TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
56.9K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ቡራዩ‼️

መርማሪ ፖሊስና አቃቢ ህግ በቡራዩና አካባቢው በተፈፀው የሽብር ድርጊት ተጠርጥረው በተያዙ 32 ግለሰቦች ላይ ፍርድ ቤቱ የፈቀደው ዋስታና እንዲነሳ #ይግባኝ ጠይቀዋል።

የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ አራተኛ የወንጀል ችሎት በዛሬ ውሎው በቡራዩ እና አካባቢው በተፈፀመው የሽብር ወንጀል ተጠርጥረው የተያዙ 33 ግለሰቦችን ጉዳይ ተመልክቷል።

ፍርድ ቤቱ ከዚህ ቀደም መርማሪ ፖሊስ በተጠርጣሪዎች ላይ ያቀረበው የሰውና የሰነድ ማስረጃ ለአቃቢ ህግ ቀርቦ ተገቢነቱ እንዲጣራ መጠየቁ ይታወሳል።

ይሁን እንጂ መርማሪ ፖሊስ በወቅቱ ጉዳት የደረሰባቸውን ሰዎች የሙሉ ምስክርነት ቃል ለመቀበል እንዲሁም ተጎጅዎችን በአካል ማነጋገር
አስፈላጊ መሆኑን ለፍርድ ቤቱ በማስረዳት፥ ለዚህም 28 ቀን ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ እንዲፈቀድለት ጠይቋል።

የተጠርጣሪ ጠበቆች በበኩላቸው ባለፈው ችሎት መርማሪ ፖሊስ ጉዳዩን አጣርቶ ለአቃቢ ህግ እንዲያቀርብ ቢያዝዝም፥ ፖሊስ ግን ይህን ማስፈፀም አለመቻሉን ለፍርድ ቤቱ አስረድተዋል።

በተጨማሪም መርማሪ ፖሊስ እያቀረባቸው ያለው ሀሳቦች ተደጋጋሚና የተከሳሾችን የዋስትና መበት የሚጋፋ በመሆኑ፥ ፖሊስ የጠየቀው ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ውድቅ እንዲደረግ ፍርድ ቤቱን ጠይቀዋል።

ከዚህ ባለፈም ፍርድ ቤቱ የተከሳሾችን መዝገብ በመዝጋት በነፃ እንዲያሰናብታቸው ወይም ደግሞ የዋስትና መብታቸው እንዲጠበቅ ፍርድ
ቤቱን ጠይቀዋል።

የግራ ቀኙን ክርክር ያዳመጠው ፍርድ ቤቱም በዛሬው ዕለት ቀጠሮ የተያዘው መርማሪ ፖሊስ በተጠርጣሪዎች ላይ ያገኘውን ማስረጃ ሪፖርት ለማድመጥ አለመሆኑን ገልጿል።

ከዚህ ባለፈም አቃቢ ህግ የተጨማሪ ጊዜውን አስፈላጊነት በፅሁፍም ሆነ በቃል መስረዳት ይጠበቅበታል ፤ ይሁን እንጅ አቃቢ ህጉ ይህንን ማድረግ አለመቻሉን አሳውቋል።

ስለሆነም መርማሪ ፖሊስ የጠየቀው ተጨማሪ የ28 ቀን የምርመራ ጊዜ ተገቢ አለመሆኑን በመግለፅ፥ ሁሉም ተጠርጣሪዎች የ 15 ሺህ ብር ዋስትና በማቅረብ #እንዲፈቱ ትዕዛዛ አስተላፏል።

በመጨረሻም መርማሪ ፖሊስና ዓቃቢ ህግ ፍርድ ቤቱ ለተከሳሾች የፈቀደው ዋስታና እንዲነሳ የጠየቁ ሲሆን፥ ፍርድ ቤቱም መርማሪ ፖሊስና ዓቃቢ ህግ በፅሁፍ ያቀረቡትን ይግባኝ መቀበሉ ተገልጿል።

ምንጭ፦ fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ድሬዳዋ ፖሊስ‼️

ሰሞኑን በድሬዳዋ ከተማ የተከሰተዉን #አለመረጋጋት ተከትሎ የከተማዉ ፖሊስ ኮሚሽን 308 ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር አዉሎ ምርመራ እያካሄደ ነዉ፡፡

በብጥብጡ እጃቸዉ #የሌለ ግለሰቦች #እንዲፈቱ የከተማዋ የሃይማኖት አባቶችና ሽማግሌዎች ጠይቀዋል፡፡

የኢፌድሪ መከላከያ ሰራዊት የምስራቅ እዝ ጠቅላይ መምሪያ እና የከተማ አስተዳደሩ በከተማዋ የሃይማኖት አባቶች ሽማግሌዎች ጋር በከተማዋ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ዉይይት አካሂዷል፡፡

