TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
212 files
4.11K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#AU2022Summit

የአፍሪካ ህብረት የሰላም እና የፀጥታ ም/ ቤት አባል ሆነው የተመረጡ 15ቱ ሀገራት ከታች ተዘርዝረዋል።

አምስቱ ለ3 ዓመታት የተመረጡ ሲሆን አስሩ ደግሞ ለ2 ዓመታት የተመረጡ ናቸው።

🇩🇯 ጅቡቲ (3 ዓመት)
🇹🇿 ታንዛኒያ (2 ዓመት)
🇺🇬 ኡጋንዳ (2 ዓመት)
🇧🇮 ቡሩንዲ (2 ዓመት)
🇨🇩 ዲሞክራቲክ ኮንጎ (2 ዓመት)
🇿🇦 ደቡብ አፍሪካ (2 ዓመት)
🇿🇼 ዚምባብዌ (2 ዓመት)
🇳🇦 ናሚቢያ (3 ዓመት)
🇲🇦 ሞሮኮ (3 ዓመት)
🇹🇳 ቱኒዚያ (2 ዓመት)
🇨🇲 ካሜሩን (3 ዓመት)
🇬🇭 ጋና (2 ዓመት)
🇳🇬 ናይጄሪያ (3 ዓመት)
🇬🇲 ጋምቢያ (2 ዓመት)
🇸🇳 ሴኔጋል (2 ዓመት)

@tikvahetheng
" ብሄራዊ ፈተናው በሰላም ተጠናቋል " - ኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር

ከጥር 24 ጀምሮ ሲሰጥ የነበረው የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና በሰላም መጠናቀቁን የኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር አስታውቋል።

በከተማ አስተዳደሩ በ3 የመፈተኛ ጣቢያዎች ላይ 1 ሽህ 299 መደበኛ ተማሪዎች እና 43 የግል ተፈታኞች በሶስት መፈተኛ ጣቢያዎች ላይ ተቀምጠዋል።

ተማሪዎቹ ትምህርታቸውን ሲማሩበት የነበረውን ዩኒፎርም ለተቸገሩ ወገኖች እንዲውል እያሰባሰቡ ሲሆን ጥር 28 ጀምሮ የሚማሩበትን ዩኒቨርሲቲ ይመርጣሉ ተብሏል።

ምንጭ፦ የኮምቦልቻ ኮሚኒኬሽን

@tikvahethiopia
ባልደራስ ባወጣው መግለጫ ምን አለ ?

ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ በዛሬው ዕለት ባወጣው መግለጫ ' ፋኖ ' ኢ-መደበኛ አደረጃጀት አይደለም ሲል አስታወቀ።

ፓርቲው ፥ " ፋኖ በጭንቅ ጊዜ አገርን ከወረራ እና ከብተና የሚታደግ፣ በሠላም ጊዜ በየሙያ ዘርፉ ተሰማርቶ ሠላማዊ ኑሮውን የሚኖር ኢትዮጵያዊ ነው " ሲል ገልጿል።

አክሎ ፥ " ፋኖ በጊዜያዊነት ተሰባስቦ በአገር ላይ የተሰነዘረ ጥቃት ሙሉ በሙሉ እስከሚወገድ በዱር በገደሉ እየተሰማራ፣ አካባቢውንና አገሩን ከጥቃት የሚከላከል ህዝባዊ ኃይል እንጂ፣ቋሚ የሆነ ኢ-መደበኛ አደረጃጀት አይደለም " ብሏል።

ባልደራስ ፥ ፋኖ “ኢ-መደበኛ አደረጃጀት” በሚል ፍረጃ ወከባና ትንኮሳ እየተፈፀመበት ይገኛል ያለ ሲሆን ፓርቲው ወከባ እና ትንኮሳውን እያደረሰ ነው ያለውን አካል በመግለጫው ላይ በግልፅ ስም ጠርቶ አላስቀመጠም።

በሌላ በኩል ባልደራስ በመግለጫው በመንግሥት እና በህወሓት መካከል በጎረቤት አገር ድርድር እየተካሄደ መሆኑን በተለያዩ ሚዲያዎች እየተገለፀ እንደሚገኝ ገልፆ ድርድሩ ከጥርጣሬ ነፃ ለማድረግ 7 ምክረ ሃሳቦችን አቅርቧል።

