TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update ቡራዩ⬆️

የቡራዩ ከተማ አስተዳደር ከነዋሪዎቹ ጋር #የሰላም እና #የልማት ዉይይት እያካሄደ ነዉ። ከቀናት በፊት በከተማዋ ተከስቶ የነበረዉን #አለመረጋጋት ወደ ነበረበት ሰላም ለመመለስ ከአገር የሽማግሌዎች፤ ወጣቶች ከተለያዩ አደረጃጀቶች ከተወከሉ ነዋሪዎች ጋር በዘላቂ ሰላም ማስጠበቅ ዙሪያ ምክክር እየተካሄደ ነዉ። የከተማዋ ከንቲባ አቶ #ሰለሞን_ፈየ የህግ የበላይነት እንዲረጋገጥ እና የዜጎች ተዘዋዉሮ መስራት እና መኖር መብት እንዲከበር ከህብረተሰቡ ጋር በጋራ እንሰራለን ብለዋል።

©etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ህፃን በፀሎት ብርሃኑ‼️

አሰቃቂ ወንጀል በሚፈጽሙ ግለሰቦች ላይ ቀደም ሲል የሚሰጠው የፍርድ ውሳኔ ተመጣጣኝ ባለመሆኑ በርካቶች ሌላ የወንጀል ድርጊት እንዲፈጽሙ እያደረገ ነው  ሲሉ የደሴ ከተማ ነዋሪዎች ቅሬታቸውን ገለጹ፡፡

በርካታ ቁጥር ያላቸው የደሴ ከተማዋ ነዋሪዎች የሰባት ዓመት ህጻን በአሰቃቂ ሁኔታ #የገደለው ግለሰብ የማያዳግምና ሌላውን ሊያስተምር የሚችል #እርምጃ እንዲወሰድበትም ትላንት በአደባባይ ጠይቀዋል፡፡

የሟች ህጻን በጸሎት ብርሃኑ እናት ወይዘሮ አበባ ሙህዬ ልጃቸው ባለፈው ጥቅምት 24 ቀን 2011 ዓ.ም ለጨዋታ እንደወጣች ሳትመለስ መቅረቷን ይናገራሉ፡፡

በልጃቸው ያልተለመደ መዘግየትና ወጥቶ መቀረት የተደናገጡት እናት ከአካባቢው ሰዎች ጋር በመሆን ፍለጋ ቢያካሂዱም ህጻኗ ሳትገኝ ቀርታለች፡፡

ጥቅምት 27 ቀን 2011 ዓ.ም ህጻኗ በአሰቃቂ ሁኔታ ተገድላ አስክሬኗ መገኘቱን የገለጹት ወይዘሮ አበባ በጥርጣሬ ከተያዙት ግለሰቦች ከአንዱ ጋር በትዳር አብረው የቆዩ መሆናቸውንና አንድ ልጅ ከወለዱለት በኋላ መፋታታቸውን ተናግረዋል።

ፍቺውን ተከትሎ ግለሰቡ ለመግደል በተደጋጋሚ ሲዝትባቸው መቆየቱን ነው የጠቆሙት፡፡

ህጻኗ በአሰቃቂ ሁኔታ ተገድላ አስክሬኗ መገኘቱ እንደተሰማ ትላንት በደሴ ከተማ #አለመረጋጋት ተፈጥሮ የነበረ ሲሆን በርካታ የኅብረተሰብ ክፍሎችም ወንጀሉን በፈጸመው ሰው ላይ የማያዳግምና ሌላውን ሊያስተምር የሚችል ርምጃ እንዲወሰድ ጠይቀዋል፡፡

የደሴ ከተማ አስተዳደርና ጸጥታ መምሪያ ኃላፊ አቶ ወንደሰን ጸጋዬ በበኩላቸው ድርጊቱ አሳዛኝ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡

የህጻኗ አስከሬን ከትናንት በስቲያ በምትኖርበት አካባቢ ከሚገኝ ጫካ በጆንያ ውስጥ #ተጠቅልሎ መገኘቱን ተከትሎ ፖሊስ ባደረገው ክትትል ከጉዳዩ ጋር ግንኙት ይኖራቸዋል የተባሉ ሦስት ሰዎችን ፖሊስ በቁጥጥር ስር ማዋሉን ገልጸዋል፡፡

🔹ዛሬ በደሴ ከተማ ተፈጥሮ የነበረው ውጥረት መረጋጋቱን ለመስማት ተችሏል።

ምንጭ፦ የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ደብረ ታቦር‼️

በደቡብ ጎንደር መስተዳድር ዞን የደብረ ታቦር ማረሚያ ቤት ትላንት ከቀኑ 11፡00 አካባቢ #አለመረጋጋት ተከስቶ ነበር።

ከቀኑ 11፡00 አካባቢ መደበኛው የታራሚዎች ቆጠራ የሚያደርጉ የመምሪያውን የፖሊስ አባላት #በማፈን እስረኞች #ለማምለጥ በመሞከራቸው ነው አለመረጋጋቱ የተፈጠረው።

የፖሊስ አባላቱን በማፈን ግርግር ፈጥረው ለማምለጥ ሙከራ ያደረጉት ደጋጋሚ እስረኞችና ከባድ ፍርደኞች መሆናቸውን የደብረ ታቦር ማረሚያ ቤት መምሪያ ኃላፊ ምክትል ኮማንደር መንጌ ከበደ ተናግረዋል፡፡

የመምሪያ ኃላፊው ለአማራ ብዙኃን መገናኛ ድርጅት እንዳስታወቁት ተጨማሪ የፖሊስ ኃይል በመጨመር የማረሚያ ቤቱን ሰላም የማረጋጋት ሥራ ተሰርቷል።

ምንጭ፦ አ.ብ.መ.ድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ድሬዳዋ ፖሊስ‼️

ሰሞኑን በድሬዳዋ ከተማ የተከሰተዉን #አለመረጋጋት ተከትሎ የከተማዉ ፖሊስ ኮሚሽን 308 ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር አዉሎ ምርመራ እያካሄደ ነዉ፡፡

በብጥብጡ እጃቸዉ #የሌለ ግለሰቦች #እንዲፈቱ የከተማዋ የሃይማኖት አባቶችና ሽማግሌዎች ጠይቀዋል፡፡

የኢፌድሪ መከላከያ ሰራዊት የምስራቅ እዝ ጠቅላይ መምሪያ እና የከተማ አስተዳደሩ በከተማዋ የሃይማኖት አባቶች ሽማግሌዎች ጋር በከተማዋ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ዉይይት አካሂዷል፡፡

ሰሞኑን በድሬዳዋ ከተማ የስራ አድማ ይደረጋል ብለዉ በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ የሚያሰራጩ አካላት ከድርጊታቸዉ #እንዲቆጠቡም የምስራቅ እዝ መምሪያ አሳስቧል፡፡

ምንጭ፦ etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETH ማጠቃለያ🗞ጥር 21/2011 ዓ.ም.