ሰሞኑን በድሬዳዋ ከተማ የስራ አድማ ይደረጋል ብለዉ በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ የሚያሰራጩ አካላት ከድርጊታቸዉ #እንዲቆጠቡም የምስራቅ እዝ መምሪያ አሳስቧል፡፡

ምንጭ፦ etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አቶ ኢሳያስ ከእስር #እንዲፈቱ ትዕዛዝ ተሰጠ‼️

የሥር ፍርድ ቤት ማለትም የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ አሥረኛ ወንጀል ችሎት በ100 ሺሕ ብር ዋስ እንዲፈቱ ትዕዛዝ ከሰጠ በኋላ፣ ትዕዛዙ በይግባኝ ታግዶ ለአንድ ወር ታስረው የከረሙት አቶ #ኢሳያስ_ዳኘው በተመሳሳይ ዋስትና ከእስር እንዲፈቱ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ማክሰኞ የካቲት 5 ቀን 2011 ዓ.ም. ትዕዛዝ ሰጠ፡፡

የሥር ፍርድ ቤትን ትዕዛዝ በመቃወም የፌዴራል ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ ይግባኝ ብሎ ወደ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመሄድ፣ በተጠርጣሪው ላይ ቀሪ ምርመራ እንዳለው በማስረዳት ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ እንዲሰጠው ጠይቆ ነበር፡፡ ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት ግን ይግባኙን ውድቅ ሲያደርግበት፣ ሐሳቡን በመቀየር የክስ መመሥረቻ ጊዜ እንዲሰጠው ጠይቋል፡፡

ፍርድ ቤቱም አሥር ቀናት በመፍቀድ በተሰጠው ቀናት ውስጥ ክስ ማቅረብ ካልቻለ፣ የሥር ፍርድ ቤት ቀደም ብሎ በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት ተጠርጣሪውን ከእስር እንዲፈታቸው ትዕዛዝ ሰጥቶ ነበር፡፡

ዓቃቤ ሕግ በይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት በተሰጠው አሥር ቀናት ውስጥ ክሱን መመሥረት ባይችልም፣ የሥር ፍርድ ቤት የክስ መመሥረቻ 15 ቀናት እንዲፈቅድለት አቅርቦ ነበር፡፡ ፍርድ ቤቱ የተጠርጣሪ ጠበቆች አስተያየት እንዲሰጡበት ሲጠይቅ፣ የሥር ፍርድ ቤት የበላይ ፍርድ ቤትን ትዕዛዝ መፈጸም እንጂ ያንን አልፎ የሚያከራክርበት ሥልጣን እንደሌለው በመግለጽ፣ ደንበኛቸው በጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ መሠረት ከእስር እንዲፈቱላቸው ጠይቀው ነበር፡፡

ዓቃቤ ሕግ በበኩሉ በወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 109(1) መሠረት ክስ የመመሥረቻ ጊዜና ቀናት ብቻ መሆኑን ቢደነገግም፣ በተለያዩ አዋጆች ተጨማሪ ጊዜ ማስፈቀድ የሚቻል መሆኑን ለማስረዳት ሞክሮ ነበር፡፡

ፍርድ ቤቱ ግን የሁለቱንም ወገኖች መከራከሪያ ሐሳብ በማለፍ፣ ቀደም ብሎ ከሰጠው ትዕዛዝ ውጪ ተጨማሪ ትዕዛዝ የመስጠት ሥልጣን እንደሌለው በመግለጽ፣ ተጠርጣሪው በሌላ ፍርድ ቤት አመልክተው ከእስር እንዲፈቱ ማድረግ እንደሚችሉ (HabeasCorpus) በመግለጽ መዝገቡን ዘግቶት ነበር፡፡

የተጠርጣሪው ጠበቆች በድጋሚ ለጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ በማለት፣ ቀደም ብሎ የሰጠው ትዕዛዝ ተግባራዊ አለመሆኑንና የሥር ፍርድ ቤት መዝገቡን እንደዘጋው በመግለጽ አመልክተዋል፡፡ ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት የሥር ፍርድ ቤት ለዓቃቤ ሕግ የተፈቀደለት አሥር ቀናት ሲጠናቀቅ ተጠርጣሪን እንዲፈታ ትዕዛዝ መስጠቱን አስታውሶ፣ ግለሰቡ አቤቱታው እስካቀረበበት ቀን ድረስ (ከየካቲት 1 እስከ 5 ቀን 2011 ዓ.ም. ድረስ) ለሕገወጥ እስር መዳረግ እንዳልነበረባቸው በመግለጽ፣ ከእስር እንዲፈቱ በድጋሚ ትዕዛዝ መስጠቱ ታውቋል፡፡ 

ምንጭ፦ ረፖርተር
@tsegabwolde @tikvahethiopia