TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.9K photos
1.49K videos
211 files
4.07K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ከፋ ዞን‼️

በካፋ ዞን ስለ ቡና መገኛነት በድረ-ገጽ በተላለፈ መረጃ የተፈጠረውን አለመረጋጋት ወደ ነበረበት #ለመመለስ እየተሰራ መሆኑን የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ #ሚሊዮን_ማቲዎስ ገለጹ።

ርዕሰ መስተዳድሩ ዛሬ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ እንዳስታወቁት በካፋ ዞን የተፈጠረው አለመረጋጋት ከቡና መገኛነት ጋር በተያያዘ በድረ-ገጾች በተላለፈ መረጃ አማካኝነት ነው።

የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን ዓለም አቀፍ የቡና ኮንፍረንስ በቅርቡ ለማዘጋጀት በሚያደርገው ሂደት በድረ-ገጹ የተላለፈው መረጃ የካፋን ወጣቶችና ህዝቡን አስቆጥቶ በአካባቢው አለመረጋጋት ተፈጥሯል።

“የቡና ባለቤትነት ጥያቄን በሚመለከትም የባለቤትን ጉዳይን የሚመራና እውቅና የሚሰጥ ራሱን የቻለ ተቋም በሃገር ደረጃ ያለ በመሆኑ ጥያቄው አሰራሩን ተከትሎ ምላሽ ያገኛል”ብለዋል፡፡

ጥያቄውን በሰላማዊ መንገድ ያቀረበው የካፋ ህዝብና ወጣት የትራንስፖርት እንቅስቃሴ ሲገታ የሚያሳድረውን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጫና በመረዳት የተዘጉ መንገዶችን እንዲከፍት ጠይቀዋል፡፡

በአካባቢው ያሉ የሃይማኖት አባቶችና የሃገር ሽማግሌዎች ይህንን በማስተባበርና ወጣቱም ከጸጥታ ሃይሉ ጋር በመተባበር የአካባቢውን ሰላም ወደ ነበረበት እንዲመልስ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።

በአንዳንድ የክልሉ አካባቢዎች የሚታዩ ግጭቶችም አሁን ላይ ወደ ሰላም እየተመለሱ መሆናቸውን ገልጸው የአብዛኛዎቹ መንስኤም ከመዋቅር ጋር የተያያዙ እንደነበሩ ጠቁመዋል።

በቅርቡ የክልሉ ምክር ቤት 44 ወረዳዎችንና 3 ዞኖችን በአዲስ መልክ ማዋቀሩን ተከትሎ አዳዲስ ፍላጎቶች የፈጠሩት ስሜትና የሚጠበቅ እንደሆነም ገልጸዋል፡፡

“ችግሮቹን በቀጣይ ከህዝቡ ጋር በሚደረግ ጥልቅ ውይይት መስመር የሚይዙ ናቸው” በማለት  በየደረጃው ያለ አመራር ከህዝቡ ጋር በሚያደርጋቸው ሰፊ የውይይት መድረኮች እንደሚኖሩ ገልጸው በዚህም የሰላም ግንባታ ስራው እንደሚጠናከር ተናግረዋል፡፡

ምንጭ፦ ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ወራቤ🔝የወራቤ ዩኒቨርሲቲ ዛሬ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ #ደመቀ_መኮንን፣ በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳድር አቶ #ሚሊዮን_ማቲዎስ፥ በሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ዶ/ር ሂሩት ወ/ማርያም እና በኢጋድ የሰላምና ደህንነት ተጠሪና የዩኒቨርሲቲው የቦርድ ሰብሳቢ አቶ ሲራጅ ፈጌሳ በይፋ ተመርቋል፡፡

ምንጭ፦ የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አቶ ሚሊዮን ማትዮስ...

የደቡብ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳደር አቶ #ሚሊዮን_ማቲዎስ:

• አሁን ባለው ሁኔታ እንደከዚህ ቀደሙ የሲዳማን የክልልነት ጥያቄ አፍኖ ለመቀጠል አዳጋች ነው፤

• የደቡብ ክልል ከአምስት ወደ አንድ ሲጠቃለል በዴሞክራሲያዊ መልኩ ህዝቦች ተወያይተውበት፤ ቋንቋዬንና ባህሌን ለማሳደግ ይመቸኛል በሚል አይደለም፤

• ደኢህዴን ህዝበ ውሳኔ እንዲካሄድ የወሰነው ዘላቂ ሰላምን ከማረጋገጥ አንፃር ህዝቦች ያዋጣል የሚሉትን ሃሳብ ማዳመጥ ተገቢ ሆኖ በመገኘቱም ጭምር ነው፤

• የሲዳማ ክልል መሆን የክልሉን #አደረጃጀት ይቀይረዋል፤ አደረጃጀቱ ሲቀየር ደግሞ በጥናት ላይ ተመስርቶ የህዝቦች ትስስርና ጥቅም ጥናት ላይ የተመሰረተውን መነሻ ከህዝቦች ጋር ውይይትና ምክክር በማድርግ መፈፀም እንዳለበት ይታመናል፤

• ሃዋሳ ከተማን አሁንም ቢሆን የሲዳማ ዞን ዋና ከተማ ናት፡፡

#ሲዳማ_ክልል ከሆነ #ሃዋሳ የሲዳማ ክልል ዋና ከተማ ሆኖ ይቀጥላል ማለት ነው፤

• በሃዋሳ የሚኖሩ የተለየዩ ብሄር ብሄረሰቦችን በሚመለከት የሃገሪቱ ህግና ህገመንግስት በሚፈቅደው መሰረት ዜጎች የመኖር የመስራት መብታቸውን የሚያግድ ነገር ይኖራል ብለን አንገምትም።

Via EPA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የአፊኒ ባህላዊ ስነ ስርዓት!!

"በሀገሪቱ የተጀመረውን ለውጥ ለማስቀጠል #የወጣቱ ሚና ከፍተኛ መሆን አለበት" – የሲዳማ ብሄር የሀገር ሽማግሌዎች
.
.
.
በኢትጵያ የተጀመረውን ለውጥ ለማስቀጠል የወጣቱ ሚና ከፍተኛ መሆን እንዳለበት የሲዳማ ብሄር የሀገር ሽማግሌዎች አሳሰቡ፡፡ በብሄሩ አመታዊው የአፊኒ ባህላዊ ስነ ስርአት #በሶሬሳ_ጉዱማሌ በሃዋሳ በዛሬው ዕለት ተካሂዷል፡፡

ሲዳማ ከሌሎች ህዝቦች ጋር ተዋዶ እና ተፍቅሮ #በአንድነት የመኖር እሴቱን ጠብቆ የኖረ ነው ያሉት የሀገር ሽማግሌዎች ወጣቱም ይህን አኩሪ ባህል ሊጠብቀውና ማንኛውም ጥያቄዎችን በሰላማዊ መንገድ ሊያቀርብ እንደሚገባ ገልፀዋል።

በውይይቱ ላይ የተገኙት የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ #ሚሊዮን_ማቲዎስ በበኩላቸው የሲዳማ ብሄር በአቃፊነቱ እንጂ በጥላቻ አይታወቅም ስለዚህም ከሁሉም ብሄር ብሄረሰቦች እና ህዝቦች ጋር በአንድነት ለመኖር የዘመናት ባህሉ ተጠናክሮ መቀጠል አለበት ብለዋል።

ወጣቱም የአባቶቹን ምክር በመስማት ሊተገብር ይገባል ያሉ ሲሆን ይህ መሰል ባህላዊ ስርአት ሌሎችም እንደተሞክሮ ሊጋሩት እንደሚገባ ርዕሰ መስተዳድሩ ተናግረዋል።

የውይይቱ ተሳታፊ ወጣቶችም የሀገር ሽማግሌዎችን ምክርና ተግሳፅ በስርአቱ መሰረት በመቀበል ለሀገራዊ ለውጡ የሚጠበቅባቸውን እንደሚወጡ fbc ገልፀዋል።

በወጣቱ ስም በሃዋሳም ሆነ በዞኑ የሚነሱ የሰላም መደፍረሶችን በመከላከል ህግና ስርአት እንዲከበር የበኩላችንን እንወጣለን ብለዋል ተሳታፊዎቹ፡፡

ክልል የመሆን ጥያቄ እና ሙሰኞችን የማጋለጥ ሂደት በሰላማዊ መንገድ እንደሚታገሉ ተናግረዋል።

በአፊኒ ስርአት የሀገር ሽማግሌዎችና ወጣቶቹ በወቅታዊ የፀጥታ ጉዳዮች ላይ ሰፊ ውይይት ካደረጉ በኋላ ቃል በመግባት አጠናቀዋል።

ምንጭ፦ fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Fake News Alert‼️

የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ለደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ #ሚሊዮን_ማቲዎስ ደብዳቤ ጻፈ በሚል በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ የተሠራጨው ደብዳቤ #የሐሰት መሆኑን ጽህፈት ቤቱ ገለፀ።

የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ባወጣው መረጃው “በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ የተሠራጨው ደብዳቤ የሐሰት መሆኑን ለሁሉም ኢትዮጵያዊ ማሳወቅ እፈልጋለሁ” ብሏል።

“ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር #አብይ_አህመድ እንዲህ ያለ ደብዳቤ እንዳልጻፉ ማሳወቅ እንወዳለን” ብሏል ጽህፈት ቤቱ።

በዚህ አጋጣሚ የማኅበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች እንዲህ የመሰሉ የሐሰት ዜናዎችን እያጣሩና #በጥንቃቄ እንዲጠቀሙ ሲልም ጥሪውን አስተላልፏል።

ምንጭ፦ FBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia