምፅ ነው፡፡ ወንዝ ለሁሉ ይፈሳል፡፡ ለምሳሌ አባይ ለኢትዮጵያ ይፈሳል፤ ለሱዳንም እንዲሁ ግብፅንም ያጠጣል፡፡ ወንዝ ንፁህ ነው "በቃ እንደውም ኢትዮጲያ ትሻለኛለች እና ኢትዮጲያ ጋር ብቻ ልፍሰስ" አይልም!! ምክንያቱም ወንዝ ተሻጋሪ ነውና ፡፡ ይቅርታም ልክ እንደዚሁ ነው፡፡ ይዞ ይሻገራል፡፡ ይቅርታ "ወንድሞቼ" ብሎ ለመጥራት ጉልበታም ያደርጋል፡፡ ይቅርታ ድልድይ ነው ሰውን ከራሱ፣ ሰውን ከሰው እና ሰውን ከእግዚአብሔር ጋር ያገናኛል፡፡ በአጠቃላይ ይቅርታ የድል አድራጊዎች ምልክት የአሽናፊዎችም ሰንደቅ ነው፡፡ የሰው ልጅ ያለ ይቅርታ:ተንቀሳቃሽ ስልክም ያለ "ኔትወርክ" ባዶ ቀፎዎች ናቸው፡፡ ስለዚህ የሰው ልጅ ኖረ ሚባለው አንድም ሲያፈቅር : አንድም ደሞ ይቅር ሲል ነው፡፡" #mamush

@tsegabwolde @tikvagethiopia
አሳዛኝ ዜና‼️

ሰባ ገደማ #ኢትዮጵያውያን በቀይ ባህር #የጀልባ_መገልበጥ አደጋ #ሞቱ:: ቀይ ባሕርን አቋርጠው ወደ ሳውዲ አረቢያ እና የመን በጀልባ በመጓዝ ላይ የነበሩ 70 ገደማ ኢትዮጵያውያን ወጣቶች የመገልበጥ አደጋ ደርሶባቸው ሞቱ። ከሟቾቹ ውስጥ ስድሳዎቹ ከትግራይ ክልል አፅቢ ወንበርታ ወረዳ የተነሱ ነበሩ ተብሏል።

ሰባ ገደማ ወጣቶች ይዛ ስትጓዝ የነበረችው ጀልባ የመገልበጥ አደጋ የደረሰባት ቅዳሜ መጋቢት 28 ለሊት መሆኑን ከአካባቢው የተገኙ መረጃዎች አመልክተዋል።

ከጀልባዋ ተሳፋሪዎች መካከል 60ዎቹ ከትግራይ ክልል አፅቢ ወንበርታ ወረዳ የተጓዙ መሆናቸው ከተሰማ በኋላ በወረዳዋ በከባድ የሐዘን እና ድንጋጤ ድባብ እንደምትገኝ የአካባቢው ነዋሪዎች ለዶይቼ ቬለ ተናግረዋል።

በተገለበጠችው ጀልባ ላይ የነበሩት ቀሪዎቹ ወጣቶች ኢትዮጵያውያን እንደነበሩ ቢነገርም ትክክለኛ ቁጥራቸውን እና ከየት አካባቢ እንደመጡ በተመለከተ እስካሁን የተባለ ነገር የለም።

በአፅቢ ወንበርታ ወረዳ አብዛኞቹ የሟች ወጣቶች ቤተሰቦች የሞት መርዶውን በአደጋው ማግስት እሁድ እና ትናንት እንደተረዱ ነዋሪዎች ለዶይቼ ቬለ አስረድተዋል። የወረዳው የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ከ40 በላይ የሟች ቤተሰቦች መርዶው እንደደረሳቸው ገልጿል። የትግራይ ክልል የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ትናንት ምሽት ባወጣው የሐዘን መግለጫ የአርባዎቹን ወጣቶች መሞት አረጋግጧል።

Via #DW
@tsegabwolde @tikvahethiopia
መግለፂ ሓዘን ብሄራዊ ክልላዊ መንግስቲ ትግራይ
------------------------------------
ብሄራዊ ክልላዊ መንግስቲ ትግራይ ክሳብ ሐዚ ብዘሎ መረዳእታ ልዕሊ 40 ዝኮኑ መናእሰይ ወገናት ካብ ወረዳ ኣፅቢ ወንበርታ ከባቢኣን ተበጊሶም ናብ ስዑዲ ዓረብን የመንን ብቀይሕ ባሕሪ ክሰግሩ ብዘጋጠሞም ሓደጋ መርከብ ጥሒሎም ህይወቶም ዝሰኣኑ ወገናት ብስም ህዝብን ብሄራዊ ክልላዊ መንግስቲ ትግራይን ዝተሰምዖ መሪር ሓዘን ብምግላፅ ንስድራ ግዳያት እቲ ሓደጋን ንመላእ ህዝቢ ትግራይን ፅንዓት ይምነ።

ቢሮ ርክብ ህዝብን መንግስትን ክልል ትግራይ
መቐለ:- 08 ሚያዝያ 2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
መላው የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት #በወገኖቻችን ሞት የተሰማንን #ጥልቅ_ሀዘን እየገለፅን ለቤተሰቦች ለወዳጅ ዘመዶች በመላ #መፅናናትን እንመኛለን!!

ነብሳቸውን በገነት ያኑርልን!
@tsegabwolde @tikvahehiopia
መብራት በመጥፋቱ ስብሰባው ተቋረጠ

ዛሬ የሚንስትር መስሪያ ቤታቸውን የ9 ወራት ሪፖርት ለማቅረብ በፓርላማ የተገኙት የባህልና ቱሪዝም ሚንስትር ዶ/ር ሂሩት ካሳው ሪፖርታቸውን ካቀረቡ በኃላ ከፓርላማ አባላት የተለያዩ ጥያቄዎች ቀርቦላቸው ነበር። ሚኒስትሯ ለቀረቡት ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት ሲዘጋጁ ግን የፓርላማው መብራት ድርግም ይላል። በጀነሬተሩ ብቃት የሚታማው የፓርላማው ሠራተኞች ጀነሬተሩን ለማስነሳት ላይ ታች ቢሉም የፓርላማ አባላቱ ሊታገሱ አልቻሉም። የአንዳንድ የፓርላማ አባላትን መውጣት የተመለከቱት አፈ ጉባዔ ታገሰ ጫፎ የፓርላማው ወንበር ባዶ ከመሆኑ በፊት ስብሰባው ከሰዓት በኃላ ይቀጥላል ብለው ወደ ቢሯቸው አምርተዋል።

Via ቁምነገር ሚዲያ/ከኤልያስ መሰረት የፌስቡክ ገፅ/
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ታራሚዎች አመለጡ...

በጋምቤላ ከተማ ማረሚያ ቤት ትላንት በተቀሰቀሰ ብጥብጥ 90 ታራሚዎች ማምለጣቸውን የከተማዋ ከንቲባ አቶ ኮት ሜንታፕ ለጀርመን ራድዮ ተናገሩ። ታራሚዎቹ ያመለጡት በአጥር ዘልለው ነው ብለዋል። በጋምቤላ ማረሚያ ቤት ብጥብጡ የተነሳው ትላንት ረፋድ ላይ በሁለት ታራሚዎች መካከል በተፈጠረ የግል ጠብ ምክንያት መሆኑን ከንቲባ ኮት ሜንታፕ ገልጸዋል። ሁለቱ ታራሚዎች ውኃ በጀሪካን ሲቀዱ መጋጨታቸውን የሚናገሩት አቶ ኮት ጠቡ የብሔር መልክ ከያዘ በኋላ ወደ ብጥብጥ ተቀይሯል ብለዋል።

ግጭቱ በተነሳበት ወቅት ከተማው ላይ ተኩስ ይሰማ እንደነበር አንድ የከተማዋ ነዋሪ ለጀርመን ራድዮ ተናግሯል። ማረሚያ ቤቱን እንደሚያውቀው የገለጸው ይሄው ነዋሪ አመለጡ የተባሉት 90 ሰዎች ከጠቅላላው የማረሚያ ቤቱ ታራሚዎች አንጻር ቁጥሩ ከፍተኛ መሆኑን ጠቁሟል።

ያመለጡትን ታራሚዎች ለማስመለስ እና በቁጥጥር ስር ለማዋል የጸጥታ አካላት የተቀናጀ ዘመቻ መጀመራቸውን የጋምቤላ ከንቲባ አስታውቀዋል። አቶ ኮት ካመለጡት አንዳንዶቹ ወደ ማረሚያ ቤቱ መመለሳቸውን ቢገልጹም ትክክለኛ ቁጥራቸውን ከመግለጽ ተቆጥበዋል። ከንቲባው በትላንትናው የጋምቤላ ማረሚያ ቤት ብጥብጥ «የተጎዳ ሰው የለም» ብለዋል።

Via የጀርመን ራድዮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በአማራ ክልላዊ መንግስት ኦሮሞ ማህበረሰብ ልዩ ዞን ባቲ ወረዳና በአፋር ክልላዊ መንግስት አጎራባች ወረዳዎች በየጊዜዉ የሚከሰቱ ግጭቶችን ለማስቆም የእርቅና የሰላም ኮንፈረንስ እየተካሄደ ነው። የእርቅና የሰላም ኮንፈረሱ እየተካሄደ ያለዉ በአፋር ክልል የሚገኙ 3 ወረዳዎች ማለትም #በአባር#በተለላክና #በጭፍራ ወረዳዎች እንዲሁም በኦሮሚያ ማህበረሰብ ልዩ ዞን ባቲ ወረዳ በሚገኙ ኗሪዎች የሀገር ሽማግሌዎች እና የሀይማኖት አባቶች በተገኙበት ነው። የኮንፈረንሱ አስተባባሪዎች እንደገለጹት በሁለቱ ማህበረሰቦች መካከል በየጊዜው የሚነሱ ግጭቶች መንስኤያቸዉ የግጦሽ መሬት እንደሆነ ተናግረዋል። የእርቅና የሰላም ኮንፈረንሱ በሁለቱ ህዝቦች መካከል የቆየዉን የባህል የቋንቋ እና የማህበረሰብ ግንኙነት ትስስር ወደ ቀድሞዉ ሰላማዊ ግንኙነት ለመመለስ እንደሚያግዝም ገልጸዋል።

Via #ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የስሜን ተራሮች እሳት ጠፍቷል...

ከኬኒያ የመጣችው ሄሊኮፕተርና ከእስራኤል የሰሜን ተራሮች ብሄራዊ ፓርክ የእሳት ቃጠሎ ለማጥፋት የመጣው ቡድን ተልዕኮአቻቸውን ዛሬ ሚያዚያ 08/2011 ዓ.ም ጨርሰው ነገ ወደየሀገራቸው ይመለሳሉ፡፡ ላበረከቱት በጎ አስተዋጽኦ ዛሬ ከቀኑ 10:00 ሰአት ጀምሮ የምስጋና ፕሮግራም በዞኑ አስተዳደር ፡ በደባርቅ ከተማ ባለሀብቶች፡ በቱሪዝም የተሰማሩ አስጎብኚዎች ማህበራትና በፓርክ ጽ/ቤት አዘጋጅነት ይካሄዳል፡፡ እሳቱም ሙሉ በሙሉ መጥፋቱን የሰሜን ጎንደር ዞን አስተዳደር ምክትል አስተዳዳሪ አቶ #ይመር_ስዩም ገልፀዋል። ቃጠሎው ደግም እንዳይነሳም የዞኑ አስተዳደር ከወረዳ አስተዳደር ጋር በቅንጅት በመስራትና ህብረተሰቡን ተጠቃሚ በማድረግ ባለቤት እንዲሆን መስራት እንደሚገባ የዞኑ ነዋሪዎች አሳስበዋል፡፡

