#update ጠ/ሚር #ዐቢይ_አሕመድ ከ30 የአውሮፓ አገራት አምባሳደሮች ጋር የኢትዮጵያን የለውጥ ምዕራፍ በተመለከተ ዛሬ ታህሳስ 5 ቀን 2011 በጽ/ቤታቸው ውይይት እያካሄዱ ነው።
#PMOEthiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#PMOEthiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ወላይታ ሶዶ‼️
በሕገ-ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀስ የነበረ 70 ኩንታል #ስኳር መያዙን የወላይታ ሶዶ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ አስታወቀ፡፡
ስኳሩ ከኅብረተሰቡ በደረሰ ጥቆማ በቁጥጥር ሥር የዋለው የሰሌዳ ቁጥር ኮድ 3 80610 አዲስ አበባ በሆነ የጭነት መኪና ከከተማው ለመውጣት እየተሰናዳ ባለበት ወቅት መሆኑን በመምሪያው የአስተዳደሩ ፖሊስ የወንጀል ምርመራ የስራ ሂደት አስተባባሪ ዋና ሳጅን ፍሬው ሰማ ገልጸዋል።
አሽከርካሪው ለጊዜው #በመሰወሩ ስኳሩ ወዴት አቅጣጫ ሊወጣ እንደነበር ማወቅ እንዳልተቻለም አመልክተዋል።
ከዚህም በተጨማሪ በከተማው የሚገኝ አንድ የሸማቾች ኅብረት ሥራ ማህበር ለኅብረተሰቡ ማከፋፈል የነበረበት ሁለት ኩንታል ስኳር #ደብቆ በመገኘቱ የወላይታ ዞን ንግድና ኢንዱስትሪ መምሪያ መረከቡን አስተባባሪው ተናግረዋል፡፡
የከተማዋ ነዋሪዎች ሕገ-ወጥ ንግድን ከመከላከልና የከተማውን ደህንነት ከመጠበቅ አንጻር ከፖሊስ ተቀናጅተው እያከናወኑት ያሉትን ተግባር እንዲያጠናክሩም ጠይቀዋል፡፡
ፖሊስ ከስኳር ዝውውሩ ጋር በተያያዘ ጉዳዩን በማጣራት ላይ እንደሚገኝ ተገልጿል፡፡
በሶዶ ከተማ የዋዱ ቀበሌ ነዋሪው አቶ ታደሰ ጋንታ በሰጡት አስተያየት አስተዳደሩ በከተማው የሚስተዋለውን የስኳር እጥረት ለመፍታት ሕገ ወጥ እንቅስቃሴ ለመቆጣጠር እየወሰደ ያለው እርምጃ ቀጣይነት ሊኖረዉ ይገባል ብለዋል፡፡
በከተማዋ አንድ ኪሎ ግራም ስኳር እስከ 60 ብር ለመግዛት እየተገደዱ ባሉበት ወቅት በሕገ-ወጥ መንገድ የሚደረገውን እንቅስቃሴ ለመከላከል የተወሰደው እርምጃ እንዳረካቸው የተናገሩት የጎላ ቀበሌ ነዋሪ ወይዘሮ ከበቡሽ ደመላሽ ተናግረዋል፡፡
ባለፈው ዓመት መጨረሻ ከወላይታ ሶዶ ከተማ ወደ ሻሸመኔ መሥመር በተመሳሳይ መንገድ በሕገ ወጥ መንገድ ሊጓዝ የነበረ ሲጓጓዝ የነበረ 20 ኩንታል ስኳር መያዙ ይታወሳል፡፡
ምንጭ፦ ኢዜአ

ህዝብን ማሸበር ይቁም‼️
"አክቲቪስት አሉላ ሰለሞን በፌስቡክ ገፁ የተላለፈውን ዶክሜንተሪ ተከትሎ በተለያዩ አካባቢዎችና በሳሪስ ብዙ ትግራውያኖች እንደታፈሱና እንደታሰሩ ፅፏል። ይህንን ተከትሎም #ሳሪስ እንደምኖር የሚያውቁና በዜናው የተረበሹ ብዙ ኢትዮጵያውያን ወንድሞቼም እህቶቼም በinbox እና በስልክ ስለ ጉዳዩ ሐቀኝነት ጠይቀውኛል። ነገር ግን እኔ የሌላውን አላውቅም የምንኖረው ሳሪስ አካባቢ እንደመሆኑ ግን በተቻለኝ አቅም በሳሪስ የታሰረ ሰው ካለ ለማጣራት ሞክሬያለሁ። በትግራዋይነቱ የታሰረም የታፈሰም መኖሩን ማረጋገጥ አልቻልኩም። ምናልባት የሚያውቀው ነገር ካለ በተጨባጭ ማስረጃ ይንገረንና እኛም ባለን ሞያ ለመርዳትና ከጎናቸው ቆመን ለማገዝ ዝግጁ ነን። ነገር ግን በሌለና ተጨባጭነት በሌለው ነገር መፃፍ ሌላው ሰርቶ የሚኖረውንና ሰላማዊ ሕይወት የሚገፋውን ትግራዋይ ማሸበርና መረበሽ ጥሩ አይደለምና ቢታረም፤ ደግሞም ለቀጣይ ሁላችንም መረጃ ሲሰጠን በቀላሉ እድሜ ለቴክኖሎጂ በተለያየ መንገድ ማረጋገጥ ስንችል ስለ እውነተኛነቱ ሳናረጋግጥ ባንለጥፍ መልካም ነው። ስለ ሐቅ እንፅፋለን እንናገራለን። ዛሬም ነገም ሕዝብን እንደ ሕዝብ #ማሸበር ይቁም እባካችሁ ልብ ግዙ። ይሄ ምስኪን ሕዝብ ምን ያድርጋችሁ።"
Via~Kibrom Adhanom Ghebreyesus

ጎንደር🔝
በጎንደር የሰላምና እርቅ ጉባኤ እየተካሄደ ነው። በአማራ እና ቅማንት ማህበረሰብ የተፈጠረውን ቁርሾ መፍትሄ ለመስጠት ያለመ ህዝባዊ #የሰላምና #የእርቅ ጉባኤ በጎንደር እየተካሄደ ነው፡፡
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር #ደመቀ_መኮንን እና የሐይማኖት አባቶች በተገኙበት መድረክ የሰላምና ጉባኤው በዛሬው ዕለት ሲካሄድ ይውላል፡፡
ዓላማውም በጎንደር በተለይም ማዕከላዊና ሰሜን ጎንደር ዞኖች ማንነትን መሰረት አድርገው የሚነሱ ግጭቶችን ሰላማዊ በሆነ መንገድ #በዘላቂነት ለመፍታት ያለመ ነው፡፡
ምንጭ፦ etv

🕊ትግራይ አማራ የሰላም መድረክ🕊
የትግራይና አማራ ክልሎች የሰላም መድረክ #በመቐለ_ዩኒቨርሲቲ አዘጋጅነት ትላንት ተካሄደ፡፡ በመድረኩ የሁለቱን ህዝቦች ዘመናት የተሻገረ ግንኙነት ይበልጥ የሚያጠነክሩ፣ ስጋት ለፈጠሩ ክስተቶች መፍትሔ የተባሉ ሃሳቦች ቀርበውበታል፡፡
በአማራ ክልል የሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ምሁራን ጨምሮ የተሻለ ምክረ ሀሳብ ለፖለቲካ መሪዎች ለማቅረብ በቀጣይነት እንደሚሰራም ተጠቁሟል፡፡
የመድረኩ አስተባባሪና ጥናት አቅራቢ ዶክተር ገብረየሱስ ተክሉ የግጭት ስጋቶች ለማምከን ፖለቲከኞች፣ የሃይማኖት መሪዎች፣ የሀገር ሽማግሌዎች እና መገናኛ ብዙሃን ገንቢ ሚና መጫወት አለባቸው ብለዋል።
በኢትዮጵያ የተለያዩ ክፍሎች የሚስተዋሉ #ግጭቶችና የግጭት ስጋቶች ለመከላከል ሁሉም ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ሊሰሩ እንደሚገባ ተጠቁሟል፡፡
ምንጭ፦ ጀርመን ድምፅ ራድዮ
@tsegabwolde @tukvahethiopia

አማራ 🕊 ቅማንት!
‹‹ድርጅት እና መሪዎች ያልፋሉ ህዝብና #ታሪክ ግን ይቀጥላል፤ የምናልፍ መሪዎች #የማያልፍ ጠባሳ ጥለን እንዳናልፍ ልንጠነቀቅ ይገባል፡፡››
‹‹ማንነትን ማክበር እና ማስከበር ስንል አጥር ማጠር እና የልዩነት ግንብ መገንባት ማለት አይደለም ፡፡ህዝብን ማድመጥ እና ታሪካዊ ወሰኑን ማስከበር እንጅ ተመልሶ ያደረ ጥያቄ ነው እያሉ ማለፍ ታሪኩ ያለፈበት ሂደት ነው፡፡››
‹‹ልታከብረን እና ልናከብራት የምንችላት ሃገር ለመገንባት በመጀመሪያ በህግ የበላይነት ልንገዛ ይገባል፡፡›› ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን
.
.
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ #ደመቀ_መኮንን ግጭት ለታላቅ ሃገር እና ተስፋ ለሰነቀ ህዝብ የሚመጥን አይደለም፤ እንዲህ አይነት ህዝብን ከህዝብ የማጋጨት ስራ ዛሬ ሳይሆን በሁለተኛው የጣሊያን ወረራ ወቅት አማራን የትኩረት ማዕከል አድርጎ ሲሰራበት ነበር ዳሩ የህዝቡን አንድንነት #ማፍረስ አልተቻላቸውም እንጅ ብለዋል፡፡
አማራን ከአገው፣ ቤተ እስራኤላዊያንን ከአማራ እንዲሁም ቅማንትን ከአማራ ለማጋጨት ጥረት ተደርጎ ነበር፤ ነገር ግን አባቶቻችን በብልጠት ሴራውን አክሽፈው እልፍ ዘመን የዘለቀ አብሮነትን አውርሰውናል ነው ያሉት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፡፡
ማንነትን ማክበር እና ማስከበር ስንል አጥር ማጠር እና የልዩነት ግንብ መገንባት ማለት አይደለም ያሉት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ህዝብን ማድመጥ እና ታሪካዊ ወሰኑን ማስከበር እንጅ ተመልሶ ያደረ ጥያቄ ነው እያሉ ማለፍ ታሪኩ ያለፈበት ሂደት ነው ብለዋል፡፡
ልታከብረን እና ልናከብራት የምንችላት ሃገር ለመገንባት በመጀመሪያ በህግ የበላይነት #ልንገዛ ይገባል፡፡ ሃገራችን ያከበረችንን ያክል አላከበርናትም ያሉት አቶ ደመቀ ሃገር ግንባታ ጊዜ ይወስዳልና በትዕግስት ሃገር ልንገነባ ይገባል ብለዋል፡፡
እኛ እና እናንተ አሉ አቶ ደመቀ ‹‹እኛ እና እናንተ ከግለሰብ እልፍ ያለ ኃላፊነት ስላለብን ስሜት ሳይገዛን እና ከንፈራችን እየመጠጥን እንዳናዳማ ትክክለኛ መሪ እና መፍትሄ ፈላጊዎች ልንሆን ይገባል ብለዋል፡፡››
ይህ ህዝብ አብሮ ኖሯል ፤ ተዋልዷል ፤ #ደም አስተሳስሮታል እና! ይህ ቀን አልፎ ነገ አብሮ መኖሩ ስለማይቀር ‹‹መሪና ድርጅት ያልፋሉ ህዝብና ታሪክ ግን በዘመናት መካከል ይቀጥላሉና በሚያልፍ የመሪነት ዘመናችን የማያልፍ የታሪክ ጠባሳ እንዳንተው ልንጠነቀቅ ይገባል››
ብለዋል፡፡
🔹በጎንደር ከተማ እየተካሄደ ያለው የሰላም መድረክ እንደቀጠለ ነው፡፡
ምንጭ፦ አብመድ

#update ዛሬ ታሕሳስ 5, 2011 ከጠ/ሚር ዐቢይ አሕመድ ጋር ተገናኝተው የተወያዩት ከ30 በላይ የአውሮፓ አገራት አምባሳደሮች ኢትዮጵያ ባለፉት ወራት በእርሳቸው አመራር ስር ያስመዘገበችውን ለውጥ በጥሩ ጎኑ እንደሚመለከቱት ገልፀዋል።
ምንጭ፦ የጠቅላይ ሚስትር ፅ/ቤት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ምንጭ፦ የጠቅላይ ሚስትር ፅ/ቤት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Update በኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ዋና ከተማ ኪንሻሳ ውስጥ በአንድ መጋዘን ላይ በደረሰ #ቃጠሎ 8ሺ የሚሆኑ የኤሌክትሮኒክስ የድምፅ መስጫ ማሽኖች በእሳት መጋየታቸውን ቢቢሲ ከስፍራው ዘግቧል፡፡ እነዚህ ማሽኖች በ4 ሚሊዮን ከሚገመተው የከተማይቱ ድምፅ ሰጪ መካከል 1/3ኛውን ያስተናግዳሉ ተብሎ ተስፋ የተጣለባቸው ነበሩ፡፡ ክስተቱን ትልቅ ኪሳራ ሲል የገለፀው የአገሪቱ የብሔራዊ ምርጫ ኮሚሽን ምርጫው በተያዘለት መርሃ-ግብር እንዲካሄድ የምንችለውን ሁሉ እናደርጋለን ብሏል፡፡ እቅዳችን ወደተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች በተጠባባቂነት ተሰራጭተው የነበሩትን ማሽኖች አሰባስበን ጉድለቱን ለማሟላት ነው ብሏል ኮሚሽኑ፡፡ስለጠመሎው መንስኤ የታወቀ ነገር ባይኖርም የተከሰተው ግን በአገሪቱ እያደገ የመጣውን ውጥረት ተከትሎ መሆኑን ዘገባው ጠቅሷል፡፡
ምንጭ፡- ቢቢሲ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ምንጭ፡- ቢቢሲ
@tsegabwolde @tikvahethiopia