TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.2K photos
1.5K videos
211 files
4.1K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
25 ዓመታት በሕብረት

ሕብረት ባንክ
በሕብረት እንደግ!

ቴሌግራም- https://t.iss.one/HibretBanket
ፌስቡክ፦ https://www.facebook.com/HibretBank
ሊንክዲን- https://www.linkedin.com/company/hibretbank/
ዌብሳይት- https://www.hibretbank.com.et/
#Hibretbank
TIKVAH-ETHIOPIA
#ትኩረት በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በሃዲያ ዞን፤ ባድዋቾ ወረዳ እና በሾኔ ከተማ በተቀሰቀሰ የኩፍኝ ወረሽኝ የ4 ህጻናትን ጨምሮ የ8 ሰዎችን ህይወት መቅጠፉን የሾኔ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል። ከሰሞኑ የተቀሰቀሰው የኩፍኝ ወረርሽኝ በአስደንጋጭ ሁኔታ መዛመቱንና ህይወት መቅጠፉን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የገልጹት በሾኔ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል የኩፍኝ ወረሽኝ ቁጥጥር አስተባባሪው…
" 8 ህፃናት ሞተዋል ፤ 500 ህፃናት በበሽታው ተይዘዋል " - የዞን ጤና መምሪያ

በሀድያ ዞን በከተሰተው የኩፍኝ ወረርሽኝ የሰዎች ህይወት እየጠፋ ነው።

የሀድያ ዞን ጤና መምሪያ የእናቶችና ህፃናት ጤናና ሥራዓተ ምግብ አገልግሎት  እንዳሳወቀው ከሆነ 8 ህፃናት ሞተዋል። 500 ህፃናት በበሽታው ተይዘዋል።

በሽታው ለመጀመሪያ ጊዜ በዱናና በምስራቅ ባደዋቾ ወረዳዎች  የተከሰተ ሲሆን ወደ  ስራሮ እና  ምዕራብ ባዳዋቾ ወረዳዎች እንዲሁም ወደ ሾኔ ከተማ አስተዳደር ተዛምቶ የሰዎችን ህይወት ቀጥፏል።

የዞኑ ጤና መምሪያ ወረርሽኙን ለመቆጣጠር ግብረ ኃይል ተቋቁሞ እየተሰራ ነው ብሏል።

በሽታው ወደ ሌሎች ወረዳዎች ሊዛመት ስለሚችል ሁሉም ባለ ድርሻ አካላት በተለይ የህክምና ባለሙያዎች ቤት ለቤት የህክምና ድጋፍና ክትትል እንዲያደርጉ ጥሪ ቀርቧል።

የዞኑ ጤና መምሪያ ፤ " የኩፍኝ በሽታ የበሽታውን  ለመከላከል የሚውለውን ክትባት በአግባቡ ባለመውሰድና በምግብ አጥረት በህፃናት ላይ የሚከሰት በሽታ ነው " ያለ ሲሆን " ይህን በሽታ በክትባት መከላከል እንደሚቻል አለፍ ሲልም በዘመቻ  መልክ መከላከል ይቻላል " ማለቱን የሀድያ ቴሌቪዥን ዘግቧል።

ከቀናት በፊት የሾኔ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጠው ቃል ፤ በወረርሽኙ የ4 ህጻናትን ጨምሮ የ8 ሰዎችን ህይወት መቅጠፉን ማሳወቁ ይታወሳል።

ወረርሽኝ በአስደንጋጭ ሁኔታ መዛመቱንና ህይወት መቅጠፉን ነው ሆፒታሉ ያመለከተው።

ችግሩ ከዚህ በላይ ጉዳት ከማስከተሉ በፊት የሚመለከተዉ አካል ሁሉ አስፈላጊዉን ትብብር እንዲያደርግም ተጠይቆ ነበር።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ይፈለጋል #Wanted ሼህ አብዱ ያሲንን በመግደል የሚጠረጠረው መሀመድ ሽኩር አበባው በቁጥጥር ስር ለማዋል ፖሊስ ክትትሉን አጠናክሮ መቀጠሉን የአዲስ አበባ ፖሊስ ገልጿል። አንዳንድ ማህበራዊ ሚዲያዎች ተጠርጠሪው እንደተያዘ በማስመሰል የሚያሰራጩት መረጃ #ሀሰተኛ መሆኑን አስታውቋል። በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ተጠርጣሪው ሳይያዝ እንደ ተያዘ አድርጎ መረጃ ማሰራጨት ተገቢ እንዳልሆነ የገለፀው የአዲስ አበባ…
" እስካሁን ፍትሕ አልተሰጠም "

በአዲስ አበባ ፣ በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ወረዳ 14 ' አስኮ አዲስ ሰፈር ' በጥይት ተመተው የተገደሉት የበድር መስጂድ ኢማምና ኸጢብ እንዲሁም በመስጂዱ የተለያዩ ኪታቦችን በማቅራት የሚታወቁት አቅሪ ሸይኽ አብዱ ያሲን ከተገደሉ ዛሬ 20 ቀን ሆኗል። 

ሸይኽ አብዱ የተገደሉት ከዒሻ ሰላት በኃላ ወደ ቤታቸው ሲሄዱ በጥይት ተመተው እንደነበር የሚዘነጋ አይደለም።

ምንም እንኳን ሼይኽ አብዱ ከተገደሉ በርካታ ቀናት ቢያልፍም እስካሁን #ፍትህ እንዳልተሰጠ ፤ ይህም በአካባቢው ነዋሪዎች ዘንድ ሃዘን እንደፈጠረ " ሃሩን ሚዲያ " ነዋሪዎችን ዋቢ በማድረግ ዘግቧል።

የአዲስ አበባ ፖሊስ በሼይኽ አብዱ ያሲን ግድያ ይጠረጠራል ያለው " መሀመድ ሽኩር አበባው " የተባለ ግለሰብ እንደነበር ይታወሳል።

ግለሰቡን በህግ ቁጥጥር ስር ለማዋል እየሰራ መሆኑን ከመግለፅ ባለፈ በማህበራዊ ሚዲያ ፎቶውን በማሰራጨት ህብረተሰቡ ያለበትን ጥቆማ በመስጠት እንዲተባበር ጥሪ አቅርቦም ነበር።

ከዛ በኃላ ግለሰቡ በቁጥጥር ስር ስለመዋሉ / ስለመገኘቱ ምንም የተባለ ነገር የለም።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update ትምህርት ሚኒስቴር በአማራ ክልል የሚገኙ የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች ከጥር 1/2016 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት 2 ሳምንታት ትምህርት ይጀምራሉ ማለቱ ይታወሳል። ይህ ተከትሎ አንዳንድ ተቋማት ለተማሪዎቻቸው ጥሪ አድርገዋል። ጥሪ ካደረጉት ውስጥ አንዱ የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ነው። ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ለነባር እና አዲስ የቅድመ-ምረቃ ተማሪዎቹ ባደረገው ጥሪ ፤ የ1ኛ ዓመት 2ኛ ወሰነ ትምህርት…
#ተራዘመ

ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የአዲስ እና የሬሜዲያል ተማሪዎችን መግቢያ ቀን #ላልተወሰነ ጊዜ አራዘመ።

ዩኒቨርሲቲው የተማሪዎችን የመግቢያ ቀን ያራዘመው የመግቢያ ቀኑ ሊደርስ 3 ቀን ሲቀረው ነው።

ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ በ2016 ዓ.ም አዲስ ለተመደቡ የጀማሪ መርሐግብር (Freshman) ተማሪዎች እና ለአቅም ማሻሻያ (Remedial) መርሐግብር ተማሪዎች እንዲሁም በ2015 ዓ.ም የአቅም ማሻሻያ (Remedial) መርሐግብር ወስደው የማለፊያ ውጤት ያመጡ ተማሪዎች ከጥር 21 እስከ 23/2016 ዓ.ም ምዝገባ እንዲያደርጉ ጥሪ አስተላልፎ ነበር።

ነገር ግን ምዝገባው ላልተወሰነ ጊዜ መራዘሙንና ወደፊት ጥሪ እስኪደረግ ተማሪዎች በትዕግስት እንዲጠብቁ ጥሪ አቅርቧል።

ተቋሙ ለምን የመግቢያ ቀኑ እንደተራዘመ የሰጠው ማብራሪያ የለም።

በሌላ በኩል ፤ በዘንዘልማ ካምፓስ ሰሞኑን ማታ ማታ ሲቪል የለበሱ ሰዎች ተኩስ ከፍተው መስተዋላቸውን ተማሪዎቹ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

አንድ የዘንዘልማ ካምፓስ ተማሪ ጥር 15 ቀን 2016 ዓ/ም ምሽት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጠው ቃል፣ በግቢያቸው ተኩስ ተከፍቶ እንደነበር ገልጿል። በአካባቢው የቦንብ ፍዳታም እንደነበር ጠቁሟል።

