#DebreBirhan የሰዓት እላፊ ገደብን ጨምሮ ሌሎች ውሳኔዎች ተላለፈ።
ትላንት የደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር ከፓሊስ እና ከቀበሌ አመራሮች ጋር በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዩ ዉይይት በማድረግ የሰዓት እላፊ ገደብን ጨምሮ የተለያዩ ዉሳኔዎችን አሳልፏል።
በዚሁ መሰረት ከዛሬ ጥቅምት 10 ጀምሮ በከተማው ውስጥ ለጥበቃ ስራ ከተሰማሩና ከጤና ተቋማት ተሽከርካሪዎች ውጪ ይሉ ተሽከርካሪዎች እንቅስቃሴ ከንጋቱ 11:00 ሰዓት - ምሽት 2:30 ድረስ ብቻ የእግረኞች እንቅስቃሴ ደግሞ ከንጋቱ 11:00 ሰዓት እስከ ምሽት 4:00 ድረስ ብቻ እንዲሆን የሰዓት እላፊ ገደብ ተጥሏል።
በተጨማሪ፦
- የአንኮበርና ጅሩ መስመርን ጨምሮ በ4ቱም ኬላዎች የተጠናከረ ፍተሻ እንዲካሄድ
- የ24 ሰዓት ፓትሮል/ጥበቃ እንዲደረግ
- በርካታ ህዝብን የሚያከብሩና የህዝቡን ህልውና አደጋ ላይ የማይጥሉ ወጣቶችን መመልመል ማደራጀትና ማሰልጠን
- የግል ታጣቂዎችን በማደራጀት ከጸጥታ ኃይለሉ ጋር በማቀናጀት ስምሪት እንዲሰጥ፣
- ተመላሽ ሰራዊት አባላትን አደራጅቶ ወደ ስራ እንዲገቡ
- አከራይ ተከራይን መለየት 50ለ5 የብሎክ አደረጃጀት ተጠናክሮ እንዲቀጥል
- የፓለቲካ አመራሩና የቀበሌ አመራሩ ህብረተሰቡን የማነቃቃት ስራ እንዲሰሩ
- በየቀበሌው የስጋት ቦታዎች ተለይተው ልዪ ጥበቃ እንዲደረግ
- ለጸጥታ ሃይሉ አስፈላጊ ግብዓቶች እንዲሟሉ
- የህብረተሰቡን ስነ ልቦና በመገንባት ማረጋጋትና ማነቃቃት እንዲቻች
- ከተለያዩ አካባቢዎች ተፈናቅለው በየቀበሌው የተጠለሉ ወይም የሚኖሩ ተፈናቃዮችን ማንነት መለየት
- ህገወጥ የጦር መሳሪያ የታጠቁ ግለሰቦችን በ1 ሳምንት ውስጥ ወደህጋዊ መስመር ማስገባት
- የመረጃ ስርዐቱ ከወትሮው በተለየ የተጠናከረ እንዲሆን ውሳኔ ተላልፏል።
ያንብቡ : telegra.ph/DB-10-20
@tikvahethiopia

#Halaba : ከፖሊስ ጋር በተደረገ የተኩስ ልውውጥ ባለሶስት እግር ተሽከርካሪ ሰርቀው ለማምለጥ የሞከሩ 2 ተጠርጣሪዎች ተያዙ።
ድርጊቱ የተፈፀመው ከሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር መሀል አራዳ ቀበሌ መንደር 39 አከባቢ ነው።
ትላንት ከለሊቱ 9:30 አከባቢ ንብረትነቱ የአቶ ፀጋዬ ዩሀንስ የሆነ ባለ ሶስት እግር ተሽክርካሪ አየተነዳ ወደ ወላይታ ሶዶ መስመር እየወጣ በነበረበት ሠዓት "ዘጻት" አከባቢ የነበሩ የእለቱ ተረኛ የፖሊስ አባላት ተከታትለው ለማስቆም ይሞክራሉ።
በዚህን ጊዜ ከተጠርጣሪዎቹ በተጀመረው የመሠሪያ ተኩስ ከተደረገው የአፀፋ ተኩስ በኃላ በሰአቱ የ3 እግር ተሽከርካሪውን እየሽከረከረ የነበረው ግለሰብ (አሸናፊ ሌንጮ) ከነተባባሪው (አወል ዴሌ) መጠነኛ ጉዳት ደርሶባቸው ሊያዙ ችለዋል።
በአሁን ሰዓት ሁለቱም ግለሰቦች በሀላባ ከተማ ሆስፒታል የህክምና እርዳታ እየተደረገላችዉ እንደሚገኝ የሀላባ ቁሊቶ ከተማ ሰላምና ፀጥታ ፅ/ቤት አሳውቋል።

#GurageZone : የጉራጌ ዞን ምክር ቤት የ2014 ዓ.ም 1ኛ ዙር አስቸኳይ ጉባኤውን እያካሄደ ይገኛል።
በዚህ ጉባኤ ምክር ቤት የዞኑን ዋና እና ም/ አፈጉባኤ እንዲሁም የዞኑን ዋና አስተዳዳሪ ፣ የመንግስት ተጠሪ፣ የዞን ካቢኔ አባላትን ሹመት ያፀድቃል።
Credit : DAVO
@tikvahethiopia
በዚህ ጉባኤ ምክር ቤት የዞኑን ዋና እና ም/ አፈጉባኤ እንዲሁም የዞኑን ዋና አስተዳዳሪ ፣ የመንግስት ተጠሪ፣ የዞን ካቢኔ አባላትን ሹመት ያፀድቃል።
Credit : DAVO
@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#GurageZone : የጉራጌ ዞን ምክር ቤት የ2014 ዓ.ም 1ኛ ዙር አስቸኳይ ጉባኤውን እያካሄደ ይገኛል። በዚህ ጉባኤ ምክር ቤት የዞኑን ዋና እና ም/ አፈጉባኤ እንዲሁም የዞኑን ዋና አስተዳዳሪ ፣ የመንግስት ተጠሪ፣ የዞን ካቢኔ አባላትን ሹመት ያፀድቃል። Credit : DAVO @tikvahethiopia
#Update
አቶ መሀመድ ጀማል የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ሆነው ተሾሙ።
እየተካሄደ በሚገኘው የጉራጌ ዞን ምክር ቤት የ2014 ዓ.ም 1ኛ ዙር አስቸኳይ ጉባኤ አቶ መሀመድ ጀማል የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ ሆነው ተሹመዋል፤ ቃለ መኃላም ፈፅመዋል።
ጉባኤው በቀጣይ የመንግስት ተጠሪን ሹመትና የካቢኔ አባላትን ሹመት መርምሮ ያጸድቃል።
Credit : DAVO
@tikvahethiopia
አቶ መሀመድ ጀማል የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ሆነው ተሾሙ።
እየተካሄደ በሚገኘው የጉራጌ ዞን ምክር ቤት የ2014 ዓ.ም 1ኛ ዙር አስቸኳይ ጉባኤ አቶ መሀመድ ጀማል የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ ሆነው ተሹመዋል፤ ቃለ መኃላም ፈፅመዋል።
ጉባኤው በቀጣይ የመንግስት ተጠሪን ሹመትና የካቢኔ አባላትን ሹመት መርምሮ ያጸድቃል።
Credit : DAVO
@tikvahethiopia
#GedeoZone : አቶ አብዮት ደምሴ በምክትል ማዕረግ የጌዴኦ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ሆነዉ ተሾሙ።
በአሁን ሰዓት የጌዴኦ ዞን ምክርቤት በዲላ ከተማ 4ኛ ዙር 9ኛ አስቸኳይ ጉባኤ እያካሄደ ይገኛል።
በዚሁ ጉባኤ አቶ አብዮት ደምሴ በምክትል ማዕረግ የጌዴኦ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ሆነዉ ተሹመዋል፤ ቃለመኃላም ፈፅመዋል።

#SilteZone : አቶ አሊ ከዲር የስልጤ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ሆነው ተሾሙ።
የስልጤ ዞን ምክር ቤት ዛሬ እያካሄደ ባለው 4ኛ ዙር 7ኛ አስቸኳይ ጉባዔው አቶ አሊ ከዲርን የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አድርጎ ሾሟቸዋል።
በተጨማሪ ምክር ቤቱ አፈጉባኤ፣ ም/አፈጉባኤ፣ የመንግስት ተጠሪ ሹመቶችን አፅድቋል።
Credit : Silte Zone Communication
@tikvahethiopia
የስልጤ ዞን ምክር ቤት ዛሬ እያካሄደ ባለው 4ኛ ዙር 7ኛ አስቸኳይ ጉባዔው አቶ አሊ ከዲርን የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አድርጎ ሾሟቸዋል።
በተጨማሪ ምክር ቤቱ አፈጉባኤ፣ ም/አፈጉባኤ፣ የመንግስት ተጠሪ ሹመቶችን አፅድቋል።
Credit : Silte Zone Communication
@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Mekelle : ዛሬ በትግራይ ክልል መዲና መቐለ የአየር ጥቃት እንደነበር መገለፁ ይታወሳል። የዓይደር ሪፈራል ሆስፒታል የድንገተኛ ህክምና ክፍል ኃላፊ አቶ አበበ ሃብቱ ለጀርመን ሬድዮ ማምሻውን በሰጡት ቃል በዛሬው ሁለት ጥቃት 8 ተጎጂዎች ወደሆስፒታሉ እንደመጡ ሁለት ህፃናትም እንደሞቱ ገልፀዋል። የሆስፒታሉ የድንገተኛ ክፍል ኃላፊ ፤ በሞሶቦ አሬና በነበረው ጥቃት 2 እድሜያቸው 12 እና 14 የሆኑ…
#Mekelle : በትግራይ ክልል መዲና መቐለ ዛሬ ጥዋት የአየር ጥቃት መፈፀሙን ሮይተርስ የክልሉን ቴሌቪዥን ዋቢ አደርጎ ዘግቧል።
አጃንስ ፍራንስ ፕሬስም በመቐለ የአየር ጥቃት መፈፀሙን የረድኤት ተቋማት ምንጮችን ዋቢ አድርጎ ዘግቧል።
የዛሬ ጥዋቱ ጥቃት በዚህ ሳምንት ሁለተኛው ነው ተብሏል።
የጥዋቱ የአየር ድብዳ መስፍን ኢንዱስትሪያል ኢንጂነሪንግ በተባለው ተቋም ኢላማ ያደረገ እንደነበርም ተሰምቷል።
በሌላ በኩል ፦ በፌዴራል መንግስት ስር ያለው የ " ወቅታዊ መረጃ ማጣሪያ ገፅ " በትግራይ ክልል ስለሚፈፀሙ የአየር ድብደባዎች መረጃ አጋርቷል።
በዚህም መከላከያ ሠራዊት እያካሄደ ያለው የአየር ድብደባን በተመለከተ የተዛባ ግንዛቤ ቢኖርም፣ በተቃራኒው ጥቃቶቹ ዒላማ ያደረጉት የህወሓት የጦር መሣሪያ ማምረቻ እና የጦር ትጥቅ ጥገና ጣቢያዎችን ብቻ ነው ብሏል።
