TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
62.8K photos
1.61K videos
216 files
4.36K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ትግራይ🕊አማራ!

የትግራይ እና አማራ ክልል ክለቦች ዛሬ ባደረጉት ስብሰባ የእርስ በርስ ጨዋታዎቻቸውን በየሜዳቸው ለማድረግ ተስማምተዋል። 

ዛሬ በጁፒተር ሆቴል ለሚድያዎች ዝግ በነበረው ስብሰባ የባህል እና ቱሪዝም ሚኒስቴር መኒስትር #ሒሩት_ካሳው (ዶ/ር)፣ የስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ርስቱ ይርዳው፣ የሁለቱ ክልሎች ክለብ ተወካዮች፣ የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን አመራሮች እና ሌሎች ባለ ድርሻ አካላት የተገኙ ሲሆን የፌዴሬሽኑ ፕሬዝዳንት አቶ #ኢሳይያስ_ጂራ በመሩት ስብሰባ ሁለቱም ወገኖች የእርስ በእርስ ጨዋታዎቻቸውን በየሜዳቸው ለማድረግ ከስምምነት መድረሳቸውን ለማወቅ ተችሏል።

በዚህም መሠረት ባለፉት አምስት ሳምንታት ሊደረጉ የነበሩና ወደ ሌላ ጊዜ ተሸጋግረው የነበሩት የባህር ዳር ከተማ እና ስሑል ሽረ፣ የፋሲል ከነማ እና መቐለ 70 እንደርታ እንዲሁም የመቐለ 70 እንደርታ እና ባህር ዳር ከተማዎች በባለሜዳዎቹ ከተማ እንዲካሄድ ተስማምተዋል።

በሀገሪቱ በቅርብ ጊዜያት የተከሰተውን ፖለቲካዊ ሁኔታ ተከትሎ በሁለቱ ክልሎች ክለቦች መካከል ከኅዳር 9 ቀን 2010 ወዲህ በየሜዳቸው የእርስ በርስ ጨዋታ ተከናውኖ አያውቅም።

ምንጭ፦ ሶከር ኢትዮጵያ
@tsegabwolde @tikvahethiopia