TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ማሳሰቢያ📌ውድ የአጠቃላይ የ2ኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ ሰርተፍኬት /የ10ኛ ክፍል/ ተፈታኝ ተማሪዎችና የተማሪ ወላጆች ከግንቦት
22-24/2010 ዓ.ም የኢትዮጵያ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ ሰርተፍኬት /የ10ኛ ክፍል ፈተና/ ለ1,200,676 ተማሪዎች እንዲሁም ከግንቦት 27-30/2010 ዓ/ም የኢትዮጵያ ዩንቨርስቲ መግቢያ ፈተና (የ12 ክፍል ፈተና) 284,312 ተማሪዎች መሰጠቱ ይታወሳል፡፡

የፈተናውን መሰጠት ተከትሎም ወደ እርማት ስራው በመግባት ከምንጊዜውም በፈጠነ መልኩ የ12ኛ ክፍል ውጤት በ24/11/2010
ዓ/ም ይፋ የተደረገ ሲሆን አስከትሎም የ10ኛ ክፍልን ወደ ማረም ሂደት ውስጥ ተገብቷል፡፡

እንደ 12ኛ ክፍሉ ሁሉ የ10ኛውም ፈተና ጥንቃቄ በተሞላበት ሁኔታ ከጥቃቅን የዳታ ማጥራት ስራዎች በስተቀር በሰላም እየተጠናቀቀ መሆኑን ልናሳውቅ እንወዳለን፡፡ ከነሐሴ 25-30/2010 ዓ.ም ይለቀቃል ተብሎ ተደራሽ ተደርጎ የነበረውን መረጃ መሰረት በማድረግ በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች የተለያዩ አሉታዊ መረጃዎች በመሰራጨት ላይ መሆናቸውን በመረዳታችን ከላይ በተገለጸው አግባብ የፈተና እርማቱ በሰላም #በመጠናቀቅ ላይ እንደሚገኝ እና በቀጣዮቹ #ጥቂት ቀናት ውስጥ ውጤቱ ይፋ እንደሚሆን እየገለጽን #በትዕግስት ትጠባበቁን ዘንድ መልዕክታችንን እናስተላልፋለን፡፡

የውጤቱን መለቀቅ አስመልክቶም ለተለያዩ ሚዲያዎች መግለጫ የምንሰጥ መሆኑን እናሳውቃለን!

መልካም ዕድል!

©NEAEA
@tsegabwolde @tikvahethiopia