1ኛ. ድርድሩ ለሕዝብ ግልጽ እንዲሆን፣ ሂደቱንም ሊከታተል በሚችልበት አውድ እንዲደረግ፣
2ኛ. የአፋር እና የአማራ ክልላዊ መስተዳድሮች በድርድሩ ጉልህ ሚና እንዲኖራቸው የሚያስችል አካሄድ እንዲኖር፣
3ኛ. በሕጋዊ መንገድ የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ድርጅቶች፣ በፖለቲካ ድርጅቶች የጋራ መድረክ በኩል በቂ መረጃ የሚያገኙበት ሁኔታ እንዲመቻች፣
4ኛ. የአገር ሽማግሌዎች ሂደቱን በታዛቢነት እንዲከታተሉ፣
5ኛ. የዲያስፖራ ኢትዮጵያውያን በማህበሮቻቸው በኩል ሂደቱን በታዛቢነት እንዲከታተሉ፣
6ኛ. ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ሂደቱን በታዛቢነት እንዲከታተል፣
7ኛ. ለመገናኛ ብዙሃን በቂ መረጃ የሚደርስበት ሁኔታ እንዲመቻች የሚሉ ናቸው።

ፓርቲው ህዝብን ያላማከለ ድርድር አገርን የሚጠቅም ባለመሆኑ፣ አስቸኳይ እርምት እንዲረግበት ሲልም አሳስቧል።

ምንም እንኳን ባልደራስ ጎረቤት ሀገር ድርድር እየተደረገ መሆኑን በተለያዩ ሚዲያዎች መስማቱን ቢገልፅም (የትኞቹ ሚዲያዎች ጎረቤት ሀገር ውስጥ ድርድር እንደተጀመረ እንደገለፁ በግልፅ አልተቀመጠም) መንግስት በተደጋጋሚ ከህወሓት ጋር ንግግር ሆነ ድርድር አለመጀመሩን ከሰሞኑን እየገለፀ እንደሚገኝ ይታወቃል።

የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ መግለጫ ሙሉ ሀሳብ በዚህ ይገኛል : https://telegra.ph/Balderas-Party-02-04

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Kereyu Incident Investigation Report.pdf
" ... የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ' ሸኔ ' ነው የገደለው ብሎ መግለጫ አውጥቷል ? እኔ አላውቅም ፤ እኔ እስከዛሬ የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን መግለጫ አላወጣም፤ ከተሰጠም ስህተት ነው " - ግርማ ገላን

ትላንት የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን መግለጫ ሰጥቶ ነበር።

መግለጫው ትኩረቱ በታህሳስ ወር ላይ በምስራቅ ሸዋ ዞን በውሰት እና ፈንታሌ ወረዳዎች ስለተገደሉ ሰዎች ነው።

ይህ መግለጫ የተሰጠው ኢሰመኮ መግለጫውን ባወጣ ከአንድ ቀን በኃላ ነው።

የኦሮሚያ ፖሊስ በውሰት እና ፈንታሌ ወረዳዎች 14 ሰዎችን ጨምሮ 11 የፖሊስ አባላት ተገድለዋል ብሏል።

ም/ኮሚሽነር እና የወንጀል ምርመራና ፍትህ ማስተባበሪያ ኃላፊ ግርማ ገላን ፥ "ማህበራዊ ሚዲያ ላይ እንደሚወራው ፖሊስ መመሪያ ሰጥቶ ሰዎችን ሊያስገድል አይችልም ህጉም የፓሊስ ስነምግባር አይፈቅድም። ተልዕኮ የተሰጠው የፖሊስ አባል ድርጊቱን ፈፅሞ ከሆነ በህግ ይጠየቃል " ሲሉ ተናግረዋል።

ኢሰመኮ ያወጣውን ሪፖርት በተመለከተ ምክትል ኮሚሽነር ገርማ ፥ " ኢሰመኮ በራሱ መንገድ ማጣራት አድርጓል፤ መግለጫም አውጥቷል፣ ኢሰመኮ ካወጣው መግለጫ አኳያ ትንሽ ከኛ ተልዕኮ ጋር አብሮ አይሄድም፤ በግልፅ መታወቅ ያለበት። እኛ መርማሪ ፖሊሶች ነን በምርመራ መርህ አንድ ሰው በወንጀል ተጠርጥሯል ተብሎ ጥቆማ ፖሊስ ሲያገኝ ያን ያገኘውን ጥቆማ አጣርቶ በህግ ማስጠየቅ ሲችል ብቻ ነው በዛ ጉዳይ ማብራሪያ መስጠት የሚችለው " ብለዋል።

