TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.4K photos
1.51K videos
215 files
4.12K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ለሚመለከተው አካል‼️

"ቴፒ ከተማ በአሁኑ ሰአት የተረጋጋች ብትመስልም አንዳንድ ነገሮች ግን ወደ ድሮው አይነት ሁኔታ ሊመለሱ አልቻሉም። ትምህርት ቤቶች እንኳን ትምህርት ሊጀምሩ ይቅርና በሮቻቸቸው ተዘግቶ ምዝገባም አላካሄዱም። ይህ ሁሉ የሆነው መንግስት የህዝቡን ጥያቄ በአፋጣኝና በአግባቡ መመለስ ስላልቻለ ነው። ስለዚህ የሚመለከተው አካል በጊዜ መፍትሄ ይስጥ።"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-AID‼️ለሀያት ህክምና ወጪ የ200,000 ብር ድጋፍ ለማድረግ እየተሰራ ያለው እንቅስቃሴ ተጠናክሮ ቀጥሏል።

🔹ዛሬም ከሻይ ወጪያችን ላይ ቀንሰን ለእህታችን ህክምና 15 ብር እናውል!

1000230747648 ወ/ሮ ሰዓዳ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የለዛ አሸናፊዎች‼️

በሸገር ኤፍ ኤም 102.1 የለዛ 8ኛው የአድማጮች ምርጥ አሸናፊዎች፦

የዓመቱ ምርጥ አዲስ ድምፃዊ - ሮፍናን ኑሪ

የዓመቱ ምርጥ ተከታታይ የቴሌቪዥን ድራማ - ምን ልታዘዝ

የዓመቱ ምርጥ ተዋናይ - ዓለማየሁ ታደሰ በ“ድንግሉ” ፊልም

የዓመቱ ምርጥ የሙዚቃ ቪዲዮ - “የመጀመሪያዬ” በናቲ ማን

የዓመቱ ምርጥ ፊልም - ድንግሉ

የዓመቱ ምርጥ ተዋናይት - አዚዛ አህመድ በ“ትህትና” ፊልም

የዓመቱ ምርጥ አልበም - የሮፍናን ኑሪ “ነፀብራቅ”

የዓመቱ ምርጥ ነጠላ ዜማ - የሮፍናን ኑሪ “ጨረቃ”

የለዛ የሕይወት ዘመን ተሸላሚ - የሙዚቃ ግጥም ደራሲ #ይልማ_ገብረአብ

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ለሚመለከተው አካል‼️

"ከደሴ ወደ መቀለ የሚወስደው መንገድ ተግቶ ወልዲያ ቆመናል። የሚመለከተው አካል ይወቅልን የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ነን ምዝገባ ሊያልፈን ነው።"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
አዲስ ፕሬዘዳንት‼️

የኢፌዴሪ አዲስ ፕሬዝዳንት ነገ ይሾማሉ። የኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች እና የፌዴሬሽን ምክር ቤቶች ነገ ሁለተኛ ልዩ ስብሰባቸውን ያካሂዳሉ።

ምክር ቤቶቹ በስብሰባቸው የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ዶ/ር #ሙላቱ_ተሾመ የሚያቀርቡትን መልቀቂያ በመቀበል #አዲስ ፕሬዚዳንት #ይሾማሉ

ፕሬዚዳንት ዶ/ር ሙላቱ መስከረም 27 ቀን 2006 ዓመተ ምህረት ነበር አቶ ግርማ ወልደጊዮርጊስን በመተካት የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት በመሆን የተሾሙት።

ሶስተኛው የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ዶክተር ሙላቱ ተሾመ ነገ ለሚተካቸው አራተኛ የኢፌደሪ ፕሬዚዳንት በምክር ቤቶቹ ፊት ስልጣን ያስረክባሉ።

ምንጭ፦ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
መቀለ⬆️20ኛው የጤናው ዘርፍ ዓመታዊ ጉባዔ በመቐለ ከተማ መካሄድ ተጀምሯል፡፡ ከሁሉም ክልሎችና የከተማ አስተዳደሮች የተውጣጡ ተሳታፊዎች በጉባኤው ላይ ተካፋይ ናቸው፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ቡራዩ⬇️

ከዚህ ቀደም በቡረዩ ተከስቶ ከነበረው የጸጥታ ችግር ጋር በተያያዘ በቁጥጥር ስር ውለው ከነበሩት 630 ወጣቶች ከተከሰተው ችግር ጋር ግንኙነት ያሌላቸው መሆኑ በምርመራ የተረጋገጠ 322 ወጣቶች ስልጠና ወስደው #ተለቀቁ፡፡

የቡራዩ ከተማ ፖሊስ ጽ/ቤት የምርመራ አስተባባሪ ኮማንደር በቃና ሚደግሳ እንደገለጹት፣ 322 ወጣቶች በቡራዩና በአዳማ ስልጠና ከወሰዱ በኋላ ነው የተለቀቁት፡፡

የተቀሩት 308 ለተፈጸመው #ወንጀል ተጠርጣሪ በመሆናቸው ጉዳያቸውን በፍርድ ቤት እየተከታተሉ መሆናቸውን ኮማንደር በቃና ገልጸዋል፡፡

