TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59K photos
1.5K videos
211 files
4.08K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#AtoBulchaDemeksa

ጉምቱው ፖለቲከኛ አቶ ቡልቻ ደመቅሳ ከዚህ አለም በሞት ተለዩ።

በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ትልቅ ስም የነበራቸው ጉምቱው ፖለቲከኛ አቶ ቡልቻ ደመቅሳ ዛሬ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል።

የኢፌዴሪ ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ በአቶ ቡልቻ ደመቅሳ ህልፈት የተሰማቸውን ሀዘን ገልጸዋል።

" አቶ ቡልቻ ደመቅሳ በማረፋቸው የተሰማኝን ኀዘን እገልጻለሁ " ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ " በሚችሉት ሁሉ ሀገራቸውንና አፍሪካን ያገለገሉ፣ በአቋማቸው ጽኑ፣ ሕዝቦችን ለማቀራረብ የተጉ፣ እውነት ነው ብለው ያመኑትን የትምና መቼም የሚናገሩ ነበሩ " ብለዋቸዋል።

" እንዲህ ዓይነት ብርቱ ሽማግሌዎችን ማጣት ጉዳቱ ለሀገር ነው። ፈጣሪ ነፍሳቸውን ይቀበላት " ሲሉም ገልጸዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
ትውስታ ...

አቶ ቡልቻ ደመቅሳ በምን ይታወሳሉ ?

በኢህአዴግ ጊዜ የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ መለስ ዜናዊ ሀገራቸውን በሚመሩበት ወቅት ፓርላማ የነበሩት ጉምቱው ፖለቲከኛ እና የኢኮኖሚ ምሁር አቶ ቡልቻ ደመቅሳ ጠንከር ያሉ ምሁራዊ ጥያቄዎችን ለጠቅላይ ሚኒስትሩ በማንሳት ይታወቃሉ።

ንግግራቸው ለዛ የነበረው ፣ የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስን ጨምሮ መላ የፓርላማ አባላትን ሳቅ በሳቅ የሚያድረግ ፤ ድፍረትና እውቀት የተሞላበት ነበር።

በተለይ  ደግሞ በኢኮኖሚ ጉዳዮች ላይ የዳበረ እውቀት ስለነበራቸው ሁሉም ሰው እሳቸው እድሉን አግኝተው እስኪናገሩ በጉጉት ነበር የሚጠብቀው።

በብዙዎች የሚታወሰው እና ሁሌም ተደጋግሞ የሚነሳው ከኢትዮጵያ ኢኮኖሚ እድገት ጋር በተያያዘ ያነሱት ጥያቄና ፓርላማውን ሳቅ በሳቅ ያደረጉበት ንግግራቸው ነው።

" ጠቅላይ ሚኒስትሩ ፣ መንግስቱም ደጋግሞ ደጋግሞ ' ኢትዮጵያ በ110 ፣ በ111 አድጋለች ' ይላል ፤ እኔ ፣ እሳቸውም የኢትዮጵያ ኢኮኖሚስቶችም ያውቃሉ በ111 ማደግ ማለት ተአምር ነው። ይሄን ተአምር የሰራችው ቻይና እንደውም አሁን እየሰራች አይደለም ፣ ታይዋን ፣ ደቡብ ኮሪያ ናቸው።

ኢትዮጵያ እንዴት አድርጋ ነው በ111 ያደገቸው ? አንጎላ አሁን በ112 እያደገ ነው ለምንድነው በአንድ ጊዜ ብዙ ዘይት አገኙ፣ ዘይት ያገኙ ሰዎች ወይም ሌላ ነገር ያገኙ በ110 ወይም በ111 ቢያድጉ አይገርምም። 111 አደግን ብለን ለዓለምስ እንዴት አድርገን ነው የምንገልጸው ?

የዓለም የገንዘብ ድርጅት ኢትዮጵያ እና ሌሎች የምስራቅ አፍሪካ ሀገሮች ቢበዛ በ106 ያድጋሉ ብሏል እኛ ግን እንቢ ብለን ' አስራ አንድ ነው ! ' እንላለን ይሄ ተገቢ ነው ? "


ሌላ በእጅጉ ከሚታወሱበት ንግግራቸው መካከል ደግሞ መንግሥት ስለሚሳተፍባቸው የተለያዩ ሽያጮች ጉዳይ ነው።

" መንግሥት ለምንድነው ማዳበሪያን የሚሸጠው ብቻውን ? ፤ መንግሥት ለምንድነው ሆቴል ውስጥ ገብቶ የሚነግደው ? ፤ መንግሥት ለምንድነው ቱሪዝም ውስጥ ገብቶ የሚነግደው ?  ፤ መንግሥት ለምንድነው ሲሚንቶ የሚሸጠው ? ፤ አልፎ ፍራፍሬ ሽንኩርት የሚሸጠው ለምንድነው ? መንግሥት ሶሻሊት ኢኮኖሚ አይደለም የሚያራምደው ? "

አቶ ቡልቻ ደመቅሳ በምዕራብ ወለጋ የተወለዱ ሲሆን በትላልቅ ዩኒቨርሲቲዎች  የተማሩ የተዋጣላቸው የኢኮኖሚ ምሁር ነበሩ። የአዋሽ ባንክ እንዲሁም የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስን (ኦፌኮ) መስራችም ነበሩ።

#AtoBulchaDemeksa

@tikvahethiopia