አክለው ፥ " መግለጫው እጅግ የሚያበረታታ መቀጠልም ያለበት ፣ ከወገናዊነትም የፀዳ የህዝብ ወገንተኝነትን ማዕከል ባደረገ መልኩ ነው ተቋሙ መግለጫ ያወጣው በተለይ እንደክልላችን ስለዚህ ተቋሙ ያወጣው መግለጫ እንደውም እኛ ምንድነው በአካባቢው ላይ ያለው የሚለውን በደንብ እንድናይ አድርጎናል " ሲሉ ገልፀዋል።

የኦሮሚያ ፖሊስ 14ቱ ሰዎች የከረዩ አባገዳዎችን ሸኔ ነው የገደለው የሚል መረጃ እንዳላወጣ ገልጾ ከወጣም ስህተት ነው ብሏል።

ምክትል ኮሚሽነሩ ግርማ ፥ " የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ' ሸኔ ' ነው የገደለው ብሎ መግለጫ አውጥቷል እኔ አላውቅም ፤ እኔ እስከዛሬ እስከዚህች ሰዓት ድረስ የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን መግለጫ አላወጣም፤ ከተሰጠም ስህተት ነው። ምክንያቱም የሆነ ነገር ሊባል ይችላል ነገር ግን ካጣራ እና ትንሽ እውነት የሚመስል ነገር ሲኖር ነው በአግባቡ ደረጃ በደረጃ መረጃ እየሰጠ መሄድ ያለበት " ነው ያሉት።

የክልሉ ፖሊስ ከወንጀሉ ጋር በተያያዘ ሁለት ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተጣራ መሆኑን ምርመራው ሲጠናቀቅ ለህዝብ እንደማያሳውቅ ገልጿል።

የከረዩ አባገዳዎች በተገደሉበት ወቅት የኦሮሚያ ክልል ኮሚኒኬሽን ግድያውን 'ሸኔ' እንደፈፀመ በመግለጭ የሀዘን መግለጫ ማውጣቱ / የምስራቅ ሸዋ ዞን አስተዳደር በተመሳሳይ ግድያውን ሸኔ እንደፈፀመ በመግለፅ መረጃ ማውጣቱ ፤ የተለያዩ የመንግስትና የግል ሚዲያዎች እንዲሁም አክቲቪስቶች " የከረዩ አባገዳ በአሸባሪው ሸኔ ተገደሉ " በሚል ዘገባዎችን ማውጣታቸው አይዘነጋም።

በውቅቱ በተለይም የሟች ቤተሰብ እና የአካባቢው ነዋሪዎች አባ ከድር ሀዋስን ጨምሮ 14 ሰዎች የተገደሉት በፀጥታ አስከባሪ ኃይሎች መሆኑን አሳውቀው ነበር።

በተለይም ደግሞ ወ/ሮ ወርቄ ሀዋስ የአባገዳ ከድር ሀዋስ እህት ወንድማቸው ከጊዳራ ቀበሌ ማህበር ተውስደው መገደላቸውን ፤ ይዘዋቸው የሄዱት ደግሞ የመንግስት የፀጥታ ኃይሎች እንደሆኑ እንዲሁም ሰዎቹ የኦሮሚያ ልዩ ኃይል እና የፖሊስ ዩኒፎርም አድርገው እንደነበር ተናግረው ነበር : በዚህ አንብቡ : https://t.iss.one/tikvahethiopia/65365

@tikvahethiopia
አስተያየት ስጡበት !

የኢትዮጵያ አገራዊ ምክክር ኮሚሽን የዕጩ ኮሚሽነሮች ላይ ህዝቡ አስተያየት እንዲሰጥባቸው ምክር ቤቱ ዝርዝራቸውን ዛሬ ይፋ አድርጓል።

በተለያዩ አግባቦች በተጠቆሙት 42 የኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን እጩ ኮሚሽነሮች ላይ ከዛሬ ጀምሮ የህዝብ አስተያየት ይሰበሰባል።

ይህን 👉https://www.hopr.gov.et/am/web/guest/dialog-candidate ማስፈንጠሪያ በመጫን አስተያየት መስጠት እንደሚቻል የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አሳውቋል።

#ሼር #Share

@tikvahethiopia
Situation_Report_Northern_Ethiopia_Humanitarian_Update_3_Feb_2022.pdf
3.4 MB
#SituationReport

በተመድ የሠብዓዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ጽ/ቤት (UNOCHA) ሪፖርቱን አውጥቷል።

በሰሜን ኢትዮጵያ ያለው ሁኔታ ውጥረት ያለበት እና ተለዋዋጭ መሆኑን ገልጿል።

ይህ ሪፖርት በተደረገበት ሳምንት በትግራይ እና በአማራ ክልሎች ያለው ሁኔታ የተረጋጋ ቢሆንም፣ በአፋር ክልል ከትግራይ አዋሳኝ አካባቢዎች መካከል በአባላ፣ በርሀሌ፣ ዳሎል፣ ኤሬብቲ፣ ኮኔባ እና መጋሌ ወረዳዎች ከፍተኛ ግጭቶች መከሰታቸው ታውቋል።

የተከሰቱት የቅርብ ጊዜ ግጭቶች የዜጎችን ህይወት ለአደጋ እያጋለጡ፣ በተለይ ከፍ ያለ የህዝብ እንዲፈናቀል እያደረጉና በህዝቡ ኑሮ ላይ ተጽዕኖ በማሳደር የሰብአዊ ፍላጎቶች እንዲጨምሩ አድርጓል።

ግጭቶቹ በአፋር ለተጎዱ አካባቢዎች ሰብአዊ አቅርቦት እንዳይደርስም ገድበዋል።

የአፋር ክልል ባለስልጣናት በቅርቡ በክልሉ በተቀሰቀሰው ግጭት ከ200 ሺ በላይ ሰዎች ከቀያቸው መፈናቀላቸውን አሳውቀዋል።

አጭር መረጃ፦

- በቅርቡ በአፋር ክልል በተቀሰቀሰው ጦርነት በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች እንዲፈናቀሉ አድርጓል፤ ለሰብዓዊ ድጋፍ ተደራሽነቱም አስቸጋሪ እንደሆነ ቀጥሏል።

- በአማራ ክልል በቅርቡ በተካሄደው የስርጭት ስራ ከ811,000 በላይ ሰዎች እና ከ420,000 በላይ ሰዎች በቀድሞው የስርጭት ስራ ከጥር 24 እስከ 30 ባለው ጊዜ የምግብ ድጋፍ ተደርጎላቸዋል።

- በሰመራ-አባላ-መቐለ መንገድ ወደ ትግራይ የሚደርሰው የሰብአዊ እርዳታ አቅርቦት እኤአ ከታህሳስ 15 ቀን ጀምሮ በተፈጠረው ግጭትና የጸጥታ ችግር እንደተቋረጠ ነው።

- በአፋር ክልል ከ2,500 በላይ ህጻናት ከ1,000 በላይ ሴት ልጆችን ጨምሮ ይህ ሪፖርት በወጣበት ሳምንት መደበኛ ባልሆነ የትምህርት መርሃ ግብሮች የትምህርት ድጋፍ እንዲያገኙ ተደርጓል።

*ሙሉ ሪፖርት በPDF ተያይዟል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#AU2022Summit የአፍሪካ ህብረት የሰላም እና የፀጥታ ም/ ቤት አባል ሆነው የተመረጡ 15ቱ ሀገራት ከታች ተዘርዝረዋል። አምስቱ ለ3 ዓመታት የተመረጡ ሲሆን አስሩ ደግሞ ለ2 ዓመታት የተመረጡ ናቸው። 🇩🇯 ጅቡቲ (3 ዓመት) 🇹🇿 ታንዛኒያ (2 ዓመት) 🇺🇬 ኡጋንዳ (2 ዓመት) 🇧🇮 ቡሩንዲ (2 ዓመት) 🇨🇩 ዲሞክራቲክ ኮንጎ (2 ዓመት) 🇿🇦 ደቡብ አፍሪካ (2 ዓመት) 🇿🇼 ዚምባብዌ (2…
#Update

የአፍሪካ ሀገራት መሪዎች በ35ተኛዉ የአፍሪካ ህብረት (AU) የመሪዎች ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ ወደ አዲስ አበባ እገቡ ናቸው።

ጥዋት ከላክልናችሁ ተጨማሪ ሌሎች መሪዎች የገቡ ሲሆን በሚከተለው ዝርዝር አስቀምጠነዋል።

🇲🇼 ዶ/ር ላዛሩስ ማካርቲ ቻክዌራ (ማላዊ - ፕሬዝዳንት)
🇬🇲 ዶ/ር ኢሳቱ ቶራይ (ጋምቢያ - ምክትል ፕሬዚዳንት)
🇳🇬 ሙሀሙዱ ቡሃሪ (ናይጄሪያ - ፕሬዝዳንት)
🇨🇮 ኦላሳን ኦታራ (ኮትዲቯር - ፕሬዝዳንት)
🇸🇳 ማኪ ሳል (ሴኔጋል - ፕሬዝዳንት)
🇲🇷 ሞሐመድ ኡልድ ኤል-ጋዝዋኒ (ሞሪታንያ - ፕሬዝዳንት)
🇹🇿 ዶ/ር ፊሊፕ እስዶር መፓንጎ (ታንዛንያ/- ምክትል ፕሬዝዳንት)
🇹🇩 አልበርት ፓሂሚ ፓዳክ (ቻድ - ጠቅላይ ሚኒስትር)
🇿🇼 ኤመርሰን ማናንጋግዋ (ዚምባቡዌ - ፕሬዝዳንት)
🇬🇦 ሮዝ ክርስቲያን ኦሳካ (ጋቦን - ጠቅላይ ሚኒስትር)

የሌሎችም ሀገራት መሪዎች እየተጠበቁ ይገኛሉ። መሪዎቹ አዲስ አበባ ሲገቡ አንድ ላይ አሰባስበን የምንልክላችሁ ይሆናል።

@tikvahethiopia
#Update

የሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ ለሁለተኛ ዙር ሲሰጥ የነበረው የ2013 ዓ.ም አገር አቀፍ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በሰላም መጠናቀቁን አሳውቋል።

የኤጀንሲው ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ተፈራ ፈይሳ ፦
- በኦሮሚያ፣
- በአማራ፣
- በአፋር እና በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች በ189 የፈተና መስጫ ጣቢያዎች ፈተናው መሰጠቱን ገልፀው የመልቀቂያ ፈተናው ካለምንም እንከን በሰላም ተጠናቋል ሲሉ ገልፀዋል።

@tikvahethiopia
#ዝናቧ_ገብረፃዲቅ

መምህሯ የተከራየችበት ግቢ ውስጥ ተቀብራ ተገኘች።

በሰሜን ሸዋ ዞን በሞረትና ጅሩ ወረዳ በጅሁር ንዑስ ወረዳ ለ3 ወራት ጠፍታ የነበረችው መምህርት በተከራየችበት ግቢ ውስጥ ተቀብራ ተገኘች፡፡

የጅሁር ንዑስ ወረዳ ፖሊስ ጽ/ቤት ዝናቧ ገ/ፃዲቅ ጥቅምት 25/02/2014ዓ/ም በግምት ከቀኑ 10 ሰዓት አካባቢ የጠፋች መሆኑን ፖሊስ በደረሰው ጥቆማ መሰረት የፀጥታ መዋቅሩና የፍትሕ አካሉ እንዲሁም የጅሁር ከተማ ማህብረሰብ እና ቤተሰቦቿ ጭምር በጋራ በተደረገው ስራ በተከራየችበት ግቢ ጓሮ ውስጥ ተቀብራ መገኘቷን ገልጿል።

ዋና አዛዥ ኮማንደር ዘነበ ሰሙንጉስ ፥ " በወረዳችን የዚህ አይነት አፀያፊ ተግባር መፈፀሙ እጅግ አሳዛኝ ነው " ብለዋል።

የመምህርት ዝናቧ አከራይ በግቢያቸው ወንጀሉ ተፈጽሞ በመገኘቱ ሙሉ ቤተሰቡን በመያዝ ምርመራ እየተጣራ መሆኑን ተገልጿል።

ኮማንደር ዘነበ "ድርጊቱ እጅግ የሚያሳዝንና የጅሩን ህዝብ የማይወክል አረመኔያዊ ተግባር በመሆኑ መላ ህዝባችን ሊያወግዘው ይገባል " ሲሉም ተናግረዋል።

ምርመራው አሁንም እየተጣራ በመሆኑ ትክክለኛ ውሳኔ እንዳረፈበት ለህዝባ እንደሚገለፅ ፖሊስ አሳውቋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ዝናቧ_ገብረፃዲቅ

የመምህርት ዝናቧ ገ/ፃዲቅ ግድያን አስመልክቶ ሰላማዊ ሰልፍ ተደረገ።

በጅሁር 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ውስጥ በመምህርነት ስታገለግል የነበረችው መምህርት ዝናቧ ገ/ፃዲቅ ግድያን አስመልክቶ ዛሬ ሰላማዊ ሰልፍ መደረጉ ተሰምቷል።

የእነዋሪ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት መምህራን ፣ ተማሪዎችና የከተማ ነዋሪዎች በአንድነት ሆነው ከጅሁር ከተማ ከመጡ ሰልፈኞች ጋር በመጣመር የመምህርቷን አሰቃቂ ሞት በአደባባይ አውግዘዋል፡፡

ሰልፈኞቹ በእነዋሪ ከተማ አደባባይ እና በጅሩ ሁለገብ ስቴዲዬም የተለያዬ መፈክሮችን ይዘው ድርጊቱን በእጅጉ ኮንነዋል፡፡

ሰልፈኞች ከያዙት መፈክር መካከል ፦

" በግፍ ለተገደለችው እህታችን መ/ርት ዝናቧ ገ/ፃዲቅ ህጋዊ ፍትህ ይሰጣት "

" እኛ መምህራን የትውልድ እናት እና አባት እንጂ ሰይፍን የማስተናገድ አቅም የለንም "

" ትክክለኛ ፍርድ ይፈረድ "

" መምህርን መግደል ትውልድን መግደል ነው "

" እኛ መምህራን የህፃንታ እናት እና አባት በመሆናችን በተከራየንበት ቤት በግፍ ተገድለን መገኘት የለብን " የሚሉ ይገኙበታል።

መምህርት ዝናቧ ገ/ፃዲቅ ለሶስት ወር ጠፍታ ስትፈልግ ከቆየ በኃላ በመጨረሻ ተከራይታ በምትኖርበት ቤት ተቀብራ ተገኝታለች።

ፎቶ ፦ ሞረትና ጅሩ ወረዳ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Tigray , #Mekelle📍 የዓለም አቀፍ ቀይ መስቀል ኮሚቴ (ICRC) በዚህ ሳምንት 2 በረራዎችን ከአዲስ አበባ ወደ መቐለ በማድረግ የህክምና ቁሳቁሶችን አድርሷል። ባለፈው ሳምንት በ5 በረራዎች እጅግ አስፈላጊ የህክምና ቁሳቁሶችን ወደ ትግራይ ክልል መቐለ ማጓጓዙና ማከፋፈል መጀመሩን መግለፁ ይታወሳል። በዚህ ሳምንት ከኢፌዴሪ ጤና ሚኒስቴር እና ከቀይ መስቀል የቀረቡ መድሃኒቶችና ሌሎች የህክምና…
#Tigray , #Mekelle 📍

10ኛው የካርጎ በረራ ዛሬ ወደ ትግራይ ክልል ተደርጓል።

ዓለም አቀፉ ቀይ መስቀል ኮሚቴ ወደ ትግራይ ክልል በአስር ቀናት ውስጥ አስረኛውን የካርጎ አይሮፕላን በረራ አስፈላጊ የሆኑ የህክምና ቁሳቁሶችን በመጫን አድርጓል።

በበረራዎቹ እንደ ኢንሱሊን ፣ ሄሞዳያሊስስ ፣ ኦክሲቶሲን ፣ ቴታነስ ቶክሳይድ ፣ ጓንት ፣ የቀዶ ጥገና ቁሳቁሶችን እና አስፈላጊ መድሃኒቶችን ለጤና ተቋማት ማድረስ ተችሏል።

በኢ.ፌ.ዴ.ሪ ጤና ሚኒስቴር እና በዓለም አቀፉ ቀይ መስቀል ኮሚቴ አማካኝነት የቀረቡት እነዚህ የህክምና ቁሳቁሶች በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን አፋጣኝ የህክምና ፍላጎቶች ለመሸፈን ይረዳሉ ተብሏል።

የዓለም አቀፉ ቀይ መስቀል ኮሚቴ ፥ የመጀመሪያው በረራ በሚመለከታቸው አካላት ድጋፍ እኤአ ረቡዕ ጥር 26 መደረጉን አስታውሶ አቅርቦቱ በመደበኝነት እንደሚቀጥል አሳውቋል።

ለሚቀጥለው ሳምንትም 5 ተጨማሪ በረራዎችን ለማድረግ አስቀድሞ መታቀዱንም ገልጿል።

@TikvahEthiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ ለሁለተኛ ዙር ሲሰጥ የነበረው የ2013 ዓ.ም አገር አቀፍ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በሰላም መጠናቀቁን አሳውቋል። የኤጀንሲው ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ተፈራ ፈይሳ ፦ - በኦሮሚያ፣ - በአማራ፣ - በአፋር እና በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች በ189 የፈተና መስጫ ጣቢያዎች ፈተናው መሰጠቱን ገልፀው የመልቀቂያ ፈተናው ካለምንም እንከን…
" ሶስተኛ ዙር ፈተና የለም " - አቶ ተፈራ ፈይሳ

ዛሬ የ2ኛው ዙር የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና መጠናቀቁ ይታወቃል።

የትምህርት ምዘና እና ፈተናዎች አገልግሎት ም/ዋና ዳይሬክተር ተፈራ ፈይሳ ፥ ፈተናው በአማራ፣ ኦሮሚያ ፣ አፋር እና ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች ያለምንም ችግር መጠናቀቁን ለ @tikvahuniversity ተናግረዋል።

ፈተናውን ከ58 ሺ እስከ 59 ሺህ ተማሪዎች እንደወሰዱ ይጠበቃል ብለዋል።

ከተፈታኞቹ ከፍተኛው ቁጥር በአማራ ክልል ሲሆን
ከ37 ሺህ በላይ ተማሪዎች ፈተናውን ለመውሰድ ተመዝግበው ነበር።

በጸጥታ ችግር ምክንያት ፈተና ያልወሰዱ ተማሪዎች ''ሁሉም በሚባል ደረጃ '' በሁለተኛው ዙር ለፈተናው የተቀመጡ በመሆኑ ሥሦተኛ ዙር ፈተና እንደማይኖር ም/ዋና ዳይሬክተሩ ገልጸዋል።

@tikvahethiopia
#AU2022Summit

" ከ40 ሺህ በላይ የፀጥታ አካላት ተሰማርተዋል " - የጸጥታ እና ደህንነት የጋራ ግብረ ኃይል

የጸጥታ እና ደህንነት የጋራ ግብረ ኃይል ባስቀመጠው አቅድ መሰረት የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ ሰላማዊ ሂደቱን ጠብቆ እየተካሄደ መሆኑን የጋራ ግብረ ኃይሉ አሰተባባሪ ኮሚቴ አስታውቋል።

የጋራ ግብረ-ኃይሉ ለጉባኤው ሰላማዊነት ከ40 ሺህ በላይ የጸጥታ አካላት በአዲስ አበባ መሰማራታቸውን የገለፀ ሲሆን ከዚህ ቀደም በኢትዮጵያ አገልግሎት ላይ ያልዋሉ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም ጉባኤው በሰላም እንዲካሄድ ቀን ከሌት እየሰራ መሆኑንም ገልጿል።

መሪዎች ባረፉባቸው እንዲሁም በሚያርፉባቸው አካባቢዎች የተጠናከረ ጥበቃ እየተከናወነ ይገኛል።

የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች ለጉባኤው ሰላማዊነት እያደረጉት ያለውን ከፍተኛ አስተዋጽኦ አጠናክረው እንዲቀጥሉ የጋራ ግብረ-ኃይሉ ጥሪ አቅርቧል።

መንግስት የአፍሪካ ህብረት ጉባኤ በሰላም ለማካሄድ ቀደም ብሎ የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ፣ የሪፐብሊካን ጥበቃ፣ ብሔራዊ የመረጃና ደህንነት አገልግሎት፣ የአዲስ አበባ ፖሊስና የኦሮሚያ ፖሊስን ያካተተ የጸጥታና ደህንነት የጋራ ግብረ-ኃይል አቋቁሞ ወደ ስራ መግባቱ ይታወቃል።

ፎቶ ፦ ፋይል

@tikvahethiopia