TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
212 files
4.11K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#UPDATE የሞሮኮ ነፍስ አድን ሰራተኞች የ5 ዓመቱን ህፃን ራያንን ከ5 ቀን በኃላ ከገባበት ጉድጓድ እንዳወጡት አረብ ኒውስ ፅፏል። @tikvahethiopia
ራያን ህይወቱ ማለፉ ተረጋገጠ።

ለ5 ቀናት ጥልቅ ጉድጓድ ውስጥ የነበረው የሞሮካውን ህጻን ከጉድጓዱ ውስጥ ማውጣት ቢቻልም ህይወቱ እንዳለፈ የሞሮኮ ባለስልጣናት በይፋዊ መግለጫ አስታውቀዋል።

@tikvahethiopia
በአፋር ክልል ምንእየሆነ ነው ያለው ?

- የአፋር ክልል መንግስት እንዳለው ህወሓት በአፋር ክልል ለ3ኛ ጊዜ ጦርነት ከከፈተ ከወር በላይ ሆኗል።

- የአፋር ክልል መንግስት እንዳሳወቀው አሁንም ጦርነቱ ተባብሶ ቀጥሏል።

- ህወሓት በኪልበቲ ረሱ ዞን የተለያዩ 5 ወረዳዎች እና አንድ ከተማ መስተዳድር ማለትም ፦ አብአላ ከተማ አስተዳደር ፣ በአብአላ ወረዳ፣ በመጋሌ ወረዳ፣ በኤረብቲ፣ በኮነባ እና በራህሌ ወረዳዎች በተደጋጋሚ ጦርነት በመክፈት ሰርዶን ለመያዝ ጥረት እያደረገ ነው።

- ሰርዶን መያዝ የፈለገው የኢትዮ-ጂቡቲን መስመር ለመቆጣጠርና አፋርን እንደ መደራደሪያ ለመጠቀም መሆኑን የአፋር ክልል ገልጿል።

- ህወሓት ከዚህ ቀደም ከያዛቸው አካባቢዎች በተጨማሪ በራህሌ እና ኮነባን በቁጥጥሩ ስር አውሏል።

- ከዚህ ቀደም የተያዙት አብአላ ከተማ አስተዳድር፣ አብአላ ወረዳ ፣ መጋሌ ወረዳ እና ኤረብቲ ወረዳዎች ናቸው።

- ህወሓት ጦርነት እያደረገ ያለው ያለ የሌለውን ኃይል ተጠቆሞ መሆኑ ተገልጿል።

- ህወሓት የኢትዮ - ጂቡቲ መተላለፊያ ኮሪደር ዋና መስመርን ለመቁረጥ ከፍተኛ ጦርነት አሁን ድረስ እያደረገ ነው።

- የአፋር ተፈናቃዮች ቁጥር ከ300 ሺህ ተሻግሯል።

- አካባቢው ባለው ግጭት ሳቢያ ሰብዓዊ እርዳታ ለማድረስ እንቅፋት መፈጠሩ ተገልጿል።

@tikvahethiopia
አሚና መሀመድ ዛሬ ኮምቦልቻ ይገኛሉ።

በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ምክትል ዋና ጸሐፊ አሚና መሀመድ የተመራ የመንግስታቱ ድርጅት ልዑክ ዛሬ ጥዋት ኮምቦልቻ ከተማ ገብቷል፡፡

የአማራ ክልል ከፍተኛ ባለስልጣናት ለልዑኩ አቀባበል ያደረጉ ሲሆን ልዑኩ በኮምቦልቻ በጦርነት ያተጎዱ አካባቢዎችን ተመልክቷል።

ልዑኩ ከጎበኛቸው ቦታዎች አንደኛው የኮምቦልቻ ቴክኒክ እና ሙያ ማሰልጠኛ ኮሌጅ ሲሆን በተቋሙ ላይ የደረሰውን ጉዳት እንዲሁም የጅምላ መቃብር ስፍራ ተዘዋውሮ ተመልክቷል።

ከሚመለከታቸው አካላት ጋርም ውይይት ያደረጉ ሲሆን የጦርነቱ ሰለባ የሆኑ ሴቶች፣ ህፃናት እና ሌሎችንም የህብረተሰብ ክፍሎች አነጋግረዋል።

@tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#ደቡብ_አፍሪካ

ሰሞኑን በደቡብ አፍሪካ ከወትሮ ለየት ከባድ ዝናብ በሀገሪቱ የተለያዩ ክፍሎች ላይ እየጣለ ይገኛል:: ሰሞኑን የጣለው ይህ ከባድ ዝናብ በኳዙሉናታል፣ ፑማላንጋ እና ሊምፖፖ እንዲሁም ሌሎች የደቡብ አፍሪካ ግዛቶች ላይ ከቀላል እስከ ከባድ ጉዳት አድርሷል።

ይህን ተከትሎ ጆሃንስበርግ ከተማ እየጣለ ባለው ከፍተኛ መጠን ያለው ዝናብ ምክንያት የ " አስቸኳይ ግዜ ምላሽ " ለመስጠት በተጠንቀቅ ላይ ነች ሲል የሀገሪቱ ሚዲያዎች ዘግቧል። ዝናቡ ቀጣይነት ሊኖረው ስለሚችል የደቡብ አፍሪካ ነዋሪዎች ጥንቃቄ እንዲያደርጉ መልዕክት ተላልፏል።

በደቡብ አፍሪካ የምትኖሩት ኢትዮጵያውያን ቤተሰቦቻችንም ጥንቃቄ ታደርጉ ዘንድ እናሳስባለን።

Video:- eNCA

Fa ya
(Tikvah-Family)
South Africa

@tikvahethiopia
#WKU

ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ያስገነባውን ዘመናዊ የመምህራን መኖሪያ እያስመረቀ ይገኛል።

ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ከ464,000,000 ብር (አራት መቶ ስልሳ አራት ሚሊዮን ብር) በላይ ወጪ በማድረግ ያስገነባው የመምህራን መኖሪያ አፓርታማ በዛሬው ዕለት በመመረቅ ላይ ይገኛል።

የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ መምህራንን የመኖሪያ ቤት ችግር በከፊልም ቢሆን ለማቃለልና በተለይም መምህራን በዩኒቨርስቲው አቅራቢያ ሆነው በተረጋጋ ሁኔታ መደበኛ ስራቸውን ለማከናወን እንዲያግዛቸው ታስቦ በዩኒቨርሲቲው አቅራቢያ በጉብሬ ክፍለ ከተማ የተገነባ ነው።

ግንባታው በ1719 ካሬ ላይ ያረፈ ሲሆን አራት ብሎኮች አሉት። ባለ ሁለት መኝታ ያላቸው 72 ቤቶችን፤ ባለ አንድ መኝታ ቤት ያላቸው 120 ቤቶችን እና 60 እስቱዲዮዎች ሲሆኑ በድምሩ 252 አባወራዎችን የሚያስተናግድ የመኖሪያ ክፍሎች ያሉት ነው።

በተጨማሪ ደግሞ ደረጃውን የጠበቀ የኪችን ካቢኔት የተገጠመለት ፤ ነዋሪዎችን የዋይፋይ አገልግሎት ተጠቃሚ እንዲሆኑ የመስመር ዝርጋታ የተደረገለት፤ የራሱ የሆነ ትራንስፎርመር ተገጥሞለት የተሟላ የመብራት አገልግሎት እንዲኖር ለማድረግ የሚያስችል ሆኖ የተገነባ ፤የውሃ እጥረት እንዳይከሰት በማሰብ የራሱ የሆነ ጥልቅ የመጠጥ ጉድጓድ ውሃ የተቆፈረለት ጭምር ነው።

ለህንጻው ነዋሪዎች አገልግሎትን የሚሰጡ 24 ሱቆች (በእያንዳንዱ ብሎክ ላይ 6 ሱቆች) ፤ 4 ካፍቴሪያዎች (በእያንዳንዱ ብሎክ ላይ 1 ሱቅ) ፤ 4 ሱፐር ማርኬት (በየብሎኩ 1 ሱፐርማርኬት)፤ አንድ ፋርማሲ ያለው ሆኖ ለዘመናዊ የአኗኗር ዘዴ አመቺ ሆኖ መገንባቱ ተገልጿል።

#WKU

@tikvahethiopia
#Biyo

ቢዮ ኃ.የተ.የግል ማህበር በተለያዩ ጊዜያት ያመጣቸውን ለመስኖ ውሃ አገልግሎት የሚውሉ የተለያዮ አይነት የውሃ ፓንፕ (Gate valve) መሸጥ እንደሚፈልግ ገልጿል። መግዛት የምትፈልጉ ከታች በተገለጹት አድራሻ ስለ ሽያጩ ዝርዝር መጠየቅ ይቻላል። አድራሸ፡- ስልክ ቁጥር 0970-72-34-66 ወይም 0116-63-01-60 መገናኛ ቢሮ
ኢሜል፡- [email protected]
#WaraJarso

የወረ ጃርሶ ወረዳ ነዋሪዎች በታጣቂዎች እንቅስቃሴ ሰላማቸውን እንዳጡ መግለፅ ከጀመሩ ሰነባብተዋል።

በአካባቢው እንደሚንቀሳቀሱ የተነገረላቸው በህ/ተ/ም/ቤት አሸባሪ ተብሎ የተፈረጀው የሸኔ ታጣቂዎች እንደሆኑ ነዋሪዎቹ ይገልፃሉ።

ከወረዳ እስከ ዞን ከፍ ሲል እስከ ክልሉ መንግስት ድረስ ለአካባቢው መፍትሄ ይፈለግ ዘንድ አቤቱታ ቢቀርብም ተጨባጭ ለውጥ ሊመጣ አልቻለም።

ከሳምንታት በፊትም አዲስ አበባ ድረስ በመምጣት የፌዴራል መንግስት መፍትሄ እንዲፈልግላቸው አቤቱታቸውን አሰምተዋል።

አርሶ አደሮች በነፃነት ለመግባትና ለመውጣት ስጋት አለን ፤ ሰዎች ይታፈናሉ፣ ደክመን የዘራነው እህል በግፍ ይቃጠላል ፣ ሌሎችም ህገወጥ እንቅስቃሴ ይደረጋል ከዚህ አለፍ ሲል የወረዳው ከተማ ጎሃፅዮን/ቀሬጎዋ/ውስጥ ቀን ቀን የመንግስት አካላት እንደሚያስተዳር ማታ ደግሞ ታጣቂ ቡድኑ እንደሚንቀሳቀስ ቀን ላይ ግን እንደማይታይ ይገልፃሉ፤ ሁኔታው ግራ የሚያጋባ እና እጅግ ትልቅ ችግር መሆኑንም አመልክተዋል።

በዚህ ወርም የወረጃርሶ ወረዳ የአርሶ አደሮች እህል ሲቃጠሉ የሚያስዩ ፎቶዎች በማጋራት፣ በአካባቢው ዝርፊያ፣የንብረት ማውደም እየደረሰና ለዚህ ህገወጥ ድርጊት ተጠያቂው ሸኔ መሆኑን ገልጾ ነበር።

ከሳምንታት በፊት በብሄራዊ ቴሌቪዥ ጣቢያ የቀረበው የኦሮሚያ ክልል የፀጥታ ቢሮ የሸኔ እንቅስቃሴ ከክልሉ በላይ እንዳልሆነ በቡድኑ ላይ እርምጃ እየተወሰደ መሆኑን በወረ ጃርሶ አካባቢ የቀሩ ካሉ አይቀጡ ቅጣት እንደሚቀጣ ተናግሮ ነበር።

በኦሮሚያ ክልል አንዳንድ አካባቢዎች ላይ የሚታየው ከፍተኛ የሆነ የፀጥታ ስጋት፣ የዜጎች መፈናቀል፣ ሞት፣ ለዓመታት ያህል አንዳች ዘላቂና አስተማማኝ መፍትሄ ሳይገኝ ዛሬም ድረስ ቀጥሏል።

@tikvahethiopia
#PLAZAPREMIUM #NHY

ብፕላዛ ፕሪሚየም ግሩፕ እና ኤን.ኤች.ዋይ የሽርክና አጋርነት ስምምነት አደረጉ፡፡

ስምምነቱ በአፍሪካ የአየር ትራንስፖርት ዋና መዳረሻ በሆነው በአዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ያለውን የተጓዦች አቀባበል እና የላውንጅ አገልግሎት ደረጃን እንደሚያሳድግ እምነት የተጣለበት ነው።

ፕላዛ ፕሪሚየም ላውንጅ ኢትዮጵያ ፤ በያዝነው አመት መጋቢት ወር በአዲስ አበባ ቦሌ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በተርሚናል 2 የሚከፈት ይሆናል፡፡

በአፍሪካ የአየር ትራንስፖርት ዘርፍ ቀዳሚ መዳረሻ የሆነው አዲስ አበባ ቦሌ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ በየአመቱ ከ12 ሚሊዮን በላይ ተሳፋሪዎችን ያስተናገዳል፡፡

ይህ አዲስ የተመሰረተ የሽርክና አጋርነት የፕላዛ ፕሪሚየም ግሩፕን የ24 ዓመታት የላቀ ልምድ እና የኤን.ኤች.ዋይን የሀገር ውስጥ የእንግዳ መስተንግዶ ልምድ በማዋሃድ በአየር ማረፊያ ውስጥ ያለውን የመንገደኞች አቀባበል እና የላውንጅ አገልግሎት ደረጃን የበለጠ ለማዘመን ያለመ ነው፡፡

በ1000 ካሬ ሜትር ላይ ያረፈው ፕላዛ ፕሪሚየም ላውንጅ ኢትዮጵያ፤ በአንድ ጊዜ ለ325 እንግዶች አለም አቀፍ ደረጃን የጠበቀ መስተንግዶ ለመስጠት እንዲያስችል ታልሞ የተደራጀ ነው።

* ተጨማሪ መረጃ ከላይ ተያይዟል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#USAIDEthiopia

የአሜሪካ ህዝብ ተራድኦ ድርጅት (USAID) የኢትዮጵያ ሚሽን ዳይሬክተር የሆኑት ሼን ጆንስ በባህር ዳር ከተማ ተዘጋጅቶ በነበረ ዝግጅት ላይ በአማራ ክልል ከ500,000 በላይ ሰዎችን ተጠቃሚ የሚያደርግ ሁለት አዳዲስ የመዋዕለ ነዋይ ፕሮጀክቶችን ይፋ አድርገዋል።

ለዚሁ ከ11 ቢሊዮን ብር በላይ የተመደበ ሲሆን ሁለቱም የመማዕለ ነዋይ ፕሮጀክቶች በቀጥታ በገንዘብ ሚኒስቴር የሚመራውን PSNP5 ይደግፋሉ ተብሏል።

የአሜሪካ ህዝብ ተራድኦ ድርጅት (USAID) ከጥቂት ከቀናት በፊት በኦሮሚያ ክልል ከ400ሺ በላይ ሰዎችን ኑሮ ሊያሻሽል የሚችል በ10.2 ቢሊዮን ብር ሁለት አዳዲስ የመዋዕለ ንዋይ ፕሮጀክቶችን ተግባራዊ እንደሚያደርግ ማስታወቁ አይዘነጋም።

#USAIDEthiopia

@tikvahethiopia
#Oromia #Borana📍

" የድርቁ ሁኔታ ምንም መሻሻል አላሳየም " - የቦረና ዞን የግብርና ፅ/ቤት

• በድርቁ ከ4 ቢሊዮን ብር በላይ የሚያወጡ ከብቶች አልቀዋል።

• ወደ 262 ሺ ከብቶች ሞተዋል።

• 280 ሺህ በላይ ከብቶች በሰው ጉልበት ነው የሚነሱት።

የቦረና ዞን የግብርና ፅ/ቤት የእንሳት ሃብት ልማት አስተባባሪ ዶ/ር ቃሲም ጉዮ በቦረና ያለው የድርቅ ሁኔታ ምንም መሻሻል እንዳላሳየ ለቪኦኤ በሰጡት ቃለ ምልልስ ተናግረዋል።

ዶ/ር ቃሲም ጉዮ ፥ " የተለያየ ድጋፍ ቢደረግም ሁኔታው እንደዛው ነው እየቀጠለ ያለው። ስለዚህ የድርቁ ሁኔታ ሄዶ ሄዶ መሃሉንም አልፎ ወደ መጨረሻ አካባቢ ነው ያለነው " ብለዋል።

በድርቁ ምክንያት ወደ 262 ሺ ከብቶች የሞቱ ሲሆን ወደ 280 ሺህ በላይ ከብቶች በሰው ጉልበት ነው ከመሬት የሚነሱት ሲሉ አክለዋል።

በግምት ከ4 ቢሊዮን ብር በላይ የሚያወጡ ከብቶችን ቦረና ዞን አጥቷል።

ዶክተር ቃሲም ጉዮ በድርቁ ምክንያት የምግብ እጥረት ማጋጠሙን የገለፁ ሲሆን ለህበረተሰቡ ሆነ ለእንስሳት ዘርፈ ብዙ ድጋፍ እየተደረገ ነው ሲሉ ተናግረዋል።

በድርቅ ከብቶቻቸው ያለቁባቸው የዞኑ ነዋሪዎች የሚደረገው ድጋፍ አሁንም በቂ ባለመሆኑ መንግስት እና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ፣ ግለሰቦች ድጋፋቸውን እንዲያጠናክሩ ጠይቀዋል።

@tikvahethiopia