#MoE #EIASC
በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ ቤት ዋና ፀሐፊ በሆኑት በሼይኽ ሐሚድ ሙሳ የተመራ ልዑክ ከኢ.ፌ.ዲ.ሪ የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ከፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ ከተመራ የሚኒስቴር መስራቤቱ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ጋር ዉይይት ማድረጉን ምክር ቤቱ ዛሬ አሳውቋል።
በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የተደረገው ውይይት ፦
- በሙስሊም ተማሪዎች የሰላት ጉዳይ ከመደበኛ ትምህርት ቤቶች እስከ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት (ዩኒቨርሲቲዎች) ፤
- የሴት ሙስሊም ተማሪዎች ሒጃብና ያጋጠሙ ችግሮች፤
- በትምህርት ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የካሪኩለም ዝግጅት እና በተማሪዎች የመማሪያ መፅሀፍት ሚዛናዊነት በሚሉ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ እንደነበር ተገልጿል።
ም/ቤቱ የነበረው ውይይት #ዉጤታማ እንደነበር ገልጾ " በቀጣይም ከመቼውም ጊዜ በተሻለ ተቋማቱ ተቀራርበው ለመስራት የጋራ ስምምነት ላይ ደርሰዋል " ብሏል።
ከዚህ በተጨማሪም በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት በሚቋቋመው እና በዘርፉ ከፍተኛ ዕውቀትና ልምድ ያላቸው ባለሙያዎች በቀጣይ ከሚኒስትር መስሪያ ቤቱ የባለሙያዎች ቡድን ጋር ዉይይት ለማድረግ ከስምምነት ላይ መደረሱ ተገልጿል።
ምንጭ፦ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት
@tikvahethiopia