TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.1K photos
1.5K videos
211 files
4.09K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ከቀይ መስቀል⬆️

"በአሁኑ ሰዓት በምስራቅ ጎህ ት/ቤት ውሰጥ 100 ተማሪዎች ቀይ መስቀል ከፌደራል ጉዳዬችና አርብቶ አደር ልማት ሚኒስቴር ትብብር ሚኒስትሩ አቶ ከበደ ጫኔ በተገኙበት ድጋፍ እየተደረገ ይገኛል። ይህም በተመሳሳይ በቀጣይ ሳምንት እስከ ስምንት መቶ ለሚደርሱ እንደሚደግፍ ለመረዳት ችለናል።"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ማሳሰቢያ📌ውድ የአጠቃላይ የ2ኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ ሰርተፍኬት /የ10ኛ ክፍል/ ተፈታኝ ተማሪዎችና የተማሪ ወላጆች ከግንቦት
22-24/2010 ዓ.ም የኢትዮጵያ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ ሰርተፍኬት /የ10ኛ ክፍል ፈተና/ ለ1,200,676 ተማሪዎች እንዲሁም ከግንቦት 27-30/2010 ዓ/ም የኢትዮጵያ ዩንቨርስቲ መግቢያ ፈተና (የ12 ክፍል ፈተና) 284,312 ተማሪዎች መሰጠቱ ይታወሳል፡፡

የፈተናውን መሰጠት ተከትሎም ወደ እርማት ስራው በመግባት ከምንጊዜውም በፈጠነ መልኩ የ12ኛ ክፍል ውጤት በ24/11/2010
ዓ/ም ይፋ የተደረገ ሲሆን አስከትሎም የ10ኛ ክፍልን ወደ ማረም ሂደት ውስጥ ተገብቷል፡፡

እንደ 12ኛ ክፍሉ ሁሉ የ10ኛውም ፈተና ጥንቃቄ በተሞላበት ሁኔታ ከጥቃቅን የዳታ ማጥራት ስራዎች በስተቀር በሰላም እየተጠናቀቀ መሆኑን ልናሳውቅ እንወዳለን፡፡ ከነሐሴ 25-30/2010 ዓ.ም ይለቀቃል ተብሎ ተደራሽ ተደርጎ የነበረውን መረጃ መሰረት በማድረግ በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች የተለያዩ አሉታዊ መረጃዎች በመሰራጨት ላይ መሆናቸውን በመረዳታችን ከላይ በተገለጸው አግባብ የፈተና እርማቱ በሰላም #በመጠናቀቅ ላይ እንደሚገኝ እና በቀጣዮቹ #ጥቂት ቀናት ውስጥ ውጤቱ ይፋ እንደሚሆን እየገለጽን #በትዕግስት ትጠባበቁን ዘንድ መልዕክታችንን እናስተላልፋለን፡፡

የውጤቱን መለቀቅ አስመልክቶም ለተለያዩ ሚዲያዎች መግለጫ የምንሰጥ መሆኑን እናሳውቃለን!

መልካም ዕድል!

©NEAEA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጥንቃቄ📌ሀላፊነት የማይሰማቸው ሰዎች የአባላት ቁጥር ለማብዛት በማሰብ የውሸት መረጃዎችን እየለቀቁ በመሆኑ ጥንቃቄ አድርጉ።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ የቻይና አፍሪካ የትብብር ፎረም ላይ ለመሳተፍ ወደ ቻይና አቅንተዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update አዲስ አበባ⬆️

የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ከሌሎች የጸጥታ አካላት ጋር በዳረገው የተቀናጀ ዘመቻ በተለያዩ የዘረፋና የኢኮኖሚ ወንጀሎች ላይ ተሳትፈዋል ያላቸውን 108 ተጠርጣሪዎች እና የወንጀሎቹ ፍሬ የሆኑ ኤግዚቢቶችን መያዙን የኮሚሽኑ የወንጀልና ትራፊክ አደጋ መከላከል
ምክትል ኮሚሽነር ዘላለም መንግስቴ ገልፀዋል፡፡

እንዲሁም ተጠርጣሪዎቹ ሲገለገሉባቸው የነበሩ ጦር መሳሪያዎችንና ሞተር ሳይክሎችን መያዙን ምክትል ኮሚሽነር ዘላለም መንግስቴ ተናግረዋል፡፡

በአዲስ አበባ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በተለያዩ አካባቢዎች እየተበራከተ የመጣውን የወንጀል ድርጊት ተከትሎ ነዋሪው ያነሳቸውን ጥያቄዎች በመቀበል የተለያዩ የፀጥታ አካላትን ያሳተፈ በጥናት ላይ የተደገፈ የወንጀል መከላከል ተግባር መከናወኑን ኃላፊው አስረድተዋል፡፡

ተጠርጣሪዎቹ በጦር መሳሪያ የታገዘ ዘረፋ ፣ ለጋራ መኖሪያ ቤት ግንባታ የሚውሉ የኤሌትሪክ ኬብሎችን መስረቅ፣ ሞተር ሳይክል በመጠቀም የቅሚያ #ወንጀሎችን ሲፈፅሙ መቆየታቸውን ም/ኮሚሽነር ዘለላም ተናግረዋል፡፡

ፖሊስ ባደረገው ክትትል ህገ ወጥ የውጭ ሀገር የገንዘብ ዝውውር ላይ ተሳትፎ የነበራቸውን ተጠርጣሪዎች እና የተለያዩ ሀገራት ገንዘቦችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን ተናግረዋል፡፡

በሌላም በኩል ወቅታዊ ሁኔታዎችን እንደ መልካም አጋጣሚ በመጠቀም በተለያዩ ክፍለ ከተሞች በህገ ወጥ መንገድ የመሬት ወረራ እየተስተዋለ መሆኑንም ም/ ኮሚሽነሩ ገልፀዋል።

በተለይም ከኦሮሚያ ልዩ ዞን ጋር በሚዋሰኑ በኮልፌ ቀራኒዮ፣ በቦሌ፣ በየካና በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተሞች ችግሩ በስፋት ይታይ እንደነበር የገለፁት ኃላፊው በአሁኑ ወቅት ችግሩን ለመፍታት እተሰራ ይገኛል ብለዋል፡፡

እስከ አሁን በልዩ ልዩ ወንጀሎች ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር የዋሉ 108 ግለሰቦች ላይ 84 የምርመራ መዝገቦችን በማደራጀት የህግ አግባብ ሂደቱ መቀጠሉን ም/ኮሚሽነር ዘላለም መንግስቴ ተናግረዋል።

ምንጭ፦ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ፎቶ⬆️የኤርትራ ልዑካን ዛሬ ትግራይ ክልል አዲግራት ከተማ ገብተዋል።

©ዶክተር ኪሮስ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update⬆️ጠ/ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ አቶ #ጌትነት_ታደሰን የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ዋና ስራ አስፈፃሚ አድርገው #ዛሬ ሾመዋል። አቶ ጌትነት ታደሰ በዋልታ ሚዲያና ኮሙኒኬሽን ኮርፖሬት ፡ የሚዲያ ኔትወርክ ስራ አስፈፃሚ ሆነው ሲያገለግሉ ነበር።

©ዋልታ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update⬆️ጠ/ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ አቶ #ይድነቃቸው_ወርቁ_ካሳ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ሆነው እንዲሰሩ ሾመዋቸዋል። አቶ ይድነቃቸው ወርቁ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ሆነው የተሾሙት የቀድሞው ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ኢንጅነር አብርሃም በላይ፥ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሃይል ዋና ስራ አስፈጻሚ ሆነው መሾማቸውን ተከትሎ ነው።

©ዋልታ
@tsegabwolde @tikvahethiopia