ይኸው ተማሪ " በዘንዘልማ ካምፓስ ተኩስ አዲሳችን አልነበረም " ሲል ገልጾ ከትላንት በስቲያ በአጥር ዘለው የገቡ አካላት ጥይት እየተኮሱ እስከ ዋና መግቢያ በር መሄዳቸውን ጠቁሟል።

" የገባነው ‘ግቡ’ ተብሎ ነው፤ ብዙ ተማሪ የለም። ወደ 100 ብንሆን ነው " ሲልም አክሏል። ተኩስን ኖርማል ሲቪል ልብስ የለበሱ ሰዎች መክፈታቸውን ነው የተናገረው።

ጥር 16 ቀን 2016 ዓ/ም በተጨማሪ ማብራሪያ የሰጠ አንድ የግቢው ተማሪ ፤ በዘንዘልማ ያለው ሁኔታው ስለሚያሰጋ ወደ ዋናው ካምፓስ መሄዱንና የቀሩት ጓደኞቹ በሁኔታው መጨነቃቸውን እንደገለፁለት ተናግሯል።

" እስከ 18 ድረስ ግቢውን ለቃችሁ ውጡ " የሚል ወረቀቶችም መበተኑን ከጓደኞቹ ዘንድ እንደሰማ በመግለፅ ያለንበትን ሁኔታ የሚመለከተው አካል ይወቅልን ብሏል።

የዩኒቨርሲቲው ሁነኛ አካል ጉዳዩን በተመለከተ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል ፤ ጉዳዩን #እንዳልሰሙና አጣርተው ምላሽ እንደሚሰጡ ቢገልጹም፣ በድጋሚ ሲደወልና የፅሑፍ መልዕክት ቢላክላቸውም ምላሽ ለመስጠት ፈቃደኛ አልሆኑም።

ዘገባውን የላከው የአ/አ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ሀርጌሳ " ሀገራችንን አልሸጥንም " - ሙሴ ባሂ አብዲ ባለፉት ቀናት ኢትዮጵያ የነበሩት የራስ ገዟ ሶማሌላንድ ፕሬዝዳንት ዛሬ ሐሙስ ዕለት ወደ ሀርጌሳ ተመልሰዋል። ፕሬዚዳንቱ ሀርጌሳ ሲገቡ ህዝቡ ወደ አደባባይ ወጥቶ ደማቅ አቀባበል አድርጎላቸዋል። አደባባይ ወጥቶ ለተቀበላቸው ህዝብ ባሰሙት ንግግር ከጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ጋር የተፈራረሙት የመግባቢያ ስምምነት ሰነድ ትልቅ ዋጋ ያለው መሆኑ…
የራስ ገዟ ሶማሌላንድ ፕሬዝዳንት ምን አሉ ?

የሶማሌላንድ ፕሬዜዳንት ሙሴ ቢሂ አብዲ ከሶማሌላንድ ቴሌቪዥን ጣቢያ ጋር በወቅታዊ ጉዳይ ሰፋ ያለ የሶማልኛ ቋንቋ ቃለ ምልልስ አድርገው ነበር።

በዚህም ቃለምልልስ ወቅት በርካታ ጉዳዮች ተነስተዋል።

ከነዚህም ውስጥ ፦
* ከኢትዮጵያ ጋር ስለተደረገው ስምምነት
* ከሶማሊያ እየተነሳ ስላለው ተቃውሞ
* ስለ ግብፅ መሪ እና የአረብ ሊግ መግለጫ
* ኢትዮጵያ ለሶማሌላንድ የሉዓላዊ ሀገርነት እውቅና ትሰጥ እንደሆነ ...የሚሉና ሌሎችም በርካታ ጉዳዮችን ተስተዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ፤ ከሰፊ ቃለምልልሱ ወሳኝ ያላቸውን የፕሬዜዳንቱን ቃል ተመልክቷል።

ፕሬዜዳንት አብዲ ባሂ ሙሴ ፤ " ለኢትዮጵያ ባህር ኃይል የባህር ኃይል ጦር ሰፈር የሚሆን ትንሽ መሬት በሊዝ ይሰጣል " ያሉ ሲሆን " ስምምነቱ ኢትዮጵያ ለገቢና ወጪ ምርቶች #የበርበራ ወደብን እንደምትጠቀም ይገልጻል " ብለዋል።

