#Halaba : ከፖሊስ ጋር በተደረገ የተኩስ ልውውጥ ባለሶስት እግር ተሽከርካሪ ሰርቀው ለማምለጥ የሞከሩ 2 ተጠርጣሪዎች ተያዙ።
ድርጊቱ የተፈፀመው ከሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር መሀል አራዳ ቀበሌ መንደር 39 አከባቢ ነው።
ትላንት ከለሊቱ 9:30 አከባቢ ንብረትነቱ የአቶ ፀጋዬ ዩሀንስ የሆነ ባለ ሶስት እግር ተሽክርካሪ አየተነዳ ወደ ወላይታ ሶዶ መስመር እየወጣ በነበረበት ሠዓት "ዘጻት" አከባቢ የነበሩ የእለቱ ተረኛ የፖሊስ አባላት ተከታትለው ለማስቆም ይሞክራሉ።
በዚህን ጊዜ ከተጠርጣሪዎቹ በተጀመረው የመሠሪያ ተኩስ ከተደረገው የአፀፋ ተኩስ በኃላ በሰአቱ የ3 እግር ተሽከርካሪውን እየሽከረከረ የነበረው ግለሰብ (አሸናፊ ሌንጮ) ከነተባባሪው (አወል ዴሌ) መጠነኛ ጉዳት ደርሶባቸው ሊያዙ ችለዋል።
በአሁን ሰዓት ሁለቱም ግለሰቦች በሀላባ ከተማ ሆስፒታል የህክምና እርዳታ እየተደረገላችዉ እንደሚገኝ የሀላባ ቁሊቶ ከተማ ሰላምና ፀጥታ ፅ/ቤት አሳውቋል።
@tikvahethiopia

#Halaba
የሀላባ ዞን አስተዳደር ፤ በዞኑ ቤተክርሲቲያን ተቃጠለ ተብሎ እየተናፈሰ የሚገኘው መረጃ ፍጹም ሀሰተኛ ነው አለ።
በተለያዩ የማህበራዊ ድረ-ገፆች ላይ " በሀላባ ቁሊቶ ከተማ ቤተክርስቲያን ተቃጠል " ተብሎ እየተሰራጨ የሚገኘው መረጃ ሀሰት መሆኑን ገልጿል።
ዞኑ " የሀላባ ህዝብ በሰላም ፣ በፍቅር እና በመቻቻል የሚኖርና የአብሮነት መልካም እሴትን የሚተገብር ፍጹም ሰላማዊ ህዝብ መሆኑ ይታወቃል ፤ ይህም ተጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል " ብሏል።
አክሎም ፤ ይህንን መልካም እሴት ለማደፍረስ ሆን ተብሎ በተጠነሰሰ የተንኮል ሴራ በዞኑ የእምነት ግጭት እንደተከሰተ ለማስመሰል ሀሰተኛ መረጃዎችን እያሰራጩ የሚገኙ አካላት ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ ዞኑ አስጠንቅቋል።
በሀይማኖት ሽፋን ውዥንብር ለመፍጠር የሚንቀሳቀሱ አካላትን መመከትና ሀሰተኛ መረጃዎችን ማጋለጥ እንደሚገባ ዞኑ አስገንዝቧል።
ሀላባ ፍጹም ሰላማዊ በሆነ ሁኔታ ላይ እንደምትገኝ የገለፀው ዞኑ በማህበራዊ ድረ-ገጾች ላይ የሚናፈሰው መረጃ ሀሰተኛ መሆኑ አሳውቋል።