TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
212 files
4.11K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#Oromia ኦሮሚያ ውስጥ የሚንቀሳቀሱ የሀገር ውስጥ መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች በችግር ላይ ላሉ ወገኖች አስቸኳይ የሰብዓዊ ዕርዳታ እንዲደረግላቸው የጋራ ጥሪ አቅርበዋል። በአጠቃላይ 12 መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች በኦሮሚያ ያለውን ሁኔታ በተመለከተ መግለጫ አውጥተዋል። በመግለጫቸው፤ በኦሮሚያ እየተከሰተ ያለውን የሰብዓዊ ቀውስ ለመፍታት ሁሉም ባለድርሻ አካላት ትኩረት እንዲሰጡ ጠይቀዋል። " በድርቅ…
#ቦረና

#ቦረና በታሪክ እጅግ አስከፊ በተባለው ድርቅ ሳቢያ የተጎዱ ወገኖቻችንን ለመርዳት የምትፈልጉ በ " #ALCHIISOO_PASTORALIST_UP " በኩል መርዳት ትችላላሁ።

የዚህ መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት (NGO) የባንክ አካውንቶች ፦

👉 የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ - 1000522499823 (Swift Code: CBETETAA)

👉 የኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ -  1011800084313 (Swift code: CBO RETAA)

👉 አዋሽ ባንክ - 013081084782900
(Swift code:  AWINETAA)

👉 ኦሮሚያ ባንክ - 1548414100001
(Swift code: ORIRETAA)

ቁጥሮች ስለ ቦረና ምን ይናግሩናል ?

- በቦረና ዞን 807 ሺህ ሰዎች እርዳታ ይፈልጋሉ። ከነዚህ ውስጥ 167 ሺህ የሚሆኑ ሰዎች አስቸኳይና ተከታታይ ድጋፍ የሚፈልጉ ናቸው።

- በዞኑ ካሉት የቀንድ ከብቶች ውስጥ 10 በመቶውን ለመታደግ 4 ነጥብ 4 ሚሊየን እስር ሳር ያስፈልጋል።

- በድርቁ ምክንያት በዞኑ ከ3 ሚሊየን በላይ እንስሳት የሞቱ ሲሆን ከዚህ ውስጥ 85 % የቀንድ ከብቶች ናቸው።

- በዞኑ የቀሩት 230 ሺህ የቀንድ ከብቶች ሲሆኑ፤ ለ3 ወር የቀንድ ከብቶቹን ለመታደግ ቢያንስ 4 ነጥብ 4 ሚሊየን እስር ሳር ማቅረብ ያስፈልጋል። በተጨማሪ 135 ሺህ ኩንታል መኖ የሚያስፈልግ ሲሆን በዞኑ ማቅረብ የተቻለው አንድ በመቶ ብቻ ነው።

- የተከሰተው ድርቅ በዞኑ 13 ወረዳዎች አጥቅቷል ፤ በዞኑ ከሚገኘው 60 በመቶ የሚሆነው ህብረተሰብ ድጋፍ ይፈልጋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ቦረና

🗣 የቦረና ዞን ተልተሌ ወረዳ ነዋሪ የሆኑት አቶ ጉዮ ቱሩ ፦

" ቆሪ ጉዮ የተባለው ልጄ 16 ዓመቱ ነበር። ጤናማ እና ጠንካራ ነበር። ነገር ግን በረሃብ ምክንያት ታመመ። ምንም አልነበረንም። የነበሩን ከብቶች በድርቁ አልቀዋል።

ሆስፒታል ወስደነው ነበር። ችግሩ ከምግብ እጥረት ጋር የተያያዘ ነው አሉን። ከዚያ ከሆስፒታል እንደተመለሰ ሞተ። "

