TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.8K photos
1.49K videos
211 files
4.07K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
“ይሄ ፌሪያቲክ ኢራፕሽን ይባላል። ብዙ ጊዜ ቅልጥ አለቱ ወደ ላይ መጠጋቱን አንዱ ማመላከቻ ነው ” - ኤልያስ ሌዊ (ዶ/ር) በአፋር ክልል የመሬት መንቀጥቀጥ ከተስተዋለባቸው አካባቢዎች ተጠቃሽ በሆነው ዱለቻ ወረዳ ዶፋን ተራራ ሰሞኑን “ የእሳተ ገሞራ ፍንዳታ ተከሰተ ” መባሉ ይታወቃል። በዚህም በነዋሪዎች ላይ ጉዳት እንዳያደርስ እየተሰራ መሆኑ ሰሞኑን ተገልጿል። ተከሰተ የተባለውን የእሳተ ገሞራ ፍንዳታ…
“ ቅልጥ አለቱ በመሬት ውስጥ የሚያደርገዉ እንቅስቃሴና ወደ ላይ የመውጣት ግፊቱ እንደቀጠለ ነው።  ግን ቀዝቅዞ እዛው ሊቀር፣ ከመሬት በላይ ሊፈነዳ ይችላል ” - ኤሊያስ ሌዊ (ዶ/ር)

በአዋሽ ፈንታሌና ዶፈን ቮልካኖዎች መካከል የሚከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ ጠንከርና ከፍ እያለ መምጣቱ በተደጋጋሚ ተገልጿል። ሰሞኑንም በተደጋጋሚ እየተከሰተ ተስተውሏል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ፣ ለመሆኑ ምን መደረግ አለበት? ሲል ለአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጂኦፊዚክስ፣ ስፔስ ሳይንስ እና አስትሮኖሚ ተቋም ዳይሬክተር ኤልያስ ሌዊ (ዶ/ር) ጥያቄ አቅርቧል።

ኤልያስ ሌዊ (ዶ/ር) ምን መለሱ ?

“ ስምጥ ሸለቆ አካባቢ ነው ያለነው። ስምጥ ሸለቆ የሚፈጠርበት ተፈጥሯዊ ሂደት ነው። ተፈጥሯዊ ስል፤ ርዕደ መሬት እያስጨነቀው ላለ ማህበረሰብም ሆነ ለእኛ ባለመያዎቹ ሲንቀጠቀጥ ያስጨንቃል። 

ወዴትስ ያመራ ይሆን? የሚለው ያሳስባል። ግን መንስዔው ይታወቃል ተፈጥሮም የራሷን ሂደት እየሄደች ነው ያለችው ለማለት ነው። የስምጥ ሸለቆ አፈጣጠር አንዱ ሂደት ነው ለማለት ነው። 

እናም ከዚህ ቀደምም እንደገለጽነው ቅልጥ አለት መሬት ውስጥ እየተንቀሳበሰ ነው። በፈንታሌና በዶፈን ተራራዎች መካከል። የምናየው ርዕደ መሬት የዛ ውጤት ነው።

የሰሞኑ ክስተት እየነሆነ ያለው የዛ እንቅስቃሴ የፈጠረው መንቀጥቀጥ ሞገድ በመሬት ውስጥ ተጉዞ ነው አዲስ አበባ ድረስ የሚሰማን። 

መጠኑ ከፍ ሊል ይችላል ወይ? ለሚለው ጥያቄ፣ ሊልም ላይልም ይችላል። ማለትም ከዚህም በላይም ከፍ ሊል ይችላል።

ነገር ግን ይሄ በሚሆንበት ጊዜ እኛ ምን ማድረግ አለብን? የሚለው ነው መታወቅ ያለበት"
የሚል ማብራሪያ ሰጥተዋል።

መደረግ ስላለበት ጥንቃቄ ኤልያስ (ዶ/ር) ምን ተናገሩ?

“እስካሁን ድረስ ከፍ ያለ የመሬት መንቀጥቀጥም አልመጣም። መደርግ ስለሚገባው ነገርም ሲጠቀስ አንዳንድ ሚዲያ ላይ ሰዎች መቀለጃ አድርገውታል። ‘ጠረንጴዛ ሊያድነን ነው ወይ?’ ይላሉ።

ግን ይሄ የዓለም አቀፍ ተሞክሮና ስታንዶርድ ነው። ብዙ ሰዎች በዚሁ መንገድ ከአደጋ ድነዋል። 

ስለዚህ ከኮለን አካባቢ ሥር መቆም፣ ከጠረንጴዛ ሥር በፍጥነት መግባት፣ አሳንሰር አለመጠቀም፣ ፎቅ ላይ ለመውረድ አለመሞከር ያስፈልጋል። 

እሳት ሊያቀጣጥሉ የሚችሉ እንደ ሻማ ያሉ ነገሮችን ማጥፋት የመሳሰሉት እርምጃዎች ቀላል ይመስላሉ ግን የብዙዎችን ሕይወት አትርፈዋል።

በጣም የአጭር ጊዜ ስለሆነ የሚሆነው ከቤት ለመውጣትም ጊዜ ላይሰጥም ይችላል። 

የጊዜ አለማግኘት ብቻም ሳይሆን ቁልፍ ቆልፈን ቁጭ ብለን እንኳ እጃችንን እየተንቀጠቀጠ ለመክፈት ያዳግታል። በመሆኑም ከላይ የተጠቀሱትን ጥንቃቄዎች ማድረግ አለብን።

ማንም ሊያቆመው አይችልም ይሄንን ክስተት። ለኛ አሁን እዚህ ካለው የመሬት መንቀጥቀጥ በይበልጥ እያሰጋን ያለው ፈንታሌ አካባቢ ያለው ሁኔታ ነው። ጥፋት ካደረሰ ከኛ በበለጠ እዛ አካባቢ ነው ብዙ ጥፋት የሚያደርሰው።

እዛም ያለው የሰው ሕይወት ነው፤ እዚህም ያለው የሰው ሕይወት ነው። ሕይወት ነው የትም ቦታ ያለው። እዛ ላሉት ወገኖቻችንም እየተጨነቅን ነን ያለነው።

እዛ አካባቢ መሬት ውስጥ የሚጓዘው ቅልጥ አለት ወደ ላይ የመውጣትም እዛው የመቅረትም የሁለቱም ፓስቢሊቲ አለው። 

ከቀን ወደ ቀን የምናየው መረጃ እንደሚያሳየው ቅልጥ አለቱ ወደ ላይ ለመውጣት በሚያደርገው ግፊት መሬት እየተወጣጠረች ነው፡፡

ይህ ማለት ግን እርግጠኛ ሆነን ይፈነዳል ማለት አይደለም። ቀዝቅዞም እዛው ሊቀር፣ መጨረሻም እዛው ሊቆም ይችላል።

ቅልጥ አለቱ ወደ ላይ የሚመጣ ከሆነ ምን ማድረግ አለብን የሚለውን የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት፣ የመንግስት አካላት፣ መስሪያ ቤቶች፣ የግል ድርጅቶች፣ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ጋር በሕብረት እየተሰራ እንደሆነ አውቃለሁ።

እኛ የምርምር ማዕከል ነን ሥራችን መረጃ ማቅረብ ነው። እነርሱ ደግሞ ያንን መረጃ ወስደው በተግባር ላይ ያውሉታል የሚል ሙሉ እምነትና ግምት አለን። አንዳንድ ሥራዎችም እንደተጀመሩ መረጃ አለኝ። 

በኛ በኩል እንደ ምርምር ተቋም መንስኤው ምንድን ነው? መጠኑ ስንት ነው? ምን መደረግ አለበት? የሚለውን እያቀረብን ነው ያለነው። 

ከዚህ በተጨማሪ ያለው ነገር መጠነ ሰፊ ሥራዎችን ናቸው የሚጠይቁት። መጠነ ሰፊ መስሪያ ቤቶችንም መቀናጀት ያስፈልጋል። 

እኛ ብቻም ሳንሆን በዓለም አቀፍ በሙያው ዘርፍ ካሉት ባለሙያዎች ጋር እንደ ኢንስቲትዩት እየተገናኘና መረጃ እያቀናጀ ነው ያለው”
ነው ያሉት።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
" ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሰው በእግሩ ነው የመጣው ፤ ቀጥሎ በትራንስፓርት እየመጣ ያለ እንግዳ አለ " - የላሊበላ ከተማ አስተዳደር

የኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በተለይ በላሊላ ውቅር አብያተ ክርስቲያን በደማቁ ይከበራል።

ድንቁ የላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያን የሚገኝበት አማራ ክልል በፋኖ ታጣቂዎችና በመንግስት የጸጥታ ኃይሎች መካከል የተኩስ ቀጠና ከሆነ አንድ አመት ከወራት በላይ ቢያስቆጥርም፣ ህዝበ ክርስያቱ በዓሉን በቦታው ለማክበር ከመጓዝ እንዳልተገደበ ተሰምቷል።

የክልሉ ህዝብ ከአንድ አመት በላይ ለሆነ ጊዜ በጦርነት ቀጠና በመሆኑ ከቦታ ቦታ በሰላም በመንቀሳቀስ የነፍስና የሥጋ ስራውን ለማከናወን ከመቸገሩ ባሻገር ሞት፣ የአካል ጉዳትና የንብረት ውድመት እያስተናገደ ይገኛል።

ከዚህ ባሻገር በቡግና ወረዳ በድርቅና በምግብ እጥረት የሚላስ የሚቀመስ እንደ ሰማይ የራቃቸው ጨቅላ ህፃናት በከፋ ችግር ውስጥ ያሉበት ክልል ነው።

ይሁን እንጂ የክልሉን ህዝብ ጨምሮ በሌሎች አካባቢዎች ያሉ ኦርቶዶክሳዊያን ወደ ቦታው ለማቅናት የክልሉ ሁኔታ እምብዛም እንዳልገደባቸው ተነግሯል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ፣ የበዓሉ የዋዜማ ድባብ እና ዝግጅት ምን ይመስላል ? ሲል ለላሊበላ ከተማ አስተዳደር ጥያቄ አቅርቧል።

የላሊበላ ከተማ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ አቶ ወንድምነው ወዳጅ ምን አሉ ?

