TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.95K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update ጠ/ሚር ዐቢይ አሕመድ አዲስ ለተቋቋመው የብሔራዊ ዕርቀ ሰላም ኮሚሽን አባላት በተዘጋጀ የመተዋወቂያ መድረክ ላይ አባላቱ ዘላቂ ሀገራዊ ትስስርን ለማሳደግ መስራት
እንዳለባቸው ተናግረው ለሌላ ሀገራት ተምሳሌት ሊሆን የሚችል ሥርዓት እንዲፈጥሩ አበረታተዋል። ኮሚሽኑ የተጣለበትን ኃላፊነት ለመወጣት #ከሰላም_ሚኒስቴር ጋር በቅርበት
ይሰራል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በአማራ ክልል በማዕከላዊና ምዕራብ ጎንደር ዞኖች የግጭት #ተፈናቃዮች መንግሥት አስቸኳይ የምግብ ዕርዳታ አላቀረበልንም፤ ለተላላፊ በሽታም ተጋልጠናል ማለታቸውን የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ዘግቧል፡፡ ከሁለቱ ዞኖች ወደ 46 ሺህ የሚጠጋ ሕዝብ ተፈናቅሏል፡፡ ከእነዚህ ውስጥ እስካሁን ዕርዳታ የደረሳቸው 2 ሺህ 700 ብቻ ናቸው፡፡ ተፈናቃዮቹ በላይ አርማጭሆና ምዕራብ ደንቢያ ወረዳዎች ባሉ ቀበሌዎች ተጠልለዋል፡፡ የማዕከላዊ ጎንደር ዞን አደጋ መከላከል ምግብና ዋስትና ቢሮ 2 ሺህ 500 ኩንታል ስንዴና 3 ሺህ ኩንታል አልሚ ምግብ አሰራጭቻለሁ ብሏል፡፡ ከዞኑ 200፣ ከፌደራል ደሞ 600 ተጨማሪ ኩንታል እህል እየተጓጓዘ ነው፡፡

Via EPA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከአዲስ አበባ🔝

"ዛሬ #የኢትዮጵያ_ቀይ_መስቀል አዲስ አበባ ቅርንጫፍ የገንዘብ ማሰባሰቢያ እና የ6546 SMS ድጋፍ መቀበያ ስራ ለመስራት ጋዜጣዊ መግለጫ በኢትዮጵያ ሆቴል ሰጥቷል። በተጨማሪ ኢትዮ ቴሌኮም በትላንትናው ዕለት ለአዲስ አበባ ቀይ መስቀል የአምቡላንስ ድጋፍ አድርጓል። በጣም ነው ደስ ያለን! ለሌሎችም ትምህርት ይሆናል! እስኬ ከአዲስ አበባ"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ብርጋዴር ጄኔራል #ተፈራ_ማሞ የአማራ ክልል ልዩ ሀይል አዛዠ ሆነው ተሾሙ። ብርጋዴር ጄኔራል ተፈራ በመፈንቅለ መንግስት ሙከራ ተከሰው ዕድሜ ልክ ተፈርዶባቸው አስር አመት በማረሚያ ቤት ከቆዩ በኅላ ከወራት በፊት #መፈታትቸው ይታወሳል።

via ELU
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የአፋርና ሱማሌ ክልሎች 30 ዘመናዊ ተሽከርካሪዎችን ከጀርመን መንግስት እና የተባበሩት መንግስታት ዓለም አቀፍ የህጻናት አድን ድርጅት /ዩኒሴፍ/ ተረክበዋል፡፡ ተሽከርካሪዎቹ በሱማሌና በአፋር ክልሎች ጤና ቢሮዎች ለሚከናወኑ #ተንቀሳቃሽ የህክምና እና የምገባ ኘሮግራም አገልግሎት እንደሚውሉ ተገልጿል፡፡

Via etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ፎቶ፦ ድምፃዊ #ዳዲ_ገላን #BBC
ዳዲ #በጥይት_ተመቶ ህይወቱ አለፈ‼️
.
.
ፖለቲካዊ ይዘት ያላቸውን ሙዚቃዎችን በመጫወት የሚታወቀውና በዘፈኖቹ በተደጋጋሚ ለእስር ተዳርጎ የነበረው የኦሮምኛ ዘፋኝ #ዳዲ_ገላን ሰኞ እለት ሙዚቃዎቹን ባቀረበበት መድረክ በጥይት #ተመትቶ ሞቷል።

በምስራቅ ሸዋ በቢሾፍቱ አቅራቢያ በምትገኘው የሊበን ዝቋላ ወረዳዋ ትንሿ የገጠር ከተማ አሹፌ ካለፈው ቅዳሜ እስከ ሰኞ ምሽት ደስታና ጭፈራ ነበር። ይጨፈር የነበረው ለአንድ ሆቴል ምርቃት ነበር። ደስታና ጭፈራው ግን አልዘለቀም።

የምርቃቱ ታዳሚዎች በደስታ ጥይት ወደላይ ይተኩሱ ነበር። የመድረኩ ፈርጥ የነበረው ታዋቂው ኦሮምኛ ዘፋኝ ዳዲ ገላን ድንገት በጥይት ተመትቶ እንደወደቀ የሆቴል ምርቃቱ የሙዚቃ ድግስ መድረክ አስተባባሪ የነበረው ጓደኛው አቶ ቱፋ ወዳጆ ይናገራል።

"ለቅሶም ላይም ይተኮሳል። ልጅም፣ አባትም ክላሽ መታጠቅ ባህል ነው። በወቅቱ እየተተኮሰ እያለ ማን እንደሆነ አይታወቅም ከመሀል ልቡን መትቶት ወደቀ" በማለት ይገልፃል።

በህግ የተከለከለ ቢሆንም በተለያዩ የአገሪቱ አካባቢዎች ለሰርግ፣ ለሃዘን፣ ለልደትና ለሌሎችም መሰል አጋጣሚዎች ጥይት መተኮስ የተለመደ ነው ማለት ይቻላል።

በሃይማኖት አባቶችና በገዳዎች ምክር ጭምር ጥይት መተኮስ ቀርቶ የነበረ ቢሆንም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እንደ አዲስ እንደተጀመረ ዘፋኙ ህይወቱን ያጣበት የሊበን ዝቋላ ወረዳ ፖሊስ ፅፈት ቤት ሃላፊ ምክትል ኢንስፔክተር #ግርማ_ሚደቅሳ ለቢቢሲ ገልፀዋል።

ከ2009 ዓ.ም የለውጡን እንቅስቃሴ ተከትሎ በተለያዩ በዓላትና አከባበሮች ላይ ደስታንም ሆነ ኃዘንን ለመግለፅ መተኮስ እንደተጀመረ ኢንስፔክተር ግርማ በተጨማሪ ገልፀዋል።

ባለፈው አመትም አቅራቢያው በሚገኝ ሌላ አካባቢ አንድ ወጣት የደስደስ ጥይት ሲተኩስ ጓደኛውን በመግደሉ መልሶ ራሱን እንዳጠፋ ኢንስፔክተር ግርማ ያስታውሳሉ።

ኦሮምኛ ሙዚቃዎችን የሚጫወተው ዳዲ አስከሬን ለምርመራ ተልኮ ከነበረበት ጳውሎስ ሆስፒታል ዛሬ ከሰዓት በኋላ የትውልድ ቀዬው አሹፌ መድረሱን ኢንስፔክተሩ ገልፀዋል።

ምንጭ፦ BBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia