TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.44K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
አሶሳ🔝የሰላም እናቶች #አሶሳ ከተማ ይገኛሉ። የሰላም እናቶች ከክልሉ ርእሰ መስተዳድር ከአገር ሽማግሌዎች ከዩኒቨርስቲ ተማሪዎችና ከአሶሳ ከተማ ከተውጣጡ የህዝብ ወኪሎች ጋር በሰላም ዙሪያ ተወያይተዋል።

©etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሞቃዲሾ‼️

የኤርትራው ፕሬዝዳንት #ኢሳያስ_አፈወርቂ ሞቃዲሾ ሶማሊያ ናቸው። የፕሬዝዳንቱ ጉብኝት አላማ የሁለቱን ሀገሮች ግንኙነት ለማሳደግ ያለመ ነው ተብሏል። ኢትዮጵያ ሶማሊያና ኤርትራ የሶስትዮሽ የጋራ ጉባዔ በባህርዳር አድርገው በደረሱት ስምምነት አንድ የኢኮኖሚ ማህበረሰብ ለመገንባትና በተላያዩ ዘርፎች ለመተባበር መስማማታቸው ይታወሳል። ሶስቱ መሪዎች በሞቃዲሾ ዳግም እንደሚገናኙም ይጠበቃል። ጅቡቲን የትብብሩ አካል ለማድረግም እቅድ አለ። ፕሬዝዳንት ኢሳያስ በዚሁ ወደ ናይሮቢ አቅንተው ኬንያን እንደሚጎበኙም ተነግሯል።

©wazemaradio
@tsegabwolde @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
መቀለ🔝በአገሪቱ የተፈፀሙ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች በአንድ ብሔር እንደተፈፀሙ አድርጐ ማቅረብ ተገቢ አለመሆኑን የመቐለ ከተማ ነዋሪዎች ገለፁ፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በህገ-ወጥ መንገድ ከአገር ሊወጡ ሲሉ የተያዙና ፍርድ ቤት ብይን የሰጠባቸው 100 ጥንታዊ የብራና መጽሐፍት ለብሄራዊ ቤተ-መዛግብትና ቤተ-መጽሐፍ ኤጀንሲ ተሰጥተዋል። የቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለስልጣን የብራና መጽሐፍቱን ዛሬ ለብሔራዊ ቤተ መዛግብትና ቤተ-መጽሐፍት ኤጀንሲ አስረክቧል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ትኩረት‼️ቡሌ ሆራ ዩኒቨር ሲቲ ያለውን ሁኔታ የሚመለከተው የመንግስት አካል ልዩ ትኩረት እንዲሰጠው እና ችግሩን እንዲፈታ ተማሪዎች አጥብቀው ጠይቀዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ🔝የተቋሙ ተማሪዎች በአሁን ሰዓት በዚህ መልኩ አዳራቸውን አድርገዋል። ተማሪዎች መንግስት በአስቸኳይ ችግሩን ፈቶ ሰላማዊ የመማር ማስተማሩ ሂደት እንዲጀመር ጠይቀዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
መደበኛ ሎተሪ ወጣ!
መደበኛ ሎተሪ!!

1611 ኛው #መደበኛ_ሎተሪ ሐሙስ ታህሳስ 4 /2011 ዓ.ም በብሔራዊ ሎተሪ ዕድል አዳራሽ ከምሽቱ 12፡00 ሰዓት ላይ በህዝብ ፊት ወጥቷል፡፡
በዚህም መሰረት የወጡት የአሸናፊ ዕጣ ቁጥሮች እንደሚከተሉት ሆነዋል፡፡