“ ቅዱስ ላሊበላ ከተማ የገና በዓልን ለማክበር በቂ ቅድመ ዝግጅት በማድረግ እንግዶቿን እየተቀበለች ነው። እንግዶች ከተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች ወደ ከተማዋ እየገቡ ይገኛሉ።

ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሰው በእግሩ ነው የሚመጣው። ከዛ ቀጥሎ በትራንስፓርት እየመጣ ያለ እንግዳ አለ። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከአዲስ አበባ፣ ከባሕር ዳር፣ ከጎንደር በዘረጋው በረራም እንግዶች ገብተዋል።

ቅዱስ ላሊበላ ከተማ እንግዷቿን በመቀበል የነበረ ግርማ ሞገሷን በመላበስ ተናገራለች። ወጣቶች ዝቅ ብለው እግር በማጠብ እንግዶችን የማስተናገድ ባህላቸውን አከናውነዋል ”
ሲሉ ገልጸዋል።

ክልሉ የጸጥታ ችግር ላይ መሆኑ ይታወቃል፤ ከዚሁ ጋር በተያያዘ የጸጥታውን ጉዳይ በተመለከተ ምን እንደተሰራ ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ጥያቄ ቀርቦላቸዋል።

አቶ ወንድምነው በሰጡት ምላሽም፣ “ ገናን ማክበር የጸጥታ ችግር ስጋት ሊሆን አይችልም ” ብለዋል።

“ ገና ሃይማኖታዊ በዓል ነው፤ ገና ህዝባዊ በዓል ነው፣ ገና እምነታዊ በዓል ነው። ገና የጸጥታ ችግር ሊሆን አይችልም። ገናን ማክበር የሚፈልግ ሰው ልቦናውን አዘጋጅቶ መገኘት ብቻ ቅድመ ሁኔታ ነው ” ሲሉ አክለዋል።

ምን ያህል እንግዶች እንደሚገኙ ሲጠየቁም፣ ከበዓሉ በኋላ እንጂ አሁን ለመገመት እንደሚያዳግት አቶ ወንድምነው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ምላሽ ሰጥተዋል።

የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተልፈው ፣ “ ጥሪያችንን አክብራችሁ በላሊበላ ታድማችሁ ከተማችንን ወደነበረ ግርማ ሞገሷ እየመለሳችሁ ላላችሁ ላቅ ያለ ክብር አለን ” ሲሉ አመስግነዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
ፎቶ ፦ በድሬዳዋ ከተማ አእላፋት የተሳተፉበት የአእላፋት ዝማሬ መርሐግብር በለገሀር አደባባይ ተከናውኗል።

ይህ የዝማሬና የምስጋና መርሐግብር የልደት በዓልን በማይገባ ቦታ የሚያሳልፉ በእግዚአብሔር ቤት ሆነው እንዲያሳልፉ ለማድረግ ዓላማ ያነገበ ነው።

ባለፈው ዓመት በአዲስ አበባ የጀመረው ይኸው የዝማሬና ምስጋና መርሐግብር ዘንድሮ ድሬዳዋን አካቶ ተካሂዷል።

የፎቶ ባለቤቶች ፦ መኮንን እንግዳው፣ ሀብታሙ አለሙ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#አእላፋትዝማሬ #TheMelodyofMyriads

በአዲስ አበባ አእላፋት የተሳተፉበት " የአእላፋት ዝማሬ / The Melody of Myriads " መርሐግብር በቦሌ በድብረ ሳሌም መድኃኔዓለም ተከናውኗል።

ይህ ዘንድሮ ለ2ኛ ጊዜ የተከናወነው መርሐግብር ከአምናውን የላቀ የምእመን ቁጥር የተገኘበት እንደሆነ በስፍራው በመገኘት ለመገንዘብ ችለናል።

መርሐግብሩ ላይ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት እንዲሁም ብፁአን አባቶች ተገኝተው ነበር።

የዝማሬና የምስጋና መርሐግብሩ የልደት በዓልን በማይገባ ቦታ የሚያሳልፉ በእግዚአብሔር ቤት ሆነው እንዲያሳልፉ ለማድረግ ዓላማ ያነገበ ነው።

የፎቶ ባለቤት ፦ ሚኪ ፎቶግራፊ
የቪድዮ ባለቤት ፦ ጃንደረባው ሚዲያ

@tikvahethiopia