አክሎም ፥ " የመከላከያ ሠራዊት የሚያከውናቸው እነዚህ ሥራዎች የሽብር ድርጅቱ ከባድ የጦር መሣሪያዎችን እና ሌሎች ሕገወጥ የጦር መሣሪያዎችን ለመሸሸግ የሚጠቀምባቸውን እና ወደ ወታደራዊ መገልገያነት የቀየራቸውን የተወሰኑ ቦታዎች ከጥቅም ውጭ ለማድረግ ያለመ ነው " ሲል ገልጿል።

#MostWanted
ከኢትዮጵያ ያመለጠው ኤርትራዊ ሰው አዘዋዋሪ ኪዳኔ ዘካሪያስ ሀብተማርያም በኔዘርላንድስ በጥብቅ ከሚፈለጉ ዝርዝር ውስጥ ተካተተ።
የኔዘርላንድስ ዐቃቤ ሕግ ኤርትራዊውን በሕገ ወጥ የሰዎች አዘዋዋሪነት የሚፈለገውን ኪዳኔ ዘካርያስ ሀብተማርያምን በሕግ በጥብቅ ከሚፈለጉ ሰዎች ዝርዝር ውስጥ አካቶታል።
ኪዳኔ ዘካርያስ ሀብተማርያም ከሚቀርቡበት በርካታ ክሶች መካከል ፦
- ግድያ፣
- ሕገ ወጥ የሰዎች ዝውውር እና
- በሕገ ወጥ መንገድ የተገኘ ገንዘብ ሕጋዊ አስመስሎ መጠቀም የሚሉት ይገኙበታል።
የኔዘርላንድስ ዐቃቤ ሕግ ኤርትራዊው ተይዞ በወንጀል እንዲጠየቅ በሚል በከፍተኛ ደረጃ ከሚፈለጉ ሰዎች ዝርዝር ውስጥ እንዳካተተው ተዘግቧል።
ኪዳኔ በአዲስ አበባ ለአንድ ዓመት ገደማ የሁለት ስደተኞች ግድያን ጨምሮ በስምንት ሰዎች ዝውውር ተከሶ የፍርድ ሂደቱን እየተከታተለ ሳለ ነው ከእስር ያመለጠው።
በወቅቱ "መጸዳጃ ቤት ውስጥ ልብስ ቀይሮ" ከፖሊስ እጅ እንዳመለጠ ተዘግቧል።
በፍርድ ቤት ቀጠሮ ዕለት ከፍርድ ቤት ማምለጡ በርካቶችን ያነጋገረ እና በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ ለፍርድ እንዲቀርብ ንቅናቄ የሚያደርጉ የመብት ተሟጋቾችን ያስቆጣ ነበር።
ኪዳኔ ከእስር ቢያመልጥም ፍርድ ቤቱ በሌለበት የእድሜ ልክ እስራት ፈርዶበታል። ኪዳኔ አሁን የት እንዳለ በትክክል አይታወቅም።
ያንብቡ👇
https://telegra.ph/BBC-10-20-2
Photo Credit : POLITIE NEDERLAND

Telegraph
BBC
#KidaneZehariasHabtemariam ከኢትዮጵያ ያመለጠው ኤርትራዊ ሰው አዘዋዋሪ ኪዳኔ ዘካሪያስ ሀብተማርያም በኔዘርላንድስ በጥብቅ ከሚፈለጉ ዝርዝር ውስጥ ተካተተ። የኔዘርላንድስ ዐቃቤ ሕግ ኤርትራዊውን በሕገ ወጥ የሰዎች አዘዋዋሪነት የሚፈለገውን ኪዳኔ ዘካርያስ ሀብተማርያምን በሕግ በጥብቅ ከሚፈለጉ ሰዎች ዝርዝር ውስጥ አካቶታል። ኪዳኔ ዘካርያስ ሀብተማርያም ከሚቀርቡበት በርካታ ክሶች መካከል ፦…
#Update
ዛሬ የተለያዩ ዞን፣ ወረዳና ከተማ ም/ ቤቶች ጉባኤ አድርገው ዋና አስተዳዳሪዎችን ፣ አፈ ጉባኤና ምክትል አፈጉባኤ፣ የመንግስት ተጠሪ እና ካቢኔ ሹመዋል።
ጉባኤ ካደረጉት ም/ቤቶች መካከል የጉራጌ ዞን ፣ የጌዴኦ ዞን ፣ የስልጤ ዞን ምክር ቤቶች ይገኙበታል።
ጥዋት ከተለዋወጥነው መረጃ በተጨማሪ ፦
• የጎፋ ዞን ምክር ቤት አቸኳይ ገባኤ አካሂዶ የነበረ ሲሆን ዶ/ር ጌትነት በጋሻውን የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አድርጎ ሾሟል።
