TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.2K photos
1.5K videos
211 files
4.1K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#MoE #EIASC

በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ ቤት ዋና ፀሐፊ በሆኑት በሼይኽ ሐሚድ ሙሳ የተመራ ልዑክ ከኢ.ፌ.ዲ.ሪ የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር  ከፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ ከተመራ የሚኒስቴር መስራቤቱ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ጋር ዉይይት ማድረጉን ምክር ቤቱ ዛሬ አሳውቋል።

በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የተደረገው ውይይት  ፦

- በሙስሊም ተማሪዎች የሰላት ጉዳይ ከመደበኛ ትምህርት ቤቶች እስከ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት (ዩኒቨርሲቲዎች) ፤

- የሴት ሙስሊም ተማሪዎች ሒጃብና ያጋጠሙ ችግሮች፤

- በትምህርት ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የካሪኩለም ዝግጅት እና በተማሪዎች የመማሪያ መፅሀፍት ሚዛናዊነት በሚሉ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ እንደነበር ተገልጿል።

ም/ቤቱ የነበረው ውይይት #ዉጤታማ እንደነበር ገልጾ " በቀጣይም ከመቼውም ጊዜ በተሻለ ተቋማቱ ተቀራርበው ለመስራት የጋራ ስምምነት ላይ ደርሰዋል " ብሏል።

ከዚህ በተጨማሪም በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት  በሚቋቋመው እና በዘርፉ ከፍተኛ  ዕውቀትና ልምድ ያላቸው ባለሙያዎች በቀጣይ ከሚኒስትር መስሪያ ቤቱ የባለሙያዎች ቡድን ጋር ዉይይት ለማድረግ ከስምምነት ላይ መደረሱ ተገልጿል።

ምንጭ፦ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ቦረና በኦሮሚያ ክልል፤ ቦረና ዞን በተራዘመ ድርቅ በርካታ የቤት እንስሳት አልቀው የሚላስ የሚቀመስ ያጡ ነዋሪዎችም ከድርቁ ጋር በተያያዘ መሞት መጀመራቸውን ነዋሪዎችን ዋቢ በማድረግ ዶቼ ቨለ ሬድዮ ዘግቧል። ቦረና ዞን የተራዘመው ድርቅ የአርሶ አደሮችን በሚሊየኖች የሚቆጠሩ የቀንድ እና የጋማ ከብቶቻቸውን በመግደል አስከፊነቱን የቀጠለ ሲሆን የሰዎችም ህይወት በድርቁ ሳቢያ እያለፈ ነው ተብሏል። በቦረና…
#ቦረና

- በቦረና ዞን ካሉት የቀንድ ከብቶች ውስጥ 10 በመቶውን ለመታደግ 4 ነጥብ 4 ሚሊየን እስር ሳር ያስፈልጋል።

- በድርቁ ምክንያት በዞኑ ከ3 ሚሊየን በላይ እንስሳት የሞቱ ሲሆን ፥ ከዚህ ውስጥ 85 በመቶዎቹ የቀንድ ከብቶች ናቸው።

- በዞኑ የቀሩት 230 ሺህ የቀንድ ከብቶች ሲሆኑ፤ ለ3 ወር የቀንድ ከብቶቹን ለመታደግ ቢያንስ 4 ነጥብ 4 ሚሊየን እስር ሳር ማቅረብ ያስፈልጋል። በተጨማሪ 135 ሺህ ኩንታል መኖ የሚያስፈልግ ሲሆን በዞኑ ማቅረብ የተቻለው አንድ በመቶ ብቻ ነው።

- እየተደረገ ያለው ድጋፍ በቂ ባለመሆኑ የታሰበውን ያህል ችግር ውስጥ የሚገኙ ከብቶችን መታደግ ከባድ ሊሆን ይችላል።

- እስካሁን በቀንድ ከብቶች ሞት ምክንያት 33 ቢሊየን የሚገመት ብር ታጥቷል።

(የቦረና ዞን አስተዳደሪ ጃርሶ ቦሩ ለኤፍ ቢ ሲ ከሰጡት ቃል)

#ኤፍቢሲ

@tikvahethiopia
አሜሪካ ...

የግድያ ወንጀል ስትዘግብ የነበረችው ጋዜጠኛ ተገደለች።

አሜሪካዊቷ ጋዜጠኛ በኦርላንዶ ፍሎሪዳ አቅራቢያ ትላንት ከሰዓታት በፊት የተፈጸመን የግድያ ወንጀል እየዘገበች በነበረችበት ወቅት #በጥይት ተመታ መገደሏን ቢቢሲ አስነብቧል።

ጋዜጠኛዋ የተገደለችው እየዘገበችው በነበረው የግድያ ወንጀል #ተጠርጣሪ (ስሙ ኬዝ ሞሰስ 19 ዓመቱ) ነው።

ከጋዜጠኛዋ በተጨማሪ የዘጠኝ ዓመት ታዳጊ በተተኮሰባት ጥይት #ተገድላለች

ሌላኛዋ ጋዜጠኛ እና የታዳጊዋ እናት በተመሳሳይ ታጣቂ ተመትተው ጉዳት እንደደረሰባቸው ፖሊስ ገልጿል።

ሁለቱ ጋዜጠኞች " ስፔክትረም ኒውስ " ለተባለው የቴሌቪዥን ጣቢያ የሚሰሩ ሲሆን በአካባቢው የጣቢያው 13 ጋዜጠኞች የአንድ ሴትን ግድያ ሲዘግቡ ነበር።

ግለሰቧን (እድሜዋ በ20ዎቹ ሲሆን መኪና ውስጥ ነበረች) የገደለው ተጠርጣሪ ተመልሶ መጥቶ እንደተኮሰባቸው ፖሊስ ገልጿል። ጋዜጠኞቹ ግድያው የተፈፀመበት ቦታ ደርሰው ሲዘግቡ ነበር።

እነሱም ኢላማ ተደርጎባቸው ስለመሆኑ ግልጽ አይደለም።

ተጠርጣሪው ጋዜጠኞቹ ላይ ከተኮሰ በኋላ በአቅራቢያው ወደሚገኝ ቤት ገብቶ አንዲት ህፃን እና እናቷ ላይ ተኩስ ከፍቶ ህጻኗን ሲገድል እናትየው በአስጊ ሁኔታ ላይ ትገኛለች።

ተጠርጣሪው በቁጥጥር ስር የዋለ ሲሆን ወቅት የጦር መሳሪያ ይዞ እንደነበርና ከፖሊስ ጋር ባለመተባበር እምቢተኝነቱን ማሳየቱን መርማሪዎች መናገራቸውን ቢቢሲ ዘግቧል።

በመላው #አሜሪካ በጦር መሳሪያ በሚደርሱ ጥቃቶች በየአመቱ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ህይወታቸውን ያጣሉ።

@tikvahethiopia
#አፖሎ

የአፖሎን የተለያዩ አገልግሎቶች አጠቃቀም ለማግኘት ትክክለኛ የማህበራዊ ትስስር ገጾችቻችንን ይቀላቀሉ!
የአፖሎ ትክክለኛ የማህበራዊ ትስስር ገጾች ፡
Website: https://apollo.bankofabyssinia.com/
Telegram: https://t.iss.one/apollodigitalproduct
Facebook: https://www.facebook.com/apollodigitalproduct
Instagram: https://www.instagram.com/apollodigitalproduct/
Twitter: https://twitter.com/ApolloBoA
Tiktok: https://www.tiktok.com/@apollodigitalproduct
YouTube: https://www.youtube.com/@apollodigitalproduct

Apollo Digital Product
#ኮካኮላ

ኮካ ኮላ ለ30 ማኅበራት በ1 ሺ ኪ.ግ በተሰበሰበ ፕላስቲክ፥ የ1 ሺ ብር ድጎማ እንደሚያደርግ ገለጸ።

ኮካ-ኮላ ቤቨሬጅስ አፍሪካ-ኢትዮጵያ በአዲስ አበባ የሚገኙ ጠርሙስ የሚሰበስቡ ማህበራት የመሰብሰቢያ አቅማቸውን ለማሳደግ ያለመ የድጎማ እንደሚያደርግ ዛሬ አስታውቋል።

ድጎማው 30 በመዲናዋ ለሚገኙ ጥቅም ላይ የዋሉ ፕላስቲኮችን የሚሰበስቡ ማህበራትን ተጠቃሚ የሚያደርግ ሲሆን በዚህም 10 ሚልዮን ብር ድረስ ድጋፍ ለማድረግ እንዲሁም ኩባንያው  በ2030 የሚያመርተውን 100% ለመሰብሰብ እና እንደገና ጥቅም ላይ ለማዋል መታቀዱ ተነግሯል።

ድጋፉ ለማህበሮቹ በአፈጻጸማቸው መሰረት የሚሰጥ ሲሆን ሲሲቢኤ ኢትዮጵያ ለእያንዳንዱ 1,000 ኪሎ ግራም የተሰበሰበ ፕላስቲክ የ1,000 ብር ድጎማ እንደሚያደርግ ተገልጿል።

በስነስርዓቱ ላይ ፕላስቲኮችን ከሚሰበስቡ ማህበራት ጋር የውል ስምምነት የተደረገ ሲሆን ውሉም ለአንድ ዓመት እንደሚቆይና በየ ስድስት ወሩ የሚታደስ መሆኑ ተብራርቷል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" እየተካሄደ ያለዉ ቤት የማፍረስ ዘመቻ የሀገሪቱን እና የዜጎችን ወቅታ ሁኔታ ግምት ዉስጥ ያላስገባ ነው " - ዶክተር እንዳለ ሀይሌ በአዲስ አበባ ዙሪያ ህገ-ወጥ ናቸዉ የተባሉ ቤቶች በዘመቻ መልክ እየፈረሱ እንደሆነ ይታወቃል። ቃላቸውን ለአሐዱ ሬድዮ እና ቴሌቪችን የሰጡት የኢትዮጵያ ህዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም ዋና እንባ ጠባቂ ዶክተር እንዳለ ሀይሌ ፤ በአዲስ አበባ ዙሪያ እና ቡራዩ አካባቢ ቤት እየፈረሰባቸዉ…
የቀጠለው የቤት ማፍረስ ዘመቻ ...

በአዲስ አበባ ዙሪያ ከሚደረግ የቤት ማፍረስ ዘመቻ ጋር በተገናኘ ቤት የፈረሰባቸው ዜጎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የተናገሩት ፦

• " ... #ቤት_ለመፈለግ እንኳን በቂ ጊዜ አልተሰጠም በዚህም እቃችንን ወደ ምናውቃቸው ሰዎች አሽሽተናል ፤ መጠለያ አጥተው ሜዳ ላይ የወደቁም ጎረቤቶችም አሉ። ቤት ለመከራየት እንኳን የቤት ኪራይ በዚህ ምክንያት ጨምሯል።"

• " የዚህኛው ዙር ይለያል ብዙ ቤቶች ናቸው የፈረሱት፥ በሺ የሚቆጠር ሰዎች ከቤታቸው ወጥተው ሜዳ ላይ ወድቀዋል፣ ድብደባም እስርም የተፈጸመባቸው ዜጎች አሉ "

የኢትዮጵያ የህዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም ዋና እምባ ጠባቂ ዶ/ር እንዳለ ኃይሌ ለባላጉሩ ቴሌቪዥን ከሰጡት ቃል ፦

" ... ጉዳዩን በሕገ-ወጥነት መነጽር ብቻ መመልከት አግባብ አይደለም” ያሉት ዋና እንባ ጠባቂዉ፤ ከዜግነት መብትና ከሰብዓዊነት አንፃር መንግስት ጉዳዩን መመልከት የሚገባው ቢሆንም ሃላፊነቱን አልተወጣም። "

ያንብቡ 👇
https://telegra.ph/ETH-02-23-4
TIKVAH-ETHIOPIA
#ቦረና - በቦረና ዞን ካሉት የቀንድ ከብቶች ውስጥ 10 በመቶውን ለመታደግ 4 ነጥብ 4 ሚሊየን እስር ሳር ያስፈልጋል። - በድርቁ ምክንያት በዞኑ ከ3 ሚሊየን በላይ እንስሳት የሞቱ ሲሆን ፥ ከዚህ ውስጥ 85 በመቶዎቹ የቀንድ ከብቶች ናቸው። - በዞኑ የቀሩት 230 ሺህ የቀንድ ከብቶች ሲሆኑ፤ ለ3 ወር የቀንድ ከብቶቹን ለመታደግ ቢያንስ 4 ነጥብ 4 ሚሊየን እስር ሳር ማቅረብ ያስፈልጋል። በተጨማሪ…
#ቦረና

የቡሳ ጎኖፋ ምክትል ኃላፊ ዶ/ር ማሊቻ ሎጄ ለኢትዮጵያ ቴሌቪዥን የሰጡት ቃል ፦

- ቦረና ዞን በተፈጠረው ድርቅ ምክንያት የተረጂዎች ቁጥር እየጨመረ መጥቶ ቁጥሩ ከ604 ሺህ በላይ ደርሷል።

- ድርቁ በቦረና ብቻ ሳይሆን ሁለቱን የጉጂ ዞኖች ጨምሮ በ10 ዞኖች የተከሰተ ነው። ቦረና ግን ቆላማነቱ ከሌሎቹ አካባቢዎች ከፍተኛ በመሆኑ የጉዳቱ መጠንም በዚያው መጠን ሊጨምር ችሏል።

- በሁለት ወቅቶች (የካቲት እና ሰኔ) የድርቁ ሁኔታ ያለበትን ለማወቅ ጥናት ይካሄዳል በዚሁ መሠረት ዘንድሮም ድርቁ መቀጠሉ ስለተረጋገጠ ክልሉ ዕቅዶችን አውጥቶ በየደረጃው እየተንቀሳቀሰ ነው።

- ለድርቁ ምላሽ ለመስጠት ለተጋላጮችም እገዛ ለማድረግ ሰፊ ርብርብ እየተደረገ ቢሆንም ካለው የችግር ስፋት አኳያ የሚፈለገውን እርዳታ ማድረግ አልተቻለም።

- አስቸኳይ የመድኃኒት አቅርቦት፣ የእናቶች እና ሕፃናት አልሚ ምግቦች እና ሌሎች ሕይወት አድን ድጋፎች ስለሚያስፈልጉ ሁሉም አካላት በትብብር ሊሠሩ ይገባል።

ያንብቡ ; https://telegra.ph/EBC-02-23

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ቦረና በኦሮሚያ ክልል፤ ቦረና ዞን በተራዘመ ድርቅ በርካታ የቤት እንስሳት አልቀው የሚላስ የሚቀመስ ያጡ ነዋሪዎችም ከድርቁ ጋር በተያያዘ መሞት መጀመራቸውን ነዋሪዎችን ዋቢ በማድረግ ዶቼ ቨለ ሬድዮ ዘግቧል። ቦረና ዞን የተራዘመው ድርቅ የአርሶ አደሮችን በሚሊየኖች የሚቆጠሩ የቀንድ እና የጋማ ከብቶቻቸውን በመግደል አስከፊነቱን የቀጠለ ሲሆን የሰዎችም ህይወት በድርቁ ሳቢያ እያለፈ ነው ተብሏል። በቦረና…
#ቦረና

" የሚላስ የሚቀመስ ያጡ ነዋሪዎች ከድርቁ ጋር በተያያዘ መሞት ጀምረዋል " - የተልተሌ  አርሶ አደር

" በርሃብ ምክንያት የሞተ ሰው የለም " - ቡሳ ጎኖፋ ኦሮሚያ

በቦረና ዞን በድርቁ ምክንያት ሰዎች በምግብ አጦት ሰውነታቸው እየተጎዳ ቢሆን " በርሃብ ምክንያት የሞተ ሰው የለም ይህንን ቦታው ድረስ ተገኝተን አረጋግጠናል " ሲል ቡሳ ጎኖፋ ኦሮሚያ ገለፀ።

ቡሳ ጎኖፋ "የሰዎች ህይወት አላለፈም" ሲል ቃሉ የሰጠው ለኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ነው።

የቡሳ ጎኖፋ ምክትል ኃላፊ ዶክተር ማሊቻ ሎጂ ፤ " በድርቅ ወደ ተጎዳው ቦረና ዞን በማምራት ያለውን ሁኔታ ተመልክቻለሁ " ያሉ ሲሆን " በድርቁ ምክንያት ሰዎች በምግብ እጥረት ሰውነታቸን እንደተጎዳ ታዝቢያለሁ " ብለዋል።

" ነገር ግን በረሃብ ምክንያት የሞተ ሰው እንደሌለ ቦታው ድረስ ተገኝቼ በአካባቢው ከሚገኙ ሰዎች አረጋግጫለሁ " ሲሉ ለብሔራዊ ቴሌቪዥን ጣቢያው ተናግረዋል።

ከሰሞኑን ቦረና ዞን በተራዘመ ድርቅ በርካታ የቤት እንስሳት አልቀው የሚላስ የሚቀመስ ያጡ ነዋሪዎችም ከድርቁ ጋር በተያያዘ መሞት መጀመራቸውን ነዋሪዎችን ለዶቼ ቨለ ሬድዮ መናገራቸው ይታወሴ።

ለሬድዮ ጣቢያው ቃላቸውን ሰጥተው የነበረው በቦረና ዞን ተልተሌ ወረዳ ነዋሪ የሆኑት አርብቶ አደር ማሊቻ ሞሌ ከድርቁ ጋር በተያያዘ ሰዎች እየሞቱ ስለመሆኑ እንዲህ ሲሉ ነበር የተናገሩት ፦

" ... በድርቁ ሰው የከፋ ችግር ውስጥ ነው ያለው ። ያላቸው ከብቶች በግ እና ፍየል እንኳ ሳይቀር አልቀዋል። ጠብ ያለ ዝናብ ባለመኖሩ የሚወጣ እህል የለም።

የሚሸጥ ከብት በሙሉ በድርቁ አልቀዋል። አሁን ሰው በችግሩ በሕይወት እስከማለፍ ደርሷል። የሚቀመስ በመጥፋቱ በዚሁ ዓመት ብቻ በዚህች ቀበሌያችን አራት ሰው የሚደርስ ተጎሳቅለው አልፈዋል ። "

ፎቶ ፦ ፋይል

@tikvahethiopia
#iCog

iCog-ACC ሕፃናትን ገና በለጋ ዕድሜያቸው መሠረታዊ የኮምፒዩተር እና የኮዲንግ ሥልጠናዎችን በመስጠት ለወደፊት ለሚጠብቃቸዋል ዲጂታል ዓለም የሚያዘጋጃቸው ሲሆን ይህ እድል ልጆች ጠቃሚ የኮዲንግ ክህሎቶችን እንዲማሩና የፈጠራ ችሎታቸውን እንዲያዳብሩ ያስችላል።

ስልጠናው ከቤት በኢንተርኔት (ኦንላይን) ወይም በአካል  የሚሰጥ ሲሆን ክፍያው፦
- በኦንላይን ለሚወስዱ 1850 ብር
- በአካል ለሚወስዱ ደግሞ 2200 ብር  ብቻ ነው።
ስልጠናው የሚካሄደው ለ3 ወር ቅዳሜ ቅዳሜ በቀን ለ3/2 ሰዓታት ነው።

ልጆችዎ በዚህ ፕሮግራም እንዲሳተፉ የምትፈልጉ ወላጆች በስልክ ቁጥራችን +251904262728/ +251901379478 በመደወል ወይም ከዚህ በታች ያለውን ማስፈንጠሪያ በመንካት የምዝገባ ቅፁን በመሙላት መመዝገብ ትችላላችሁ።
https://icogacc.com/register
#MoE

106 ሺህ ተማሪዎች ለመጀመሪያ ጊዜ በሚሰጠው የአቅም ማሻሻያ የትምህርት ፕሮግራም ተካተዋል፡፡

በ2014 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ ፈተና ወስደው #ከ50_በመቶ በታች ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች ለአራት ወራት ያህል በሀገሪቱ በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች በሚሰጠው የአቅም ማሻሻያ ፕሮግራም ይሳተፋሉ፡፡

#Remedial ፕሮግራሙ ከአ/አ ዩኒቨርሲቲ፣ ከአ/አ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ እንዲሁም ከአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ውጪ ባሉ ሁሉም የመንግስት እና የግል ዩኒቨርሲቲዎች ይሰጣል፡፡

ትምህርት ሚኒስቴር ከዩኒቨርሲቲዎች የተውጣጡ ባለሙያዎች እና ፕሮፌሰሮች ኮሚቴ በማዋቀር ከ9ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ያሉት የትምህርት አይነት ይዘቶችን መለየቱን በሚኒስቴሩ የአካዳሚክ ጉዳዮች መሪ ሥራ አስፈጻሚ ኤባ ሚጀና (ዶ/ር) ለኢፕድ ተናግረዋል፡፡

በአቅም ማሻሻያ ፕሮግራሙ የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ፊዚክስ፣ ባዮሎጂ፣ ኬሚስትሪ፣ እንግሊዘኛ፣ የተፈጥሮ ሳይንስና ሂሳብ የትምህርት አይነቶችን የሚወስዱ ሲሆን፤ የማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ታሪክ፣ ጂኦግራፊ፣ እንግሊዘኛ፣ ማህበራዊ ሳይንስና ሂሳብ ትምህርት አይነቶችን እንደሚወስዱ መሪ ሥራ አስፈጻሚው ገልጸዋል፡፡

የትምህርት ይዘቶቹን መሰረት አድርጎ በተቋማት የሚዘጋጅ (ከ30 በመቶ) እና በማዕከል የሚዘጋጅ (ከ70 በመቶ) የሚያዝ ፈተና በመፈተን በድምሩ 50 በመቶ እና ከዚያ በላይ የሚያገኙ ተማሪዎች መደበኛ የዩኒቨርሲቲ ትምህርታቸውን በመንግስት እና በግል ዩኒቨርሲቲዎች መቀጠል ይችላሉ ብለዋል፡፡ #EPA

More : @tikvahuniversity
#Oromia

ኦሮሚያ ውስጥ የሚንቀሳቀሱ የሀገር ውስጥ መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች በችግር ላይ ላሉ ወገኖች አስቸኳይ የሰብዓዊ ዕርዳታ እንዲደረግላቸው የጋራ ጥሪ አቅርበዋል።

በአጠቃላይ 12 መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች በኦሮሚያ ያለውን ሁኔታ በተመለከተ መግለጫ አውጥተዋል።

በመግለጫቸው፤ በኦሮሚያ እየተከሰተ ያለውን የሰብዓዊ ቀውስ ለመፍታት ሁሉም ባለድርሻ አካላት ትኩረት እንዲሰጡ ጠይቀዋል።

" በድርቅ እና ግጭቶች ከ14 ሚሊዮን በላይ ሰዎች አስቸኳይ ሰብዓዊ እርዳታ ያስፈልጋቸዋል " ያሉት ድርጅቶቹ " ከነዚህ መካከል በግጭቶች እና በድርቅ ሳቢያ #የተፈናቀሉ 3.4 ሚሊዮን ያህል ሰዎች ይገኙበታል " ሲሉ ገልጸዋል።

የሰብዓዊ ድጋፍ አጋር ድርጅቶች በክልሉ ያለውን ሰብዓዊ ሁኔታ በዝርዝር እንዲገመግሙ እና ለድንገተኛ ሰብዓዊ ቀውስ ምላሽ ለመስጠት ተጨማሪ የሰብዓዊ ድጋፍ ፈንድ እንዲሰጡ ጥሪ አቅርበዋል።

" የውስጥ ተፈናቃዮች የመጠለያ፣ የንፅህና አገልግሎት፣ የምግብ፣ የትምህርትና የጤና አገልግሎት ያስፈልጋቸዋል " ያሉት ድርጅቶቹ ፤ በኦሮሚያ በአጠቃላይ ከ3.7 ሚሊዮን በላይ ሰዎች አስቸኳይ የውሃ ድጋፍ እንደሚያስፈልጋቸው አመላክተዋል።

እነዚሁ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች፤ #በቦረና በአየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖ ሳቢያ በአንዳንድ አካባቢዎች ለ5 ተከታታይ የዝናብ ወቅቶች ዝናብ ባለመዝናቡ 46 በመቶ የሚሆኑት የቀንድ ከብቶች እንዲጠፉ ምክንያት እንደሆነና በርካታ አባወራዎች ሁሉንም ያላቸውን ከብቶች እንዳጡ ጠቁመዋል።

ድርጅቶቹ፤ በተለይ በቦረና ዞን ከዚህ ቀደም በታሪክ ታይቶ አይታወቅም ባሉት ድርቅ ምክንያት የህዝቡ ሁኔታ አሁን ላይ ወደ ለህይወት ወደሚያሰጋ ደረጃ ተቀይሯል ሲሉ አሳውቀዋል።

(ሙሉ መግለጫው ከላይ ተያይዟል)

Pic. Jawar Mohammed

@tikvahethiopia