" ይህ የባህር ሃይል ጦር ሰፈር ለወታደራዊ አገልግሎት ብቻ የሚውል እና ምንም አይነት የንግድ እንቅስቃሴዎች ወይም ሸቀጦችን መጓጓዣ የማይጨምር መሆኑን አጽንኦት መስጠቱ ወሳኝ ነው " ሲሉም ተናግረዋል።

" በዚህም ሳቢያ በስምምነቱ ዙሪያ በሶማሊያ በኩል የሚነሳው ተቃውሞ በተዛባ መረጃ ላይ የተመሰረተ ይመስላል። " ሲሉ አክለዋል።

ፕሬዜዳንቱ ፤ " በእርግጠኝነት ! በስምምነቱ ኢትዮጵያ እንደ ሉዓላዊ ሀገር ለሶማሌላንድ እውቅና ትሰጣለች። " ያሉ ሲሆን " በይፋ የሚፈረመው የስምምነት ሰነድ የሶማሌላንድን እውቅና በግልፅ ይጠቅሳል። የዚህ ስምምነት ይዘት ሶማሊላንድን እንደ የተለየ አካል በመቀበል ማረጋገጫ ይሰጣል ፤ ይህ እውነታ በሰነዱ ውስጥ በግልፅ ተቀምጧል " ሲሉ አሳውቀዋል።

ፕሬዜዳንቱ ከሶማሌላንድ ቴሌቪዥን ጣቢያ ጋር ያደረጉት የሶማልኛ ቃለምልልስ ወደ እንግልዘኛ ቋንቋ ተተርጉሞ በዚህ ቀርቧል ፦ https://telegra.ph/Tikvah-Ethiopia-01-26

(ቲክቫህ ኢትዮጵያ ፤ የፕሬዜዳንቱን ቃለምልልስ ወደ እንግሊዘኛ ቋንቋ ተርጉሞ ይፋ ያደርገው የሶማሌላንድ ፕሬዚዳንት ፅህፈት ቤት መሆኑን ያሳውቃል)

@tikvahethiopia
#ሶማሌላንድ

" ከአካባቢው ጋር በተያያዘ ሰፊ ሌላ ዓላማ ላላቸው #ግብፆች ምን አስጨነቀን ? " - አምባሳደር አብዱላሂ ሞሀመድ

ኢትዮጵያ እና ሶማሊላንድ የተፈራረሙትን የመግባቢያ ስምምነት ለማጠናቀቅ " አሁን ከሁለቱም ወገኖች የቴክኒክ ኮሚቴ በመዋቀር ላይ ነው " ሲሉ በኢትዮጵያ የሶማሊላንድ ተወካይ አምባሳደር አብዱላሂ ሞሀመድ ተናገሩ።

አምባሳደር አብዱላሂ ይህን ያሉት ለዶቼ ቨለ ሬድዮ ጣቢያ በሰጡት ቃል ነው።

የሶማሊላንዱ ተወካይ ፦ " ጉዳዩን ለማጠናቀቅ አሁን ከሁለቱም ወገኖች የቴክኒክ ኮሚቴ በማዋቀር ላይ ነን። እና ይህ ቀድሞውኑ በሂደት ላይ እንደሆነ እርግጠኛ ነኝ።

(ፊርማውን ትከትሎ) ግንኙነቶች ነበሩ። በሁለቱ ሀገሮች መካከል ጉብኝቶች ነበሩ።

የውጭ ጉዳይ እና የአለም አቀፍ ግንኙነት ሚኒስትራችን ባለፈው ሳምንት ነው የተመለሱት። እሳቸው እዚህ (አዲስ አበባ) ከእኔ ጋር ነበሩ። ዋና ተግባራቸውም ጉዳዩ መሠረት እንዲይዝ ከኢትዮጵያ አቻዎቻቸው ጋር ለመምከር ነበር።

ይዋል ይደር እንጂ ሁለቱ ኮሚቴዎች ወደ ስራ እንዲገቡ እናደርጋለን። ስለዚህ ይህ በጣም በቅርቡ ይከናወናል ብዬ አስባለሁ " ብለዋል።

ሶማሊላንድ አለምአቀፍ እውቅና ያገኘ ባይሆንም ባለፉት 30 ዓመታት ፦
* ራሱ የሚቆጣጠረው ድንበር ፣
* የራሱ ሰንደቅ ዓላማ ያለው
* ምርጫ ሲያካሂድ የነበረ ፣
* ሕዝቡንም ሲያስተዳድር የቆየ መንግሥት መሆኑን ነው ሲሉ ተናግረዋል።

ከሶማሊያ እና ሌሎች ሀገሮች የተነሳውን ተቃውሞ እንዴት እንደሚመለከቱት የተጠየቁት አምባሳደሩ ፦ " የዓረብ ሊግ፣ ግብፅና ሶማሊያን በተመለከተ፣ በኔ እምነት በዚህ ረገድ ምንም ማድረግ የማይችሉ ይመስለኛል። ያለቀለት የተደመደመ ጉዳይ ነው። ከአካባቢው ጋር በተያያዘ ሰፊ ሌላ ዓላማ ላላቸው ግብፆች ምን አስጨነቀን " ብለዋል።

በመግባቢያ ስምምነቱ መሠረት ሶማሌላንድ በአፀፋው ምን ታገኝ እንደሆንም ተጠይቀው ፥ " ለሶማሌላንድ ዕውቅና መስጠት። ይህ እርግጥ ነው። የዚህ ፕሮግራምም አካል ነው። የስምምነቱም ክፍል እና አካል ነው " ብለዋል።

አምባሳደር አብዱላሂ ሶማሊያ የኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን የቀጣናው አለመረጋጋት ምንጭ ናት ብለዋል።

ይልቁንም ሶማሊላንድ ለቀጣናው መረጋጋት ጉልህ ድርሻ ያላት መሆኑን ገልፀዋል።

" ኢትዮጵያም፣ ድንበሯም እንዲከበር እንጠብቃለን። ሁለተኛ ፣ ሶማሊላንድ በሕግ የፀና እውቅና ያለው ግዛት ሆኖ መታወቅ አለበት። ምክንያቱም እኛ የአካባቢው ጂኦ ፖለቲካዊ መረጋጋት አካል እና ባለድርሻ ነበርን። ባለፉት አመታት አልሸባብን እና ሽብርተኝነትን እየተዋጋን ነበር። " ብለዋል።

የሶማሊላንድ የኢትዮጵያ ተወካይ አምባሳደር አብዱላሂ ሞሀመድ ፤ " ሶማሊላንድ የሌሎች ሀገሮችም ድጋፍ አላት " ሲሉ ተናግረዋል።

" ሶማሊላንድ በቀጣዩ የአፍሪካ ሕብረት ጉባኤ ይህንን ጉዳይ በሚገባ ትይዘዋለች " ያሉት አምባሳደሩ ፤ " ኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ሌሎች ወዳጆችም አሉን። ከ5 የተለያዩ ክልሎች፤ ለጉዳያችን በጣም በጣም አዎንታዊ አመለካከት ያላቸው አባል ሀገራት (የአፍሪካ ሕብረት) አሉን። " ብለዋል።

" እኛ ሕጋዊ ጉዳይ አለን ፣ የሞራል ጉዳይም አለን ፣ የሚቀረው የፖለቲካ ጉዳይ ብቻ ነው። ለአካባቢው እና ለአህጉሪቱ የምናደርገው በጎ አስተዋፅኦ ተዘንግቷል። የትኛውም አካል የህዝባችን ውሳኔ ላይ ሊወስን አይችልም። ህዝባችን ሕዝበ ውሳኔ አድርጎል። 97.5 በመቶው ነፃ ሀገር መሆንን በመደገፍ ድምጽ ሰጥቷል " ሲሉ ሃሳባቸውን ደምድመዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ይህ ቃለምልልስ እና መረጃ የዶቼ ቨለ ሬድዮ መሆኑን ያሳውቃል።

@tikvahethiopia
ግምትዎን በቴሌግራም ቻናላችን ብቻ https://t.iss.one/GlobalBankEth ይስጡ!

ለ5 ትክክለኛ ገማቾች ሽልማቱ ይበረከታል፣ ከአምስት በላይ ትክክለኛ ገማቾች ከተገኙ አምስቱ የሚለዩት በዕጣ ይሆናል፡፡

ከአንድ በላይ ግምት መስጠት ለሽልማት ብቁ አያደርግም::

#GlobalBankEthiopia #OurSharedSuccess #BankInEthiopia #Bank #GBE #nigcam #nigeria #cameroon #afcon #winner
#እንድታውቁት

አልኮል ፦

- አልኮል በዓለም ላይ 3 ሚለዮን ለሚሆኑ ሞቶች አስተዋፅኦ ያደርጋል፤ እንዲሁም ደግሞ ከ200 በላይ ላሉ አካላዊ እና አዕምሮአዊ የጤና ችግሮች መንስኤ ነው፡፡

