TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update ከአዲስ አበባ ወደ ናይሮቢ ሲጓዝ የተከሰከሰው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላን ሟቾች የመታሰቢያ ሥነ ሥርዓት ነገ እሁድ መጋቢት 8 ቀን 2011 ዓ.ም እንደሚካሄድ የኢትዮያ አየር መንገድ አስታወቀ።

Via etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
AAU🔝

"ሐሰተኘ ዜና: ለኢትዮጵያ ስጋት?" በሚል ርዕስ BBC እና AAU የጋዜጠኝነትና ኮሚዩኒኬሽን ትምህርት ክፍል ያዘጋጁት የፓናል ውይይት በFBE ግቢ እሸቱ ጮሌ አዳራሽ ተካሂዷል። በውይይቱም የAPው ጋዜጠኛ #ኤልያስ_መሠረትን ጨምሮ የጋዜጠኝነት መምህራን እና በርካታ ተማሪዎች ተሳትፈውበታል።

Via ሠለሞን ከበደ (AAU)
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ኒውዚላንድ🔝

በኒውዚላንድ #ክሪስትቸርች ከተማ ሁለት መስጊዶች ላይ ጥቃት በመፈፀም 49 #ሰላማዊ ዜጎችን ህይዎት በማጥፋት ከተጠረጠሩ ግለሰቦች ውስጥ አንደኛው በዛሬው ዕለት ፍርድ ቤት ቀርቧል።

ድርጊቱን የፈፀመው ተጠርጣሪ ብሬንቶን ታራንት የሚባል ሲሆን፥ በዜግነትም አውስትራሊያዊ መሆኑ ነው የተገለፀው።

የ28 ዓመቱ ብሬንቶን ታራንት በዛሬው ዕለት ፍርድ ቤት የቀረበውም በነፍስ ግድያ ወንጀል ተጠርጥሮ ነው ተብሏል።

ፅንፈኛ #ቀኝ_ዘመም_አሸባሪ የተባለው ተጠርጣሪ #ብሬንቶን_ታራንት ፍርድ ቤቱ ያቀረበበትን ክስ በዝምታና በአርምሞ አድምጧል ነው የተባለው ።

ፍርድ ቤቱ የተጠርጣሪውን የይግባኝ መብት በመከልከል ጉዳዩን በድጋሜ ለመመልከት ለፊታችን ሚያዝያ 5 ቀጠሮ ይዟል።

በሽብር ጥቃቱ የተጠረጠሩ ሁለት ተጨማሪ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር የዋሉ ሲሆን ፥ ሁለቱም ከዚህ በፊት በምን አይነት የወንጀል ተጠርጥረው  ፍርድ ቤት ቀርበው የማያውቁ መሆኑ ተገልጿል።

የኒውዚላንድ ጠቅላይ ሚኒስትር #ጃሲንዳ አርደርን ድርጊቱን የሽብር ጥቃት በማለት ያወገዙ ሲሆን፥ በጥቃቱ የተጎዱ ዜጎችን ማንነት  የመለየት ስራ እየተሰራ መሆኑን አስታውቀዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተጠርጣሪዎች  ድርጊቱን ለመፈፀም የተጠቀሙበት #መሳሪያ ዘመናዊና የተሻሻለ መሆኑን በመጥቀስ፥ የፀጥታ አካላት ባደረጉት #እርብርብ በፍጥነት በቁጥጥር ስር በማዋል የሚደርሰውን እልቂት ለመታደግ ተችሏል ብለዋል።

ምንጭ፦ ቢቢሲ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
60,000 ብርእስከ ጥዋቱ 4 ሰዓት ድረስ ብቻ በTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት በኩል የተሰባሰበው ገንዘብ ከ60,000 ብር አልፏል! አሁንም ምን ያህል እንደደረስን በየሰዓቱ እየተከታተልኩ አሳውቃችኃለሁ!

Account number(CBE): 1000277462439

@tsegabwolde @tikvahethiopia
መንግሥት ለተፈናቀሉ የጌዴኦ ማህበረሰብ አባላት እያደረገ ያለዉን እርዳታ አስመልክቶ ከጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት የተሰጠ ዝርዝር መግለጫ፦

@tsegabwolde @tikvahethiopia
በሻሸመኔ አሰቃቂ ግድያ ሊመሰክር የነበረው ሰው ደብዛው ጠፍቷል‼️
.
.
ሻሸመኔ ላይ ሰው #ገድለው በመስቀል በአስከፊ ግድያ ወንጀል የተከሰሱ ወጣቶች ላይ ሊመሰክር የነበረው ሰው #ደብዛው_ጠፍቶብኛል ሲል የኦሮሚያ ክልል ፍትህ ቢሮ አስታወቀ።