1ኛ. 600,000 ብር የሚያስገኘው የ1ኛ ዕጣ ቁጥር 110749

2ኛ. 300,000 ብር የሚያስገኘው የ2ኛ ዕጣ ቁጥር 078905

3ኛ. 150,000 ብር የሚያስገኘው የ3ኛ ዕጣ ቁጥር 129287

4ኛ. 60,000 ብር የሚያስገኘው የ4ኛ ዕጣ ቁጥር 104306

5ኛ. 30,000 ብር የሚያስገኘው የ5ኛ ዕጣ ቁጥር 228690

6ኛ. 6ኛ ዕጣ 3 ዕጣዎች እያንዳንዳቸው ብር 1,200 የሚያስገኙት ዕጣ ቁጥሮች 099058፣ 013909 እና 073560

7ኛ. 7ኛ ዕጣ 3 ዕጣዎች እያንዳንዳቸው ብር 600 የሚያስገኙት ዕጣ ቁጥሮች 160897፣ 105369 እና 073270

8ኛ. 8ኛ ዕጣ 34 ዕጣዎች እያንዳንዳቸው ብር150 የሚያስገኘው ዕጣ ቁጥር 2014

9ኛ . 9ኛ ዕጣ 34 ዕጣዎች እያንዳንዳቸው ብር 120 የሚያስገኘው ዕጣ ቁጥር 2940

10ኛ. 10ኛ ዕጣ 34 ዕጣዎች እያንዳንዳቸው ብር 90 የሚያስገኘው ዕጣ ቁጥር 8933

11ኛ. 11ኛ ዕጣ 340 ዕጣዎች እያንዳንዳቸው ብር 60 የሚያስገኘው ዕጣ ቁጥር 569

12ኛ. 12ኛ ዕጣ 340 ዕጣዎች እያንዳንዳቸው ብር 45 የሚያስገኘው ዕጣ ቁጥር 445

13ኛ. 13ኛ ዕጣ 3400 ዕጣዎች እያንዳንዳቸው ብር 30 የሚያስገኘው ዕጣ ቁጥር 43

14. 14ኛ 34,000 ዕጣዎች እያንዳንዳቸው ብር 15 የሚያስገኘው ዕጣ ቁጥር (የማስተዛዘኛ ዕጣ) ደግሞ ቁጥር 1 በመሆን ወጥቷል፡፡

አስተዳደሩ በወጡት ዕጣ ቁጥሮች ዕድለኛ ለሆኑ እንኳን ደስ ያላችሁ ብሏል። ዜናውን ጓደኞቻችሁ በማጋራት (share በማድረግ) ለሌሎች እንዲደርስ ታደርጉ ዘንድ በትህትና እ ንጠይቃለን!

የብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የ600 ሺ ብር ባለ ዕድለኛ!

#ተማሪ_ታዲዎስ_ተፈሪ በመደበኛ ሎተሪ 600,000 ብር ዕድለኛ ሆነ፡፡ ታዲዎስ የወላይታ ሶዶ ከተማ ነዋሪ ሲሆን ቤተ ክርስቲያን ገብቶ ሲወጣ በኪሱ ካለው 18 ብር ውስጥ የ15 ብር ሎተሪ ይገዛል፡፡ በገዛው ሎተሪ በ1ኛ ዕጣ የ600,000 ብር አሸናፊ ሆኗል፡፡ ተማሪ ታዲዎስ በደረሰው ብር የመጀመሪያ ዕቅዱ ቤት ለመስራት እንደሆነ ተናግሯል፡፡

ምንጭ፦ የብሄራዊ ሎተሪ አስተዳደር
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ትግራይ🕊አማራ!

የትግራይ እና አማራ ክልል ክለቦች ዛሬ ባደረጉት ስብሰባ የእርስ በርስ ጨዋታዎቻቸውን በየሜዳቸው ለማድረግ ተስማምተዋል። 

ዛሬ በጁፒተር ሆቴል ለሚድያዎች ዝግ በነበረው ስብሰባ የባህል እና ቱሪዝም ሚኒስቴር መኒስትር #ሒሩት_ካሳው (ዶ/ር)፣ የስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ርስቱ ይርዳው፣ የሁለቱ ክልሎች ክለብ ተወካዮች፣ የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን አመራሮች እና ሌሎች ባለ ድርሻ አካላት የተገኙ ሲሆን የፌዴሬሽኑ ፕሬዝዳንት አቶ #ኢሳይያስ_ጂራ በመሩት ስብሰባ ሁለቱም ወገኖች የእርስ በእርስ ጨዋታዎቻቸውን በየሜዳቸው ለማድረግ ከስምምነት መድረሳቸውን ለማወቅ ተችሏል።

