TIKVAH-ETHIOPIA
#መግለጫ : " የአእላፋት ዝማሬ/The Melody of Myriads " ሰኞ በአዲስ አበባ እና በድሬዳዋ በተመሳሳይ ሰዓት ይካሄዳል። ይህንን አስመልክቶ የተሰጠው መግለጫ ከላይ ተያይዟል። የዘንድሮው የእላፋት ዝማሬ / The Melody of Myriads በአዲስ አበባ በቦሌ ደብረ ሳሌም መድኃኔዓለም ካቴድራል (ቦሌ መድኃኔዓለም) ፤ በድሬዳዋ ደግሞ ለገሀር አደባባይ ብቻ ነው የሚካሄደው። (መግለጫውን ያንብቡ)…
#የአእላፋትዝማሬ #TheMelodyofMyriads
“ ኦርቶዶክሳዊያን ወጣቶች ልደትን በቤተ ክርስቲያን አሳልፉ ፤ በአዲስ አበባና በድሬዳዋ የምትገኙም በዝማሬው ላይ እንድትገኙ ” - የኢትዮጵያ ጃንደረባው ትውልድ (ኢጃት)
ታኅሳስ 29 ቀን 2017 ዓ/ም የሚከበረውን ኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል ምክንያት በማድረግ የኢትዮጵያው ጃንደረባ ትውልድ ያዘጋጀው “ልደትን በባለ ልደቱ ቤት” የተሰኘውን የአእላፍ ዝማሬ በተመለከተ አዘጋጆቹ ዛሬ በስካይ ላይት ሆቴል መግለጫ ሰጥተዋል።
የዝማሬ ጉባዔው በአዲስ አበባ በድሬዳዋ እንደሚከናወን የገለጹት አዘጋጆች፣ “ ላለፉት ስምንት ወራት ለዚህ ታላቅ የዝማሬ ጉባዔ ከፍተኛ ዝግጅት ሲደረግ ቆይቷል ” ብለዋል።
የጉባዔው ዋነኛ ዓላማ በአልባሌ ቦታ የሚውሉ ወገኖች በዓሉን በቤተክርስቲያን የመላክትን ዝማሬ በመዘመር እንዲያሳልፉ ለማድረግ ያለመ መሆኑ ተመልክቷል።
የኢትዮጵያው ጃንረባ ትውልድ ቦርድ ምክትል ሰብሳቢ አቶ ቢንያም አሕመድ ፤ “ ኦርቶዶክሳዊያን ወጣቶች ልደትን በቤተ ክርስቲያን አሳልፉ ፤ በአዲስ አበባና በድሬዳዋ የምትገኙም በዝማሬው ላይ እንድትገኙ ” ብለዋል።
“ በሌሎች አካባቢዎች ላይ የተዘጋጁ ዝግጅቶች ካሉም በእዛው በመገኘት እንድታሳልፉ የኢትዮጵያ ጃንደረባው ትውልድ ጥሪ ያቀርባል ” ሲሉ አሳስበዋል።
በመርሃ ግብሩ በቤተክርስቲያን ቅጽር ግቢ ውስጥ ምንም አይነት ሽያጭ እንደማይከናውን አዘጋጆቹ አሳውቀዋል።
በሌላ በኩል፣ “ አእላፋት ዝማሬ ነጭ ልብስ ልበሱ ” ተብሏል በሚል ነጭ ልብስ በተጋነነ ዋጋ የሚቸበችቡ ሁነቱን የተከተሉ ነጋዴዎች ተስተውለዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ፣ ነጭ ልብስ በውድ ወጋ እየተቸበቸበ ነው የሚል አስተያዬት እየተሰጠ ተስተውሏል፣ ለመርሀ ግብሩ ነጭ ልብስ ብቻ ለብሶ መምጣት ግዴታ ነው ? ሲል ለአዘጋጆቹ ጥያቄ አቅርቧል።
የኢትዮጵያው ጃንረባ ትውልድ ቦርድ ምክትል ሰብሳቢ አቶ ብንያም አሕመድ በሰጡት ምላሽም፣ “ ነጭ ልብስ የሌለን ያለንን ልብስ ንጹህ አድርገን እንምጣ። ዓላማችን ልብሱ ለመቁረቢያ እንዲሆን ነው ” ብለዋል።
