TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
212 files
4.11K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
እሁድ የማጠቀለያው ዝግጅት🔝የክብር እንግዶች በተገኙበት #StopHateSpeech #WKU
@tsegabwlde @tikvahethiopia
#WKU እጅግ በጣም እናመሰግናለን፤ ያደረጋቹልን ታሪካዊው የአቀባበል ሁሌም በአባላቶቻችን ዘንድ ሲታወስ ይኖራል። የመጣንበትን አላማ እንዲሰካ ለማድረግ የደከማችሁ ቅን ሰዎች እናመሰግናለን!! መላው የተቋሙን አመራሮች፤ ሰራተኞች እና የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ በጠቅላላ #እናመሰግናለን!! የተማሪዎች ህብረቱ በ3 ቀን የእንመጣለን መልዕክት ዝግጅት አድርጎ በትልቅ ክብር ስለተቀበለን እናመሰግናለን!!

#ፍቅር_አሸንፏል!!
የጥላቻ ንግግር ይቁም!!
የጥላቻ ንግግር ሀገር ያፈርሳል!!

ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ በዚህ ሳምንት🔁 #StopHateSpeech!!

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Breaking

ታላቁና ታሪካዊው የፈረንሳይ ካቴድራል ኖትር ዳም በእሳት እየጋየ ነው። በፓሪስ እምብርት የሚገኘው ይህ ካቴድራል ግንባታው በ1345 ዓ/ም የተጠናቀቀ፣ 128 ሜትር ርዝመትና 69 ሜትር ቁመት ያለው የ4ኛው ክፍለ ዘመን አስደናቂው የፈረንሳይን የጎቲክ ሥነ ሕንፃ ምጥቀት የሚንፀባረቅበት የካቶሊክ ካቴድራል ነው። ኖትር ዳም ማለት እመቤታችን እንደማለት ነው።

ይህ ታሪካዊ ካቴድራል ድንቁ ደራሲ ቪክቶር ሂጎ በ1831 ባሳተመው The Hunchback of Notre Dame ወይም (Notre-Dame de Paris) በሚለው ልብወለድ መፅሃፉ ዝናው ከናኘ በኋላ በአለማችን ከፍተኛ ጎብኚዊች መሳብ የቻለና በአመት 13 ሚሊዮን ቱሪስቶች የሚመለከቱት አስደናቂ ቦታ ሆኗል።

የፈረንሳይ አብዮት ባመጣባቸው ጣጣ የመፍረስና የመዘረፍ ዕጣ እንደደረሰባቸው አብዛኞቹ የፈረንሳይ ካቴድራሎች ኖትር ዳምም የተጎዳ ቢሆን፤ ከአብዮት በኋላ ወደ ስልጣን የመጣው ናፖሊዮን ቦናፓርት ካቴድራሉን ከታደጉት የሃገሪቱ መሪዎች በግንባር ቀደምትነት ተጠቃሽ ነው።

ኖትር ዳም የፓሪስ ሃገረ ስብከት መንበር (Archdiocese) በመሆኑ የከተማይቱ ሊቀ ጳጳስ ሚሼል ኦፐቲ መቀመጫም ነው። ይህ ታሪካዊ ገዳም በእድሳት ላይ በሚገኝበት በአሁኑ ወቅት በደረሰ የእሳት አደጋ በሚያሳዝን ሁኔታ በመውደም ላይ ይገኛል። እስካሁን የአደጋው መንስዔ በትክክል አልታወቀም።

Via Petros Ashenafi Kebede
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከጎንደር...

"የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ማርኬቲንግ ማኔጅመንት ተማሪዎችና መምህራን በቀን 04/08/11 የአእምሮ ውስንነት ያለባቸውንና ጧሪ የሌላቸውነ አዛውነቶ በመጎብኘት የቁሳቁስ እርዳታ አድርገዋል።"

@tsegabwolde @tikvahethiopia