በዚህም መሠረት ባለፉት አምስት ሳምንታት ሊደረጉ የነበሩና ወደ ሌላ ጊዜ ተሸጋግረው የነበሩት የባህር ዳር ከተማ እና ስሑል ሽረ፣ የፋሲል ከነማ እና መቐለ 70 እንደርታ እንዲሁም የመቐለ 70 እንደርታ እና ባህር ዳር ከተማዎች በባለሜዳዎቹ ከተማ እንዲካሄድ ተስማምተዋል።

በሀገሪቱ በቅርብ ጊዜያት የተከሰተውን ፖለቲካዊ ሁኔታ ተከትሎ በሁለቱ ክልሎች ክለቦች መካከል ከኅዳር 9 ቀን 2010 ወዲህ በየሜዳቸው የእርስ በርስ ጨዋታ ተከናውኖ አያውቅም።

ምንጭ፦ ሶከር ኢትዮጵያ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Update በጋና የአክራ ዩኒቨርሲቲ በቅጥሩ ይገኝ የነበረውን የማህተመ ጋንዲን ሀውልት #አፈረሰ። ሃውልቱ የፈረሰው የዩኒቨርሲቲው አንድ ፕሮፌሰር ጋንዲ #ዘረኛ ነበሩ በማለት ሃውልቱ እንዲፈርስ ፊርማ ማሰባሰባቸውን ተከትሎ ነው። ምንም እንኳ ጋንዲ አገራቸው ህንድ ከእንግሊዝ አስተዳደር ነፃ እንድትወጣ ባደረጉት ትግል የነፃነት ተምሳሌት ቢሆኑም ስለ አፍሪካዊያን የተናገሯቸው ነገሮች ለብዙዎች አወዛጋቢ ናቸው።

©BBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የቡራዩ ከተማ አስተዳደርን #በክፍለ_ከተማ ደረጃ ለመዋቀር ዝግጅት መጠናቀቁን የከተማዋ ከንቲባ አቶ ሰለሞን ፈዬ አስታወቁ። በአሁኑ ወቅት በአራት ቀበሌዎች ብቻ ተዋቅራ የምትገኘው ከተማዋ በአዲሱ አወቃቀር አራት ክፍለ ከተሞችና 16 ቀበሌዎች ይኖሯታል ተብሏል። አዲሱ አወቃቀር ከህዝብ ቁጥር ጋር ተያይዞ እየጨመረ ለመጣው የህዝብ ፍላጎት ተመጣጣኝ አገልግሎት ለመዘርጋት እንደሚያስችልም ከንቲባው ገልፀዋል።

©ena
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Audio
#Update በምዕራብ ሐረርጌ በሶማሌ ክልል አዋሳኝ ወረደ “ጭናክሰን” ውስጥ አዲስ ጥቃት እንደተከፈተባቸው ነዋሪዎች ለአሜሪካ ድምፅ ገለፁ። በጥቃቱም በሁለት ሳምንት ውስጥ ብቻ 16 ሰዎች መገደላቸውን፣ 18 ሰዎች ደግሞ የመቁሰል አደጋም እንደደረሰባቸው ተናግረዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Update ብሉምበርግ ስለ ሼክ አላሙዲን በአንድ ቀን ውስጥ ሁለተኛውን ዘገባ ይዞ የወጣ ሲሆን ዋና ዋና ነጥቦቹ:

- ከታሰሩ ጀምሮ ሀብታቸው በስድስት ፐርሰንት ጨምሮ አሁን 8.3 ቢልዮን ዶላር አላቸው

- ከዚህ ውስጥ 425 ሚልዮን ዶላሩ ካሽ (ጥሬ ገንዘብ) ነው

- አሁን ላይ የአላሙዲንን ንብረት እያስተዳደረ ያለው ወንድማቸው ሀሰን አላሙዲን ነው

- የባለሀብቱ ዋና ኢንቨስትመንት ስዊድን ሲሆን (5.1 ቢልዮን ዶላር የሚገመት) በኢትዮጵያ ያላቸው አጠቃላይ ኢንቨስትመንት ደግሞ 1.1 ቢልዮን ዶላር ነው።

via~ኤልያስ መሰረት
@tsegabwolde @tikvahethiopia