TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57.1K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#አፊኒ #ሲዳማ

በሲዳማ በህዝብ ዘንድ ቁጣ ፈጥሯል የተባለው መፅሀፍ ጉዳይ ምንድነው ?

ከሰሞኑ በዶ/ር አራርሶ ገረመዉ የተጻፈ " አፊኒ " የተሰኘ መጽሀፍ በአእምሮአዊ ንብረት ባለስልጣን ተመዝግቦ የባለቤትነት ፈቃድ ማግኘቱን ተከትሎ በሲዳማ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ በኩል ጥያቄ ተነስቷል።

ቢሮው ለአእምሯዊ ንብረት ባለስልጣን በላከው የቅሬታ ደብዳቤ " ለዶክተር አራርሶ ገረመዉ ' አፊኒ ' በሚል ስያሜ የተሰጠው የባለቤትነት እዉቅና በህዝቡ ዘንድ ቅሬታ ፈጥሯል " በማለት ገልጿል።

የተሰጠዉ እውቅና " የባለቤት " የሚል ሀሳብ የያዘ ሲሆን ይህም የድርሰት ስራ በመሆኑ የቅጅና ተዛማጅ መሆን እንደሚገባዉና " የፈጠራው ባለቤት " የሚለው ቃልም አግባብ አይደለም በማለት ገልጿል።

በመሆኑም ' አፊኒ ' የመላዉ የሲዳማ ህዝብ እንጅ የደራሲዉ የዶ/ር አራርሶ ገረመዉ የፈጠራ ንብረት አለመሆኑ ታዉቆ ማስተካከያ እንዲደረግ በማለት ማብራሪያና ማስተካከያ ጠይቋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያም ጉዳዩን ሰምቶ የመጽሀፉን ደራሲ አነጋግሯል።

ዶ/ር አራርሶ ገረመው ፤ የተፈጠረዉ ሁኔታ ከርሳቸዉ ቀድሞ ሶሻል ሚዲያዉን ማጥለቅለቁን ገልጸዋል ፤ " በዚህም አዝኛለሁ " ብለዋል።

ሁኔታውን በንግግር እንደፈቱት ገልጸው ጥያቄውን ሰላማዊ በሆነ መልኩ ለመመለስና ማህበረሰቡን ለማስቀደም በማሰብ ' አፊኒ ' የሚለዉ ርእስ እንዲስተካከል በመወሰን ስራ መጀመራቸውን አስረድተዋል።

' አፊኒ ' የሚለው ርዕስ ተቆርጦ የወጣ መሆኑን የገለጹት ዶ/ር አራርሶ ፥ አሁን ላይ መጽሀፉ ላይ ያለው ሙሉ አርእስት ' አፊኒ የሲዳማ ድንቅ ባህል ታላቅ ተቋም አስደማሚ የሰላም እሴት ' በሚል ለማስተካከል በደብዳቤ የአእምሯዊ ንብረት ባለስልጣንን መጠየቃቸውን ባለስልጣኑም እንደተቀበላቸውና ማስተካከያ እንደተደረገበት ገልጸዋል።

" ይህንን መጽሐፍ የጻፍኩት #የህዝቤን_ታሪክ ለማስተዋወቅ እና ለማጉላት መሆኑን በውስጡ ያሰፈርኩት አሳብ ይመሰክራል " ያሉት ደራሲው " በርዕሱ ምክኒያት የተፈጠረውን ቅራኔ በቀላሉ ከፈቃድ ሰጪው ጋር ተነጋግሮ መፍታት የሚቻል ቢሆንም በማህበራዊ ሚድያ የጥቂቶች ሀሳብ በዚህ ደረጃ መንጸባረቁ አስገርሞኛል " ሲሉ ተናግረዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyHawassa

@tikvahethiopia