TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
33,343 ብር----የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት በከፍተኛ ችግር ውስጥ ናቸው ለተባሉት #ለጌዴኦ_ተፈናቃዮች ዜጎቻችን በ18 ሰዓት ውስጥ የተሰባሰበ!

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ክብርት የሰላም ሚኒስትር ወይዘሮ ሙፈርያት ከሚል ከደቂቃዎች በኃላ በጌዴኦ ተፈናቃዮች ዙሪያ ጋዜጣዊ መግለጫ ይሰጣሉ። ከቦታው የሚደርሰንን መረጃ ወደእናተ እናደርሳለን!

@tsegabwolde @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ሱሉልታ‼️

የሱሉልታ ከንቲባ ወ/ሮ ሮዛ ዑመር ፤ \\"በሰባት ቀን ይፈርሳል አላልንም!\\" ብለዋል።

ከንቲባዋ አያይዘዉም፦ "በ7 ቀናት ማስረጃ አቅርቡ አልን እንጂ ይፈርሳል አልልንም " ማለታቸውን ሸገር ዘግቧል።

አክለውም፦ "ጊዜ ወስደን፣ ከሕዝቡ ጋር ተነጋግረን፣ ተግባብተን ነው የምናደርገውም። ...አሁን ገና የማጣራት ሥራ ላይ ነን ያለነው። ይፈርሳል የተባለ ነገር የለም" ብለዋል።

Via Shegr FM 102.1
©Getu
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የአክሱም ዩኒቨርሲቲ የጨርቃጨርቅና አልባሳት ምህንድስና ትምህርት ክፍል ሊከፍት መሆኑን አስታውቋል። በአድዋ ከተማ በ60 ሚሊዮን ብር እየተገነባ የሚገኘው የትምህርት ክፍሉ ህንጻ በመጪው ሰኔ ወር መጨረሻ ሙሉ በሙሉ እንደሚጠናቀቅ ተገልጿል።

Via ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አስራ አንዱ ገፆች--የሳሚ ዳን አዲስ አልበም በቅርቡ!
#update የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጅዳ በሚገኘው ቆንስላ ጽ/ቤት በኩል ከሳኡዲ አረቢያ መንግስትና ከዓለም አቀፉ የፍልሰተኞች ድርጅት ጋር በመረተባበር በትላንትናው እለት መጋቢት 6 ቀን 2011 ዓ.ም ያለመኖሪያ ፈቃድ ይኖሩ የነበሩ 450 ኢትዮጵያዊያንን በራሳቸው ፈቃድ ከሳኡዲ አረቢያ እንዲመለሱ አድርጓል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
Audio
#update ባለፈው ማክሰኞ በድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት የተካሄደውን የአመራር ለውጥ #እንደማይቀበለው የጉርጉራ ጎሳ ጋዜጣዊ ጉባዔ አስታወቀ፡፡ የጉባዔው ልዩ ፀሐፊ አቶ ጀማል ዑመር በተለይ ለቪኦኤ እንዳስታወቁት ጋዜጣዊው ጉባዔ ባወጣው መግለጫ ሹም ሽረቱ የአንድ ጎሳን የበላይነት ያንፀባረቀ ነው ብለዋል፡፡

Via VOA 24
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ፖላንድ

በህገ ወጥ መንገድ ስራ እናስቀጥራችኋለን በሚሉ ደላሎች ተታለው ወደ ፖላንድ ያቀኑ ኢዮጵያውያን ለከፋ ችግር መዳረጋቸው ተገለፀ።

ከጊዜ ወደ ጊዜ ህጋዊ ባልሆነና ትክክለኛ መረጃ ሳይዙ ወደ ተለያዩ ሀገራት ለስራ ፍለጋ ጉዞ የሚያደርጉ ኢትዮጵያዊያን ቁጥር #እየተበራከተ መምጣቱን መረጃዎች ያመላክታሉ።

የእነዚህ ዜጎች የጉዞ መነሻ ምክንያትም ነፃ የትምህርት እድል ለማግኘት አሊያም ዳጎስ ያለ ክፍያ የሚያስገኝ የስራ ዕድል ታገኛላቹህ በሚሉ ህገ ወጥ ድላሎች እና ድርጅቶች በመታለል ነው።

በአሁኑ ወቅት በብዛት በዚህ የህግ ወጥ ደላሎች ወጥመድ ገብተው ከሚጓዙት መካከል ወደ ቻይና የሚጓዙ ኢትዮጵያን ተጠቃሽ ሲሆኑ፥ ከቅርብ ወራት ወዲህ ደግሞ ወደ ፖላንድ የሚጓዙ ኢትዮጵያዊያን ቁጥር እያሻቀበ ነው።

ፖላንድ የሚገኘው የኢትዮዽያ እና ፖላንድ ማህበር ሰላም ሊቀመንበር መርሻ ወልዱ ለfbc እንደተናገሩት፥ ኢትዮጵያዊያኑ ፖላንድ ውስጥ ትልቅ ክፍያ የሚያስገኝ ስራ ትቀጠራላቹ በሚል እየተታለሉ ለከባድ ችግር እየተዳረጉ ነው ብለዋል።

ኢትዮጵያዊያን ዜጎቻችን ዋርሶ ውስጥ የተሻለ ስራ ታገኛላቹ ተብለው መጥተው ያሰቡት ሳይሆን ቀርቶ ለእንግልት እየተዳረጉ ነው ያሉት ሃላፊው፥ ይህም እንደ ማህበረሰብ ሆነ እንደ አንድ ኢትዮጵያዊ የሚያስጨንቅ እና የሚያሳስብ ጉዳይ ነው ነው ይላሉ።

አቶ መርሻ ወደ ፖላንድ ጉዞ ማድረግ የሚፈልጉ ዜጎች በአሁኑ ወቅት ፖላንድ በስደተኞች እና ፍልሰተኞች እንዲሁም በህገ ወጥ ኗሪዎች ላይ ጠንካራ ህግ የምትከተል መሆኗን ማወቅ እንደሚገባቸውም ጠቁመዋል።

የዋርሶ ቀኝ አክራሪ ፖለቲከኞች አባል የሆኑበትን የአውሮፓ ህብረት የስደተኞች ጉዳይ ፖሊሲ ሳይቀር እየተቃወሙ ስደተኞችን በኮታ የመቀበልን ጥያቄ ውድቅ እያደረጉ ናቸው ብለዋል።

አቶ መርሻ ፖላንድ አሁን ላይ ጥገኝነት ጠያቂዎችን በሀገሯ ከማስትናገድ ይልቅ ወደ መጡበት ሀገር በመመለስ በሀገራቸው መንግስት ጋር የማቋቋም ስራ ነው እየሰራች ያለቸው ብለዋል።

በድርጅቶች እና በግለሰቦች ቅስቅሳ እየተገፋፉ ከ8 ሺህ ዶላር እስክ 300 ሺ ብር የሚከፍሉ ወገኖቻቸን አካሄዳቸውን ቆም ብለው ሊያጤኑት ይገባልም ነው ያሉት።

ከተሰጡት ሃላፊነቶች መካከል አንዱ የዜጋ ዲፕሎማሲን ማካሄድ የሆነው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፥ ይህን ጉዳይ እንዴት ያየዋል በሚል ላቀረብንላቸው ጥያቄ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አቶ ነብያት በአሁኑ ወቅት በውጭ ሀገራት ለሚገኙ ዜጎች ደህንነት ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ መሆኑን ተናገረዋል።

ቃል አቀባይ ነብያት መንግስት ይህን መሰል ድርጊት ለመከላከል ልዩ ትኩረት ሰጥቶ ከኤምባሲዎች ጋር እየሰራ ነው ያሉ ሲሆን፥ ዜጎች በራሳቸው ሊወስዱት የሚገባ ሃላፊነት እንዳለም አንስተዋል።

የስራ እድል ተገኝቷልና ነጻ የትምህርት እድል አግኝታቹሃል ሲባሉ እንቅስቃሴ ውስጥ ከመግባት አስቅድመው ስለ መረጃው ትክክለኛነት ከሚመለከታቸው ተቋማት ማረጋገጫ ማግኘት እንዳለባቸውም አሳስበዋል።

ቃል አቀባዩ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በውጭ ሀገራት ችግር እያጋጠማቸው ያሉ ዜጎችን ወደ ሀገር ቤት ከመመለስ ባለፈ፥ ለዚህ ችግር የዳረጋቸውን መነሻ ክፍተት ለመድፈን ከባለድርሻ አካላት ጋር እየሰራ ነው ብለዋል።

ምንጭ፦ FBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ዕሁድ ዐለት የተከሰከሰው የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን እክል የገጠመው ገና ከመነሳቱ እንደነበር ኒው ዮርክ ታይምስ ከበረራ መቆጣጠሪያ ክፍል ያገኘውን አዲስ መረጃ ጠቅሶ አስነብቧል፡፡ አውሮፕላኑ ገና በ3ኛው ደቂቃ ባልተለመደ ፍጥነት በመብረሩ ካፒቴኑ በጭንቀት ድምጸት ተመልሶ እንዲያርፍ ጠይቋል፡፡ ከካፕቴኑ ጥያቄ በፊትም የበረራ መቆጣጠሪያ ባለሙያዎች አውሮፕላኑ ወደ ላይ ሲወጣና ሲወርድ እክል እንደገጠመው ተረድተው ነበር፡፡ ካፕቴን ያሬድ ጌታቸው ከበረራ ተቆጣጣሪ ባለሙያዎች ጋር ያደረጋቸው የቃላት ልውውጦች በረራ ክፍሉ ውስጥ ምን እንደተፈጠረ ከፍተኛ ጠቀሜታ ያለው መረጃ ይሰጣሉ ተብሏል፡፡

Via ኒው ዮርክ ታይምስ(በዋዜማ)
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የሰላም ሚኒስቴር ከተፈናቃዮች ጋር በተያያዘና በሌሎች ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ በተሰጠው መግለጫ የተነሱ አንኳር ነጥቦች፦

• ተፈናቃዮች ከጌዲዮ ብቻ ሳይሆን ከምእራብና ምስራቅ ጉጂም የተፈናቀሉ ዜጎች ነበሩ፡፡ ዜጎቹን ወደ ቀያቸው በጊዜያዊነት ለመመለስ ከእርዳታ ድርጅቶች ጋር በመተባበር ተሰርቷል፡፡

• ለተረጂዎች የሚደርሰው የሰብአዊ እርዳታ እስካሁንም ያልተቋረጠና በቀጣይም የሚቀጥል ነው

• ከምስራቅ ጉጂ የተፈናቀሉ 13 ሺህ ገደማ የሚሆኑ ዜጎች ብቻ ሲቀሩ ከምእራብ ጉጂ የተፈናቀሉት በሙሉ ወደ ቀያቸው ተመልሰዋል፡፡

• ተፈናቃዮችን በቋሚነት የማቋቋም ስራ ለመስራት 3 አካላት ሀላፊነቱን ወስደዋል፡፡ እነሱም፡- የኦሮሚያ ክልል መንግስት፣ የደቡብ ክልል መንግስትና የፌደራል መንግስት ናቸው፡፡

• ተፈናቃዮች በቋሚነት እስኪቋቋሙ ባሉበት ሆነው ሲረዱ ቆይተዋል፡፡

• ትናንት በነበረው ውይይት ከተፈናቃዮች ጋር ለ8 ወራት እርዳታ አላገኘንም የተባለው ትክክል አለመሆኑን ተግባብተናል፡፡

• ሚድያዎችም ሲዘግቡ በዚህ መንገድ የዘገቡት ትክክል አይደለም።

• በመሀል በአካባቢው የፀጥታ ችግር ስላለ የተደራጁ ቡድኖች እርዳታውን የመቀማትና ለራስ ጥቅም የማዋል ችግሮች ነበሩ።

• በአመራር ችግር ምክንያት መድረስ ያለበት መጠን ሳይደርስ የቀረበት ሁኔታዎች ነበሩ።

Via etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
404,659$-----በግሎባል አልያንስ በኩል በውጭ የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ለጌዴኦ ተፈናቃዮች በአንድ ቀን ውስጥ 404,659$ ድጋፍ አድርገዋል!

Via አርቲስት #ታማኝ_በየነ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ከሶማሌ ክልል ተፈናቅለው በኦሮሚያ ክልል ቢሻን ጉራቻ የሚገኙ ተፈናቃዮች ያሉበት ሁኔታ...

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በ2 ነጥብ 4 ቢሊየን ብር ወጪ የሚገነባው የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዋና መስሪያ ቤት ግንባታ ተጀምሯል። ህንፃው ከመሬት ሥር የሚገነቡትን ወለሎች ጨምሮ 38 ፎቅ እንደሚኖረው የተገለጸ ሲሆን፥ 47 ሺህ 881 ሜትር ስኩዌር መሬት ላይ እንደሚርፍም ነው የተገለጸው።

Via ena
@tsegabwolde @tikvahethiopia