- ምንም እንኳን እንደሚወሰደው መጠንና የጊዜ ብዛት ቢለያይም የትኛውም አልኮል መጠን ጤና ላይ ተፅዕኖ አለው፡፡

ከሚያስከትለው የጤና ችግር በጥቂቱ ፦
አዕምሮን ነገሮችን የሚመለከትበትን መንገድ በመቀየር የባህሪ ችግር እንዲኖርና ነገሮችን በትክክል ማሰብ እንዳይችል ያደርጋል፤ አልፎም ተርፎም ከሰዎች ጋር ያለን ግንኙነት በከፍተኛ ሁኔታ በማወክ ለአዕምሮ ቀውስ ይዳርጋል።
የልብ አመታት ችግር
የልብ ጡንቻዎች መድከም
ስትሮክ
የደም ግፊት
የጉበት ህመም ፤ ጉበትን ከጥቅም ውጪ በማድረግ ስራውን እንዲያቆም ብሎም ለሞት ሊዳርግ ይችላል፡፡
የተለያዩ ንጥረ ቅመሞችን የሚያመርተው ቆሽት መርዛማ ንጥረ-ነገሮችን እንዲያመርት፤ በዚህም ምክንያት ለራሱም እንዲሁም ሌሎች አካላትን እንዲጎዱ ያደርጋል፤ ይህ ደግሞ ለስኳር እና ለተለያዩ በሽታዎች ያጋልጣል፡፡
በቀን ውስጥ 1 የአልኮል መጠጥ የምትጠጣ ሴት በጡት ካንሰር የመያዝ እድሏ ከ 5-9% ያህል ከማይጠጡት ይልቅ ይጨምራል፡፡
የአንጀት ካንሰርን ጨምሮ አልኮል የብዙ ካንሰር ዓይነቶች መንስኤ ነው፡፡
ብዙ አልኮል መጠቀም የበሽታ መከላከል አቅምን በመቀነስ ለተለያዩ በሽታዎች ያጋልጣል፡፡ 
ትምህርት ላይ ባለው ተፅዕኖ፤ የጤና እክልን በማምጣትና ያለዕድሜ ህይወት እንዲያልፍ በማድረግ ምርታማነትን በእጅጉ ይቀንሳል፡፡

በየቀኑ ወይም ደግሞ በአንድ ጊዜ ብዙ የአልኮል መጠን መውሰድ በየቀኑ ለምንሰራቸው ስራዎች እንቅፋት ይሆናል፤ በአካልም በስነልቦናም የአልኮሉ ጥገኛ ሆነን ራሳችንን ልናገኘው እንችላለን፤ ይህን ችግር ራሳችን ላይ ካየነው እርዳታ በመፈለግ ህክምና ማግኘት ይኖርብናል፡፡

በቅርብ ያሉ ቤተሰቦቻችን ወይም ጓደኞቻችን ላይ ይህን ችግር ካየን ለአዕምሮቸውም እንዲሁም ለአካላቸው ጤና ስንል ከማግለል ይልቅ ተገቢውን እርዳታ እንዲያገኙ ማድረግ ይኖርብናል፡፡

#PAHO #WHO

#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia
#መርከቦች

የየመን ሁቲ ታጣቂዎች በቀይ ባሕር ላይ በሚመላለሱ #መርከቦች ላይ ከፍተኛ የተባለ የድሮን እና የሚሳዬል ጥቃት መፈፀም ከጀመሩ ሰንበትበት ብለዋል።

ታጣቂዎቹ ጥቃት እፈፀሙ ያሉት እስራኤል #በጋዛ የምታካሂደውን ጦርነት እንድታቆም #ለማስገደድ እንደሆነ ተናግረዋል።

ጥቃቱ በዓለም አቀፍ የንግድ ስርዓት ላይ ትልቅ አደጋን ደቅኗል።

ጥቃቶቹ ከእስራኤል ጋር ግኑኝነት በሌላቸው መርከቦች ላይም የሚፈጸሙ ሲሆን፣ እስያን እና መካከለኛው ምሥራቅን ከአውሮፓ ጋር የሚያገናኘውን የንግድ መተላለፊያ አውኳል።

ለሁቲዎቹ ምላሽ አሜሪካ ቡድንኑን በድጋሚ አሸባሪ በማለት ፈርጃ ከሰሞኑን ከእንግሊዝ የባሕር ኃይሎች ጋር ሆና የሁቲን ተወንጫፊዎች ላይ እርምጃ እየወሰደች ነው።