🗣 የቦረና ዞን የተልተሌ ወረዳ አስተዳዳሪ የሆኑት አቶ ኤንጌ ዋሪዮ፦

" በወረዳው ከተከሰተ የምግብ እጥረት ጋር ተያይዞ የሰባት ሰዎች ሕይወት አልፏል።

ከምግብ እጥረት ጋር በተያያዘ ሕይወታቸውን ካጡት መካከል የሁለት ወር ጨቅላ ይገኝበታል።

በተልተሌ ወረዳ፣ ከሁለት ወር ህጻን ጀምሮ እስከ አዛውንቶች ድረስ በረሃብ ምክንያት ሰባት የሚሆኑ ሰዎች ሞተዋል።

ሰዎች ያለ ምግብ ብዙ ቀን እየቆዩ ነው። ያሏቸውም ከብቶች አልቀውባቸዋል። "

🗣 የተልተሌ ወረዳ የአደጋ መከላከል እና ምግብ ዋስትና ኃላፊ ገልመ ሞሉ፦

" በረሃብ ምክንያት ሰዎች እየሞቱ ነው ለሚለው ስለሚለው የደረሰኝ መረጃ የለም።

ይሁን እንጂ ሕጻናት አረጋውያን በምግብ እጥረት ምክንያት ከቀላል በሽታዎች ማገገም እየቻሉ አይደለም። "

CREDIT : #BBC

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያንን ጉዳይ የሚከታተለው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሁለተኛ መሠረታዊ መብቶች እና ነጻነቶች ምድብ ችሎት #የዕግድ ትዕዛዝ መስጠቱ ተገለፀ። ፍርድ ቤቱ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የእግድ አቤቱታ መሠረት ቤተ ክርስቲያኗ አውግዛ በለየቻቸው ተጠሪዎች ላይ የእግድ ትእዛዝ መስጠቱን የቤተክርስቲያኗ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። በዚህ ጉዳይ…
የእነ አባ ሳዊሮስ እግድ ተነሳ።

የካቲት 3 ቀን 2015 ዓ.ም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያንን ጉዳይ ሚከታተለው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሁለተኛ መሠረታዊ መብቶች እና ነጻነቶች ምድብ ችሎት በሕገ ወጥ መንገድ በተፈጸመው ሹመት ላይ የተሳተፉት ግለሰቦች ላይ እግድ ማስተላለፉ ይታወሳል።

በቅርቡ የተፈጸመውን ዕርቅ ተከትሎ ፦

- የአባ ሳዊሮስ፣
- የአባ ኤዎስጣቴዎስ
- የአባ ዜና ማርቆስ #ዕግድ_መነሳቱን የቤተክርስቲያና መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።

ቀሪዎቹ 26 ግለሰቦች በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅጽር ግቢ ውስጥ እንዳይገቡ የተጣለው ዕግድ እንዲቀጥል ፍርድ ቤቱ መወሰኑ ተገልጿል።

#ተሚማ

@tikvahethiopia
ባሰራጨው ፎቶ ይቅርታ የጠየቀው ቢሮ !

የትግራይ ኮሚኒኬሽን ከዓድዋ በዓል ጋር  በተያያዘ በይፋዊ የፌስቡክ ገፁ ባሰራጨው ምስል ይቅርታ ጠየቀ።

ቢሮው የዘንድሮውን በዓል በተመለከተ በአዲስ አበባ የሚገኘው የ " አፄ ሚኒሊክ " ሃውልት ፎቶ ከሌሎች ሁለት ፎቶዎች ጋር " የዓድዋ ድል የፅንአት እና የነፃነት ምልክት ነው " በሚል   አጋርቶ ነበር (ከላይ ይመልክቱ) ።

ቢሮው ይህን ፎቶ ካጋራ በኃላ በጥቂት ደቂቃዎች በርከታ አስተያየቶች ሊሰጡ ችለዋል።

ብዙም ሳይቆይ ቢሮው በፌስቡክ ገፁ የ " አፄ ሚኒልክ " ሃውልት ያለበትን ፎቶ ጨምሮ ሌሎች አብረው የነበሩ ፎቶዎችን አውርዷቸዋል።

ከደቂቃዎች በኃላ የኮሚኒኬሽን ቢሮው እንደ አዲስ በተመሳሳይ መልዕክት የራስ አሉላ አባነጋ ፎቶ ያለበትን መልዕክት አስራጭቷል።

ቢሮው ቀደም ብሎ ባሰራጨው መልዕክት " ይቅርታ " ጠይቆ ከዓድዋ በዓል ጋር በተያያዘ ከዚህ ቀደም የተለጠፈውን ፎቶ ያስተካክላችሁን ሁሉ እናመሰግናለን። " ብሏል።

አፄ ሚኒሊክ ኢትዮጵያ ጣልያንን ድል ባደረገችበት የዓድዋ ድል ወቅት የኢትዮጵያ ንጉስ / መሪ እንደነበሩ ይታወቃል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ቦረና 🗣 የቦረና ዞን ተልተሌ ወረዳ ነዋሪ የሆኑት አቶ ጉዮ ቱሩ ፦ " ቆሪ ጉዮ የተባለው ልጄ 16 ዓመቱ ነበር። ጤናማ እና ጠንካራ ነበር። ነገር ግን በረሃብ ምክንያት ታመመ። ምንም አልነበረንም። የነበሩን ከብቶች በድርቁ አልቀዋል። ሆስፒታል ወስደነው ነበር። ችግሩ ከምግብ እጥረት ጋር የተያያዘ ነው አሉን። ከዚያ ከሆስፒታል እንደተመለሰ ሞተ። " 🗣 የቦረና ዞን የተልተሌ ወረዳ አስተዳዳሪ የሆኑት…
" ይቅርታ ይጠይቅ "

የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት " ቢቢሲ አማርኛ " አገልግሎት ይቅርታ ይጠይቅ እርምትም ያድርግ አለ።

የክልሉ መንግሥት በኮሚኒኬሽን ቢሮው በኩል ዛሬ ባሰራጨው መልዕክት ነው ይህንን ያለው።

" መረጃን ማጥራት የጋዜጠኝነት ሙያ 'ሀ ሁ' ነው። " ያለው የኦሮሚያ ኮሚኒኬሽን " BBC አማርኛ የተሰኘ ድረገፅ በቦረና የተከሰተውን ድርቅ አስመልክቶ በድረገፁ  ያሰራጨው መረጃ ፍፁም ስህተት ነው። " ብሏል።

" በድርቅ ምክንያት #በተልተሌ_ወረዳም ሆነ በቦረና ዞን በአጠቃላይ ያለፈ የሰው ህይወት የለም " ያለው ቢሮው " ድረ ገፁ ዘገባውን እውነት ለማስመሰል አቶ ዴንጌ ዋሪዮ የሚባል ገፀ ባህሪ በመፍጠር የተልተሌ ወረዳ አስተዳዳሪ አድርጎ መሰየሙ ከአንድ ሃላፊነት ከሚሰማው ሚዲያ የሚጠበቅ ባህሪ አይደለም " ሲል ገልጿል።

የኦሮሚያ ክልል ፤ ትክክለኛው የተልተሌ ወረዳ አስተዳዳሪ ኣብ ዱባ ኮንሶ የሚባሉ እንደሆነ ገልጾ " ድረ ገፁ እንደ መረጃ ምንጭነት የተጠቀመው አካል ትክክለኛ አለመሆኑን ያመለክታል " ብሏል።

የኦሮሚያ ክልል መንግሥት ኮሚኒኬሽን " ድረ ገፁ አንባቢዎቹን ይቅርታ በመጠየቅ አስፈላጊውን እርምት እንድያደርግ እንጠይቃለን " ብሏል።

ከቦረና ዞን ድርቅ ጋር በተያያዘ ከቢቢሲ በተጨማሪ የጀርመን ሬድዮ ጣቢያ የሰው ህይወት ማለፍ መጀመሩን ነዋሪዎችን ዋቢ አድርጎ መዘገቡ ይታወሳል።

ከቢቢሲ አማርኛ አገልግሎት ዘገባ፦https://t.iss.one/tikvahethiopia/76633

ከጀርመን ሬድዮ ዘገባ ፦ https://t.iss.one/tikvahethiopia/76589

@tikvahethiopia
#ቱርክ

ቱርክ በመሬት መንቀጥቀጥ ምክንያት ቤት አልባ ለሆኑ 1 ነጥብ 5 ሚሊዮን ዘጎቿ ቤት መስራት መጀመሯ ተሰምቷል።

የሀገሪቱ መንግስት በደረሰው ከባድ የመሬት መንቀጥቀጥ የወደሙ የመኖሪያ ቤቶችን መልሶ የመገንባት ስራ መጀመሩን ገልጿል።

በመሬት መንቀጥቀጡ 520 ሽህ አፓርትመንቶችን የያዙ ከ160 ሽህ በላይ ህንጻዎች ፈርሰዋል ወይም ከባድ ጉዳት ደርሶባቸዋል ተብሏል።

ፕሬዝዳንት ሬሲጵ ጣይብ ኤርዶጋን በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ቤቶችን ለመገንባት ቃል ገብተዋል።

ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ አንድ ባለስልጣን ለሮይተርስ በሰጡት ቃል ፤ " ለበርካታ ፕሮጀክቶች ጨረታዎች እና ኮንትራቶች ተከናውነዋል። ሂደቱ በጣም በፍጥነት እየሄደ ነው " ብለዋል።

በደህንነት ላይ ምንም አይነት ድርድር አይኖርም ሲሉም ተናግረዋል።

የቱርክ መንግስት የመጀመሪያ እቅድ 200 ሽህ አፓርትመንቶች እና 70 ሽህ ቤቶችን ቢያንስ በ15 ቢሊየን ዶላር መገንባት ነው ተብሏል። 

የአሜሪካው ባንክ ጄፒ ሞርገን አንካራ ቤቶችን መልሶ ለመገንባትና ለመሰረተ ልማት 25 ቢሊዮን ዶላር እንደምታወጣ ገምቷል። 

ምንጭ፦ አል ዓይን ኒውስ / ሮይተርስ

@tikvahethiopia
#ብርሃን_ባንክ
እንደ ስማችን ብርሃን ነው ስራችን!
አዳዲስ እና ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት ከታች የሚገኙትን ሊንኮች በመጫን የማህበራዊ ድህረ-ገጾቻችንን ይቀላቀሉ !
Facebook: https://www.facebook.com/berhanbanksc
Telegram: https://t.iss.one/berhanbanksc
Instagram: https://www.instagram.com/berhanbanksc/
Twitter: https://twitter.com/berhanbanksc
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/76151001
YouTube: https://www.youtube.com/channel/UCvOxWe439dzMSvNnMrjcYVQ
TIKVAH-ETHIOPIA
#US አሜሪካ በአስከፊው ጓንታናሞ ቤይ እስር ቤት አስራው የነበረችውን አልጄሪያዊ ወደ ሀገሩ መለሰች። አሜሪካ በሀገሯ ውስጥ የ "ቦምብ ጥቃት ለማድረስ አቅደሃል" ብላ ለ20 ዓመታት ገደማ ያሰረችውን ሱፊያን ቡርሃሚ የተባለ አልጄሪያው ወደ ሀገሩ እንዲመለስ አድርጌዋለሁ ብላለች። በአስከፊው ጓንታናሞ ቤይ እስር ቤት አሜሪካ አስራ ያቆየችው እና አሁን መልሸዋለሁ ያለችው አልጄሪያዊ በፈረንጆቹ 2002 ፓኪስታን…
#አሜሪካ

አሜሪካ ያለ አንዳች ፍርድ ለ20 ዓመታት በ " ጓንታናሞ ቤይ " በሚገኘው እስር ቤት አስራ የቆየቻቸውን ሁለት ፓኪስታናውያን ወንድማማቾችን ከእስር ስለመልቀቋ ተነግሯል።

ጓንታናሞ ቤይ ውስጥ በሚገኘው የአሜሪካ ወታደራዊ እርስ ቤት ውስጥ ለ20 ዓመታት ያህል ታስረው የቆዩት ሁለቱ ፓኪስታናውያን ወንድማማቾች ምንም ክስ ሳይቀርብባቸው ነው የተለቀቁት።

አብዱል እና ሞሐመድ አህመድ ራባኒ ፓኪስታን " ካራቺ " ውስጥ ተይዘው ከአገራቸው የተወሰዱት በአውሮፓውያኑ በ2002 ነበር።

የአሜሪካ መከላከያ መ/ቤት አብዱል ራባኒ የተባለው ግለሰብ የ " አልቃኢዳን የመደበቂያ ቤት ያስተዳድራል " እንዲሁም ወንድሙ " የቡድኑ መሪዎችን ጉዞ እና ገንዘብን ይመራል " ብሎ ነበር።

ወንድማማቾቹ ወደ ጓንታናሞ ከመሸጋገራቸው በፊት ከአገራቸው ውጪ በሲአይኤ (CIA) መኮንኖች #ማሰቃየት እንደተፈጸመባቸው ገልጸዋል።

ሁለቱ ፓኪስታናውያን ከአስፈሪው ወታደራዊው እስር ቤት ከተለቀቁ በኋላ ወደ አገራቸው እንዲመለሱ ተደርጓል ተብሏል።

ጓንታናሞ ኩባ ውስጥ የሚገኝ ሲሆን የአሜሪካ ባሕር ኃይል ሰፈር ከመስከረም 11 የሽብር ጥቃት በኋላ ተጠርጣሪዎችን ለማቆያነት በቀድሞ ፕሬዝዳንት ጆርጅ ቡሽ የተቋቋመው ነው።

ካምፑ ባለፉት ሁለት አስርት ዓመታት አሜሪካ ካካሄደችው " ፀረ ሽብር ጦርነት " ጋር በያያዘ ከተፈጸሙ መጥፎ ድርጊቶች ጋር ስሙ ይነሳል።

በተለይ ተጠርጣሪዎች በምርመራ ጊዜ #ከባድ_ሰቆቃ እንደተፈጸመባቸው እና ያለፍርድ ለረጅም ጊዜ በእስር እንዲቆዩ መደረጋቸው ይነገራል።

ከ20 ዓመት በፊት በጓንታናሞ ውስጥ 680 አስረኞች የነበሩት ሲሆን፣ በአሁኑ ወቅት ግን 32 እስረኞች ብቻ የሚገኙበታል።

#BBC

@tikvahethiopia
#አፖሎ

አፖሎ የዲጂታል መተግበርያን በመጠቀም ወደፈለጉት ባንክ ገንዘብ ይላኩ።

መተግበሪያውን ለማውረድ ሊንኩን ይጠቀሙ። https://apollo.bankofabyssinia.com/download-apollo

የአፖሎ ትክክለኛ የማህበራዊ ትስስር ገጾች
Website: https://apollo.bankofabyssinia.com/
Telegram: https://t.iss.one/apollodigitalproduct
Facebook: https://www.facebook.com/apollodigitalproduct
Instagram: https://www.instagram.com/apollodigitalproduct/
Twitter: https://twitter.com/ApolloBoA
Tiktok: https://www.tiktok.com/@apollodigitalproduct
YouTube: https://www.youtube.com/@apollodigitalproduct
TIKVAH-ETHIOPIA
የትምህርት ሚኒስትሩ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ በሰጡት መግለጫ ምን ምን ጉዳዮችን አነሱ ? - በ2014 የትምህርት ዘመን ለፈተና የተመዘገቡ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች በጠቅላላ 985 ሺህ 354 ተማሪዎች ሲሆኑ ለፈተና የቀረቡት 92 ነጥብ 2 % 908 ሺህ 256 ተማሪዎቹ ሲሆኑ 77 ሺህ 98 ተማሪዎች ፈተና አልወሰዱም። - በደንብ ጥሰት ፣ለመኮራረጅ በመፈለግ እና በሌሎች ምክንያቶች 50 ሺህ 170 ተማሪዎች ሳይፈተኑ…
#MoE

የትምህርት ሚኒስቴር በሀገር አቀፍ ፈተና ከፍተኛ ውጤት ላመጡ ተማሪዎች እና ት/ቤቶች እውቅናና ሽልማት ሊሰጥ ነው።

ሚኒስቴሩ በ2014 ዓ/ም በሀገር አቀፍ ፈተና ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎች እና ትምህርት ቤቶች ሀገር አቀፍ እውቅናና ሽልማት እንደሚሰጥ አሳውቋል።

የእውቅናና ሽልማት ፕሮግራሙ የፊታችን የካቲት 21 ቀን 2015 ዓ/ም እንደሚካሄድ ነው ሚኒስቴሩ የገለፀው።

@tikvahethiopia