Via North Gondar Communication
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ሹመት ሰጥተዋል፡፡ በዚሁም መሰረት፣ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ተባባሪ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ፣ መምህር የሆኑት፣ ዶ/ር ሙሉጌታ ፍስሃ፣ የቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ሆነው ተሹመዋል፡፡ ዶ/ር ሙሉጌታ ፍስሃ፣ ባለስልጣኑን ለስምንት አመታት የመሩትን አቶ ዮናስ ደስታን ይተካሉ፡፡ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ፣ በሥነ-ጥበብና ታሪክ በረዳት ፕሮፌሰርነት ማዕረግ መምህር የሆኑት አቶ አበባው አያሌው፣ የቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለስልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር ሆነው ተሹመዋል፡፡

Via Sheger FM
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በቤንች ማጂ በአለመረጋጋት ተዘግተው የነበሩ መንገዶች ተከፈቱ‼️

በደቡብ ክልል ቤንች ማጂ ዞን በታጠቁ ኃይሎች ለወራት ተዘግተው የነበሩ መንገዶች ዳግም እንዲከፈቱ መደረጉን አንድ ከፍተኛ የአገር መከላከያ ሰራዊት አመራር አስታወቁ። ከባለፈው ዓርብ ጀምሮ የተከፈቱት መንገዶች የማጂን፣ የሱርማን እና የቤሮ ወረዳዎችን እርስ በእርሳቸው እና ከቤንች ማጂ ዞን ዋና ከተማ ሚዛን ተፈሪ ጋር የሚያገናኙ ናቸው ተብሏል።

በመከላከያ ሰራዊት ምዕራብ ዕዝ የዐሥራ ሁለተኛ ክፍለ ጦር ዋና አዛዥ ብርጋዲየር ጄነራል አበበ በየነ ለዶይቼ ቬለ (DW) እንደተናገሩት ሰራዊቱ መንገዶቹን ያስከፈተው ከፌደራል ፖሊስ፣ ከደቡብ ክልል ልዩ ኃይል ጋር ያዋቀረው የዕዝ አመራር (ኮማንድ ፖስት) በወሰደው የማረጋጋት ርምጃ ነው።

በአካባቢው ኮማንድ ፖስቱ ሥራ ከጀመረ ወዲህ አንጻራዊ ሰላም መገኘቱን DW ያነጋገራቸው አንድ የቤንች ማጂ ዞን ቤሮ ወረዳ ነዋሪ ገልጸዋል። ሆኖም በወረዳው “ንጹሃን ዜጎችን የገደሉ እና ንብረት ያቃጠሉ” ያሏቸው ግለሰቦች እስካሁን ለሕግ አለመቅረባቸው ቅር እንዳሰኛቸው ተናግረዋል።

የነዋሪዎቹን ቅሬታ የሚጋሩት ብርጋዲየር ጄነራል አበበ በበኩላቸው ኮማንድ ፖስቱ ቅድሚያ ትኩረት የሰጠው አካባቢውን የማረጋጋት ሥራ መሆኑን ገልጸው በቀጣይ ቀናት ተጠርጣሪ ወንጀለኞችን የመለየት ሥራዎች እንደሚጀመሩ አመልክተዋል።

ካለፈው ዓመት መጨረሻ አንስቶ በደቡብ ክልል በሱርማ፣ በቤሮና፣ በማጂ ወረዳዎች በተከሰተው አለመረጋጋት በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች መሞታቸውን ከአካባቢው አስተዳደር የተገኘው መረጃ ያመለክታል። በአካባቢው ባለው አለመረጋጋት በርካቶች ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለው እንደሚገኙም የአካባቢው አስተዳደር ጠቁሟል።

Via የጀርመን ራድዮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia