#AtoBulchaDemeksa
ጉምቱው ፖለቲከኛ አቶ ቡልቻ ደመቅሳ ከዚህ አለም በሞት ተለዩ።
በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ትልቅ ስም የነበራቸው ጉምቱው ፖለቲከኛ አቶ ቡልቻ ደመቅሳ ዛሬ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል።
የኢፌዴሪ ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ በአቶ ቡልቻ ደመቅሳ ህልፈት የተሰማቸውን ሀዘን ገልጸዋል።
" አቶ ቡልቻ ደመቅሳ በማረፋቸው የተሰማኝን ኀዘን እገልጻለሁ " ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ " በሚችሉት ሁሉ ሀገራቸውንና አፍሪካን ያገለገሉ፣ በአቋማቸው ጽኑ፣ ሕዝቦችን ለማቀራረብ የተጉ፣ እውነት ነው ብለው ያመኑትን የትምና መቼም የሚናገሩ ነበሩ " ብለዋቸዋል።
" እንዲህ ዓይነት ብርቱ ሽማግሌዎችን ማጣት ጉዳቱ ለሀገር ነው። ፈጣሪ ነፍሳቸውን ይቀበላት " ሲሉም ገልጸዋል።
@tikvahethiopia

TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
ትውስታ ...
አቶ ቡልቻ ደመቅሳ በምን ይታወሳሉ ?
በኢህአዴግ ጊዜ የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ መለስ ዜናዊ ሀገራቸውን በሚመሩበት ወቅት ፓርላማ የነበሩት ጉምቱው ፖለቲከኛ እና የኢኮኖሚ ምሁር አቶ ቡልቻ ደመቅሳ ጠንከር ያሉ ምሁራዊ ጥያቄዎችን ለጠቅላይ ሚኒስትሩ በማንሳት ይታወቃሉ።
ንግግራቸው ለዛ የነበረው ፣ የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስን ጨምሮ መላ የፓርላማ አባላትን ሳቅ በሳቅ የሚያድረግ ፤ ድፍረትና እውቀት የተሞላበት ነበር።
በተለይ ደግሞ በኢኮኖሚ ጉዳዮች ላይ የዳበረ እውቀት ስለነበራቸው ሁሉም ሰው እሳቸው እድሉን አግኝተው እስኪናገሩ በጉጉት ነበር የሚጠብቀው።
በብዙዎች የሚታወሰው እና ሁሌም ተደጋግሞ የሚነሳው ከኢትዮጵያ ኢኮኖሚ እድገት ጋር በተያያዘ ያነሱት ጥያቄና ፓርላማውን ሳቅ በሳቅ ያደረጉበት ንግግራቸው ነው።
" ጠቅላይ ሚኒስትሩ ፣ መንግስቱም ደጋግሞ ደጋግሞ ' ኢትዮጵያ በ110 ፣ በ111 አድጋለች ' ይላል ፤ እኔ ፣ እሳቸውም የኢትዮጵያ ኢኮኖሚስቶችም ያውቃሉ በ111 ማደግ ማለት ተአምር ነው። ይሄን ተአምር የሰራችው ቻይና እንደውም አሁን እየሰራች አይደለም ፣ ታይዋን ፣ ደቡብ ኮሪያ ናቸው።
ኢትዮጵያ እንዴት አድርጋ ነው በ111 ያደገቸው ? አንጎላ አሁን በ112 እያደገ ነው ለምንድነው በአንድ ጊዜ ብዙ ዘይት አገኙ፣ ዘይት ያገኙ ሰዎች ወይም ሌላ ነገር ያገኙ በ110 ወይም በ111 ቢያድጉ አይገርምም። 111 አደግን ብለን ለዓለምስ እንዴት አድርገን ነው የምንገልጸው ?
የዓለም የገንዘብ ድርጅት ኢትዮጵያ እና ሌሎች የምስራቅ አፍሪካ ሀገሮች ቢበዛ በ106 ያድጋሉ ብሏል እኛ ግን እንቢ ብለን ' አስራ አንድ ነው ! ' እንላለን ይሄ ተገቢ ነው ? "
ሌላ በእጅጉ ከሚታወሱበት ንግግራቸው መካከል ደግሞ መንግሥት ስለሚሳተፍባቸው የተለያዩ ሽያጮች ጉዳይ ነው።
" መንግሥት ለምንድነው ማዳበሪያን የሚሸጠው ብቻውን ? ፤ መንግሥት ለምንድነው ሆቴል ውስጥ ገብቶ የሚነግደው ? ፤ መንግሥት ለምንድነው ቱሪዝም ውስጥ ገብቶ የሚነግደው ? ፤ መንግሥት ለምንድነው ሲሚንቶ የሚሸጠው ? ፤ አልፎ ፍራፍሬ ሽንኩርት የሚሸጠው ለምንድነው ? መንግሥት ሶሻሊት ኢኮኖሚ አይደለም የሚያራምደው ? "
አቶ ቡልቻ ደመቅሳ በምዕራብ ወለጋ የተወለዱ ሲሆን በትላልቅ ዩኒቨርሲቲዎች የተማሩ የተዋጣላቸው የኢኮኖሚ ምሁር ነበሩ። የአዋሽ ባንክ እንዲሁም የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስን (ኦፌኮ) መስራችም ነበሩ።

#MoE
የመውጫ ምዘና ከየካቲት 10 እስከ የካቲት 12 /2017 ዓ/ም ድረስ እንደሚሰጥ ተገለጸ።
በክረምት በመምህርነት ሙያ ከዲፕሎማ ወደ መጀመሪያ ድግሪ የትምህርት ደረጃ ማሻሻያ ስልጠና ሲከታተሉ ቆይ የመውጫ ምዘና ለሚጠባበቁ መምህራን የመውጫ ምዘና የሚሰጥበት ቀን ይፋ ተደርጓል።
በዚህም የመውጫ ምዘናው ከየካቲት 10 እስከ የካቲት 12/2017 ዓ.ም የሚሰጥ ሲሆን መምህራኑ አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት እንዳያድረጉ ሲል ትምህርት ሚኒስቴር አሳስቧል።
ሚኒስቴሩ ምዘናው በየአቅራቢያ ባሉ ዩኒቨርስቲዎች የሚሰጥ መሆኑን ገልጾ " በቀጣይ ክልል / ከተማ አስተዳደር ት/ቢሮዎች በኩል የምናሳውቃችሁ ይሆናል " ብሏል።
#MinistryofEducation

#የአእላፋትዝማሬ #TheMelodyofMyriads “ ኦርቶዶክሳዊያን ወጣቶች ልደትን በቤተ ክርስቲያን አሳልፉ ፤ በአዲስ አበባና በድሬዳዋ የምትገኙም በዝማሬው ላይ እንድትገኙ ” - የኢትዮጵያ ጃንደረባው ትውልድ (ኢጃት) ታኅሳስ 29 ቀን 2017 ዓ/ም የሚከበረውን ኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል ምክንያት በማድረግ የኢትዮጵያው ጃንደረባ ትውልድ ያዘጋጀው “ልደትን በባለ ልደቱ ቤት” የተሰኘውን የአእላፍ…
#የአእላፋትዝማሬ #TheMelodyofMyriads
በዓልን በማይገባ ቦታ የሚያሳልፉ በእግዚአብሔር ቤት ሆነው እንዲያሳልፉ ለማድረግ ዓላማ ያለው የአእላፋት ዝማሬ / The Melody of Myriads መርሐግብር ዛሬ ሰኞ በገና ዋዜማ በአዲስ አበባ እና ድሬዳዋ ይከናወናል።
ቦታው ፦
👉አዲስ አባባ ፦ ቦሌ በድብረ ሳሌም መድኃኔዓለም
