ጥንቃቄ..ጥንቃቄ..ጥንቃቄ!
/ውብሸት ታዬ/
ከቀናት በፊት ኡራኤል አቅራቢያ በካሰንስ ሕንጻና ኤቢ ዞን ሕንፃ በግንባታ ላይ ከነበረ ህንጻ አምስተኛ ፎቅ ላይ በሥራ ላይ የነበረ አንድ ወጣት #ወድቆ ሕይወቱ አልፏል። ከወራት በፊት አንዲት በቀን ሥራ ላይ የነበረች ወጣት በተመሳሳይ ሁኔታ ሕይወቷ እንዳለፈ ጓደኞቿ በሐዘን ገልጸዋል። ለአደጋው መንስኤ የሆነው ሕንጻው(በምስሉ ላይ እንደምታዩት) ምንም መከለያ የሌለው በመሆኑ እንደሆነ መመልከት ይቻላል።
የዕለት ጉርሳቸውን ለመሸፈን በሚባትሉ ኩሩ ዜጎቻችን ላይ የዚህ አይነት አሰቃቂ አደጋ በተደጋጋሚ እየደረሰ ቢሆንም አስገዳጅ በሆነ ሁኔታ በግንባታ ላይ ያሉ ሕንጻዎች ለሠራተኞቻቸው ደህንነት ጥበቃ ስለማያደርጉ ችግሩ እየተባባሰ ሄዷል።
Via ውብሸት ታዬ
@tsegabwolde @tikvahethiopia