#update ሀረር⬇️
በሀረሪ ክልል የንጹህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት በመቋረጡ ነዋሪዎች #ለችግር መዳረጋቸውን የገለጹት የክልሉ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ተወለደ አብዶሽ ናቸዉ፡፡
ችግሩ በአፋጣኝ ሊፈታ ባለመቻሉ ነዋሪዎቹ አንድ ቦቴ ውሃ በ240 ብር እንዲሁም አንድ ጀሪካን ውሃ ከ10 እስከ 14 ብር ለመግዛት መገዳዳቸውን ገልጸዋል፡፡
የችግሩ ዋነኛ ተጎጂዎች አቅም የሌላቸው ህጻናትና አረጋውያን በመሆናቸው የሚመለከተው ሁሉ ትኩረት ሰጥቶት በአስቸኳይ መፈታት ያለበት ሰብዓዊ ችግር ነው ብለዋል፡፡
የተፈጠረውን የንጹህ ውሃ አቅርቦት መቋረጥ በዘላቂነት ለመፍታት የሀረሪና የኦሮሚያ ክልሎች አመራሮች በአስቸኳይ ተገናኝተው መነጋገር እንዳለባቸው አቶ ተወለደ አሳስበዋል፡፡
የሀረሪ ክልል የውሃ አቅርቦት የተዘረጋው በየረር-ሀረማያ-ድሬዳዋ መስመር ሲሆን 1/3ኛውን የክልሉን የውሃ ፍላጎት እንደሚሸፍን ከክልሉ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡
ምንጭ፦ etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia