#መርከቦች
የየመን ሁቲ ታጣቂዎች በቀይ ባሕር ላይ በሚመላለሱ #መርከቦች ላይ ከፍተኛ የተባለ የድሮን እና የሚሳዬል ጥቃት መፈፀም ከጀመሩ ሰንበትበት ብለዋል።
ታጣቂዎቹ ጥቃት እፈፀሙ ያሉት እስራኤል #በጋዛ የምታካሂደውን ጦርነት እንድታቆም #ለማስገደድ እንደሆነ ተናግረዋል።
ጥቃቱ በዓለም አቀፍ የንግድ ስርዓት ላይ ትልቅ አደጋን ደቅኗል።
ጥቃቶቹ ከእስራኤል ጋር ግኑኝነት በሌላቸው መርከቦች ላይም የሚፈጸሙ ሲሆን፣ እስያን እና መካከለኛው ምሥራቅን ከአውሮፓ ጋር የሚያገናኘውን የንግድ መተላለፊያ አውኳል።
ለሁቲዎቹ ምላሽ አሜሪካ ቡድንኑን በድጋሚ አሸባሪ በማለት ፈርጃ ከሰሞኑን ከእንግሊዝ የባሕር ኃይሎች ጋር ሆና የሁቲን ተወንጫፊዎች ላይ እርምጃ እየወሰደች ነው።
በኢራን ይደግፋሉ የሚባሉት ሁቲዎች #በቀይባሕር ላይ በተከታታይ እየፈፀሙ ባሉት ጥቃት ምክንያት በአካባቢው የሚመላለሱ መርከቦች
* ሚሳዬል እየተተኮሰባቸው፣
* ድሮን ከሰማይ እያንዣበባቸው
* በትናንሽ ጀልባዎች እጅባና ክትትል እየተደረገባቸው ነው የሚጓዙት።
ከዚህ ከመርከብ ጥቃት ጋር በተያያዘ ፤ ትላንት ምሽት አንድ ነዳጅ ጫኝ መርከብ በሁቲዎች ተመቷል።
በኢራን ይደገፋሉ የሚባሉት የሁቲ ኃይሎች በቁጥጥራቸው ስር ከሚገኙት የየመን አካባቢዎች አንድ ፀረ-መርከብ ባሊስቲክ ሚሳኤል በመተኮስ የማርሻል ደሴቶችን ባንዲራ የያዘ የነዳጅ መርከብ ኤም/ቪ ማርሊን ሉዋንዳ መምታታቸው ተነግሯል።
መርከቧ በጥቃቱ ጉዳት እንደደረሰባትም አሳውቃለች።
ዩኤስኤስ ካርኔይ (DDG 64) እና ሌሎች የህብረት መርከቦች ከመርከቧ የቀረበውን የእርዳታ ጥሪ ተከትሎ የእርዳታ ምላሽ ሰጥተዋል።
እስካሁን ሰው ላይ ምንም አይነት ጉዳት አልደረሰም ተብሏል።
ይህንን ጥቃት ተከትሎ ፤ ዛሬ የአሜሪካ ማዕከላዊ ኮማንድ ሃይል በቀይ ባህር ላይ ያነጣጠረ እና ሊወነጨፍ በተዘጋጀ የሁቲ ፀረ መርከብ ሚሳኤል ላይ ጥቃት መፈፀሙን አሳውቋል።
የአሜሪካ ጦር በየመን የሁቲ ኃይሎች በሚቆጣጠሯቸው አካባቢዎች ያሉ ሚሳኤሎችን ለይቶ ማወቁንና በአካባቢው ላሉ የንግድ መርከቦች እና የአሜሪካ የባህር ኃይል መርከቦች ስጋት መሆኑን ገልጿል።
በዚህም " እራስን ለመከላከል " በሚል ሚሳኤሉን መትቶ እንዳወደሙ ተናግሯል።
ይህ እርምጃ የመርከብ ጉዞ ነጻነትን ለማረጋገጥ እና ዓለምአቀፍ የውሃ አካባቢዎች የበለጠ ደህንነታቸው የተጠበቀ እንዲሆን ለአሜሪካ የባህር ኃይል መርከቦች እና የንግድ መርከቦች የበለጠ ደህንነቱ የተጠበቀ እንዲሆን ያደርጋል ስትል አሜሪካ አሳውቃለች።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ ፤ በሰሞኑን የንግድ መርከቦች በሚያልፍባቸው መስመሮች ላይ እየተፈፀመ ያለው ጥቃት ምን ያህል ተፅእኖ እያሳደረ እንደሆነ በንግድ ላይ ለተሰማሩ አንድ ኢትዮጵያዊ ጥያቄ አቅርቦ ነበር።
እኚህ ተሽከርካሪ እና ሌሎች መገልገያዎችን በማስማጣት ስራ ላይ የተሰማሩ የንግድ ሰው ጥቃቱን ተከትሎ መርከቦች ወደ መዳረሻቸው ለመድረስ መዝግየት እየተፈጠረባቸው እንደሆነ ገልጸዋል።
በተጨማሪ መርከቦች #በእጀባ ስለሚመጡ ለዚህም ተጨማሪ ክፍያ የመጠየቅ ነገር እንዳለ አስረድተዋል።
ያለው ሁኔታ በዚህ ከቀጠለ በዓለም አቀፍ የንግድ እንቅስቃሴ ላይ ያለው ተፅእኖ ከባድ እንደሚሆን ጠቁመዋል።
ተጫማሪ የውጭ ጉዳዮችን በ @thiqaMediaEth ይከታተሉ።