👉 ድሬዳዋ ፦ ለገሀር አደባባይ
ከነዚህ ከተሞች ውጭ በኢትዮጵያዊው ጃንደረባ ትውልድ / ኢጃት አማካኝነት የተዘጋጀት የአእላፋት ዝማሬ መርሐግብር የሌለ ቢሆንም ሁሉም ምእመናን ፣ ኦርቶዶክሳዊያን ሁሉ በዓሉን ቤተክርስቲያን እንዲያሳልፉት ጥሪ ቀርቧል።
በአዲስ አበባ እና ድሬዳዋ ምእመናን ከዝማሬው በፊት ልክ 10:00 ሰዓት ላይ ተገኝተው የአንድ ሰዓት ጸሎተ የምሕላና ጸሎተ ኪዳን ላይ እንዲሳተፉ አደራ ተብሏል።
የዘንድሮው የአእላፋት ዝማሬ ከአምናው በተለየ ጥራት ለማካሄድ በየትኛውም ቦታ የቆመ ሰው የሚሰማው ድምጽ ሆነ የሚያየው ምስል እኩል እንዲሆን ጥረት ተደርጓል።
ለነፍሰ ጡሮች እና የአካል ጉዳተኞች ልዩ ስፍራ የተዘጋጀ ሲሆን ለአስተባባሪዎች በመንገር ቦታ ማግኘት ይቻላል።
የጤና እክል ለሚያጋጥማቸው ተንቀሳቃሽ ክሊኒኮች አሉ።
የመኪና ማቆሚያን በተመለከተ በቤተክርስቲያን ቅፅጽረ ግቢ ሆነ አስፋልት ዳር መኪና ማቆም ተከልክሏል። መኪና ማቆም የሚቻለው ከህንጻዎቹ ጀርባ ነው።
መኪና ያላችሁ መርሐግብሩ ሲጠናቀቅ ወደናተ አቅጣጫ የሚሄዱትን በመጫን የትራንስፖርት ሰርቪስ እንድትሰጡ አደራ ተብሏል።
ወደ መርሐግብሩ የምትመጡ ነጭ ልብስ አድርጋችሁ እንድትመጡ ያንን ማድረግ ያልቻላችሁ ያላችሁን ልብስ ንጹህ አድርጋችሁ እንድትመጡ ጥሪ ቀርቧል።
በቂ ከበሮ ስለተዘጋጀ ከበሮ ይዞ መምጣት አያስፈልግም።
ቦሌ መድኃኔዓለም በጊብሰን በኩል ያለው በር ለቅዱስ ፓትርያርኩና ለሊቃነ ጳጳሳት መግቢያ ስለሆነ ምእመናን ሌሎች በሮችን እንዲጠቀሙ ተብሏል።
ድሬዳዋ ምድር ባቡር አደባባይ የሚያስገቡትን 5 በሮች መጠቀም ይቻላል።
በመርሐግብሩ በቂ ጥበቃ የተመደበ ሲሆን ፍተሻም ይኖራል።
ምን ይዞ መገኘት / መግባት አይቻልም ?
➡ መሳሪያዎች
➡ ተቀጣጣይ ነገሮች
➡ የግል ካሜራ ፣ ድሮን
➡ ሽቶና ስፕሬይ
➡ ኮስሞቲክስ
➡ ክብሪት
➡ ስክሪብቶና የሾሉ ነገሮች
➡ የግል ከበሮ ይዞ መምጣት ክልክል ነው።
ወደ አእላፋት ዝማሬ የሚመጡ ምዕመናን እስከ 10 ጧፍ ይዘው እንዲመጡ ጥሪ ቀርቧል።
ሦስቱ ጧፎች የአእላፋት ዝማሬ / The Melody of Myriads / እስኪጠናቀቅ የሚበሩ ሲሆን የቀሩትን ለደብሩ በመባ መልክ ያስረክቡ። በደብሩ በኩልም ለገጠር አብያተ ክርስትያናት ድጋፍ ይደረጋል ተብሏል።
NB. የዕለቱን ሁነት የሚቀርጹ ፣ በቀጥታም የሚያስተላልፉ መገናኛ ብዙሃን ስላሉ ምእመናን በዝማሬና ምስጋና ላይ ብቻ ትኩረት እንዲያደርጉ ጥሪ ቀርቧል።
' ልደቱን በባለ ልደቱ ቤት ! '
#TheMelodyofMyriads
#TikvahEthiopiaFamilyAA

#ብርሃን_ባንክ
እንኳን ለጌታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል አደረሳችሁ!
በዚህ የበዓል ወቅት ከውጭ ሃገራት የሚላክልዎትን ገንዘብ በብርሃን ባንክ በኩል ሲቀበሉ ወይም በእጅዎ ያለውን የውጭ ሃገር ገንዘብ በባንካችን ሲመነዝሩ ከእለቱ የውጭ ምንዛሪ ተመን በተጨማሪ 2% እና ልዩ የበዓል ስጦታ ያገኛሉ!
እንደ ስማችን ብርሃን ነው ሥራችን!
#Christmas #moneytransfer #Stressfreebanking #berhanbank #bank #finance #bankinethiopia
➡️ Facebook
➡️ Telegram
➡️ Instagram
➡️ Twitter
➡️ LinkedIn
➡️ YouTube
እንኳን ለጌታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል አደረሳችሁ!
በዚህ የበዓል ወቅት ከውጭ ሃገራት የሚላክልዎትን ገንዘብ በብርሃን ባንክ በኩል ሲቀበሉ ወይም በእጅዎ ያለውን የውጭ ሃገር ገንዘብ በባንካችን ሲመነዝሩ ከእለቱ የውጭ ምንዛሪ ተመን በተጨማሪ 2% እና ልዩ የበዓል ስጦታ ያገኛሉ!
እንደ ስማችን ብርሃን ነው ሥራችን!
#Christmas #moneytransfer #Stressfreebanking #berhanbank #bank #finance #bankinethiopia
➡️ Telegram
➡️ YouTube
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
ፎቶ ፦ የ2017 ዓ/ም የአእላፋት ዝማሬ / The Melody of Myriads በአዲስ አበባና ድሬዳዋ እየተከናወነ ይገኛል።
በአዲስ አበባ መርሐግብር እጅግ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ምዕመን ተገኝቶ የልደት በዓል ዋዜማን በዝማሬ እንዲሁም በምስጋና እያከበረ ይገኛል።
@tikvahethiopia
በአዲስ አበባ መርሐግብር እጅግ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ምዕመን ተገኝቶ የልደት በዓል ዋዜማን በዝማሬ እንዲሁም በምስጋና እያከበረ ይገኛል።
@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" አሁን ያለው የመሬት መንቀጥቀጥ ማብቃቱ አይቀርም፤ ነገር ግን መች እንደሚያበቃ ማወቅ አይቻልም " - አታላይ አየለ (ፕ/ር) በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጂኦ ፊዚክስ ሕዋ ሣይንስ እና አስትሮኖሚ ተቋም የሴስሞሎጂ ትምህርት ክፍል ኃላፊ፣ የመሬት መንቀጥቀጥ ሣይንስ መምህርና ተመራማሪ አታላይ አየለ (ፕ/ር) ምን አሉ ? " ዛሬ በአፋር ክልል ፥ በዱለቻ ወረዳ በዶፋን ተራራ ላይ የተከሰተው ጭስ እና እንፋሎት…
“ይሄ ፌሪያቲክ ኢራፕሽን ይባላል። ብዙ ጊዜ ቅልጥ አለቱ ወደ ላይ መጠጋቱን አንዱ ማመላከቻ ነው ” - ኤልያስ ሌዊ (ዶ/ር)
በአፋር ክልል የመሬት መንቀጥቀጥ ከተስተዋለባቸው አካባቢዎች ተጠቃሽ በሆነው ዱለቻ ወረዳ ዶፋን ተራራ ሰሞኑን “ የእሳተ ገሞራ ፍንዳታ ተከሰተ ” መባሉ ይታወቃል።
በዚህም በነዋሪዎች ላይ ጉዳት እንዳያደርስ እየተሰራ መሆኑ ሰሞኑን ተገልጿል።
ተከሰተ የተባለውን የእሳተ ገሞራ ፍንዳታ በተመለከተ፣ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጂኦፊዚክስ፣ ስፔስ ሳይንስ እና አስትሮኖሚ ተቋም ዳይሬክተር ኤልያስ ሌዊ (ዶ/ር) ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ማብራሪያ ሰጥተዋል።
ዳይሬክተሩ ምን አሉ ?
“ እሳተ ገሞራ እስካሁን አልፈነዳም። እሳተ ገሞራ ፈነዳ የሚለው መታረም አለበት። እስካሁን የመጣውን ፌሪያቲክ ኢራፕሽን እንለዋለን።
እንፋሎት እና የአለት ስብርባሪዎች ናቸው በከፍተኛ ግፊት ወደ ላይ ወደ መሬት እየተወረወሩ የሚወጡት። ይሄም የጋለ መሬት ውስጥ ያለ ውሃ አለ። ያም ከታች ማግማው እየተጠጋ ሲሄድ ይግላል።
ውሃው በከባድ ፕሬዠር መሬት ውስጥ ታምቆ ስለሚቆይ ቅልጥ አለቱ ወደ ላይ እየተጠጋ ሲመጣና ውሃውን ያቀፈውን አለት ሲያበላው ውሃው በጣም ስለሚፈላ በጉልበት በየስንጥቁ ተመንጭቆ ነው የሚወጣው።
ከትላንትና በስቲያ የሆነው ይሄ ነው። እርግጥ የጭቃ፣ የድንጋይ ስብርባሪዎች ጠራርጎ ይዞ ወጥቷል። ይሄ ፌሪያቲክ ኢራፕሽን ይባላል። ብዙ ጊዜ ቅልጥ አለቱ ወደ ላይ መጠጋቱን አንዱ ማመላከቻ ነው።
ይሄ ማለት ግን ይፈነዳል ብቻ ማለትም አይደለም። ሊፈነዳ ይችላል፤ ላይፈነዳም ይችላል እንጂ።
ነገር ግን ከትላንትና በስቲያ በብዙ ቦታ ላይ ‘ተነፈሰ፣ ፈነዳ’ ሲባል ነበር። ይህ ትክክል አይደለም። እሳተ ገሞራ ሲፈነዳ እንዲህ ቀላል አይደለም።
ለማንኛውም ግን ይሄም ቢሆን ለጤና አደገኛ የሆኑ ጋዞች ይዞ ሊወጣ ስለሚችል ይህን ስብስቦ ከአካባቢው ማራቅ አስፈላጊ ነው።
ብዙ ሰዎች አካባቢው ሲሯሯጡ አንዳንድ መረጃዎች ያሳዩ ነበር።
ስለዚህ እስካሁን ቅልጥ አለት ወደ መሬት ላይ አልመጣም። እሳተ ገሞራ ፍንዳታ አልነበረም። ይሄ መታረም ያለበት ነገር ነው ማስረዳትም ያስፈልጋል።
አልፈነዳም። ቮልካኒክ ኢራፕሽን የለም። ነገር ግን ይሄ ፌሪያቲክ ኢራፕሽን ራሱ ጋዝ፣ ሽታ ሊፈጥር ይችላል።
የፈላው ውሃ ራሱ ሰዎችን ያቃጥላል፣ እንፋሎት ነውና። ተስፈንጥሮ የሚወጣው ጭቃ ራሱ የጋለ ጭቃ ነው። ያ፣ ያአደጋ ሊያደርስ ይችላል። ግን የእሳተ ገሞራ ፍንዳታ እኛ እስካሁን አልሰማንም" ብለዋል።
#TikvahEthipiaFamilyAA