TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.2K photos
1.5K videos
211 files
4.1K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የአፍሪካ ሀገራት መሪዎች በ35ተኛዉ የአፍሪካ ህብረት (AU) የመሪዎች ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ ወደ አዲስ አበባ እገቡ ናቸው። ጥዋት ከላክልናችሁ ተጨማሪ ሌሎች መሪዎች የገቡ ሲሆን በሚከተለው ዝርዝር አስቀምጠነዋል። 🇲🇼 ዶ/ር ላዛሩስ ማካርቲ ቻክዌራ (ማላዊ - ፕሬዝዳንት) 🇬🇲 ዶ/ር ኢሳቱ ቶራይ (ጋምቢያ - ምክትል ፕሬዚዳንት) 🇳🇬 ሙሀሙዱ ቡሃሪ (ናይጄሪያ - ፕሬዝዳንት) 🇨🇮 ኦላሳን…
#Update

የአፍሪካ ሀገራት መሪዎች በ35ተኛዉ የአፍሪካ ህብረት (AU) የመሪዎች ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ ወደ አዲስ አበባ እገቡ ናቸው።

እስካሁን የገቡ ፦

🇲🇼 ዶ/ር ላዛሩስ ማካርቲ ቻክዌራ (ማላዊ - ፕሬዝዳንት)
🇬🇲 ዶ/ር ኢሳቱ ቶራይ (ጋምቢያ - ምክትል ፕሬዚዳንት)
🇳🇬 ሙሀሙዱ ቡሃሪ (ናይጄሪያ - ፕሬዝዳንት)
🇨🇮 ኦላሳን ኦታራ (ኮትዲቯር - ፕሬዝዳንት)
🇸🇳 ማኪ ሳል (ሴኔጋል - ፕሬዝዳንት)
🇲🇷 ሞሐመድ ኡልድ ኤል-ጋዝዋኒ (ሞሪታንያ - ፕሬዝዳንት)
🇹🇿 ዶ/ር ፊሊፕ እስዶር መፓንጎ (ታንዛንያ- ምክትል ፕሬዝዳንት)
🇹🇩 አልበርት ፓሂሚ ፓዳክ (ቻድ - ጠቅላይ ሚኒስትር)
🇿🇼 ኤመርሰን ማናንጋግዋ (ዚምባቡዌ - ፕሬዝዳንት)
🇬🇦 ሮዝ ክርስቲያን ኦሳካ (ጋቦን - ጠቅላይ ሚኒስትር)
🇿🇲 ሃካይንዴ ሂቺሌማ (ዛምቢያ - ፕሬዜዳንት)
🇨🇫 ፕሮፌሰር ፎስቲን አካንግ ቶንዳራ (ማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ - ፕሬዜዳንት)
🇳🇪 መሀመድ ባዙም (ኒጀር - ፕሬዜዳንት)
🇺🇬 ጄሲካ አሉፖ (ዩጋንዳ - ምክትል ፕሬዝዳንት)
🇸🇿 ክሊዮፓስ ዲላሚኒ (ስዋቲኒ - ጠቅላይ ሚኒስትር )
🇨🇻 ጆዜ ማሪያ (ኬፕ ቨርዲ - ፕሬዝዳንት)
🇨🇩 ፊሊክስ ሺሴኬዲ (ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ - ፕሬዚዳንት እና የወቅቱ የአፍሪካ ህብረት ሊቀ-መንበር)
🇧🇮 ኤቫሬስት ንዳያሽሜ (ብሩንዲ - ፕሬዚዳንት)
🇰🇲 አዛሊ አሱማኒ (ኮሞሮስ - ፕሬዝዳንት)
🇪🇭 ብራህሚ ጋሊ (ሳህራዊ አረብ ሪፐብሊክ - ፕሬዝዳንት)
🇬🇭 ናና አኩፎ አዶ (ጋና - ፕሬዚዳንት)
🇸🇱 ጁሌስ ማዳ ቢዮ (ሴራሊዮን - ፕሬዚዳንት)
🇨🇬 ዴኒስ ሳሱ ንግኤሶ (ኮንጎ ሪፐብሊክ - ፕሬዝዳንት )
🇱🇾 መሀመድ ዩኑስ አል መንፊ (ሊቢያ - የፕሬዝዳንታዊ ም/ቤት ፕሬዝዳንት)
🇲🇿 ፊሊፕ ኒየሲ (ሞዛምቢክ - ፕሬዜዳንት)
🇩🇯 ኢስማኤል ኦማር ጌሌ (ጅቡቲ - ፕሬዜዳንት)
🇸🇴 መሀመድ አብዱላሂ ፈርማጆ (ሶማሊያ - ፕሬዜዳንት)
🇰🇪 ኡሁሩ ኬንያታ (ኬንያ - ፕሬዜዳንት)

በተጨማሪም ለዚሁ ጉባኤ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ምክትል ፃሀፊ ኦሚና መሀመድ እንዲሁም የፍልስጤም ጠቅላይ ሚኒስትር ሞሃመድ ሽታይ አዲስ አበባ ይገኛሉ።

የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ ዛሬ ይጀምራል።

@tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
እጅግ ፈታኙ የነፍስ አድን ርብርብ ...

በአፍሪካዊቷ ሀገር ሞሮኮ ታምሩት ከተማ በጨዋታ ላይ የነበረ ስሙ ራያን የተባለ የ5 ዓመት ህፃን ልጅን ህይወት ለመታደግ ቀናትን የፈጀ ርብረብ እየተደረገ ነው።

ህፃኑ 32 ሜትር ጥልቀት ባለው ጉድጓድ ውስጥ የወደቀ ሲሆን ለ4 ቀንም እዛው ይገኛል።

የህፃኑን ህይወት ለመታደግ በርካታ የነፍስ አድን ሰራተኞች ርብርብ ላይ ሲሆኑ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በስፍራው ይገኛሉ፤ ጉዳዩንም ሚሊዮኖች በማህበራዊ ሚዲያ በጭንቀት እየተከታተሉት ነው።

ሞሮካውያን #SaveRayan በሚልም በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ድጋፋቸውን እየገለፁ ለህፃኑ በሰላም መውጣት እየፀለዩ ይገኛሉ።

ራያን የወደቀው በጠባቡ የጉድጓዱ አፍ በመሆኑ የነፍስ አድን ጥረቱን አዳጋች ማድረጉ ተነግሯል።

ከሰዓታት በፊት ቢቢሲ ይዞት በወጣው ዘገባ የነፍስ አድን ስራው ወደ መጨረሻው ደረጃ መድረሱን ያመለክታል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update 35ኛው የአፍሪካ ህብረት (AU) የመሪዎች ጉባኤ መካሄድ ጀምሯል። @tikvahethiopia
#Live

የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ እየተካሄደ ይገኛል።

በአሁን ሰዓት ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ለጉባኤው ንግግር በማድረግ ላይ ይገኛሉ።

ይህንን ጉባኤ በብሄራዊ የቴሌቪዥን ጣቢያ (ኢቲቪ) አልያም በአፍሪካ ህብረት (AU) የትዊተር ገፅ ላይ በቀጥታ መታተል ይቻላል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Live የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ እየተካሄደ ይገኛል። በአሁን ሰዓት ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ለጉባኤው ንግግር በማድረግ ላይ ይገኛሉ። ይህንን ጉባኤ በብሄራዊ የቴሌቪዥን ጣቢያ (ኢቲቪ) አልያም በአፍሪካ ህብረት (AU) የትዊተር ገፅ ላይ በቀጥታ መታተል ይቻላል። @tikvahethiopia
#AU2022Summit

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ በ35ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ መክፈቻ ላይ ባደረጉት ንግግር አፍሪካ በተመድ ፀጥታ ም/ቤት ቋሚ መቀመጫ እንዲኖራት የሚሠራበት ጊዜ መሆኑን ገለፁ።

ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ፥ " አሁን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሚሻሻልበት እና አፍሪካም በፀጥታው ምክር ቤት ቋሚ መቀመጫ እንዲኖራት የሚሠራበት ጊዜ ነው " ሲሉ ተናግረዋል።

ከዚህ ባለፈ የአፍሪካን ድምፅ በተገቢው ሁኔታ የሚያስተጋባ አንድ አህጉራዊ ፓን አፍሪካኒዝም ዕሳቤ የተቃኝ ሚዲያ ሊቋቋም እንደሚገባ ገልፀዋል።

" አፍሪካዊያን ከተባበርን ወደ ፊት እንራመዳለን ከተከፋፈልን ግን ለአደጋ እንጋለጣለን " ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ " አህጉራዊው ነጻ የንግድ ቀጣና ሙሉ በሙሉ ወደ ተግባር በመግባት የአፍሪካን ሕዳሴ ማረጋገጥ አለብን " ብለዋል።

ያልተነካውን የአፍሪካ የቱሪዝም ሀብት ጥቅም ላይ ማዋል አለብንም ሲሉ ተናግረዋል።

ዶ/ር ዐቢይ በንግግራቸው የተለያዩ ጉዳዮችን ያነሱ ሲሆን ኢትዮጵያን በተመለከተ ፥ ባለፉት ሁለት ዓመታት ለመሥኖ ሥራ ልዩ ትኩረት ሰጥታ በመሥራቷ ውጤት እያስመዘገበች ነው ብለዋል።

የአካባቢ መራቆትን እና የአየር ንብረት ለውጥን ለመቋቋም የአረንጓዴ አሻራን እየተገበረች መሆኑንና ለጎረቤቶቿም ልምድ እያካፈለች እና ችግኝ እያጋራች መሆኑን ገልፀዋል።

ከወቅታዊ ሁኔታ ጋር በተያያዘ መንግስት ለተሻለ ሰላም ሲል እስረኞችን መፍታቱን ፤ ሁሉን አሳታፊ ሀገራዊ ምክክር ለማድረግ ኮሚሽን ተቋቁሞ ወደ ሥራ መግባቱን ለጉባኤው ተናግረዋል።

ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ፤ ኢትዮጵያ እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው በመምጣት ኢትዮጵያ ሰላም እና ለቱሪዝም ምቹ መሆኗን ለተቀረው ዓለም አረጋግጠዋል ሲሉም ተደምጠዋል።

@tikvahethiopia
#AU2022Summit

ማኪ ሳል የአፍሪካ ህብረትን ሊቀመንበርነትን ተረከቡ።

የሴኔጋል ፕሬዚዳንት ማኪ ሳል የአፍሪካ ህብረትን በሊቀመንበርነት የመምራት ሃላፊነቱን ከዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ፕሬዚዳንት ፊሊክስ ሺሴኬዲ ተረክበዋል።

35ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች መደበኛ ጉባኤ መካሄዱን ቀጥሏል።

ፎቶ ፦ ፋይል

@tikvahethiopia
#EastGojjam

ሰርግ ላይ በተተኮሰ ጥይት 4 ሰዎች ህይወታቸው ሲጠፋ 5 ሰዎች ቆሰሉ።

የምስራቅ ጎጃም ዞን ፖሊስ በሰርግ ላይ በተተኮሰ ጥይት የ4 ሰው ህይወት ሲጠፋ ተጨማሪ 5 ሰዎች የመቁሰል አደጋ መድረሱን አስታወቀ።

ክስተቱ የተፈጠረው በሁለት እጁ እነሴ ወረዳ በጥሩ ሰላም ቀበሌ በ24/5/2014 ዓ/ም ሲሆን ተጠርጣሪው ከሌላ ሠው መሣሪያ በመዋስ እና በመፎከር ላይ እያለ ጥብቅ ከፍቶ አውቶማቲክ ላይ ሆኖ ሲተኮስ አራት ሰዎች ወዲያውኑ ህይወታቸው ሲያልፍ መሣሪያ የሠጠውን ሰው ጨምሮ በአምስት ሰዎች ላይ የመቁሰል አደጋ መድረሱን ፖሊስ አስረድቷል።

የምስራቅ ጎጃም ዞን ፖሊስ መምሪያ የማህበሠሰብ አቀፍ የፖሊስ አገልግሎት ዋና ክፍል ሀላፊ ዋና ኢንስፔክተር አጃናው አዲስ ፥ ከቅርብ ግዜ ወዲህ በሰርግ ላይ እና በሀዘን ላይ ጥይት እየተተኮሰ ቀላል በማይባሉ የህብረተሰሰብ ክፍሎች ላይ የሞት እና የአካል ጉዳት በመድረሱ በማህበረሰቡ ላይ ከፍተኛ የሆነ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ጉዳትን እያስከተለ መሆኑን ገልፀዋል።

የጉዳዩን አሳሳቢነት በተለያዩ ሚዲያዎች ፣ በሶሻል ሚዲያና መድረኮች እየተዘጋጁ ውይይቶች ቢደረጉም ችግሩን ግን በዘላቂነት ለመፍታት አለመቻሉንም አስረድተዋል።

በመሆኑም ህብረተሰቡ ሰርግ ላይና በለቅሶ ላይ አላስፈላጊ ጥይት መተኮስ በህብረተሰቡ ላይ እያደረሠ ያለውን ከፍተኛ ችግር በመገንዘብ በህጉ ከተቀመጡ አሰራሮች በተጨማሪ በእድር እና መሠል የማህበረሰቡ አደረጃጀት ህገ ደንቦችን በማውጣት ለመከላከል ለስራው እገዛ እንዲያደርጉ አሳስበዋል።

መረጃው ምስራቅ ጎጃም ዞን ፖሊስ ነው።

@tikvahethiopia
#AmharaRegion

የጠቅላላ ሀኪም የቋሚ ቅጥር ፦

የአማራ ክልል ጤና ቢሮ በክልሉ ስር ባሉ ጤና ተቋማት ጠቅላላ ሀኪሞችን መድቦ ማሰራት ይፈልጋል።

👉 የስራ መደቡ መጠሪያ - ጠቅላላ ሀኪም
👉 ደመወዝ - 9,056 ብር (ዘጠኝ ሺ ሃምሳ ስድስት ብር)
👉 ብዛት - 631 (#ስድስት_መቶ_ሰላሳ_አንድ)
👉 የስራ ቦታ - በክልሉ ባሉ የጤና ተቋማት ክፍት ቦታዎች
👉 ተፈላጊ የትምህርት ዝግጅት - በጠቅላላ ሀኪም የመጀመሪያ ዲግሪ እና 0 (#ዜሮ) ዓመት የስራ ልምድ
👉 የሞያ ፍቃድ ያለው / ያላት

የመመዝገቢያ ቦታ በአብክመ ጤና ቢሮ እና በሁሉም ዞን ጤና መምሪያዎች ማስረጃዎቻችሁን ዋናውንና የማይመለስ ኮፒ በመያዝ መመዝገብ ትችላላችሁ ተብሏል።

የዞን ጤና መምሪያዎች ምዝገባው ከተጠናቀቀበት ቀን ጀምሮ ባሉት 3 ተከታታይ ቀናት ውስጥ በሶፍት ኮፒ እና በሃርድ ኮፒ እንዲልኩ ማሳሰቢያ ተሰጥቷል።

ማሳሰቢያ ፦

1ኛ. በማንኛውም ጤና ተቋም ዕጣ በደረሰው ቦታ ላይ ለመስራት ፍቃደኛ የሆነ/የሆነች
2ኛ. ከዚህ በፊት በመንግስት ጤና ተቋም በቋሚ ቅጥር ያልተቀጠረ/ያልተቀጠረች

#ሼር #Share

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የአፋር ክልል ተፈናቃዮች ከ250 ሺህ በልጠዋል። የአፋር ክልል ኮሚኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ አህመድ ካሎይታ ህወሓት በሁለት ዙር ባካሄደው ወረራ የኢትዮጵያ የወጪ እና ገቢ ንግድ የሚሳለጥበትን ሚሌን ለመያዛ እና ለመዝጋት አስቦ ነበር ያ ግን ሳይሳካ ቀርቷል አሁን ደግሞ በሶስተኛ ዙር ወራር በሰርዶ በኩል ያሰበውን ለማሳካት ተነስቷል ብለዋል። አቶ አህመድ ፤ ክልሉ ከዚህ ቀደም ቡድኑ ባካሄደው…
#Update

በአፋር ክልል ጦርነቱ ተባብሶ መቀጠሉ ተሰምቷል።

የአፋር ክልል መንግስት ዛሬ ቅዳሜ ባወጣው መግለጫ ህወሓት ሰርዶን ለመቆጣጠር እንደ አዲስ በኪልበቲ ረሱ ዞን የከፈተውን ከባድ ጦርነት አጠናክሮ ቀጥሏል ብሏል።

የክልሉ መንግስት ህወሓት ከታህሳስ 10 ቀን 2014 ጀምሮ እንደ አዲስ በአፋር በኩል ጦርነት መክፈቱን አስታውሷል።

በኪልበቲ ረሱ ዞን የተለያዩ 5 ወረዳዎችና አንድ ከተማ መስተዳድር ማለትም ፦ አብአላ ከተማ አስተዳደር ፣ በአብአላ ወረዳ፣ በመጋሌ ወረዳ፣ በኤረብቲ፣ በኮነባ እና በራህሌ ወረዳዎች በተደጋጋሚ ጦርነት በመክፈት ሰርዶን ለመያዝ ጥረት እያደረገ መሆኑን ገልጿል።

ቡድኑ ሰርዶን መያዝ የፈለገው የኢትዮ-ጂቡቲን መስመር ለመቆጣጠርና አፋርን እንደ መደራደሪያ ለመጠቀም መሆኑን የገለፀው የአፋር ክልል በፊት ሚሌን ለመቆጣጠር ያደረገውን ትግል በጠነከረ መልኩ ውጊያ በማካሄድ በራህሌ እና ኮነባን በቁጥጥሩ ስር ማዋሉን ገልጿል።

የአፋር ክልል በመግለጫው " የአፋር አናብስቶች አሸባሪው ህወሓት ከተቆጣጠራቸው አብአላ ከተማ አስተዳድር፣ አብአላ ወረዳ ፣ መጋሌ ወረዳ እና ኤረብቲ ወረዳዎች እንዲሁም ከባድ ጦርነት ከከፈተባቸው በበራህሌ እና ኮነባ ተጨማሪ ማስፋፋት እንዳያደርግ ከባድ ፊልሚያ አድርገዋል " ሲል ገልጿል።

ነገር ግን ህወሓት ይዞት በመጣው ሜካናይዝድ ጦር በከባድ መሳሪያ በመታገዝ በራህሌና ኮነባ ወረዳን በመቆጣጠር የተለመደውን ጅምላ ግድያና ዘረፋ እያካሄደ ነው ብሏል።

አሁንም ህወሓት የኢትዮ - ጂቡቲ መተላለፊያ ኮሪደር ዋና መስመርን ለመቁረጥ ያለ የሌለ ኃይሉን በመጠቀም ትልቅ ሜካናይዝድ የሆነ ውጊያ እያካሄደ መሆኑንና ጦርነቱን አጠናክሮ መቀጠሉን የአፋር ክልል አሳውቋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update በአፋር ክልል ጦርነቱ ተባብሶ መቀጠሉ ተሰምቷል። የአፋር ክልል መንግስት ዛሬ ቅዳሜ ባወጣው መግለጫ ህወሓት ሰርዶን ለመቆጣጠር እንደ አዲስ በኪልበቲ ረሱ ዞን የከፈተውን ከባድ ጦርነት አጠናክሮ ቀጥሏል ብሏል። የክልሉ መንግስት ህወሓት ከታህሳስ 10 ቀን 2014 ጀምሮ እንደ አዲስ በአፋር በኩል ጦርነት መክፈቱን አስታውሷል። በኪልበቲ ረሱ ዞን የተለያዩ 5 ወረዳዎችና አንድ ከተማ መስተዳድር…
የአፋር ተፈናቃዮች ቁጥር ከ300 ሺህ አለፈ።

የአፋር ክልል ዛሬ ባወጣው መግለጫ ህወሓት እንደአዲስ በከፈተው ጦርነት ተቆጣጥሮ በሚገኝባቸው አካባቢዎች ከባድ ሰብዓዊና ቁሳዊ ኪሳራ አድርሷል ሲል አመልክቷል።

በአካባቢዎቹ ዝርፊያ እንዲሁም ውድመት ደርሷል የሚለው የአፋር ክልል መንግስት ከ300 ሺህ በላይ ሰዎች ከቤት ንብረታቸው መፈናቀላቸውን ገልጿል።

ጦርነቱ ከወር በላይ እንደሆነው የተገለፀ ሲሆን አሁንም ድረስ ተባብሶ መቀጠሉ ታውቋል።

@tikvahethiopia
#AU2022Summit

ህብረቱ በዝግ እየመከረ ነው።

35ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ ዛሬ ከሰዓት #በዝግ በተለያዩ ጉዳዮች እየመከረ ይገኛል፡፡

በአህጉሪቱ ሰላምና ደህንነት እንዲሁም የኮቪድ-19 ወረርሽኝን ለመቆጣጠር በተከናወኑ ስራዎችና በተገኙ ውጤቶች ዙሪያ ነው በዝግ እየመከረ የሚገኘው።

ዛሬ ምሽት ላይ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ዶ/ር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ለአፍርካ ሀገራት መሪዎች የእራት ግብዣ እንደሚያደርጉ ኢብኮ ዘግቧል።

@tikvahethiopia
PHOTO : የጌዴኦ ብሔር ዘመን መለወጫ ዳራሮ በዓል የመዝግያ ፕሮግራም በደማቅ ስነ-ስርዓት በዲላ ሁለገብ እስቴድየም ዛሬ ተካሂዷል።

Photo Credit : የዲላ ከተማ ሚኒኬሽን

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
እጅግ ፈታኙ የነፍስ አድን ርብርብ ... በአፍሪካዊቷ ሀገር ሞሮኮ ታምሩት ከተማ በጨዋታ ላይ የነበረ ስሙ ራያን የተባለ የ5 ዓመት ህፃን ልጅን ህይወት ለመታደግ ቀናትን የፈጀ ርብረብ እየተደረገ ነው። ህፃኑ 32 ሜትር ጥልቀት ባለው ጉድጓድ ውስጥ የወደቀ ሲሆን ለ4 ቀንም እዛው ይገኛል። የህፃኑን ህይወት ለመታደግ በርካታ የነፍስ አድን ሰራተኞች ርብርብ ላይ ሲሆኑ በሺዎች የሚቆጠሩ…
#Update

ፈታኙ የነፍስ አድን ስራ እየተጠናቀቀ ይመስላል።

በሞሮኮ የታምሩት ከተማ በጨዋታ ላይ የነበረ ስሙ ራያን የተባለ የ5 ዓመት ህፃን ልጅን ከገባበት ጉድጓድ ውስጥ ለማውጣትና ህይወቱን ለመታደግ ቀናትን የፈጀ ርብረብ እየተደረገ ሲሆን ርብርቡ ወደ መጨረሻ መድረሱ ታውቋል።

አሁን ላይ አድካሚው እና ፈታኙ የነፍስ አድንስ ስራ ወደ መጠናቀቁ የተቃረበ ሲሆን የነፍስ አድን ሰራተኞች ወደ ራያን እጅጉን ተቃርበዋል።

አንድ የሞሮኮ ጋዜጠኛ ደግሞ ራያን ሲወጣ እሱን ወደ ሆስፒታል የሚወስድ ሂሊኮፕተር መዘጋጀቱን ገልጿል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update ፈታኙ የነፍስ አድን ስራ እየተጠናቀቀ ይመስላል። በሞሮኮ የታምሩት ከተማ በጨዋታ ላይ የነበረ ስሙ ራያን የተባለ የ5 ዓመት ህፃን ልጅን ከገባበት ጉድጓድ ውስጥ ለማውጣትና ህይወቱን ለመታደግ ቀናትን የፈጀ ርብረብ እየተደረገ ሲሆን ርብርቡ ወደ መጨረሻ መድረሱ ታውቋል። አሁን ላይ አድካሚው እና ፈታኙ የነፍስ አድንስ ስራ ወደ መጠናቀቁ የተቃረበ ሲሆን የነፍስ አድን ሰራተኞች ወደ ራያን እጅጉን…
#Update

ራያን መገኘቱን ፤ የሞሮኮ የነፍስ አድን ሰራተኞችና የህክምና ቡድኖች በጥልቅ ጉድጓድ ውስጥ ለ4 ቀናት ያህል የቆየውን ህፃን ለማውጣት እየተዘጋጁ መሆኑን አረብ ኒውስ ፅፏል።

ክሰተቱ መላው ዓለም ላይ መነጋገሪያ የሆነ ሲሆን ሰብዓዊነት ገደብ የሌለው መሆኑንና ለአንዲት ነፍስ መትረፍ መከፈል ያለበት ዋጋ ሁሉ መከፈል እንዳለበት የሚያሳይ መሆኑ እየተገለፀ ነው።

ሞሮካውያን እና ጉዳዩን በማህበራዊ ሚዲያ የሚከታተሉ ሁሉ የሞሮኮ የነፍስ አድን ሰራተኞች ህፃኑን ከጉድጓድ ለማውጣት እያደረጉት ያለውን እጅግ ፈታኝ ስራ እያወደሱ ፤ ለህፃኑ በደህና መውጣት እየፀለዩ ናቸው።

መጨረሻውን ተከታትለን እንሳውቃችኃለን።

@tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#Update

ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ የመጀመሪያ ቴክኒካል ጥሪ ሙከራው መሳካቱን አስታወቀ።

ሳፋሪኮም አትዮጵያ የቴክኖሎጂ ክፍሉና መላው ባልደረቦቹ ባለፉት ሳምንታት አገልግሎቱን ለማስጀመር ዋና የሆኑትን የሙከራ ሥራዎች በትጋት ሲያከናውኑ እንደነበር ገልጿል።

@tikvahethiopia