TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
212 files
4.11K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#EastGojjam

ሰርግ ላይ በተተኮሰ ጥይት 4 ሰዎች ህይወታቸው ሲጠፋ 5 ሰዎች ቆሰሉ።

የምስራቅ ጎጃም ዞን ፖሊስ በሰርግ ላይ በተተኮሰ ጥይት የ4 ሰው ህይወት ሲጠፋ ተጨማሪ 5 ሰዎች የመቁሰል አደጋ መድረሱን አስታወቀ።

ክስተቱ የተፈጠረው በሁለት እጁ እነሴ ወረዳ በጥሩ ሰላም ቀበሌ በ24/5/2014 ዓ/ም ሲሆን ተጠርጣሪው ከሌላ ሠው መሣሪያ በመዋስ እና በመፎከር ላይ እያለ ጥብቅ ከፍቶ አውቶማቲክ ላይ ሆኖ ሲተኮስ አራት ሰዎች ወዲያውኑ ህይወታቸው ሲያልፍ መሣሪያ የሠጠውን ሰው ጨምሮ በአምስት ሰዎች ላይ የመቁሰል አደጋ መድረሱን ፖሊስ አስረድቷል።

የምስራቅ ጎጃም ዞን ፖሊስ መምሪያ የማህበሠሰብ አቀፍ የፖሊስ አገልግሎት ዋና ክፍል ሀላፊ ዋና ኢንስፔክተር አጃናው አዲስ ፥ ከቅርብ ግዜ ወዲህ በሰርግ ላይ እና በሀዘን ላይ ጥይት እየተተኮሰ ቀላል በማይባሉ የህብረተሰሰብ ክፍሎች ላይ የሞት እና የአካል ጉዳት በመድረሱ በማህበረሰቡ ላይ ከፍተኛ የሆነ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ጉዳትን እያስከተለ መሆኑን ገልፀዋል።

የጉዳዩን አሳሳቢነት በተለያዩ ሚዲያዎች ፣ በሶሻል ሚዲያና መድረኮች እየተዘጋጁ ውይይቶች ቢደረጉም ችግሩን ግን በዘላቂነት ለመፍታት አለመቻሉንም አስረድተዋል።

በመሆኑም ህብረተሰቡ ሰርግ ላይና በለቅሶ ላይ አላስፈላጊ ጥይት መተኮስ በህብረተሰቡ ላይ እያደረሠ ያለውን ከፍተኛ ችግር በመገንዘብ በህጉ ከተቀመጡ አሰራሮች በተጨማሪ በእድር እና መሠል የማህበረሰቡ አደረጃጀት ህገ ደንቦችን በማውጣት ለመከላከል ለስራው እገዛ እንዲያደርጉ አሳስበዋል።

መረጃው ምስራቅ ጎጃም ዞን ፖሊስ ነው።

@tikvahethiopia