TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.4K photos
1.51K videos
215 files
4.12K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update ሀረር⬇️

በሀረሪ ክልል የንጹህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት በመቋረጡ ነዋሪዎች #ለችግር መዳረጋቸውን የገለጹት የክልሉ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ተወለደ አብዶሽ ናቸዉ፡፡

ችግሩ በአፋጣኝ ሊፈታ ባለመቻሉ ነዋሪዎቹ አንድ ቦቴ ውሃ በ240 ብር እንዲሁም አንድ ጀሪካን ውሃ ከ10 እስከ 14 ብር ለመግዛት መገዳዳቸውን ገልጸዋል፡፡

የችግሩ ዋነኛ ተጎጂዎች አቅም የሌላቸው ህጻናትና አረጋውያን በመሆናቸው የሚመለከተው ሁሉ ትኩረት ሰጥቶት በአስቸኳይ መፈታት ያለበት ሰብዓዊ ችግር ነው ብለዋል፡፡

የተፈጠረውን የንጹህ ውሃ አቅርቦት መቋረጥ በዘላቂነት ለመፍታት የሀረሪና የኦሮሚያ ክልሎች አመራሮች በአስቸኳይ ተገናኝተው መነጋገር እንዳለባቸው አቶ ተወለደ አሳስበዋል፡፡

የሀረሪ ክልል የውሃ አቅርቦት የተዘረጋው በየረር-ሀረማያ-ድሬዳዋ መስመር ሲሆን 1/3ኛውን የክልሉን የውሃ ፍላጎት እንደሚሸፍን ከክልሉ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

ምንጭ፦ etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update አልብኮ⬆️

ቀዳማዊት እመቤት #ዝናሽ_ታያቸው በደቡብ ወሎ ዞን አልብኮ ወረዳ በ20 ሚሊየን ብር ለሚገነባው ጦሳ ፈላና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ግንባታ የመሠረት ድንጋይ አስቀምጠዋል። በስነ-ስርዓቱ ላይ የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ይልቃል ከፍያለው እና የደቡብ ወሎ ዞን አስተዳዳሪ አቶ እጅጉ መላኬን ጨምሮ ሌሎች የመንግስት ባለስልጣናት እና የአካባቢው ነዋሪዎች ተገኝተዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update አዲስ አበባ⬆️

በአዲስ ከተማ ክፍከ ከተማ ወረዳ 7 ቀበሌ 34 በመኖሪያ ቤት ውስጥ በህገ-ወጥ መንገድ የታተሙ 56 የሴት ፓስፖርቶች፣ 1 ማተሚያ ማሽን እና 1 ፋቃድ የሌለው ሽጉጥ በቁጥጥር ስር ውሏል፡፡

ምንጭ፦ የአዲስ ከተማ ኮሚኒኬሽን
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከሀዋሳ⬆️

"በሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ትምህርት መምሪያ በአዲሱ የትምህርት ፍኖተ ካርታ ዙሪያ ለ3 ተከታታይ ቀናት የሚደረግ ውይይት ተጀምሯል። ውይይቱ ከጥቅምት 13 - 15/2011ዓ.ም የሚካሄድ ይሆናል።"

© ትልቅሰው
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በላልይበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት ላይ እየደረሰ ያለውን ጉዳት ለመቅረፍና #እድሳቱን ለማስጀመር የሚያስችል ገንዘብ #በመገኘቱ ወደ
ሲራ ለመግባት ተወስኗል።

ምንጭ፦ አብመድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
179,000የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት ቁጥር ከቀን ወደቀን በሚያስደንቅ ፍጥነት እየጨመረ ነው። ለቻናሉ እዚህ መደረስ ላደረጋችሁት ከፍተኛ ጥረት ምስጋና ይገባችኋል!

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Update ከሚሴ⬆️

የኦሮሞ ብሄረሰብ አስተዳደር ነዋሪዎች የአማራ እና የኦሮሞ ህዝቦችን አንድነት በማጠናከር በኩል ትልቅ ኃላፊነት እንዳለባቸው አክቲቪስት #ጃዋር_መሃመድ ተናግሯል፡፡ ህግን #በማክበርና #በማስከበር ወጣቶች #ትልቁን ሚና እንዲጫወቱ ጠይቋል፡፡ ጃዋር ሙሃመድ ዛሬ በከሚሴ ከተማ አቀባበል ተደርጎለታል፡፡ ከብሄረሰብ አስተዳደሩ ለተውጣጡ ነዋሪዎችም መልዕክት አስተላልፏል፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ሱል-ሶማሊያ⬇️

ሰሜናዊው የሶማሊያ ክፍለ ግዛት ሱል ውስጥ የተቀናቃኝ ነገዶች ታጣቂዎች ተጋጭተው ቢያንስ ሥልሳ ሰዎች #መገደላቸውን ነዋሪዎችና ባለሥልጣናት ትላንት አስታወቁ።

ዱሁልባሃንቴ በሚባለው ነገድ ውስጥ ሁለት የተለያዩ ቡድኖች ሚሊሽያዎች ሰኞ ጥዋት ያነሱ ሲታኮሱ የቆዩት በመሬት ባለቤትነትና በቂም በቀል ምክንያት መሆኑን ነው የገለፁት።

ከሞቱት ሌላ ከዘጠና የሚበልጡ ሰዎች መቁሰላቸው ታውቋል። አንዳንዶቹ በተኩስ ልውውጡ መሃል የተጠመዱ ሲቪሎች ናቸው ተብሏል።

የሶማሊያ መንግሥት ሁለቱ ወገኖች ተኩስ አቁመው የሰላም ንግግር እንዲያካሂዱ ተማፅኗል።

ምንጭ፦ VOA አማርኛ
@tsegabwolde @tikvahethiopia