በኢራን ይደግፋሉ የሚባሉት ሁቲዎች #በቀይባሕር ላይ በተከታታይ እየፈፀሙ ባሉት ጥቃት ምክንያት በአካባቢው የሚመላለሱ መርከቦች
* ሚሳዬል እየተተኮሰባቸው፣
* ድሮን ከሰማይ እያንዣበባቸው
* በትናንሽ ጀልባዎች እጅባና ክትትል እየተደረገባቸው ነው የሚጓዙት።

ከዚህ ከመርከብ ጥቃት ጋር በተያያዘ ፤ ትላንት ምሽት አንድ ነዳጅ ጫኝ መርከብ በሁቲዎች ተመቷል።

በኢራን ይደገፋሉ የሚባሉት የሁቲ ኃይሎች በቁጥጥራቸው ስር ከሚገኙት የየመን አካባቢዎች አንድ ፀረ-መርከብ ባሊስቲክ ሚሳኤል በመተኮስ የማርሻል ደሴቶችን ባንዲራ የያዘ የነዳጅ መርከብ ኤም/ቪ ማርሊን ሉዋንዳ መምታታቸው ተነግሯል።

መርከቧ በጥቃቱ ጉዳት እንደደረሰባትም አሳውቃለች።

ዩኤስኤስ ካርኔይ (DDG 64) እና ሌሎች የህብረት መርከቦች ከመርከቧ የቀረበውን የእርዳታ ጥሪ ተከትሎ የእርዳታ ምላሽ ሰጥተዋል።

እስካሁን ሰው ላይ ምንም አይነት ጉዳት አልደረሰም ተብሏል።

ይህንን ጥቃት ተከትሎ ፤ ዛሬ የአሜሪካ ማዕከላዊ ኮማንድ ሃይል በቀይ ባህር ላይ ያነጣጠረ እና ሊወነጨፍ በተዘጋጀ የሁቲ ፀረ መርከብ ሚሳኤል ላይ ጥቃት መፈፀሙን አሳውቋል።

የአሜሪካ ጦር በየመን የሁቲ ኃይሎች በሚቆጣጠሯቸው አካባቢዎች ያሉ ሚሳኤሎችን ለይቶ ማወቁንና በአካባቢው ላሉ የንግድ መርከቦች እና የአሜሪካ የባህር ኃይል መርከቦች ስጋት መሆኑን ገልጿል።

በዚህም " እራስን ለመከላከል "  በሚል ሚሳኤሉን መትቶ እንዳወደሙ ተናግሯል።

ይህ እርምጃ የመርከብ ጉዞ ነጻነትን ለማረጋገጥ እና ዓለምአቀፍ የውሃ አካባቢዎች የበለጠ ደህንነታቸው የተጠበቀ እንዲሆን ለአሜሪካ የባህር ኃይል መርከቦች እና የንግድ መርከቦች የበለጠ ደህንነቱ የተጠበቀ  እንዲሆን ያደርጋል ስትል አሜሪካ አሳውቃለች።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ፤ በሰሞኑን የንግድ መርከቦች በሚያልፍባቸው መስመሮች ላይ እየተፈፀመ ያለው ጥቃት ምን ያህል ተፅእኖ እያሳደረ እንደሆነ በንግድ ላይ ለተሰማሩ አንድ ኢትዮጵያዊ ጥያቄ አቅርቦ ነበር።

እኚህ ተሽከርካሪ እና ሌሎች መገልገያዎችን በማስማጣት ስራ ላይ የተሰማሩ የንግድ ሰው ጥቃቱን ተከትሎ መርከቦች ወደ መዳረሻቸው ለመድረስ መዝግየት እየተፈጠረባቸው እንደሆነ ገልጸዋል።

በተጨማሪ መርከቦች #በእጀባ ስለሚመጡ ለዚህም ተጨማሪ ክፍያ የመጠየቅ ነገር እንዳለ አስረድተዋል።

ያለው ሁኔታ በዚህ ከቀጠለ በዓለም አቀፍ የንግድ እንቅስቃሴ ላይ ያለው ተፅእኖ ከባድ እንደሚሆን ጠቁመዋል።

ተጫማሪ የውጭ ጉዳዮችን በ @thiqaMediaEth ይከታተሉ።
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#TPLF

" ላለፉት 39 ቀናት ያካሄድኩትን ሰብሰባ በሚቀጥሉት ሁለት ቀናት አጠናቅቃለሁ " - የህወሓት ማእከላዊ ኮሚቴ

" ለ64 ቀናት ስብሰባ ተቀምጠን ህዝብን የሚረባ ጠብ ያለ ቁምነገር የለም " - የጊዚያዊ አስተዳደሩ ፕሬዜደንት ጌታቸው ረዳ

ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ጥር 17 ቀን 2016 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ ፤ የህወሓት ማእከላይ ኮሚቴ ላለፉት 39 ቀናት ከፀጥታ ሃይሎች ፣ ከተተኩ ነባር አመራርሮች በጥምር ያካሄደውን ገምገም፤ ግለሂስና ሂስ በዚህ ሳምንት እንደሚያጠቃልል አስታውቋል።

" የግምገማ ፣ የግለሂስና ሂስ መድረኩ ከሁለት ቀናት በማይበልጥ ጊዜ ይጠናቀቃል " ያለው መግለጫው ፤ " ቀጥሎ የድርጅቱ ካድሬዎችና አባላት የሚሳተፉትበት ጉባኤ ይካሄዳል " ብሏል።

" የቀጠለው መድረክ ከተጠናቀቀ በኃላ በድርጅቱ ማእከላዊ ኮሚቴና ቁጥጥር ኮሚሽን መካከል በተደረሰ ስምምነት መሰረት መላ አመራር ፣ አባላትና ህዝብ የሚሳተፉበት ጉባኤ ይካሄዳል " ሲልም አሳውቋል።

አሁን ህወሓት ጉባኤው የሚያካሂድበት የተቆረጠ ቀን አላስቀመጠም።

ህወሓት ለ39 ቀናት ስብሰባ እንደተቀመጠ ቢገልፅም ፤ የጊዚያዊ አስተዳደሩ ፕረዚደንት ጌታቸው ረዳ ባላፉት ሳምንት በሽረ እንዳስላሴና በማይጨው ከተሞች በመገኘት ከህዝብ ጋር ባደረጉት ውይይት ስብሰባው ለ64 ቀናት መካሄደውንና ለህዝብ የሚረባ ጠብ የሚል ቁምነገር እንዳልተገኘ ተናገረዋል።

የትግራይ ህዝብ ከጦርነቱ ማግስት በከባድ ድርቅና ረሃብ እንዲሁም ጦርነት ወለድ ችግሮች ተተብትቦ እያለ ይህን ያህል ቀናት አመራሮች ሰብሰባ መቀመጣቸውን የሚነቅፉት እጅግ በርካቶች ናቸው ሲል የመቐለ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ዘግቧል።
                                      
@tikvahethiopia            
Tecno Spark 20 pro+ !

‘Spark 20 pro+’ ከርቭድ እስክሪን (curved screen)  የተገጠመለት ሲሆን ስልኩን ሲይዙት ቀላል እና ምቹ በሆነ ቴክኖሎጂ የተመረተ እና ውበቱን እንደጠበቀ ለረጅም ጊዜ  እንዲቆይ IP-53 የተሰኝ አዋራ እና ውሃ የሚቋቋም ቴክኖሎጂን አካቶ የቀረበ  ምርጥ የዘመኑ ስልክ ከቴክኖ ሞባይል!

ቴክኖ ሞባይል ኢትዮጵያ
#Spark20pro+ #TecnoMobile #TecnoEthiopia
ከች ብለናል #ከሳፋሪኮም!

ዘወትር ቅዳሜ ከሰዓት በEBS TV ላይ!

ሰሞነኛ፣ አዳዲስ የቴክኖሎጂ፣ የስነጥበብ እንዲሁም ሌሎች አስደሳች መረጃዎችን በከች ፕሮግራም እንመልከት!

ከች ሾው በሳፋሪኮም ኢትዮጵያ የቀረበ!

የሳፋሪኮም ኢትዮጵያን ትክክለኛ መረጃዎችን በቀላሉ ለማግኘት ቀጥሎ በሚገኙት ይፋዊ የማህበራዊ ሚዲያዎች እንዲከታተሉ እንጋብዛለን።

Facebook: https://www.facebook.com/SafaricomET
Telegram: https://t.iss.one/Safaricom_Ethiopia_PLC
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/safaricom-ethiopia
Twitter:
https://x.com/SafaricomET?t=y2XAHAhPNvFeZqXa2YE6aQ&s=08
Instagram: https://www.instagram.com/safaricomet?igsh=MWJtcjJrMzNhMzVsNg==
YouTube: https://youtube.com/@safaricomethiopia2751?si=w2o8uz61oHeZM9gm