• የአማሮ ወረዳ ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው አስቸኳይ ጉባኤ አቶ ወገኔ ብዙነህን ዋና አስተዳዳሪ አድርጎ ሾሟል።
• የአማራ ክልል ዋና ከተማ የባህር ዳር ከተማ አስተዳደር ዛሬ ባካሄደው ጉባኤ ዶ/ር ድረስ ሳህሉን በድጋሚ የከተማው ተቀዳሚ ከንቲባ አድርጎ ሾሟል።
** የኦሮሞ ብሄረሰብ አስተዳደር ምክር ቤት ትላንት ባካሄደው ጉባኤ አቶ አህመድ የሱፍን የብሄረሰብ አስተዳደሩ ዋና አስተዳዳሪ አድርጎ ሾሟል።

የመምህራን ጉዳይ ! " በትግራይ ክልል የሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎችና የወልዲያ ዩኒቨርሲቲ መምህራን ጊዚያዊ ምደባ ይሰጣቸዋል " - ዶ/ር ሰለሞን አብርሃ በትግራይ ክልል የሚገኙ 4 ዩኒቨርሲቲዎች እና የወልዲያ ዩኒቨርሲቲ መምህራን ጉዳይን በተመለከተ ለትምህርት ሚኒስቴር የአስተዳደርና መሰረተ-ልማት ጉዳዮች ዳይሬክተር ጀነራል ሰለሞን አብርሃ (ዶ/ር) ጠይቀናል። የትግራይ ዩኒቨርሲቲዎች እና የወልዲያ ዩኒቨርሲቲ…
#ተጨማሪ
በትግራይ ክልል ከሚገኙ አራት ዩኒቨርሲቲዎች እና ከወልዲያ ዩኒቨርሲቲ የተመለሱ ተማሪዎች Official Transcript የሚያገኙበት መንገድ ለማመቻቸት እየሠራ መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር ገልጿል።
ተማሪዎቹ ከ'Official Transcript'፣ የትምህርት ማስረጃ እና ወጪ መጋራት ጋር ተያይዞ ያደረሱንን ጥያቄዎች ለትምህርት ሚኒስቴር የአስተዳደርና መሰረተ ልማት ጉዳዮች ዳይሬክተር ጀነራል ሰለሞን አብርሃ (ዶ/ር) አቅርበናል።
ሁለተኛ ዲግሪ ለመማር 'Official Transcript' የሚያስፈልጋቸው ተማሪዎችን ለማስተናገድ ፎርም መዘጋጀቱን ዳይሬክተር ጀነራሉ ገልጸዋል።
ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎቹን እንዲቀበሉ መመሪያ በማዘጋጀት ትምህርት እንዲቀጥሉ አቅጣጫ መቀመጡን ኃላፊው ተናግረዋል።
የወጪ መጋራት /Cost Sharing መክፈል ለሚፈልጉ ተማሪዎቹ ከገቢዎች ሚኒስቴር ጋር በመነጋገር እንዲከፍሉ እንደሚደረግ ገልጸዋል።
የትምህርት ማስረጃ/ዲግሪ የመስጠት ስልጣን ያላቸው ዩኒቨርሲቲዎች በመሆናቸው ተማሪዎች መጠበቅ እንደሚኖርባቸው ኃላፊው ጠቁመዋል።
@tikvahuniversity

የብሔራዊ የደም ባንክ አገልግሎት በአሁኑ ሰዓት ከፍተኛ የሆነ የደም ክምችት እጥረት እንዳጋጠመው አሳውቋል።
ሰለዚህ ማንኛውም የበጎ ፍቃደኛ በአቅራቢያው በሚገኝ በአዲስ አባ እና የክልል ደም ባንኮች በመገኘት ደም እንዲለግስ ጥሪ አስተላልፏል።
ለወገን ደራሽ ወገን ነው !