#በሻሸመኔ_ከተማ ነሐሴ ስድስት ቀን 2010 ዓ.ም አንድን ወጣት #ቦንብ ይዟል በሚል ገድለው የዘቅዝቁ ወጣቶች መኖራቸው ይታወሳል። በዚህ በአሰቃቂ ግድያ ወንጀል ከተከሰሱ ስድስት ሰዎች መካከል ሁለቱ የዕድሜ ልክ እስራት እንደተፈረደባቸው እና የተቀሩት አራት ተጠርጣሪዎቸ ደግሞ ምስክሩ ደብዛው በመጥፋቱ በነጻ መለቀቃቸውን የኦሮሚያ ክልል ፍትህ ቢሮ ምክትል አቃቢ ህግ አቶ #አሽማው_ሰይፉ ገልጸዋል። ተከሳሾች የምስክሩን ደብዛ አጥፍተዋል የሚል ግምት እንዳለ የገለጹት አቶ አሽማው፤ ምስክሩ ባስመዘገበው ስልክ ቁጥርም ሆነ በአድራሻው ተፈልጎ እስከአሁን ሊገኝ አለመቻሉን ተናግረዋል።

በተለያዩ #ማህበራዊ_ሚዲያዎች ጨመሮ በግለሶችና በተቋማት የሚገኙ የምስል እና ድምጽ ማስረጃዎች እንደምስክርነት ለምን ጥቅም ላይ አልዋሉም የሚል ጥያቄ ከአዲስ ዘመን የቀረበላቸው አቶ አሽማው፤ የምስልና ድምጽ #ማስረጃዎቹ ከፖሊስና ከተለያዩ አካላት ለፍርድ ቤቱ መቅረባቸውን ተናግረዋል። ይሁንና ዘመኑ የቴክኖሎጂ በመሆኑ #ቅንብረ የተደረገበት ስለመሆኑ እና ስላለመሆኑ ማረጋገጫ ባለማግኘቱ ማስረጃው ፍርድቤቱን ሊያሳምን አልቻለም።

እንደ አቶ አሽማው ከሆነ፤ አራቱ ተከሳሾች በነጻ ቢለቀቁም የሰው ምስክሩ በተገኘ ሰዓት ክሱ መጀመሩ አይቀርም። በፍርድ ሂደቱ ላይ የአራቱ ሰዎቸ በነጻ መለቀቅ በአቃቤ ህግ በኩል ተቀባይነት ባለማግኘቱ ይግባኝ ተጠይቄ ውሳኔ እየተጠበቀ ይገኛል ብለዋል።

ምንጭ፦ አዲስ ዘመን(የኦሮሚያ ክልል ፍትህ ቢሮ)
@tsegabwolde @tikvahethiopia
76,939 ብር---TIKVAH-ETHIOPIA

Account number(CBE): 1000277462439

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የሚኒስትሮች ም/ቤት በተንቀሳቃሽ ንብረት ያለ የዋስትና መብት ረቂቅ አዋጅን ተመልክቶ ማሻሻያ በማድረግ ይፀድቅ ዘንድ ለህዝብ ተወካዮች ም/ቤት እንዲተላለፍ ወስኗል።


@tsegabwolde @tikvahethiopia
Sumsung
Curved
uHD TV 4K 7 series
European standard
Price 37,000
On hand

Phone no=0910208090
ጥንቃቄ..ጥንቃቄ..ጥንቃቄ!
/ውብሸት ታዬ/

ከቀናት በፊት ኡራኤል አቅራቢያ በካሰንስ ሕንጻና ኤቢ ዞን ሕንፃ በግንባታ ላይ ከነበረ ህንጻ አምስተኛ ፎቅ ላይ በሥራ ላይ የነበረ አንድ ወጣት #ወድቆ ሕይወቱ አልፏል። ከወራት በፊት አንዲት በቀን ሥራ ላይ የነበረች ወጣት በተመሳሳይ ሁኔታ ሕይወቷ እንዳለፈ ጓደኞቿ በሐዘን ገልጸዋል። ለአደጋው መንስኤ የሆነው ሕንጻው(በምስሉ ላይ እንደምታዩት) ምንም መከለያ የሌለው በመሆኑ እንደሆነ መመልከት ይቻላል።
የዕለት ጉርሳቸውን ለመሸፈን በሚባትሉ ኩሩ ዜጎቻችን ላይ የዚህ አይነት አሰቃቂ አደጋ በተደጋጋሚ እየደረሰ ቢሆንም አስገዳጅ በሆነ ሁኔታ በግንባታ ላይ ያሉ ሕንጻዎች ለሠራተኞቻቸው ደህንነት ጥበቃ ስለማያደርጉ ችግሩ እየተባባሰ ሄዷል።

Via ውብሸት ታዬ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
86,660 ብር ደርሰናል!

ምዕራፍ አንድ በ24 ሰዓት ውስጥ ሊጠናቀቅ ነው! 13,340 ብር ብቻ ይቅረናል(100,000 ብር)። የብሩን ማጠን ሳይሆን #አብሮነታችንን ማስመስከራችን ለቀጣይ ጉዟችን ትልቅ አቅም ይሆነናል። የዛሬው ህብረታችን ነገም ሌሎች ወገኖቻችን ለማገዝ ትልቅ አቅም ይፈጥርልናል።

#ኦሮሚያ #ሀረሪ #ደቡብ #ትግራይ #ሱማሌ #አፋር #ቤንሻንጉል #ጋምቤላ #አማራ #አዲስ_አበባ_ከተማ_አስተዳደር #ድሬዳዋ_ከተማ_አስተዳደር የምትገኙ የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት ትልቅ ክብር አለን!

Account number(CBE): 1000277462439

@tsegabwolde @tikvaethiopia