“ ኦርቶዶክሳዊ ኢኮኖሚ እንዲፈጠር ይፈለጋል ግልጽ ነው። በዚህ ምክንያት ወደ ስራ የሚገቡ፣ ሥራቸውን የሚያስፋፉ፣ የሚለወጡ ኦርቶዶክሳዊያን ቢኖሩ ይሄ የማኀበራችን አንዱ ዓላማ ነው ” ሲሉ ነው የተናገሩት።
“ ስለዚህ ይህን በቀና ዓይን ነው የምናየው ” ያሉት አቶ ብንያም፣ “ በእርግጥ በዚሁ ምክንያት ደግሞ አጋጣሚውን የሚጠቀሙ፣ Accidental Entrprenuers የምንላቸው መጥተው ባለሃብት ለመሆን የሚጥሩ ይኖራሉ ” ሲሉም አክለዋል።
“ ልደቱ የሰዎች የመላክት ዝማሬ ነው። ስለዚህ ይህንን በማሰብ ነጭ ለብሰን እንመጣለን ” ብለው፣ “ ዘወትር ወደ ቤተ ክርስቲያን ስንሄድ የምናደርገው ነው፣ የተለዬ ነገር የለውም ” ነው ያሉት።
ሆኖም ነጭ ልብስ የሌላቸው ያላቸውን ልብስ በአግባቡ ለብሰው በዝማሬ መርሀ ግብሩ መገኘታቸው እንዳይዘነጋ መልዕክት ተላልፏል።
ዝማሬው ዘማሪያን እየዘመሩ ምዕመናን የሚቀበሉበት ሂደት ሳይሆን ልደቱን በሚያወሱ ዝማሬዎች ሁሉም በጋራ ምስጋና እንዲያቀርብ መሆኑ ተሰምሮበታል።
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia

#የአእላፋትዝማሬ #TheMelodyofMyriads “ ኦርቶዶክሳዊያን ወጣቶች ልደትን በቤተ ክርስቲያን አሳልፉ ፤ በአዲስ አበባና በድሬዳዋ የምትገኙም በዝማሬው ላይ እንድትገኙ ” - የኢትዮጵያ ጃንደረባው ትውልድ (ኢጃት) ታኅሳስ 29 ቀን 2017 ዓ/ም የሚከበረውን ኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል ምክንያት በማድረግ የኢትዮጵያው ጃንደረባ ትውልድ ያዘጋጀው “ልደትን በባለ ልደቱ ቤት” የተሰኘውን የአእላፍ…
#የአእላፋትዝማሬ #TheMelodyofMyriads
በዓልን በማይገባ ቦታ የሚያሳልፉ በእግዚአብሔር ቤት ሆነው እንዲያሳልፉ ለማድረግ ዓላማ ያለው የአእላፋት ዝማሬ / The Melody of Myriads መርሐግብር ዛሬ ሰኞ በገና ዋዜማ በአዲስ አበባ እና ድሬዳዋ ይከናወናል።
ቦታው ፦
👉አዲስ አባባ ፦ ቦሌ በድብረ ሳሌም መድኃኔዓለም
👉 ድሬዳዋ ፦ ለገሀር አደባባይ
ከነዚህ ከተሞች ውጭ በኢትዮጵያዊው ጃንደረባ ትውልድ / ኢጃት አማካኝነት የተዘጋጀት የአእላፋት ዝማሬ መርሐግብር የሌለ ቢሆንም ሁሉም ምእመናን ፣ ኦርቶዶክሳዊያን ሁሉ በዓሉን ቤተክርስቲያን እንዲያሳልፉት ጥሪ ቀርቧል።
በአዲስ አበባ እና ድሬዳዋ ምእመናን ከዝማሬው በፊት ልክ 10:00 ሰዓት ላይ ተገኝተው የአንድ ሰዓት ጸሎተ የምሕላና ጸሎተ ኪዳን ላይ እንዲሳተፉ አደራ ተብሏል።
የዘንድሮው የአእላፋት ዝማሬ ከአምናው በተለየ ጥራት ለማካሄድ በየትኛውም ቦታ የቆመ ሰው የሚሰማው ድምጽ ሆነ የሚያየው ምስል እኩል እንዲሆን ጥረት ተደርጓል።