የኢትዮጵያ መንግስት “የጤፍ ባለቤት ነኝ” ያለውን የሆላንድ ድርጀት በዓለም አቀፉ የግልግል ፍርድ ቤት ሊከስ ነው።
.
.
በደቡብ ክልል አማሮ ወረዳ ሁለት አርሶ አደሮች በኦሮሞ ነፃ አውጪ ግንባር "ኦነግ ታጣቂዎች" መገደላቸውንና አንድ አርሶ አደር መቁሰሉን የአከባቢው ነዋሪዎች ተናግረዋል።
.
.
በአዲስ አበባ ቀላል ባቡር የሴፍቲና ሲኬዩሪቲ ዲፓርትመንት ባለሙያዎች በባቡሩ ላይ #ድንገተኛ የእሳት አደጋ ቢከሰት እንዴት መቆጣጠር እንደሚቻል የሚያሳይ ልምምድ አካሂደዋል።
.
.
ጠ/ሚር ዐቢይ አሕመድ በዛሬው እለት የቀጠለውን የሚኒስትርና ተጠሪ መስሪያ ቤቶችን የ100 ቀን እቅድ አፈፃፀም ግምገማ መርተዋል።
.
.
የብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፓሬሽን/ሜቴክ/ይቅርታ መጠየቅና #እርቅ ማውረድ ካለበት አካል ጋር ሁሉ እንደሚያደርግ የድርጅቱ ዋና ዳይሬክተር ብርጋዴር ጀነራል #አህመድ_ሀምዛ አስታውቀዋል።
.
.
በሰቆጣ ከተማ ሦስት #ፓኪስታናውያን በሕገ ወጥ የሞባይል ሽያጭ ተሰማርተው እጅ ከፈንጅ ተይዘዋል።
.
.
በአዲስ አበባ ከተማ የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ሰርተፍኬት፣ የመሬት ይዞታ ማረጋገጫ ካርታ ፣ የልደትና ሞት ሰርተፍኬት እንዲሁም የጋብቻ እና ፍቺ ሰርተፍኬቶች በዲጂታል ሰርተፍኬት ሊቀየሩ ነው ተብሏል።
.
.
ኢ/ር #ታከለ_ኡማ ቦሌ አራብሳ ተብሎ በሚጠራው አከባቢ የፈረሰውን መስጂድ በመጎብኘት የአከባቢውን የሙስሊም ማህበረሰብም አነጋግረዋል፡፡
.
.
#የፌዴራል_መንግሥት አመራሮች የድሬዳዋ ነዋሪዎችን በከተማዋ ወቅታዊ ሁኔታ ላይ አወያይተዋል፡፡
.
.
በተፈጥሮ ሀብት ጥበቃና በማህበራዊ ፍትህ ላይ ያተኮረ የመጀመሪያውን አረንጓዴ የፖለቲካ ፓርቲ (Green Party) ለማቋቋም ጊዜያዊ አስተባባሪ ፓርቲ መሰየሙን ዋዜማ ራድዮ ዘግቧል።
.
.
ከሳውዲ አረቢያ ጋር በተደረገው የሁለትዮሽ ስምምነት መሰረት በህጋዊ መንገድ ለሚሄዱ ሰራተኞች የቪዛ አገልግሎት መሰጠት መጀመሩን የሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚንስቴር አስታውቋል።
.
.
ግምታዊ ዋጋው 400 ሺህ ብር የሚያወጣ የባህርዛፍ አጠና ያለምንም ህጋዊ ሰነድ ከአገር ሊወጣ ሲል #በጅግጅጋ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት መያዙን የገቢዎች ሚኒስቴር አስታውቋል።
.
.
ከጥር 19 እስከ 21 ለተከታታይ ሦስት ቀናት #በሀዋሳ_ከተማ ሲካሄድ የቆየው የኢህአዴግ ወጣቶች ሊግ 4ኛ ድርጅታዊ ጉባዔውን ሊቀመንበርና ምክትል ሊቀመንበሩን በመምረጥ ተጠናቋል።
.
.
ከጭናግሰን ከተማ የማርያምን ክብረ በዐል አክብረው ይመለሱ በነበሩ ምዕመናን ላይ ወጣቶች መንገድ መዝጋታቸውን ተከትሎ #በጅግጅጋ_ከተማ ተፈጥሮ የነበረው ግጭት መረጋጋቱ ታውቋል። በግጭቱ የ2 ሰው ህይወት አልፏል።
.
.
ቀዳማዊት እመቤት #ዝናሽ_ታያቸው የአንደኛ ደረጃ ትምህርታቸውን ለተከታተሉበት የጎንደሩ ጻዲቁ ዮሐንስ 1ኛ ደረጃ ሙሉ ሳይክል ትምህርት ቤት የኮምፒዩተር ድጋፍ አድርገዋል፡፡
.
.
#በድሬዳዋ_ከተማ የትራንስፖርትና የግብይት #አድማ ለማድረግ ያቀዱ ነዋሪዎች ከድርጊታቸው ይቆጠቡ ዘንድ #የምስራቅ_ዕዝ_ጠቅላይ_መምሪያ አስጠነቅቋል።
.
.
አቃቤ ሕግ የቀድሞ #የሜቴክ የስራ #ሀላፊዎች በነበሩት ሻለቃ #ክንደያ_ግርማይና ሌተናል ኮሎኔል #አሰፋ_ዮሐንስ ላይ ክስ መስርቷል።
.
.
የኦጋዴን ብሄራዊ ነፃነት ግንባር (ኦብነግ) በዚህ ሳምንት ሐሙስ በይፋ ትጥቅ ይፈታል።
.
.
በቅርቡ በመንግስት እና ኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) መካከል በአምቦ በተደረገው ስምምነት መሠረት እርቁን ተግባራዊ ለማድረግ የተመረጠው የቴክኒክ ኮሚቴ ሥራውን በተግባር መጀመሩን የቴክኒክ ኮሚቴው አባል አቶ #ጀዋር_መሀመድ አስታውቀዋል።
.
.
ቀዳማዊት እመቤት ወይዘሮ #ዝናሽ_ታያቸው ከሁለት ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጡ የህክምናና የኢንፎርሜሸን ቴክኖሎጂ መሳሪያዎችን ለጎንደር ዩኒቨርሲቲ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታልና ለሁለት ትምህርት ቤቶች ድጋፍ አድርገዋል።
.
.
#የኢፌዲሪ_አየር_ሃይል በሶማሊያ ከባይደዋ በስተምስራቅ 75 ኪሎ ሜትር ላይ ቡርሃይቤ በተባለ የአልሻባብ ይዞታ ላይ ጥር 16 ቀን 2ዐ11 ዓ.ም ድብደባ በመፈፀም ከፍተኛ ሰብአዊና ቁሳዊ ኪሳራ ማድረሱን የኢፌዲሪ መከላከያ ሚኒስቴር አስታውቋል።
.
.
ሰሞኑን በድሬዳዋ ከተማ የተከሰተዉን #አለመረጋጋት ተከትሎ የከተማዉ ፖሊስ ኮሚሽን 308 ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር አዉሎ ምርመራ እያካሄደ ነዉ፡፡