የብሔራዊ የደም ባንክ አገልግሎት
ለበለጠ መረጃ : 0983424242

#Amhara : በአማራ ክልል በጦርነት ቀጠና ውስጥ 4 ሚሊዮን ህዝብ የሚገኝ ሲሆን አጠቃላይ የተፈናቃዮች ቁጥር ደግሞ 1,700,000 ደርሷል።
ጦርነት ቀጠና ውስጥ ያሉና ህወሓት በያዛቸው አካባቢዎች ያሉ ወገኖችን ለመርዳት አንዳንድ ዓለም አቀፍ ረጂ ድርጅቶች ጥያቄ ቢቀርባላቸውም እስካሁን ድረስ ግን ምንም ነገር እንዳላደረጉ የአማራ ክልል አደጋ መከላከል እና ምግብ ዋስትና ልዩ ድጋፍ የሚሹ አካባቢዎች ማስተባበሪያ ኮሚሽን አሳውቋል።
ሰሞኑን ደግሞ እንደአዲስ ተባብሶ በቀጠለው ጦርነት ህፃናት ፣ ሴቶች ፣ አቅመ ደካሞች ከመኖሪያቸውን ከገዛ ቄያቸው በከፍተኛ ሁኔታ እየተፈናቀሉ ይገኛሉ።

#Turkey_Africa
የቱርክ ፕሬዜዳንት ሬሲፕ ጣይብ ኤርዶጋን በአፍሪካ ሀገራት 4 ቀናት ይፋዊ የስራ ገብኝት እያደረጉ ይገኛሉ።
በመጀመሪያው ቀን ጉብኝታቸው በአንጎላ፣ ላውንዳ ተገኝተው ከሀገሪቱ ፕሬዜዳንት ጃኦ ሎሬንኮ ጋር መክረዋል።
በመቀጠል በበቶጎ ሎሜ ከፕሬዚዳንት ፋውሬ ናሲንግቤ ጋር ተገናኝተው መክረዋል፤ በተጨማሪ ከቡርኪና ፋሶ ፕሬዜዳንት ሮች ማርክ ክርስትያን ካቦሬ እንዲሁም ከላይቤሪያ ፕሬዝዳት ጆርጅ ዊሃ ጋር ተገናኝተው መክረዋል (ሁሉም ምክክሮች ለሚዲያ ዝግ ነበሩ) ።
ዛሬ በመጨረሻው የስራ ጉብኝት መርሃግብራቸው ፕሬዜዳንት ሬስፕ ጣይብ ኤርዶጋን ወደናይጄሪያ አቅንተው በአቡጃ በፕሬዜዳንት ሙሀመድ ቡሃሪ አቀባበል ተደርጎላቸዋል፤ መሪዎቹ ምክክርም አድርገዋል።
ቱርክ እና ናይጄሪያ ከኃይል እስከ መከላከያ ድረስ በርካታ የሁለትዮሽ ስምምነቶችን ተፈራርመዋል፤ ግንኙነታቸውን ይበልጥ ለማጠናከርም ስምምነት አድርገዋል።
ፕሬዝዳንት ኤርዶጋን እ.ኤ.አ በ2003 ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ስልጣን ከመጡ ወዲህ ቱርክ በአፍሪካ ውስጥ ያላትን ተሳትፎ እና ከሀገራት ጋር ያላትን ግንኙነት በከፍተኛ ደረጃ እያሳደገች ነው።

ዕለታዊ የኮቪድ-19 ሪፖርት #Ethiopia ፦
ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 29 ሰዎች ሲሞቱ ከተደረገው 8,444 የላብራቶሪ ምርመራ 622 ሰዎች ለቫይረሱ ተጋላጭ ሆነው ተገኝተዋል።
የዛሬው ሪፖርት እንደሚያሳየን 542 ሰዎች በፅኑ ታመዋል።
#ጥንቃቄ 😷 #TikvahFamily