ለነፍሰ ጡሮች እና የአካል ጉዳተኞች ልዩ ስፍራ የተዘጋጀ ሲሆን ለአስተባባሪዎች በመንገር ቦታ ማግኘት ይቻላል።
የጤና እክል ለሚያጋጥማቸው ተንቀሳቃሽ ክሊኒኮች አሉ።
የመኪና ማቆሚያን በተመለከተ በቤተክርስቲያን ቅፅጽረ ግቢ ሆነ አስፋልት ዳር መኪና ማቆም ተከልክሏል። መኪና ማቆም የሚቻለው ከህንጻዎቹ ጀርባ ነው።
መኪና ያላችሁ መርሐግብሩ ሲጠናቀቅ ወደናተ አቅጣጫ የሚሄዱትን በመጫን የትራንስፖርት ሰርቪስ እንድትሰጡ አደራ ተብሏል።
ወደ መርሐግብሩ የምትመጡ ነጭ ልብስ አድርጋችሁ እንድትመጡ ያንን ማድረግ ያልቻላችሁ ያላችሁን ልብስ ንጹህ አድርጋችሁ እንድትመጡ ጥሪ ቀርቧል።
በቂ ከበሮ ስለተዘጋጀ ከበሮ ይዞ መምጣት አያስፈልግም።
ቦሌ መድኃኔዓለም በጊብሰን በኩል ያለው በር ለቅዱስ ፓትርያርኩና ለሊቃነ ጳጳሳት መግቢያ ስለሆነ ምእመናን ሌሎች በሮችን እንዲጠቀሙ ተብሏል።
ድሬዳዋ ምድር ባቡር አደባባይ የሚያስገቡትን 5 በሮች መጠቀም ይቻላል።
በመርሐግብሩ በቂ ጥበቃ የተመደበ ሲሆን ፍተሻም ይኖራል።
ምን ይዞ መገኘት / መግባት አይቻልም ?
➡ መሳሪያዎች
➡ ተቀጣጣይ ነገሮች
➡ የግል ካሜራ ፣ ድሮን
➡ ሽቶና ስፕሬይ
➡ ኮስሞቲክስ
➡ ክብሪት
➡ ስክሪብቶና የሾሉ ነገሮች
➡ የግል ከበሮ ይዞ መምጣት ክልክል ነው።
ወደ አእላፋት ዝማሬ የሚመጡ ምዕመናን እስከ 10 ጧፍ ይዘው እንዲመጡ ጥሪ ቀርቧል።
ሦስቱ ጧፎች የአእላፋት ዝማሬ / The Melody of Myriads / እስኪጠናቀቅ የሚበሩ ሲሆን የቀሩትን ለደብሩ በመባ መልክ ያስረክቡ። በደብሩ በኩልም ለገጠር አብያተ ክርስትያናት ድጋፍ ይደረጋል ተብሏል።
NB. የዕለቱን ሁነት የሚቀርጹ ፣ በቀጥታም የሚያስተላልፉ መገናኛ ብዙሃን ስላሉ ምእመናን በዝማሬና ምስጋና ላይ ብቻ ትኩረት እንዲያደርጉ ጥሪ ቀርቧል።
' ልደቱን በባለ ልደቱ ቤት ! '
#TheMelodyofMyriads

Photo
#አእላፋትዝማሬ #TheMelodyofMyriads
በአዲስ አበባ አእላፋት የተሳተፉበት " የአእላፋት ዝማሬ / The Melody of Myriads " መርሐግብር በቦሌ በድብረ ሳሌም መድኃኔዓለም ተከናውኗል።
ይህ ዘንድሮ ለ2ኛ ጊዜ የተከናወነው መርሐግብር ከአምናውን የላቀ የምእመን ቁጥር የተገኘበት እንደሆነ በስፍራው በመገኘት ለመገንዘብ ችለናል።
መርሐግብሩ ላይ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት እንዲሁም ብፁአን አባቶች ተገኝተው ነበር።
የዝማሬና የምስጋና መርሐግብሩ የልደት በዓልን በማይገባ ቦታ የሚያሳልፉ በእግዚአብሔር ቤት ሆነው እንዲያሳልፉ ለማድረግ ዓላማ ያነገበ ነው።
የፎቶ ባለቤት ፦ ሚኪ ፎቶግራፊ
የቪድዮ ባለቤት ፦ ጃንደረባው ሚዲያ