በቡራዩ ተከስቶ በነበረው የጸጥታ ችግር በንብረትና በሰው ሕይወት ላይ ጉዳት መድረሱ ይታወሳል፡፡

ምንጭ:- የኦሮሚያ ኮሙኒኬሽ ቢሮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ክቡር ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር አብይ አህመድ በቅርቡ በአዲስ መልክ ላዋቀሩት ካቢኔ የ55 ሚንስትር ዴኤታዎች ሹመት ሰጡ።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ትረስት ፈንድ በተደራጀ ሁኔታ ገንዘብ የማሰባሰብ ተግባሩን ጀመሯል። ይህንን አስመልክቶ ከጠቅላይ ሚንስትሩ ጽ/ቤት የወጣውን መግለጫ ከላይ አንብቡት።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ኢትዮ-ቴሌኮም በአዲስ አበባ ስራ አጥነትን ለመቀነስ በሚደረገው ጥረት የራሱን #አስተዋፃኦ ለማበርከት ተዘጋጅቻለሁ አለ። የድርጅቱ ሀላፊ ወ/ሮ ፍሬሕይወት ታምሩ እንደገለፁት በቴክኖሎጂ ለስራ ፈጠራ ዕገዛ በማድረግም ሆነ በሌሎች የስራ ዘርፎች ስራ ፈላጊዎች እንዲሳተፉ ለማድረግ በሩ ክፍት ነው።

ምንጭ፦ ዋዜማ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የብሄር ብሄረሰቦች ቀን⬇️

የዘንድሮ የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች በዓል #የተራራቁና #የተኳረፉ ሕዝቦችን በማስታረቅና በማቀራረብ #ይከበራል ተባለ፡፡

የበዓሉን አከባበር አስመልክቶ የፌዴሬሽን ምክር ቤትና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በጋራ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡

የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ኬሪያ ኢብራሂም በዓሉ እስካሁን ሲከበርበት የቆየው መንገድ የተለያዩ #ክፍተቶች እንዳሉበት በጥናት #ተረጋግጧል ብለዋል፡፡

በሕዝቦች መካከል የቆየውን አብሮ የመኖር፣ የመቻቻልና የመከባበር እሴቶች ከማስጠበቅ አንፃር ክፍተቶች ነበሩ ብለዋል፡፡

አሁን ኢትዮጵያ ላይ እየታየ ያለው ሁኔታም ለዚህ ማሳያ ነው ያሉት አፈ ጉባኤዋ የብሔር ማንነትንና ኢትዮጵያዊነትን በማጣመር የዘንድሮውን በዓል ለማክበር ዝግጅት መደረጉን ተናግረዋል፡፡

ሰው በብሔሩ ብቻ የሚፈናቀልበት፣ የሚጠቃበትና የሚገደልበት ጊዜ ላይ ደርሰናል ያሉት አፈ ጉባኤዋ በኢትዮጵያ ሕዝቦች መካከል መጠራጠርና አለመተማመን ተፈጥሯል፣ በህብረተሰቡ ውስጥም በርካታ ቁስል አለ ብለዋል፡፡

የዘንድሮ በዓል የተራራቁ የሚቀራረቡበትና ለመፃኢ የጋራ ተስፋቸው የሚተባበሩበት መንገድ የሚታሰብበት ሆኖ እንደሚከበር ተናግረዋል፡፡

በተለይም የጎላ ግጭት ባለባቸው አካባቢዎች በጥናት ላይ የተመሰረተ የሰላምና የማረጋጋት ስራ ይሰራል ብለዋል፡፡

ባህላዊ፣ ሃይማኖታዊና ሳይንሳዊ የግጭት አፈታት ዘዴዎችን በመጠቀም ዘላቂነት ያለው ሰላም ለመፍጠር ከወዲሁ ስራዎችን ጀምረናል ማለታቸው ተሰምቷል፡፡

ለ13ኛ ጊዜ የሚከበረው የዘንድሮ የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በአዲስ አበባ አስተናጋጅነት ይካሄዳል፡፡

በበዓሉ ዝግጅት ወጣቶችና የኪነ ጥበብ ሰዎች እንደሚሳተፉ የተናገሩት ምክትል ከንቲባ ታከለ ኡማ የከተማ አስተዳደሩ እለቱን የኢትዮጵያውያን ቀን አድርጎ ያከብራል ብለዋል፡፡

ለበዓሉ አከባበር የሚወጣው ወጪም ለወጣቶች የስራ እድል ፈጠራ የሚውል ሲሆን ድግስ የማይበዛበት ዝግጅት ይደረጋል ብለዋል፡፡

የዘንድሮ የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች በዓል በብዝሃነት የደመቀ ኢትዮጵያዊነት በሚል መሪ ቃል ይከበራል፡፡

ምንጭ፦ ሸገር 102.1
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን⬆️የሰላም ሚኒስትሯ ወይዘሮ #ሙፈሪያት_ከሚል ዛሬ የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽንን ጎብኝተዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia