TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57.1K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ሲዳማ🕊ወላይታ‼️

በሲዳማና ወላይታ ሕዝቦች መካከል ዘላቂ ዕርቀ ሠላም ለማውረድ #በገለልተኛ ሀገር ሽማግሌዎችና የኃይማኖት አባቶች ካለፈው ሐምሌ 2010 ዓ.ም ጀምሮ ሲካሄድ የነበረው የዕርቅ ውይይት በሁለቱ ሕዝቦች ተወካይ ሽማግሌዎች መካከል ሰፊና ጥልቀት ያለው ውይይት ሲደረግ ቆይቷል።

በተደረገውም ውይይት የሚያቀራርብና እጅግ #ጠቃሚ በሚባሉ ጉዳዮች ላይ መግባባት የተደረሰ ሲሆን ይህንን በሕዝባዊ ኮንፈረንስ ለማጠቃለል ከሁለቱም ወንድም ሕዝቦች የተወከሉ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የኃይማኖት መሪዎች፣ ወጣቶች፣ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች በተገኙበት ኀዳር 9/2011 ዓ.ም በሀዋሳ #ሲዳማ_ባህል_አዳራሽ የዕርቅ ኮንፈረንስ የሚደረግ ሲሆን ኀዳር 11 /2011 ዓ.ም ተመሳሳይ መድረክ #በወላይታ_ሶዶ ተካህዶ የዕርቅ ኮንፈረንስ እንደሚጠናቀቅ ከወጣው መርሀ ግብር ለማወቅ ተችሏል።

ዕርቁ በሁለቱም #ወንድም ሕዝቦች መካከል የተፈጠረውን መሻከር በማስወገድ መተማመንና ዘላቂ ሰላምን ለማውረድ ጉልህ ሚና ይጫወታል ተብሎ እምነት ተጥሎበታል።

ምንጭ፦ የሲዳማ ዞን ባህል ቱሪዝም፤የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሲዳማ🕊ወላይታ!

🔹ኀዳር 9/2011 - ሀዋሳ(ሲዳማ ባህል አዳራሽ)
🔹ኀዳር 11/2011 - ወላይታ ሶዶ

በሲዳማና ወላይታ ሕዝቦች መካከል ዘላቂ ዕርቀ ሠላም ለማውረድ #በገለልተኛ ሀገር ሽማግሌዎችና የኃይማኖት አባቶች ካለፈው ሐምሌ 2010 ዓ.ም ጀምሮ ሲካሄድ የነበረው የዕርቅ ውይይት በሁለቱ ሕዝቦች ተወካይ ሽማግሌዎች መካከል ሰፊና ጥልቀት ያለው ውይይት ሲደረግ ቆይቷል።

በተደረገውም ውይይት የሚያቀራርብና እጅግ #ጠቃሚ በሚባሉ ጉዳዮች ላይ መግባባት የተደረሰ ሲሆን ይህንን በሕዝባዊ ኮንፈረንስ ለማጠቃለል ከሁለቱም ወንድም ሕዝቦች የተወከሉ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የኃይማኖት መሪዎች፣ ወጣቶች፣ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች በተገኙበት ኀዳር 9/2011 ዓ.ም በሀዋሳ #ሲዳማ_ባህል_አዳራሽ የዕርቅ ኮንፈረንስ የሚደረግ ሲሆን ኀዳር 11 /2011 ዓ.ም ተመሳሳይ መድረክ #በወላይታ_ሶዶ ተካህዶ የዕርቅ ኮንፈረንስ እንደሚጠናቀቅ ከወጣው መርሀ ግብር ለማወቅ ተችሏል።

ዕርቁ በሁለቱም #ወንድም ሕዝቦች መካከል የተፈጠረውን መሻከር በማስወገድ መተማመንና ዘላቂ ሰላምን ለማውረድ ጉልህ ሚና ይጫወታል ተብሎ እምነት ተጥሎበታል።

ምንጭ፦ የሲዳማ ዞን ባህል ቱሪዝም፤የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አቶ ሚሊዮን ማትዮስ...

የደቡብ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳደር አቶ #ሚሊዮን_ማቲዎስ:

• አሁን ባለው ሁኔታ እንደከዚህ ቀደሙ የሲዳማን የክልልነት ጥያቄ አፍኖ ለመቀጠል አዳጋች ነው፤

• የደቡብ ክልል ከአምስት ወደ አንድ ሲጠቃለል በዴሞክራሲያዊ መልኩ ህዝቦች ተወያይተውበት፤ ቋንቋዬንና ባህሌን ለማሳደግ ይመቸኛል በሚል አይደለም፤

• ደኢህዴን ህዝበ ውሳኔ እንዲካሄድ የወሰነው ዘላቂ ሰላምን ከማረጋገጥ አንፃር ህዝቦች ያዋጣል የሚሉትን ሃሳብ ማዳመጥ ተገቢ ሆኖ በመገኘቱም ጭምር ነው፤

• የሲዳማ ክልል መሆን የክልሉን #አደረጃጀት ይቀይረዋል፤ አደረጃጀቱ ሲቀየር ደግሞ በጥናት ላይ ተመስርቶ የህዝቦች ትስስርና ጥቅም ጥናት ላይ የተመሰረተውን መነሻ ከህዝቦች ጋር ውይይትና ምክክር በማድርግ መፈፀም እንዳለበት ይታመናል፤

• ሃዋሳ ከተማን አሁንም ቢሆን የሲዳማ ዞን ዋና ከተማ ናት፡፡

#ሲዳማ_ክልል ከሆነ #ሃዋሳ የሲዳማ ክልል ዋና ከተማ ሆኖ ይቀጥላል ማለት ነው፤

• በሃዋሳ የሚኖሩ የተለየዩ ብሄር ብሄረሰቦችን በሚመለከት የሃገሪቱ ህግና ህገመንግስት በሚፈቅደው መሰረት ዜጎች የመኖር የመስራት መብታቸውን የሚያግድ ነገር ይኖራል ብለን አንገምትም።

Via EPA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ሲአን #ሲዳማ_ዞን #ሞረቾ #ወተረሬሳ #ሀገረሰላም

በደቡብ ክልል በሐዋሳ ከተማ እና በሲዳማ ዞን የገጠር ከተሞች በተከሰቱ ግጭቶች የሞቱት ሰዎች ቁጥር 21 መድረሱን የሲዳማ አርነት ንቅናቄ አስታወቀ። የሲዳማ አርነት ንቅናቄ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ደሳለኝ ኔሳ ዛሬ ለጀርመን ራድዮ እንደተናገሩት በሲዳማ ዞን ከፀጥታ አስከባሪዎች ጋር በነበረ ግጭት 21 ሰዎች መሞታቸው ተናግረዋል። በሲዳማ ዞን ስር ባለው ወተረሬሳ 12 ሰዎች መሞታቸውን የሚናገሩት አቶ ደሳለኝ በሞሮቾ ሶስት እና በሀገረሰላም ደግሞ ሁለት ሰዎች በግጭቱ ህይወታቸው እንዳለፈ አስረድተዋል።

በሐዋሳ በነበረው ግጭት አራት ሰዎች መሞታቸውን እና ሌሎች ሰባት ሰዎች በፅኑ መቁሰላቸውን የከተማይቱ ከንቲባ አቶ ስኳሬ ሾዳ ዛሬ በሰጡት መግለጫ ተናግረዋል። በግጭቱ የተጠረጠሩ 150 ሰዎች በህግ ቁጥጥር ስር መዋላቸውንም ከንቲባው ጠቁመዋል። ግጭቱን ተከትሎ የክልል እና የፌደራል አካላት ባደረጉት የማረጋጋት ስራ በሐዋሳ ከተማ እና በአካባቢው ያለው የፀጥታ ሁኔታ መሻሻሉን አቶ ስኳሬ ገልፀዋል። በሐዋሳ በዛሬው ዕለት የትራንስፖርት እንቅስቃሴ እንደታየና የማህበራዊ አገልግሎት መስጫዎች ተከፍተው ስራ መጀመራቸው ተሰምቷል። የኢንተርኔት አገልግሎት እና የማህበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ግን አሁንም ዝግ ናቸው።

ምንጭ፦ የጀርመን ራድዮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ሲዳማ_ዞን

በሲዳማ ዞን ስለጠፋው ክቡር የሰው ህይወት የተቃዋሚ ፓርቲዎች እና ዓለም ዓቀፍ ሚዲያዎች ነዋሪዎችን ዋቢ አድርገው ከሚገልፁት ቁጥር ውጪ በመንግስት በኩል ይፋ የተደረገ መረጃ የለም። እኛም በተለያየ መልኩ ስለጠፋው የሰው ህይወት የተረጋገጠ መረጃ ለማግኘት እየጣርን ነው። የወደመ የተቋማት እና የግለሰቦች ንብረትን በተመለከተም አስተማማኝ መረጃ ወድናተ ለማድረስ ጥረት እያደረግን ነው።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ሲዳማ

የ " በላይነህ ክንዴ ግሩፕ "  በሲዳማ ክልል በሎካ አባያ ወረዳ 550 ሔክታር መሬት ተረክቦ በፍራፍሬ እና በበጋ መስኖ ስንዴ ልማት 4 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ በመመደብ ልማት መጀመሩን የበላይነህ ክንዴ ግሩፕ የእርሻ ዘርፍ አስፈጻሚ ዶ/ር አንተነህ አብዋ ለሪፖርተር ጋዜጣ  በሰጡት ቃል ተናግረዋል።

ዶ/ር አንተነህ አብዋ ምን አሉ ?

- በሲዳማ ክልል ሎካ አባያ ወረዳ 550 ሔክታር መሬት ተረክበረን 380 ሔክታር መሬት ላይ አትክልት ከማልማት አስቀድሞ የበጋ ስንዴ እያለማን እንገኛለን ፤ ምርታችንን ለውጭ ገበያ ለማቅረብም አቅደናል።

- በሔክታር ከ30 እስከ 50 ኩንታል ለምግብ ፍጆታ የሚውል ስንዴ ለማልማትና ከዚህም በጥቂቱ ከ11,400 በላይ ኩንታል ስንዴ ለመሰብስብ ታቅዷል። ለዚህም ከ600 በላይ ኩንታል ስንዴ ለዘር ተጠቅመናል።

- ለስንዴና ማዳበሪያ ግዥ ከ300 እስከ 400 ሚሊዮን ብር ወጪ አድርገናል። 400 ኩንታል ኤንቲኤስ፣ እንዲሁም 400 ኩንታል ዩሪያ መሬቱን ለማሰናዳት ማዳበሪያ ተጠቅመናል።

- የእርሻ ልማቱን ለማከናወን በአጠቃላይ ከ4 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ ተደርጓል፤ ከ20 ኪሎ ሜትር መንገድ እንዲሁም ወደ እርሻው የሚፈሰውን የወንዝ ውኃ ለመቆጣጠር 4 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለው ግድብ ተገንብቷል።

-  የአባያ ሐይቅና የብላቴ ወንዝን ለእርሻው በዋነኛነት እንጠቀማለን፤ ለዚህም ዘመናዊ ፓምፖችን ለመጠቀም ተሰናድተናል።

- በአካባቢው የዝናብ እጥረት ያለበት አካባቢ በመሆኑ ከአባያ ሐይቅ እስከ እርሻው መዳረሻ ድረስ ሦስት ኪሎ ሜትር ያለውን ርቀት በፓምፕ ስቦ ለማምጣት መሠረተ ልማት ተዘርግቷል።

- የበጋ ስንዴ ማልማቱ ሲጠናቀቅ የአትክልትና የፍራፍሬ ልማቱ ይቀጥላል ፤ አቮካዶ፣ ሙዝና ፓፓዬ ለማልማት የችግኝ ግዥ ተፈጽሞ ለመትከል ዝግጅት ላይ ነን።

- መሬቱን ከተረከብን 4 ወራት ብቻ  ሲሆን አትክልትና ፍራፍሬ ማልማቱንም ለማስቀጠል ከ40 ሔክታር መሬት በላይ አቮካዶ ተተክሏል። በቀሪዎቹ ሙዝ፣ ብርቱካን፣ ሎሚ፣ እንዲሁም ፓፓዬ ለማልማት ታቅዷል። በዚህ መሬት ላይ ተጨማሪ ፍራፍሬዎችን ለማሰናዳት የችግኝ ማፍላት ሥራ እየተሰራ ነው። ለጊዜው ለ200 የአካባቢው ሠራተኞች፣ የሥራ ዕድል ተፈጥሯል፤ ይኼም ቁጥር ወደ 500 ለማሳደግ ታቅዷል።

በሌላ በኩል ፤ በላይነህ ክንዴ ግሩፕ ከሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ጋር በመተባበር በአካባቢው ለምትገኘው #መራሬ_ከተማ #የውኃ እና #የኤሌክትሪክ_ኃይል ለመዘርጋት የኮንክሪትና የእንጨት ፖል ዝርጋታ በማጠናቀቅ ላይ እንደሚገኝ ተሰምቷል።

ምንጭ፦ ሪፖርተር ጋዜጣ

@tikvahethiopia
ስለ ሀገሬ ምን ያህል አውቃለሁ ?

" ፊቼ ጨምባላላ "

የሲዳማ ሕዝብ የጨረቃና ከዋክብትን አቀማመጥ በማጥናት አዲስ ዓመት ያከብራል ፤ ይኸው በዓል ፊቼ ጨምበላላ ነው የሚባለው።

እንደ ሲዳማ የሀገር ሽማግሌዎች " ፊቼ ጫምባላላ " መከበር ከጀመረ ከ1800 ዓመታት በላይ አስቆጥሯል።

በዓሉ የሲዳማ ሕዝብ ማንነቱን ከተረዳበት ጊዜ አንስቶ በድምቀት ሲከበር ቆይቷል፤ አሁንም እየተከበረ ይገኛል።

ፊቼ ጨምበላላ በዓል የሚከበርበት ቋሚ ቀን የለውም። በዓሉ የሚከበርበት ቀን በአያንቱዎች ጥቆማ መሰረት ነው የሚቃረጠው።

'የፊቼ ጨምበላላ ዋነኛ ትርጉም ሰላም ነው' ፤ አንድነትና ፍቅር የበዓሉ መለያ ነው። በዚህ በላይ የተጣሉ ሰዎች ይታረቃሉ። ሃዘን ላይ የነበሩ ሰዎችም የሃዘን ልብሳቸውን ይቀይራሉ።

በዚህ በዓል ከቀዬው ርቆ የነበረ ሰው ወደቀዬው ይመለሳል፤ ለዚህ በዓል ተብሎ እርድ አይፈጸምም፤ ስጋም አይበላም። ክብቶችን #መምታትም ክልክል ነው። ላሞች ሳር የበዛበት መስክ ላይ ይሰማራሉ።

ሌላው በሲዳማ ሕዝብ ዘንድ በፊቼ ጨምበላላ በዓል ወቅት ማረስ #ነውር ነው፤ ለዚህም ምክንያቱ ደግሞ የፊቼ ጨምበላላ በዓል የሲዳማ ሕዝብ ብቻ ሳይሆን #የተፈጥሮም ነው ተብሎ ስለሚታመን ነው።

" ፊቼ " የአዲስ ዓመት በዓል ዋዜማ ሲሆን፤ " ጨምበላላ " ደግሞ የአዲስ ዓመት መጀመሪያው ቀን ሲሆን የሲዳማ ሕዝብ አዲስ ዓመትን ሲቀበል፤ ዓመቱ የብልጽግና እንዲሆንላቸው 'ፊቼ ጄጂ' ይላሉ።

ፊቼ ጄጂ !
#ኢትዮጵያ
#ሲዳማ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ሲዳማ

የሲዳማ ክልል መንግሥት ፤ " የተሰጣቸውን የመንግስትና የህዝብ አደራ ወደ ጎን በመተው በሙስናና ብልሹ አሰራር ላይ ተሳትፈዋል " ባላቸው አመራሮች ላይ የፖለቲካ ውሳኔ መተለለፉን አሳወቀ።

ክልሉ እኚሁ አመራሮች እንደየሥራቸው ከህግ ተጠያቂነት አያመልጡም ብሏል።

የሲዳማ ክልል ፕሬዝዳንት  አቶ ደስታ ሌዳሞ በሰጡት መግለጫ ፤ የተሰጣቸውን ኃላፊነት በአግባቡ ያልተወጡና በብልሹ አሰራር ላይ የተሳተፉ አመራሮችን በክልሉ ማዕከል ሀዋሳ ከተማ ሲደረግ በቆየው አካላዊ ግምገማ የፖለቲካ ውሳነ መተላለፉን ገልጸዋል።

" ማንም ባጠፋው ጥፋት ልክ ከህግ አግባብ እንዲጠየቅም ይደረጋል " ብለዋል።

ፕሬዜዳንቱ ባለፉት ለ10 ቀናት ሲካሄድ ከርሟል ባሉት የሲዳማ ክልል የፓርቲና የመንግሥት ሥራዎች አፈጻጸም ግምገማ ላይ በአፈፃፀም ላይ ዝቅተኛ ዉጤት ያስመዘገቡ ዘርፎች ላይ ትኩረት ተሰጥቶ ግምገማ መደረጉን ገልጸዋል።

በብልሹ አሰራር ላይ የተሳተፉ አካላት ላይ ፖለትካዊ እርምጃ የተወሰደ መሆኑና የህግ ተጠያቂ እንደሚሆኑ አመልክተዋል።

አቶ ደስታ ፤ በሀዋሳ ከተማ ላይ ከፍተኛ ሌብነትና ብልሹ አሰራር በመታየቱ ያለውን ሁነታ በመሸሽ ስብሰባ ረግጠው ወጥቶ የሄዱ አመራሮች መኖራቸውን አንስተው በዚህ ብቻ የምተወው አይደለም ተጠያቂነት ይቀጥላል ብለዋል።

የትኞቹ አመራሮች ስብሰባ ረግጠው እንደወጡ በስም ጠቅሰው አልተናገሩም።

በተደረገ ማጣራት 97 ሰዎች በተለይ በመዳበሪያ ግብዓት ጋር ተያይዘው ከአራት ወረዳ ፦
- ከቀበሌ ልቀመምበር ጀምሮ፣
- ስራ አስኪያጅዎች፣
- የልማት ሰራተኞች፣
- የመጋዘን ጠባቂዎችና ሀላፊዎች ሁለት ወረዳ አስተዳደር ጨምሮ ለህዝብ የሚደርሰውን በማስተጎያጉል በዝርፊያ ጉዳይ ተሳታፊ መሆናቸው ተለይቶ ተጠያቂ እንዲሆኑ አድርገናል ብለዋል።

የክልሉ ፕሬዜዳንት የሁለት ወረዳ አስተዳደሮችን ጨምሮ ተይዘዋል ያሏቸውን 97 ሰዎች በስም አልገለፁም።

ፕሬዜዳንቱ ፤ " በግምገማ መድረኩ 25 ግለሰቦች በብልሹ አሰራር በህግ ቁጥጥር ስር ሆነዋል " ያሉ ሲሆን በተጨማሪም 10  አመራሮች ከሀላፊነት እንድነሱ ተደርገዋል ሲሉ አሳውቀዋል።

እነዚህ በቁጥጥር ስር ውለዋል የተባሉት አመራሮች ስም በይፋ አልተገለፀም ፤ በተጨማሪ ከኃላፊነት ተነሱ የተባሉትንም አመራሮች በግልፅ ስማቸውን አልተናገሩም።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከሰሞኑን ከክልሉ ግምገማ ጋር በተያያዘ የሀዋሳ ከንቲባ ረ/ፕሮፌሰት ፀጋዬ ቱኬ ከኃላፊነት መነሳታቸውንና በህግ እንዲጠየቁም ውሳኔ መተላለፉን ሌሎች በርካታ አመራሮች ላይ መሰል እርምጃ እንደሚወሰድ የክልሉን ብልፅግና ፓርቲ ዋቢ በማድረግ መዘገቡ አይዘነጋም።

የክልሉ ነዋሪዎችም በክልሉ ያለው እጅግ ህዝብን የሚያማርር ብልሹ አሰራር፣ ሙስናና ዘረፋ ስር የሰደደ መሆኑን በመግለፅ እያንዳንዱ አመራር ከታች እስከ ላይ እንዲጣራ መጠየቃቸውም ይታወሳል።

የሲዳማ ክልል በሙስና እና በብልሹ አሰራር በቁጥጥር ስር ዋሉ፣ ከኃላፊነታቸውም እንዲነሱ ተደረጉ ስላላቸው አመራሮች ይፋዊ ዝርዝር የሚያወጣ ከሆበ ተከታትለን እናሳውቃለን።

@tikvahethiopia
#ሲዳማ

የሲዳማ ክልል የትምህርት ቢሮ የ2015 ዓ/ም የ8ኛ ክፍል  ክልል አቀፍ የፈተና ውጤትን በቀን 04/01/2016 ዓ.ም ይፋ አድርጓል።

ተማሪዎች ውጤታቸውን በኦንላይ (ከታች ባለው ሊንክ) በመግባት ማየት ይችላሉ ተብሏል።

ተማሪዎች ውጤታቸውን ለማየት ወደ ድረገፁ ሲገቡ በቅድሚያ ቪፒኤን ማጥፋት እንዳለባቸው ተጠቁሟል።

ተማሪዎች ሲስተሙን ለመጠቀም ፦ ይህን ሊንክ  https://sidama.ministry.et  በመጫን ፤ ፊት ለፊት በሚታየው  ቅጽ(form) ላይ የተማሪውን መለያ ቁጥር በማስገባት ፤ " ውጤት ይመልከቱ " የሚለውን ቁልፍ በመጫን ውጤታቸውን ማየት እንደሚችሉ ተገልጿል።

@tikvahethiopia
#ሲዳማ

የሲዳማ ክልል ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ባወጣው መግለጫ ማህበራዊ ሚዲያ በመጠቀም ህብረተሰቡ የሚረብሹ አካላትን ሲያስጠነቅቅ ተቃዋሚው የሲዳማ ፊደራሊስት ፓርቲ  በበኩሉ የቢሮው ሰሞነኛ መግለጫ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመሸፋፈን በር የሚከፍት ነዉ ብሎታል።

የሲዳማ ክልል ሠላምና ፀጥታ ቢሮ ምንድነው ያለው ?

ቢሮው ፤ የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የፀጥታ ግብረሃይል ወቅታዊ ክልላዊና የሀገራዊ ፀጥታ በተመለከተ ውይይት ማድረጉን ገልጿል።

ግብረኃይሉ በክልሉ አንዳንድ ግለሰቦች በክልሉ መንግሥትና በሕብረተሰቡ መካከል ጥርጣሬ ለመፈጠር፣ በተለያዩ ማህበራዊ ሚድያዎችን በመጠቀም፣ ሀሰተኛ መረጃዎች በማሰራጨት ላይ ናቸው ብሏል።

የክልሉ መንግሥት በተለያዩ ጊዜ እንዲህ አይነት ድርጊት ውስጥ በማወቅም ሆነ ባለማወቅ ተሳታፊ የሆኑ አካላት ከድርጊታቸው እንዲመለሱ ቢነገራቸውም መመለስ ባለመቻላቸው የክልሉን ሰላም ለማስጠበቅ ሲባል በየደረጃው የሚገኙ ፀጥታ አካላት አስፈላጊውን ህግ የማስከበር ኃላፊነታቸውን መወጣት እንደሚገባቸው አሳስቧል።

መንግሥት ህግን ለማሰከር በሚወስደው እርምጃ ጣልቃ ለመግባት የሚሞክሩ አካላት ከወዲሁ መጠንቀቅ ይገባቸዋል ብሏል።

ከፀጥታ ቢሮው በተጨማሪ የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ትላንት አንድነትን በሰበኩ አፋቸው ዛሬ ጎሰኝነት እየሰበኩ በማህበራዊ ሚድያ ሀሰተኛ ወሬ እያሰራጩ ህብረተሰቡ ሳይወክላቸው ለግል ጥቅማቸው ከውጭና ከውስጥ ተልዕኮ ተቀብሎ እኩይ ተግባራቸው ለመፈጸም የሚንቀሳቀሱ አካላት አሉ ያለ ሲሆን እነዚህን አካላት የክልሉ መንግሥት አይታገሳቸውም ብሏል።

የሲዳማ ፌዴራሊስት ፓርቲ ፤ የክልሉ ጸጥታ ጉዳይ ቢሮ ያወጣው መግለጫ ልክ እንዳልሆነና በክልሉ ዉስጥ ያሉ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመሸፋፈን በር የሚከፍት ነዉ ብሏል።

ለቲኪቫህ ኢትዮጵያ አስተያየታቸዉን የሰጡት የሲዳማ ፌደራሊስት ፓርቲ ጽህፈት ቤት ሀላፊዉ አቶ ገነነ ሀሳና ፤ ይህ የክልሉ መንግስት አካሄድ በሶሻል ሚዲያ የሚታገሉትን ወጣቶች ድምጽ በማፈን በመንግስት ስር ሆነዉ የህዝብን ሀብት የሚዘርፉ አካላትን ከለላ የሚሰጥ ነዉ ብለዋል።

አቶ ገነነ አክለዉም ካሁን በፊት በክልሉ የሚከሰቱ በርካታ ችግሮችን አስመልክተን ለሰላም ሚኒስትር ለፌደራል ፖሊስና ለምርጫ ቦርድ የተለያዩ ደብዳቤዎችን ፅፈናል ያሉ ሲሆን አሁንም የክልሉ መንግስት እየሄደበት ያለዉን መንገድ ለማስተካከል እንደሚጥሩ ገልጸዋል።

ካሁን በፊት ለሚጽፉት የቅሬታ ደብዳቤዎች ፈጣን ምላሽ የሚያገኙት ከምርጫ ቦርድ መሆኑን የሚያነሱት ሀላፊዉ አሁን ላይ ከሌሎችም ሚኒስትር መስሪያቤቶች ጋር በመነጋገር ችግሮችን ለመቅረፍ እንደሚሰሩ ጠቁመዋል።

@tikvahethiopia
#ሲዳማ

- " እየታየ ያለው ከህግ ያፈነገጠ አካሄድ ሊቆም ይገባል " - ሲዴፓ

- " ተቃዋሚም ሆነ የገዥዉ ፓርቲ  አባል ሁሉም ጥፋት ላይ ከተገኘ ተጠያቂ ይሆናል " - የሲዳማ ክልል ሰላምና ጸጥታ ቢሮ

በሲዳማ መንግስት ባለስልጣናት እየታዬ ያለዉ  ከህግ ያፈነገጠ አካሄድ ሊቆም  ይገባል ሲል የሲዳማ ፌደራሊስት ፓርቲ አሳሰበ።

ፖርቲዉ ከሰሞኑ በተደጋጋሚ በክልሉ ባለስልጣናት የሚፈጸመዉ ህገወጥ እስርና ዉክቢያ እየከፋ መጥቷል ሲል ነዉ ክሱን ያቀረበዉ።

ለቲኪቫህ ኢትዮጽያ አስተያየታቸዉን የሰጡት የሲዳማ ፌደራሊስት ፓርቲ  ሊቀመንበር  አቶ  ተሰማ ኤልያስ   እንደሚገልጹት አሁን ላይ በርካታ ወጣቶች በክልሉ መንግስት የጸጥታ ሀይሎች ተይዘዉ ራቅ ወዳለ ቦታ መታሰራቸዉን በመግለጽ እነዚህ ግለሰቦች በ48 ሰአት ፍርድ ቤት የመቅረብ መብታቸዉ መጣሱንም ገልጸዋል።

እስካሁን ከ10 በላይ ከፍተኛ አመራሮችን ጨምሮ ለእስር ተዳርገዉብኛል የሚሉት ሀላፊዉ በቁጥጥር ስር የዋሉ አባሎቻችን ቤተሰብ እንዳይጠይቃቸዉ ሁሉ  መከልከሉን ገልጸዉ እርሳቸዉን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ አመራሮችም ዉክቢያ ዉስጥ መሆናቸዉን ገልጸዋል።

በዚህ ጉዳይ ለ ' አዲስ ስታንዳርድ ' ድረገፅ ከሰሞኑ ምላሽ የሰጡት የሲዳማ ክልል ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ኃላፊዉ አቶ አለማየሁ ጢሞቲዎስ በበኩላቸዉ ከህግ አግባብ ዉጭ የተያዘ ሰዉ አለመኖሩን በመግለጽ ተቃዋሚም ሆነ የገዥዉ ፓርቲ  አባል ሁሉም ጥፋት ላይ ከተገኘ ተጠያቂ ይሆናል ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል።

መረጃው በሀዋሳ የቲክቫህ ቤተሰብ አባል የተዘጋጀ ነው።

@tikvahethiopia
#አሁን #ሲዳማ

የሲዳማ ክልል ም/ ቤት አስቸኳይ ጉባዔ በሀዋሳ እያካሄደ ነው።

ምክር ቤቱ 6ኛ ዙር 3ኛ የስራ ዘመን 1ኛ አስቸኳይ ጉባኤ ነው እያካሄደ ያለው።

ለአንድ ቀን ብቻ ይካሄዳል በተባለው በዚህ አስቸኳይ ጉባኤ በሶሰት የተለያዩ አጃንዳዎች ላይ ውይይት ይደረጋል ተብሏል።

- ለጉባኤው ሞሽን ቀርቦ ይጸድቃል።

- የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ የስራ ሃላፊዎች ሹመት ለምክር ቤቱ አቅርበው ያፀድቃሉ።

- የምክር ቤቱ አባላት #የህግ_ከለላ ማንሳት ላይ ተወያይተው ውሳኔ ይሰጣሉ።

#ኢዜአ

@tikvahethiopia
#ሲዳማ_ክልል 

" 26,000 ኢንተርፕራይዞች የከሰሙ መሆናቸውን አረጋጥጠናል " - የሲዳማ ክልል ሥራ፣ ክህሎትና ኢንተርፕራይዞች ቢሮ

በአነስተኛ እና ጥቃቅን የተደራጁ ኢንተርፕራይዞች በቦታ ጥበትና ሌሎች መሰል ችግሮች ሥራ ለማቆም እየተገደዱ  መሆናቸውን ተደራጆቹ በተደጋጋሚ  ቅሬታ ሲያነሱ ይደመጣሉ። 

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ስለሚነሱ ቅሬታዎች የሲዳማ ክልል ሥራ፣ ክህሎትና ኢንተርፕራይዞች ቢሮ ምክችል ኃልፊ  እና የሥራ ዕድል ፈጠራ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ከፍያለው ከበደን ጠይቋል።

አቶ ከፍያለው ፤ " 26,000 ኢንተርፕራይዞች የከሰሙ መሆናቸውን አረጋጥጠናል። " ብለዋል።

" ከዛ ውጭ ያሉት 48 በመቶ አካባቢ የሚሆኑት ድጋፍ የሚያስፈልጋቸው ናቸው። ሌሎች ወደ 52 በመቶ አካባቢ የሚሆኑት የተሻለ ደረጃ ላይ ናቸው " ሲሉ ተናግረዋል።

ኢንተርፕራይዞቹ የከሰሙበት ችግር ምን እንደሆነ ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ለቀረበላቸው ጥያቄ ፦
- ድርቅ፣
- የፀጥታ ችግር
- ወደ ከተማ ያሉት ደግሞ በገበያ ማጣት፣
- በማኅበር እስከ 30 ድረስ የሚደራጁት እርስ በእርሳቸው ባለመስማማት
- ሌሎችም በግል ምክንያት
- በቂ ስልጠና እና አግኝተው ካለመግባታ ጋር የተያያዘ ነው ብለዋል።

አዲስ አበባን ጨምሮ በሌሎች አካባቢዎች የተደራጁ ኢንተርፕራይዞች በመሬት ጥበት ሥራ ለማቋረጥ እንደሚገደዱ ይገልፃሉ።

ሲዳማ ክልልም አዲስ ክልል ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ብዙ ቅሬታዎች ሲነሱ ይደመጣልና በመሬት ጥበት ምክንያት ያለው ችግር ለመቅረፍ ምን እየተሰራ እንደሆነ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ለቢሮው ጥያቄ አቅቧል።

ያንብቡ ፦ https://telegra.ph/Tikvah-Ethiopia-12-17

@tikvahethiopia
#አፊኒ #ሲዳማ

በሲዳማ በህዝብ ዘንድ ቁጣ ፈጥሯል የተባለው መፅሀፍ ጉዳይ ምንድነው ?

ከሰሞኑ በዶ/ር አራርሶ ገረመዉ የተጻፈ " አፊኒ " የተሰኘ መጽሀፍ በአእምሮአዊ ንብረት ባለስልጣን ተመዝግቦ የባለቤትነት ፈቃድ ማግኘቱን ተከትሎ በሲዳማ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ በኩል ጥያቄ ተነስቷል።

ቢሮው ለአእምሯዊ ንብረት ባለስልጣን በላከው የቅሬታ ደብዳቤ " ለዶክተር አራርሶ ገረመዉ ' አፊኒ ' በሚል ስያሜ የተሰጠው የባለቤትነት እዉቅና በህዝቡ ዘንድ ቅሬታ ፈጥሯል " በማለት ገልጿል።

የተሰጠዉ እውቅና " የባለቤት " የሚል ሀሳብ የያዘ ሲሆን ይህም የድርሰት ስራ በመሆኑ የቅጅና ተዛማጅ መሆን እንደሚገባዉና " የፈጠራው ባለቤት " የሚለው ቃልም አግባብ አይደለም በማለት ገልጿል።

በመሆኑም ' አፊኒ ' የመላዉ የሲዳማ ህዝብ እንጅ የደራሲዉ የዶ/ር አራርሶ ገረመዉ የፈጠራ ንብረት አለመሆኑ ታዉቆ ማስተካከያ እንዲደረግ በማለት ማብራሪያና ማስተካከያ ጠይቋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያም ጉዳዩን ሰምቶ የመጽሀፉን ደራሲ አነጋግሯል።

ዶ/ር አራርሶ ገረመው ፤ የተፈጠረዉ ሁኔታ ከርሳቸዉ ቀድሞ ሶሻል ሚዲያዉን ማጥለቅለቁን ገልጸዋል ፤ " በዚህም አዝኛለሁ " ብለዋል።

ሁኔታውን በንግግር እንደፈቱት ገልጸው ጥያቄውን ሰላማዊ በሆነ መልኩ ለመመለስና ማህበረሰቡን ለማስቀደም በማሰብ ' አፊኒ ' የሚለዉ ርእስ እንዲስተካከል በመወሰን ስራ መጀመራቸውን አስረድተዋል።

' አፊኒ ' የሚለው ርዕስ ተቆርጦ የወጣ መሆኑን የገለጹት ዶ/ር አራርሶ ፥ አሁን ላይ መጽሀፉ ላይ ያለው ሙሉ አርእስት ' አፊኒ የሲዳማ ድንቅ ባህል ታላቅ ተቋም አስደማሚ የሰላም እሴት ' በሚል ለማስተካከል በደብዳቤ የአእምሯዊ ንብረት ባለስልጣንን መጠየቃቸውን ባለስልጣኑም እንደተቀበላቸውና ማስተካከያ እንደተደረገበት ገልጸዋል።

" ይህንን መጽሐፍ የጻፍኩት #የህዝቤን_ታሪክ ለማስተዋወቅ እና ለማጉላት መሆኑን በውስጡ ያሰፈርኩት አሳብ ይመሰክራል " ያሉት ደራሲው " በርዕሱ ምክኒያት የተፈጠረውን ቅራኔ በቀላሉ ከፈቃድ ሰጪው ጋር ተነጋግሮ መፍታት የሚቻል ቢሆንም በማህበራዊ ሚድያ የጥቂቶች ሀሳብ በዚህ ደረጃ መንጸባረቁ አስገርሞኛል " ሲሉ ተናግረዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyHawassa

@tikvahethiopia