@tikvahethiopia
ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 29 ሰዎች ሲሞቱ ከተደረገው 8,444 የላብራቶሪ ምርመራ 622 ሰዎች ለቫይረሱ ተጋላጭ ሆነው ተገኝተዋል።
የዛሬው ሪፖርት እንደሚያሳየን 542 ሰዎች በፅኑ ታመዋል።
#ጥንቃቄ 😷 #TikvahFamily
@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Waghimra : በአማራ ክልል የዋግኽምራ ብሄረሰብ አስተዳደር የአደጋ መከላከል እና ምግብ ዋስትና ፅ/ቤት በጦርነት ቀጠና ያሉ ከ635 ሺህ በላይ ወገኖች በከፋ የረሃብ አደጋ ውስጥ እንደሚገኙ አመልክቷል። የፅ/ቤቱ ኃላፊ አቶ መልካሙ ደስታ ለጀርመን ድምፅ ዛሬ በሰጡት ቃል ፤ በዋግኽምራ በጦርነት ቀጠና ያሉ ከ635 ሺ በላይ ሰዎች ለከፋ የረሃብ አደጋ መጋለጣቸውን ተናግረው ዓለም አቀፍ ረጂ ድርጅቶች…
በምግብ እጦት የሰው ህይወት እያለፈ ነው።
በጦርነት ቀጠና ባሉት የአማራ ክልል አካባቢዎች በከፋ ችግር ላይ ያሉ ወገኖችን እንዲረዱ ዓለም አቀፍ ረጂ ድርጅቶች ቢጠየቁም አፋጣኝ ምላሽ አልሰጡም።
በዚህ ሳምንት ብቻ በዋግኽምራ ብሄረሰብ አስተዳደር በዝቋላ እና በጋዝጊብላ ወረዳዎች በረሃብ እና በመዳኒት እጥረት 11 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል።
የብሄረሰብ አስተዳደሩ የአደጋ መከላከል እና ምግብ ዋስትና ፅ/ቤት መምሪያ ኃላፊ አቶ መልካሙ ደስታ ዛሬ ለጀርመን ሬድዮ በሰጡት ቃል ፥ በጋዝጊብላ ወረዳን ጨምሮ በሌሎችም ወረዳዎች ሙሉ በሙሉ እንቅስቃሴ የሚባል ነገር መቆሙን ገልፀዋል።
በየትኛውም አቅጣጫ ምግብ የሚገባበት ሁኔታ እንደሌለም አስረድተዋል።
በዚህም ምክንያት ስር የሰደደ ህመም ያለባቸው እንዲሁም በምግብ እጦት በርካታ ወገኖች እየተጎዱ ነው ብለዋል።
አቶ መልካሙ ፥ በዚህ ሳምንት በጋዝጊብላ ወረዳ 10 በዝቋላ 1 በአጠቃላይ 11 ሰዎች በምግብ እጦት እንዲሁም በጤናና ሌሎች አገልግሎት ባለማግኘት እንደሞቱ ተናገረዋል።
የዋግኽምራ ብሄረሰብ አስተዳደር ም/አስተዳዳሪ አቶ ተስፋዬ ገብሬ በበኩላቸው ፥ የዕለት እርዳታ ለማድረስ ስምምነት ያደረጉና ቃል የገቡ ዓለም አቀፍ ረጂ ድርጅቶች ቃላቸውን መጠበቅ ባለመቻላቸው በጥቂት ቀናት ውስጥ በብሄረሰብ አስተዳደሩ ከፍተኛ ሰብዓዊ ቀውስ ሊፈጠር እንደሚችል ለሬድዮ ጣቢያው በሰጡት ቃል አስጠቅቀዋል።