ምንጭ፦ ዋዜማ ራድዮ፣ etv፣ fbc፣ VOA፣ ኢዜአ፣ ኢ.ፕ.ድ፣ የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት፣ የጠ/ሚ ፅ/ቤት፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ አብመድ
.
.
ሰላም እደሩ!!
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ድሬዳዋ ፖሊስ‼️

በድሬዳዋ ከተማ ተፈጥሮ በነበረው #አለመረጋጋት እና የተቃውሞ ቀናት ጉዳት ሳይደርስበት በሀሰት ጉዳት የደረሰበት በማስመሰልና ይህንን የሃሰት ፎቶ በማህበራዊ ድረ ገፅ በመልቀቅ ግጭቶች እንዲፈጠሩ ለማድረግ የሞከረው ግለሰብ በቁጥጥር ስር ውሏል፡፡

በፎቶው ላይ ምስሉ የሚታየው ተጠርጣሪ #ወርሰሜ_ሀሸ_መሀመድ የተባለው ግለሰብ በፀጥታ ሀይሎች ጉዳት የደረሰበት በማስመሰል ነው በፌስቡክ ገፁ ላይ ይፋ ያደረገው ፡፡ እንደ ፖሊስ ገለፃ ግለሰቡ ምንም አይነት አካላዊ ጉዳት ያልደረሰበት መሆኑን ገልጾ ከእንዲህ አይነት ተግባሮች መጠበቅ እንደሚገባ ያሳሰበ ሲሆን ግለሰቡ በበኩሉ ለፖሊስ በሰጠው ቃል ይቅርታ ጠይቋል ሲል የድሬዳዋ ፖሊስ የህዝብ ግንኙነት ዘግቧል።

ምንጭ፦ waltainfo.com
@tsegabwolde @tikvahethiopia