#update አዲስ አበባ⬆️
የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ከሌሎች የጸጥታ አካላት ጋር በዳረገው የተቀናጀ ዘመቻ በተለያዩ የዘረፋና የኢኮኖሚ ወንጀሎች ላይ ተሳትፈዋል ያላቸውን 108 ተጠርጣሪዎች እና የወንጀሎቹ ፍሬ የሆኑ ኤግዚቢቶችን መያዙን የኮሚሽኑ የወንጀልና ትራፊክ አደጋ መከላከል
ምክትል ኮሚሽነር ዘላለም መንግስቴ ገልፀዋል፡፡
እንዲሁም ተጠርጣሪዎቹ ሲገለገሉባቸው የነበሩ ጦር መሳሪያዎችንና ሞተር ሳይክሎችን መያዙን ምክትል ኮሚሽነር ዘላለም መንግስቴ ተናግረዋል፡፡
በአዲስ አበባ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በተለያዩ አካባቢዎች እየተበራከተ የመጣውን የወንጀል ድርጊት ተከትሎ ነዋሪው ያነሳቸውን ጥያቄዎች በመቀበል የተለያዩ የፀጥታ አካላትን ያሳተፈ በጥናት ላይ የተደገፈ የወንጀል መከላከል ተግባር መከናወኑን ኃላፊው አስረድተዋል፡፡
ተጠርጣሪዎቹ በጦር መሳሪያ የታገዘ ዘረፋ ፣ ለጋራ መኖሪያ ቤት ግንባታ የሚውሉ የኤሌትሪክ ኬብሎችን መስረቅ፣ ሞተር ሳይክል በመጠቀም የቅሚያ #ወንጀሎችን ሲፈፅሙ መቆየታቸውን ም/ኮሚሽነር ዘለላም ተናግረዋል፡፡
ፖሊስ ባደረገው ክትትል ህገ ወጥ የውጭ ሀገር የገንዘብ ዝውውር ላይ ተሳትፎ የነበራቸውን ተጠርጣሪዎች እና የተለያዩ ሀገራት ገንዘቦችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን ተናግረዋል፡፡
በሌላም በኩል ወቅታዊ ሁኔታዎችን እንደ መልካም አጋጣሚ በመጠቀም በተለያዩ ክፍለ ከተሞች በህገ ወጥ መንገድ የመሬት ወረራ እየተስተዋለ መሆኑንም ም/ ኮሚሽነሩ ገልፀዋል።
በተለይም ከኦሮሚያ ልዩ ዞን ጋር በሚዋሰኑ በኮልፌ ቀራኒዮ፣ በቦሌ፣ በየካና በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተሞች ችግሩ በስፋት ይታይ እንደነበር የገለፁት ኃላፊው በአሁኑ ወቅት ችግሩን ለመፍታት እተሰራ ይገኛል ብለዋል፡፡
እስከ አሁን በልዩ ልዩ ወንጀሎች ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር የዋሉ 108 ግለሰቦች ላይ 84 የምርመራ መዝገቦችን በማደራጀት የህግ አግባብ ሂደቱ መቀጠሉን ም/ኮሚሽነር ዘላለም መንግስቴ ተናግረዋል።
ምንጭ፦ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን
@tsegabwolde @tikvahethiopia

#ቤንች_ሸኮ
በቤንቺ ሸኮ ዞን ተፈጥሮ በነበረው የጸጥታ ችግር በመሳተፍ የተለያዩ #ወንጀሎችን ፈጽመዋል የተባሉ ግለሰቦች በህግ ተጠያቂ እየተደረጉ መሆኑ ተገለፀ። ካለፈው ህዳር ወር ጀምሮ በቤንች ሸኮ ዞን ተፈጥሮ በነበረው የጸጥታ ችግር በመሳተፍ በሰው ግድያ፣ የአካል ጉዳት በማድረስ፣ ንብረት በማውደምና ዘረፋ በመፈጸም ወንጀል ተሳትፈዋል በሚል የተጠረጠሩ ግለሰቦች በህግ ተጠያቂ እየተደረጉ ነው።
የቤንች ሸኮ ዞን ፖሊስ መምሪያ አዛዥና የኮማንድ ፖስት አባል ዋና ኢንስፔክተር ምናሉ ታደሰ እንደገለፁት ከ100 በላይ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ውለው ጉዳያቸው በፍርድ ቤት ተጣርቶ በእስራት እንዲቀጡ እየተደረገ ነው። በጦር መሳሪያ ታግዘው ከባድ ወንጀል የፈጸሙና በአስገድዶ መድፈር መሳተፋቸው በማስረጃ የተረጋገጠባቸው አራት ግለሰቦች ከ8 እስከ 20 ዓመት በሚደርስ እስራት እንዲቀጡ መደረጉን ዋና ኢንስፔክተሩ ተናግረዋል።
Via #ENA

👍1